2010–2019 (እ.አ.አ)
እነርሱ እንደሚያውቁ ከማወቅ የበለጠ የሚያስደስት ነገር የለም።
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


እነርሱ እንደሚያውቁ ከማወቅ የበለጠ የሚያስደስት ነገር የለም።

በዚህ አለም ላይ ልጆቻችን አዳኝን እንደሚያውቁ ከማወቅ በላይ የበለጠ ደስታ እና ሀሴትን የሚያመጣ ነገር መኖሩን አላውቅም።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ይሄን ጥያቄ ሰሞኑንን ሳሰላስለው ነበር፤ “ልጆቻችሁ ያላቸው የወንጌል እውቀት የመጣው ከእናንተ ብቻ ቢሆን—ያ ብቻ ቢሆን ምንጫቸው—ምን ያህል ያውቁ ነበር?” ይሄ ጥያቄ ልጆቻቸውን ለሚወዱ፣ ለሚመክሩ እና ተፅኖ ለሚያሳድሩ ሁኑ ነው።

ቤዛችን ህያው መሆኑን እንደምናውቅ በልጆቻችን ልቦች ውስጥ በጥልቀት ከማስረፅ በላይ ለእነርሱ የምናካፍለው ስጦታ አለን? እኛ እንደምናውቅ እነሱ ያውቃሉ? እናም በተለይ፣ እርሱ ህያው እንደሆነ እነርሱ ወደ ማወቅ መጥተዋል?

ልጅ ሳለሁ፣ እኔ ለማሳደግ በጣም አስቸጋሪ የሆንኩ የእናቴ ትንሽ ልጅ ነበርኩ። የተትረፈረፈ ጉልበት ነበረኝ። እናቴ እንደነገረችኝ የእርሷ ፍራቻ እስከ ጉልምስና በህይወት ላልቆይ እንደምችል ነበር። በጣም ፈጣን ነበርኩ።

ልጅ ሆኜ በአንድ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ከቤተሰቦቻችን ጋር ቁጭ ብለን አስታውሳለሁ። እናቴ አዲስ የቅዱስ መፅሀፍት ስብስብ መቀበሏ ነበር። ይሄ ስብስብ ሁሉንም ዋና መጽሐፍት በአንድ ላይ ያቀፈ ነው እና በመሀከሉ ላይ ለማስታወሻ መያዣ የሚሆን የመስመር ወረቀት አለው።

በስብሰባው ወቅት፣ ቅዱስ መጽሐፍቶቿን መያዝ እንደምችል ጠየኩ። በፀጥታ እንደምሆን ተስፋ በማድረግ፣ በመቀመጫው ታች አቀበለችኝ። ቅዱስ መፅሐፍቶቿን በጥንቃቄ እያነበብኩ ሳለሁ፣ በማስታወሻው በኩል የግል እቅዷን እንደፃፈች አስተዋልኩ። እቅዷ አግባብ እንዲኖረው ለማድረግ፣ ከስድስት ልጆች ሁለተኛው እንደሆንኩ እና ስሜ ብሬት እንደሆነ ልነግራችሁ ግድ ነው። እናቴ በቀይ አንድ እቅድ ብቻ እንዲህ ብላ ነበር የፃፈችው፤ “ብሬትን መታገስ!”

የእኛን ቤተሰብ በማሳደግ ውስጥ ወላጆቼ የተጋፈጡትን ፈተና እንድትረዱ በበለጠ መረጃ ለማገዝ፣ ስለ እኛ ቤተሰብ የቅዱስ መፅሐፍት ንባብ ልንገራችሁ። በእያንዳንዱ ጠዋት፣ በቁርስ ሰአት እናቴ ለእኛ መጽሐፈ ሞርሞን ታነብ ነበር። በዚህ ጊዜ፣ ታላቅ ወንድሜ ዴቭ እና እኔ ያለ አክብሮት ፀጥ ብለን እንቀመጣለን። ሙሉ በሙሉ እውነት ለማውራት፣ እያዳመጥን አልነበረም። የእህል ካርቶኑ ላይ ጽሁፍ ነበር የምናነበው።

በስተመጨረሻም፣ አንድ ጠዋት፣ ለእናቴ ግልፅ ለመሆን ወሰንኩ። ጮክ ብዬ ተናገርኩ፣ “እማ፣ ይህን ለእኛ የምታደርጊው ለምንድነው? ሁሌ ጠዋት መጽሐፈ ሞረሞን የምታነቢው ለምንድነው?” ከዛም ለመቀበል አሳፋሪ የሆነውን አርፍተ ነገር ተናገርኩ። በእርግጥም፣ ያንን ማለቴን ማመን አልችልም። “እማዬ፣ አላዳምጥም እኮ!” ብዬ ነገርኳት።

የፍቅር ምላሸዋ በህይወቴ ውስጥ ትረጉም ሰጪ ነበር። እንዲህ አለች፣ “ልጄ፣ ፕሬዝዳንት ማሪዮን ጂ. ሮምኒይ ስለ ቅዱሳት መፅሀፍት የማንበብ በረከት ሲያስተምሩ ስብሰባ ላይ ነበርኩ። በዚህ ስብሰባ ወቅት፣ ለልጆቼ በየቀኑ መጽሀፈ ሞርሞን ካነበብኩላቸው፣ እንደማላጣቸው ቃል ኪዳን ተቀብዬ ነበር።” ከዛም አይኖቼን ቀጥታ በሙሉ ቆራጥነት አየች እና፣ እንዲ አለች፣ “እናም አላጣህም!””

ቃላቶቿ ልቤን ዘልቀው ገቡ። ፍፁም አለመሆኔ እንዳለ ሆኖ፣ ለመዳን ብቁ ነበርኩ! እኔ የአፍቃሪው የሰማይ አባት ልጅ እንደሆንኩ ዘለአለማዊ እውነትን አስተማረችኝ። ሁኔታው ምንም ቢሆን፣ እኔ ዋጋ እንደነበረኝ ተማርኩ። ይሄ ፍፁም ላልሆነ ትንሽ ልጅ ፍፁም ወቅት ነበር።

እንደ መላእክ ለሆነችው እናቴ እና ፍፁም አለመሆናቸው እንዳለ ሆኖ ፍፁም በሆነ መልኩ ልጆቻቸውን ለሚወዱ መላእክቶች ሁሉ ለዘለአለም አመስጋኝ ነኝ። መላእክት ብዬ የምጠራቸው እህቶች ሁሉ—በጺዮን ውስጥ ያሉ እህቶች እንደሆኑ በፅኑ አምናለሁ፣ በዚህ ምድራዊ ተሞክሮ ወቅት አግብተው ወይም ልጅ ወልደው ቢሆንም ባይሆንም።

ከአመታት በፊት የቀዳሚ አመራር እንዲህ አወጁ፤ “እናትነት ወደ መለኮታዊነት የቀረበ ነው። በሰው ፍጥረት ከሚገመተው በጣም ከፍተኛ፣ በጣም ቅዱስ አገልግሎት ነው። ቅዱስ ጥሪውን እና አገልግሎት የምትቀበለውን እሷን ከመላእክት ተርታ ያስቀምጣታል።”1

ለሰማይ አባት ልጆች ዘለአለማዊ እውነትን በቁርጠኝነት እና በፍቅር በመላ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለሚያውጁ መላእክቶች አመስጋኝ ነኝ።

ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ስጦታ አመስጋኝ ነኝ። ይህ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ! የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ሙሉነት የያያዘ ነው። በትጋት መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ በንጹህ ልብ እና በክርስቶስ እምነት እያነበበ ምስክርነቱን ያጣ እና የወደቀ ማንንም ሰው አላውቅም። የሞሮኒ ትንቢታዊ ቃልኪዳን የሁሉንም ነገሮች እውነታ የማወቅን ቁልፍ ይዟል—የጠላትን ማታለል ለይቶ ማወቅን እና የማስወገድንም አቅም ያካትታል። (ሞሮኒ 10፥4–5 ተመልከቱ።)

ስለ አፍቃሪው የሰማይ አባት እንዲሁም ስለ ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም አመስጋኝ ነኝ። አዳኝ ፍፁም እና ተገቢ ባልሆነ አለም ውስጥ እነዴት እንደሚኖር ፍፁም ምሳሌን አቅርቧል። “እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን” (1 John 4፥19)። ለእኛ ያለው ፍቅር የሚለካ አይደለም። እውነተኛ ጓደኛችን ነው። ለእኔ እና ለእናንተ በትልቅ የደም ጠብታዎች አላበው (ሉቃስ 22፥44)። ይቅር እንደማይባሉ የሚመስሉትን ይቅር አለ። የማይወደዱትን ወደደ። ምድራዊ ሰው የማያደርገውን አደረገ፤ መተላለፎችን፣ ህመሞችን፣ እና የሁሉንም የሰው ዘር በሽታዎች ለማሸነፍ የሀጢአት ክፍያውን አቀረበ።

በኢየሱስ የሀጢአት ክፍያ አማካኝነት፣ ትግላችን ምንም ቢሆን፣ “ለማዳን ሁሉን ቻይ በሆነው” በእርሱ ሁሌም ተስፋ ማድረግ በመቻላችን፣ በዛ ቃልኪዳን መኖር እንችላለን (2 ኔፊ 31፥19)። በእርሱ የሀጢአት ክፍያ አማካኝነት፣ ሀሴት፣ ሰላም፣ ደስታ፣ እና ዘለአለማዊ ህይወት ሊኖረን ይችላል።

ፕሬዘዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር እንደገለፁት፥ “ለጥፋት ከደከሙት በጣም ጥቂቶች በስተቀር፣ ሙሉ ለሙሉ ይቅር መባልን የማያገኝ ምንም ልምድ፣ ምንም ሱስ፣ ምንም አመፅ፣ ምንም መተላለፍ፣ ምንም ክህደት፣ ምንም ወንጀል የለም። ያ የክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ ቃልኪዳን ነው።”2

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጣም ድንቅ ከሆኑት ክስተቶች አንዱ አዳኝ ለጥንት የአሜሪካ ሰፋሪዎች ያደረገው የአገልግሎት ጉብኝት ነው። እዛ መሆን ምን ሊመስል እንደሚችል በአእምሮአችሁ ሳሉት። በቤተመቅደስ ለነበሩት የቅዱሳን ስብስብ ያሳየው ፍቅሩ እና ርህራሄ ሳሰላስል፣ ከህይወት እራሱ አስበልጬ የምወዳቸውን እያንዳንዱ ልጆችን እስባለሁ። ትንንሽ ልጆቻችን ለግላቸው እያንዳንዱን ልጆች ወደ እርሱ እንዲመጡ አዳኝ ሲጋብዝ መመልከት፣ የተዘረጉትን የአዳኝ እጆች መመልከት፣ አንድ በአንድ እንደ እያንዳንዱ ልጆች መቆም፣ በእርጋታ በእጆቹ እና እግሮቹ ላይ ያሉትን ምልክቶች መዳሰስ፣ እናም እያንዳንዱ ቆመው እርሱ ህያው እንደሆነ ሲመሰክሩ ማየትን ለማሰብ ሞክሬያለሁ! (3 ኔፊ 11፥14–17 ተመልከቱ፤ ደግሞም 17፥2118፥25 ተመልከቱ።) ልጆቻችን ዞር ብለው እንዲህ ሲሉ፣ “እማዬ፣ አባዬ፣ እርሱ እኮ ነው!”

ምስል
አዳኝ ከልጆች ጋር

ልጆቻችን አዳኝን እንደሚያውቁ እና “ለሀጢያታቸው ስርየት ወዴትኛው ምንጭ መመልከት እንዳለባቸው” መረዳታቸውን ከማወቅ በላይ ደስታ እና ሀሴትን ሊያመጣ የሚችል በዚህ አለም ውስጥ ምንም ነገር አላውቅም። በዛም ምክንያት “ስለ ክርስቶስ እንሰብካለን” እና ስለክርስቶስ እንመሰክራለን (2 ኔፊ 25፥26)።

  • ለዛ ነው ከልጆቻችን ጋር በየቀኑ የምንፀልየው።

  • ለዛ ነው ከነርሱ ጋር ቅዱሳት መፅሐፍትን በየቀኑ የምናነበው።

  • ለዛ ነው ሌሎችን እንዲያገለግሉ የምናስተምራቸው፣ ሌሎችን በማገልገል ውስጥ እራሳቸውን በመርሳት እራሳቸውን የማግኘትን በረከቶች ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ነው። (ማርቆስ 8፥35ሞዛያ 2፥17 ተመልከቱ)።

እራሳችንን በዚህ ቀላል የደቀመዝሙርነት ሂደት ውስጥ ስናደርግ፣ የጠላትን አደገኛ ንፋስ ሲጋፈጡ ልጆቻችን በአዳኝ ፍቅር እና በመለኮታዊ ምሬት እናም ጥበቃ ሀይል እንሰጣቸዋለን።

ወንጌል በእውነትም ስለ አንዱ ነው። ስለጠፋው አንዱ በግ ነው (ሉቃስ 15፥3–7 ተመልከቱ)፤ በውሃ ጉድጓዱ ጋር ስላለችው አንድ ሰማራዊት ሴት ነው (ዮሀንስ 4፥5–30 ተመልከቱ)፤ ስለአንዱ አባካኝ ልጅ ነው (ሉቃስ 15፥11–32 ተመልከቱ)።

እናም እያዳመጠ አለመሆኑን ስለተቀበለ አንድ ትንሽ ልጅ ነው።

ስለ እያንዳንዳችን ነው—ፍጹም እንዳለመሆናችን—እርሱ ከአባቱ ጋር አንድ እንደሆነ እኛም ከአዳኝ ጋር አንድ ስለመሆን ነው (ዮሀንስ 17፥21 ተመልከቱ)።

እኛን በስማችን የሚያውቀን፣ አፍቃሪ የሰማይ አባት እንዳለን እመሰክራለሁ! ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው የሆነው የእግዚአብሔር ህያው ልጅ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ብቸኛ ልጅ እና ከአብ ጋር የእኛ ብቸኛ አማላጅ ነው። ደህንነት በእርሱ እና በእርሱ ስም እንጂ በሌላ መንገድ እንደማይመጣ ቀጥዬም እመሰክራለሁ።

ሁሉም የሰማይ አባት ልጆች እርሱን እንዲያውቁት እና ፍቅሩ እንዲሰማቸው ለመርዳት ልቦቻችንን እና እጆቻችንን እንድንሰጥ ፀሎቴ ነው። ያንን ስናደርግ፣ ዘለአለማዊ ሀሴት እና በዚህ ምድር እንዲሁም በሚመጣው ህይወት ደስታ እደሚኖረን ቃል ገብቷል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “Message of the First Presidency,” in Conference Report, Oct. 1942, 12–13; በፕሬዘደንት ጄ. ሩብን ክላርክ ዳግማዊ ተየነበበ።

  2. ቦይድ ኬ. ፓከር፣ “The Brilliant Morning of Forgiveness፣” Ensign፣ ህዳር 1995 (እ.አ.አ)፣ 20።