2010–2019 (እ.አ.አ)
መልካም እንድታደርጉ በሚመራችሁ በዛ መንፈስ ተማመኑ
ኤፕረል 2016


መልካም እንድታደርጉ በሚመራችሁ በዛ መንፈስ ተማመኑ

በንፁህ ፍቅር ሌሎችን ለእርሱ ስናገለግልለት ወደ አዳኙ እንደምንቀርብ እመሰክራለሁ።

በዚህ የአምልኮ፣ የትውስታና የቡራኬ ምሽት ውስጥ አብሬአችሁ ስላለሁኝ አመስጋኝ ነኝ። በጋራ ፀልየናል። የሚወደን የሰማይ አባታችንም ሰምቶናል። አዳኛችንን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለእርሱ ክብር በሚሰጡ መዝሙሮች ስንነካ አስታውሰናል። የሰማይ አባታችንን ልጆች ከፍ ለማድረግና ለመርዳት መምህራችንን በስራው ውስጥ ለማገዝ የበለጠ ለመስራት ተነሳስተናል።

ሌሎችን የማገልገል ፍላጎታችን አዳኙ ላደረገልን ነገር አመስጋኞች በመሆናችን ጎልቷል ። “ብዙ ስለተሰጠን፣ መስጠጥ፡ይገባኛል” የሚባለው መዝሙር ቃላት ሲዘመሩ ስንሰማ ለዚህ ነው ልባችን የሚሞላው1 ታላቅ ስብከቱ በመጽሐፈ ሞርሞን ላይ እንደተመዘገበው፣ ንጉስ ቢኒያም ያንን የአመስጋኝነት ስሜት ቃል ገባ (ሞዛያ 2፥17–19ተመክለቱ)።

በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት ለይቅርታው ደስታ ብቁ እንድንሆን ሲመራን፣ ሌሎችን ለእርሱ ለማገልገል ፍላጎት ይሰማናል። ንጉስ ቢኒያም ይቅርታ በትንሽ ጊዜ ውስጥ የሚከናወን እንዳልሆነ አስተምሯል።

በዚህ መንገድ ተናገረ፥ “እናም አሁን፣ ለእናንተ ለተናገርኳቸው ለእነዚህ ነገሮች ሲባል ፡— ይህም ማለት በእግዚአብሔር ፊት ከበደል ነፅታችሁ ትራመዱ ዘንድ ከቀን ወደ ቀን ለኃጢአታችሁ ስርየትን እንድታገኙ ፡— የራሳችሁን ነገር ለድሃ እንድትሰጡ፣ እያንዳንዱ ሰው ባለው መጠን፣ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጎብኘት እናም እንደፍላጎታቸው ለነፍሳቸውም ሆነ ለስጋቸው ደህንነት በቂ እርዳታን እንድትለግሱ እፈልጋለሁ” (ሞዛያ 4፥26)።

የአልማ ታላቅ ጓደኛ አሙሌቅ እንዲሁም ይቅርታን ለማግኘት ለእርሱ ያለንን አገልግሎት መቀጠል እንደሚገባን አስተማረ፥ “እናም አሁን እነሆ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ይህ ብቻ ነው ብላችሁ አትገምቱ፤ ምክንያቱም ይህንን ነገር በሙሉ ካደረጋችሁ በኋላ፣ የተቸገሩትንና፣ የታረዙትን ካልረዳችሁ፣ እናም የተሰቃዩትን፣ የታመሙትን ካልጎበኛችሁ፣ እናም ካላችሁ ነገር ካላካፈላችሁ፣ እያላችሁ ለሚሹት ካልሰጣችሁ ፡— እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፥ ከእነዚህ ነገሮች የትኛውንም ካላደረጋችሁ፣ እነሆ፣ ፀሎታችሁ ከንቱ ነው፣ እናም ለእናንተ የሚጠቅማችሁ ምንም የለም፤ እናም እናንተ እምነትን የምትክዱ ግብዞች ናችሁ” (አልማ 34፥28)።

ዛሬ ማታ በሕይወቴ ውስጥ ያገኘኋቸውን ሴቶች አሰብኩኝ። ከባለቤቴ ጀምሮ ሶስት ሴቶች የልጅ ልጅ ልጆችን ጭምር ወርዶ በቤተሰባችን ውስጥ 31 ሴቶችና ልጃ ገረዶች አሉ። የተወሰኑት በዛሬው ምሽት ከኛ ጋር ነው ያሉት። አምስቱ ከ12 አመት በታች ናቸው። ከእህቶቻቸው ጋር በአዳኙ ቤተክርስቲያን በጉባኤ አዳራሽ መአከል ውስጥ ይህ የመጀመሪያ ስብሰባቸው ሊሆን ይችላል። እያንዳንዳቸው በዚህ ምሽት የተለየ ትውስታዎችን ይወስዱና ከዚህ ልምድ የራሳቸውን ዝግጁነትያደርጋሉ ።

በመላ ሕይወታቸው ውስጥ እናም ከዛ ባሻገር ከእነርሱ ጋር እንዲቆይ የምፀልየው ሶስት ትውስታዎችና ዝግጁነቶች አሉ። ትውስታዎቹ የስሜት ናቸው። እዲሁም ዝግጁነቶቹ የሚደረጉ ነገሮች ናቸው።

ታላቁ የወሳኝነት ስሜት ፍቅር ነው። ንግግር ያደረጉትን የታላቅ እህት መሪዎች ፍቅር ተሰምቷችኋል። የሰማይ አባትና አዳኙ ለእናንተ ያላቸውን ፍቅር ስለተሰማቸው ሳያውቋችሁ እንደሚወዷችሁ በመንፈስ ተሰምቷችኋል። ለዛ ነው እንዲያገለግሏችሁና የእግዚአብሔርን በረከቶች እድትቀበሉ እጅግ በጣም የሚፈልጉት።

ዛሬ ማታ ለሌሎች ፍቅር ተሰምቷችኋል፣ ማለትም ለጓደኞች፣ ለትምህርት ቤት ጓደኞች፣ ለጎረቤቶች እንዲሁም ወደ ሕይወታችሁ ለመጣ እንግዳ ፍቅር ተሰምቷችኋል። ያ የፍቅር ስሜት ከእግዚአብሔር የመጣ ስጦታ ነው። ቅዱሳት መጽሐፍት “ልግስና” እና “የክርስቶስ ንፁ ፍቅር” ብለው ይጠሩታል (ሞሮኒ 7፥47)። ዛሬ ማታ ያ ፍቅር ተሰምቷችኋል እዲሁም ከፈለጋችሁት በተደጋጋሚ መቀበል ትችላላችሁ።

ዛሬ ማታ የነበራችሁ ሁለተኛው ስሜት የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ነበር ። መንፈስ ቅዱስ ጌታ ለእርሱ ለሌሎች እንድትሰጡለት የሚፈልጋችሁን አገልግሎት እንድታገኙ አንደሚመራችሁ እህቶች በዚህ ቀን ቃል ገብተውላችኋ። በመንፈስ የእነሱ ቃል-ኪዳን ከጌታና እውነት እንደነበረ ተሰምቷችኋል።

ጌታ እንዳለው፣ “እናም አሁን፣እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ወደ መልካም፣ አዎን፣ በትክክል ለመስራት፣ በትህትና ለመራመድ፣ በጽድቅ ለመፍረድ፣ በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ፤ እና መንፈሴም ይህ ነው።” (ትምህርት እና ቃ ኪዳን 11፥12)።

ያንን በረከት ዛሬ ማታ ተቀብላችሁት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፣ በዚህ ስብሰባ ጊዜ እርዳታ የሚፈልግ የአንድ ሰው ስም ወይም ፊት ወደ አዕምሮአችሁ መጥቶ ሊሆን ይችላል ። በራሪ ሃሳብ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ዛሬ ማታ ስለሰማችሁ እግዚአብሔር ለእነሱ የሚፈልገውን መልካም ስራ እንድታደርጉ እንደሚመራችሁ በማመን ትፀልዩበታላችሁ ። እንደነዚህ አይነት ፀሎቶች በሕይወታችሁ ውስጥ ተደጋጋሚ ሲሆኑ፣ እናንተና ሌሎች ወደ መልካምነት ትለወጣላችሁ።

ዛሬ ማታ የነበራችሁ ሶስተኛው ስሜት ወደ አዳኙ ለመቅረብ የምትፈልጉት ነው። እዚህ ካሉት መካከል ትንሽዬዋ ልጅ እራሱ በዚህ መዝሙር ውስጥ ያለውን የግብዣ እውነተኛነት ተሰምቷታል ፥ “‘ኑ፣ ተከተሉኝ፣’ አዳኙ አለ። ከዛ በእግሮቹ አሻራ ላይ እንራመድ።”2

ስለዚህ ከነዛ ስሜቶች ጋር በመጀመሪያ ለማድረግ መዘጋጀት ያለባችሁ ነገር ብቻችሁን እንደማትሄዱ በማወቅ ለመሄድና ለማገልገል ነው። ለአዳኙ ማንኛውንም ሰው ለማፅናናትና ለማገልገል በምትሄዱበት ወቅት መንገዱን ከፊታችሁ ያዘጋጃል። አሁን፣ ዛሬ ማታ እዚህ ያሉት ከሚስዮን ተመልሰው የመጡት እንደሚነግሯችሁ ከእያንዳንዱ በር ጀርባ ያለው እያንዳንዱ ሰው ሊቀበላችሁ ዝግጁ ነው ወይም ለማገልገል የምትሞክሩት እያንዳንዱ ሰው ያመሰግናችኋል ማለት አይደለም። ነገር ግን ጌታ መንገዱን ሊያዘጋጅ ከፊት ፊታችሁ ይሄዳል።

በተደጋጋሚ ፕሬዘደንት ቶማስnb}ኤስ. ሞንሰን የጌታን ቃል-ኪዳን እውነተኛነት እንደሚያውቁ ተናግረዋል፥ “እናም የሚቀበሏችሁም፣ በእዚያም እገኛለሁ፣ በፊታችሁ እሄዳለሁና። በቀኛችሁ እና በግራችሁ እሆናለሁ፣ እናም መንፈሴም በልቦቻችሁ ውስጥ ይገኛል፣ እናም መላእክቶቼም እንዲያዝሏችሁ ይከብቧችኋል” (D&C 84፥88)።

ከፊት ፊታችሁ የሚሄድበት መንገዶች አንዱ እንድታገለግሉ የጠየቃችሁን ሰው ልብ ማዘጋጀት ነው። የእናተንም ልብ ያዘጋጃል።

ጌታ እረዳቶችን ከጎናችሁ፣ በቀኛችሁ፣ በግራችሁና በዙሪያችሁ አስቀምጦ ታገኛላችሁ። ሌሎችን ለእርሱ ለማገልገል ብቻችሁን አትሄዱም።

ይህንን ለኔ ዛሬ ማታ አድርጎልኛል። ጌታ በቃሎችም በመዝሙርም እንድናገር የፈለገውን ኃይል ለማሰባሰብና ለማባዛት “የምስክሮችን ደመና” (ዕብራውያን 12፥1)አዘጋጀ። በእርሱ አወቃቀር ውስጥ የድርሻዬን ማስተካከል እንደምችል እርግጠኛ መሆን ነበረብኝ። ጌታ ለእርሱ እድታገለግሉ ከሌላ ሰዎች ጋር ሲያጣምራችሁ ምስጋናን እና ደስታን እንዲሰማችሁ ተስፋ አደርጋለሁ እንዲሁም እፀልያለሁ።

ያ ልምድ በተደጋጋሚ ሲኖራችሁ “ስራው አስደሳች ነው”3የሚለውን ስንዘምር እንደ እኔም ፈገግ ትላላችሁ።

ይህንን ጥቅስ ስታስታውሱም ፈገግ ትላላችሁ፥ “ጉሱም መልሶ እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል” (ማቴዎስ 25፥40)።

ማድረግ ያለባችሁ ሁለተኛው ነገር ለእርሱ ለማገልገል ስትሄዱ ጌታን ማስታወስ ነው ። ጌታ ከፊታችን ብቻ ሳይሆን የሚሄደው እንዲሁም መልአክቶችን ከእኛ ጋር እንዲያገለግሉ ብቻ ሳይሆን የሚልከው፣ ነገር ግን ለሌሎች የምንሰጣቸውን መፅናናት ለእርሱ የሰጠነው ያክል ይሰማዋል ።

የእዚህን ስብሰባ መልዕክት የምትሰማና የምታምን እያንዳንዷ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ይህን ትጠይቃለች፣ “ጌታ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ምን በማድረግ እንድረዳ ይፈልጋል?” የእያንዳንዷ ሴት ሁኔታ ልዩ ነው። ያ ለኔ ሴት ልጆች፣ የወንድ ልጆቼ ሚስቶች፣ የልጅ ልጆችና፣ የልጅ ልጅ ልጆች እውነት ነው። ለእነሱና ለሁሉም የሰማይ አባት ሴት ልጆች የእህት ሊንዳ ኬ በርተንን የጥበብ ምክር እደግመዋለሁ።

በሁኔታችሁ ውስጥ ጌታ ምን እንድታደርጉ እንደሚፈልግ ለማወቅ በእምነት እንድትፀልዩ ጠያቃችኋች። ከዛም ድሃዎችን ተሸጦ መርዳት በሚቻልበት ውድ በሆነ ዘይት እራሱን ስለቀባችው ትችት ስለደረሰባት ሴት ጌታ እራሱ ጣፋጭ መፅናናት የሰጣትን ለእናንተም ተናገረች።

“ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፣ ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ስራ ሰርታልኛለች“።

“ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉ፣ በማናቸውም በወደዳችሁት ጊዜ መልካ ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፥ እኔ ግር ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም።

“የተቻላትን አደረገች፥ አስቀድማ ለመቃብሬ ስጋዬን ቀባችው“።

“እውነት እላችኋሁ ይህ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይናገራሉ” (ማርቆስ14፥6–9)።

ያ አጭር ጥቅስ በዚህ ሁካት ጊዜ በጌታ መንግስት ውስጥ ለአማኝ እህቶች የሚሆን ውድ እና ፍፁም ምክር ነው። አብ ለእርሱና ለአዳኛችን ባለን ፍቅር ማንን እንድታለግሉ እንደሚፈልግ ለማወቅ ትፀልያላችሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ በማርቆስ ዘገባ ውስጥ የአለም አዳኝን ለማክበር ያደረገችው ቅዱስ ስራዋ እንጂ ስሟ ያልታወሰውን ሴት ምሳሌ በመከተል የህዝብ ማስታወሻ አትጠብቁም ወይም አትፈልጉም።

በቤተሰባችን ውስጥ ያሉ እህቶች ለእግዚአብሔር ባላቸው ፍቅር የተነሳ እርዳታ ለሚፈልጉ እንዲያገለግሉ የሚቻላቸውን ለማድረግ መልካም ተስፋዬ ነው። እናም ሶስተኛው ተስፋ የማደርገው ነገር ለመልካም ስራቸው ጉራተኛ ያልሆኑ እንዲሆኑ ነው። ግን፣ ሁላችንም ማዳመጥ የሚያስፈልገንን፣ ይህን በሚልበት ጊዜ የጌታን ምክር እንዲቀበሉ ጸሎቴ ነው፥

“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምፅዋታችሁን በፊታችሁ እንዳታዳታደርጉ ተጠንቀንቁ፥ ያለዚያ በሰማያ ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።

ከዚያም እንዲህ አለ፥

“ነገር ግን መልካም ስራ በምትሰሩበት ጊዜ ቀኝ እጃችሁ ግራ እጃችሁ የሚያደርገውን አይወቅ፤

“ምፅዋታችሁ በስውር ይሁን፤ በስውር የሚያያችሁ አባታችሁ በግልፅ ይከፍላችኋል” (ማቴዎስ 6፥1፣ 3–4)።

የትም ይሁኑ ወይም በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ይሁኑ፣ በመንግስቱ ውስጥ ላሉ እህቶች ፀሎቴ በአዳኙና በሃጢያት ክፍያው ላይ ያላቸው እምነት ጌታ እንዲያገለግሉ ለሚጠቃቸው ሰዎች ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ እዲያደርጉ እዲመራቸው ነው። ያን ሲያደርጉ አዳኙና የሰማይ አባታችን ሞቅ ባለ ሁኔታ የሚቀበሏቸውና በግልፅ የሚባርኳቸ ቅዱስ ሴቶች ለመሆን በመንገድ ላይ እንደሚጓዙ ቃል እገባለሁ።

ይህ ትንሳኤ ያደረገው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደሆነ እመሰክራለው። እርሱ ተነስቷል። ለኃጢአቶቻችን በሙሉ ዋግ ከፍሏል። በእርሱ ምክንያት ከሞት እንደምንነሳ እና የዘለአለም ህይወት ሊኖረን እንደምንችል አውቃለሁ። ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን የእርሱ ሕያው ነቢይ ናቸው። የሰማይ አባት ጸሎታችንን ይሰማል እናም ይመልሳል። በንፁህ ፍቅር ሌሎችን ለእርሱ ስናገለግልለት ወደ አዳኙ እንደምንቀርብ እመሰክራለሁ። እርግጠኛ ምስክር የምሰጣችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “Because I Have Been Given Much፣” Hymns፣ ቁጥር 219።

  2. “Come, Follow Me፣” Hymns፣ ቁጥር 116።

  3. “Sweet Is the Work፣” Hymns፣ቁጥር 147።