2010–2019 (እ.አ.አ)
መርሆች እና ቃልኪዳኖች
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


መርሆች እና ቃልኪዳኖች

በመለኮታዊ በተዘጋጀው እቅድ፣ የጥበብ ቃል ውስጥ የተሰጡትን መርሆዎች በመከተል ለሰውነታችን እና ለአይምሮአችን እናስብ።

ወንድሞች፤ በዚህ ምሽት መልዕክቴን ከእናንተ ጋር ሳካፈል ለሰማይ አባታችን ምሬት እፀልያለሁ።

በ1833 ጌታ ስለጤናማ አኗኗር ዕቅድ ለነብዩ ዮሴፍ ስሚዝ ራዕይ ገለፀለት። ያም እቅድ በትምህርት እና ቃልኪዳኖች ክፍል 89 ውስጥ ይገኛል እናም የጥበብ ቃል ተብሎ ይታወቃል። ስለምንመገበው ምግብ ግልፅ የሆነ መመሪያ ይሰጣ እናም ለሰውነታችን ጎጂ የሆኑ ንጠረ ነገሮችን እንዳንወስድ ይከለክለናል።

እነዛ ለጌታ ትዕዛዝ ታዛዥ የሆኑት እና በታማኝነት የጥበብ ቃልን የሚጠብቁ ለየት ያለ በረከት እንደሚኖራቸው ቃል አላቸው፣ ከነዚህም መካከል ጥሩ ጤና እና ቀጣይነት ያለው የአካል ቅልጥፍና ናቸው። 1

በቅርቡ እንዚህን ቃልኪኖችን የሚዘግብ ስለ አንድ አስዳናቂ ሀተታ አንብቤ ነበር። የቤተክርስቲያኗ ታማኝ አባል ጆን ኤ. ላርሰን፣ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ በአሜሪካ በዩ.ኤስ.ኤስ ካምብሪያ መርከብ ላይ የባህር ጠባቂነት አገልግሎት ላይ ነበር። በፊሊፒንስ ውስጥ ጦርነት በነበረ ጊዜ፣ በመቅረበ ላይ ስላለ የቦንብ የባህር ሀይል እና ተዋጊ አጥቂ አውሮፕላኖች ወሬ መጣ። አፋጣኝ የሆነ ጥሎ የመውጣት ትዕዛዝ ተሰጠ። ዩ.ኤስ.ኤስ ካምብሪያው ሄዶ ስለነበር ጆን እና ጓደኞቹ እቃቸውን በፍጥነት በመሰብሰብ እየሄዱ ካሉት አንዱ መርከብይዞን ይሄዳል ብለው ተስፋ በማድረግ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሄዱ። እንደእድል ሆኖ አንድ እያረፈ ያለ ጀልባ በእለቱ የመጨረሻ ተጓዥ ወደ ሆነው መርከብ ይዟቸው ሄደ። በዛ በሚሄደው መርከብ ላይ ያሉት ወንዶች፣ በተቻላቸው መጠን ቶሎ ለቀው ለመሄድ በሚያደርጉት ጥረት፣ በመርከቡ ውጥረት ላይ ስለነበሩ የነበራቸው ጊዜ ለአራቱ ሰዎች ገመዱን የመወርወሪያ ብቻ ነበር፣ ይዘው ይወጣሉ ብለው ተስፋ በማድረግ።

ጆን፣ ከባድ የሆነ ሬዲዮ ጀርባው ላይ ጠፍሮ፣ ግልፅ ወደ ሆነው ባህር በሚያመራው መርከብ ላይ 12 ሜትር ገመድ ጫፍ ላይ በመወዛወዝ ደረሰ። ካመለጠው እንደሚጠፋ በማወቅ ከአንድ እጅ በኋላ ሌላኛውን እጅ እያሳለፈ እራሱን ወደ ላይ ማውጣት ጀመረ። አንድ ሶስተኛውን ብቻ ከወጣ በኋላ እጆጁ በህመም ነደዱ። በጣም ከመድከሙ የተነሳ ከዚያ በላይ መንጠላጠል እንደማይችል ተሰማው።

ጥንካሬው በማለቅ ላይ ሆኖ፣በሰቆቃ እጣውን በማሰላሰል፣ ጆን በትህትና ወዳ እግዚአብሔር አለቀሰ፣ ሁሉግዜም የጥበብ ቃልን እንደጠበቀ እና ህይወቱን በንፅህና እንደኖረ—እና የተገባለትን ቃልኪዳን አሁን በጣም እንደሚያስፈልገው ነገረው።

ጆን በኋላ ሲናገር ፀሎቱን እንደጨረሰ፣ ከፍተኛ ጥንቃሬ ተሰማው። በድጋሜ መውጣቱን ቀጠለ እንዲሁም በገመዱ ወደ ላይ በረረ። መርከቡ ጫፍ ላይ ሲደርስ አተነፋፈሱ የተለመደ ነበር— ምንም የሰራ አይመስልም። በጥበብ ቃል ውስጥ ቃል የተገቡት ጭማሬ ጤና እና የአካል ብርታት በረከቶች፣ የእርሱ ነበሩ። በዛ ጊዜ እና በህይወቱ ሙሉ ለእርዳታ በፀለየው ፀሎት ስላገኘው መልስ ለእግዚአብሔር ምስጋና ሰጠ።2

ወንድሞች፣ በመለኮታዊ በተዘጋጀው እቅድ፣ የጥበብ ቃል ውስጥ የተሰጡትን መርሆዎች በመከተል ለሰውነታችን እና ለአይምሮአችን እናስብ። በሙሉ ልቤ እና ነፍሴ፣ ይህንን ስናደርግ ድንቅ የሆኑ በረከቶች እንደሚጠብቁን እመሰክርላችኋለሁ። ይህ ይሆን ዘንድ እፀልያለሁ፣ በጌታችን እና አዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥18–21 ተመልከቱ።

  2. ጆን ኤ. ላርሰን፣ በሮበርት ሲ. ፍሪማን እና ዴኒስ ኤ. ራይት፣ comps., Saints at War: Experiences of Latter-day Saints in World War II (2001), 350–51 ይመልከቱ፤ በፍቃድ የተወሰደ።