2010–2019 (እ.አ.አ)
ንስሀ፥ የደስታ ምርጫ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


ንስሀ፥ የደስታ ምርጫ

ንስሀ መግባት በአዳኝ ምክንያት የሚቻል ብቻ ሳይሆን ደስተኛ ነው።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አስራ ሁለት አመቴ ሳለሁ ቤተሰቤ በደቡብ ስዊድን በባህር ዳርቻ በሚገኝ በጎትቦርግ ኖረው ነበር ይህም ውዱ አብሮን ይሰሩ የነበሩት፣ ባለፈው በጋ የሞቱት፣ የሽማግሌ ፐር ጂ. ማልም1 የቤት ከተማቸው ነበር። እንናፍቃቸዋለን። ለክብር አገልግሎታቸው እና በታም ተወዳጅ ለሆኑት ለቤተሰባቸው ምሳሌ ምስጋና ይሰማናል። የእግዚአብሖእር በረከቶች ከእነርሱ ጋር እንዲሆን እንጸልያለን።

ከሀምሳ አምት በፊት፣ ድጋሚ በተሰራ ትልቅ ቤት ውስጥ ቤተክርስቲያን እንካፈል ነበር። አንድ እሁድ፣ በቅርንጫፉ ውስጥ ሌላኛው ብቸኛ ዳያቆን የሆነው የእኔ ጓደኛ ስቲፋን2 በጣም በደስታ ሰላም አለኝ። በተጥለቀለቀው ቀጥሎ ወዳለው የፀሎት ቤት ሄድን ከዛም ርችት እና ክብሪት ከኪሱ አወጣ። በወጣትነ የይዩልኝ ጀግንነት እርችቱን በመውሰድ ጫፉ ላይ ያለውን ረጅም ክር ለኮስኩት። ርችቱ ከመፈንዳቱ በፊት እፍ ብይ አጠፋዋለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ለማጣፋት ስሞክ ጣቶቼን አቃጠልኳቸው ከዛም እርችቱን ጣልኩት። ስቲፋን እና እኔ በድንጋጤ ክሩ መቀጣጠሉን ሲቀጥል ተመለከትን።

ርችቱም በመፈንዳት ሰልፈራዊ ጭስ ሰው የሞላውን አካባቢ እና የፀሎት ቤቱን አጠነው። በየዋህነት ማንም ሰው ልብ አይልም በማለት የርችቱን የተበታተነ ቅሪት በፍጥነት ሰበሰብን እና ጭሱ እንዲወጣ ለማድረግ መስኮቶቹን ከፋፈትን። እንደ እድል ማንም አልተጎዳም እንዲሁም ምንም ነገር አልወደመም።

አባላቱ ወደ ስብሰባው ሲመጡ በጣም የሚሸተውን ሽታ ልብ አሉት። ላለማስተዋል ከባድ ነበር። ሽታው የስብሰባውን የተቀደሰ ባህሪውን ሳብ አዛባ። የአሮናዊ የክህነት ተሸካሚዎች በቁጥር ትንሽ ብቻ በመሆናቸው፣ ራስን ማገልገል ተብሎ በሚገለፅ አስተሳሰብ ቅዱስ ቁርባን ለመካፈል ብቁ እንዳልሆንኩ ቢሰማኝም አሳለፍኩ። የቅዱስ ቁርባኑ ሰሀን ሲዘረጋልኝ ውሃውንም ዳቦውንም አልተቀበልኩም። የሚያሳቅቅ ስሜት ተሰማኝ። ተዋረድኩም፣ እናም ያደረኩት ነገር እግዚአብሔርን እንዳላስደሰተው አወኩኝ።

ከቤተክርስቲያን በኃዋላ፣ የቅርንጫፉ ፕሬዝዳንቱ ፍራንክ ሊንድበርግ፣ ለየት ያለ ሽማግሌ ፀጉሩ ብርማ ሽበት ያለው ሰውዬ ወደ ቢሮው እንድመጣ ጠየቀኝ። ቁጭ ካልኩም በኃዋላ በደግነት እይታ አየኝ እናም ቅዱስ ቁርባን እንልተካፈልኩ እንዳየ ነገረኝ። ለምን ሲል ጠየቀኝ። ለምን እደሆነ እንዳወቀ ጠረጠርኩ። ምን እንዳደረኩ ሁሉም ሰው እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነበርኩ። ከነገርኩት በኃዋላ ምን እንደተሰማኝ ጠየቀኝ። በእንባ ንግግሬ ቁርጥ ቁርጥ እያለ እንዳዘንኩ እና እግዚአብሔርን እነዳስከፋሁተ ነገርኩት።

ጵሬዘደንት ሊንድበርግ በደንብ የተነበበ የትምህርት እና ቃል ኪዳን መፅሐፍ ከፈቱና የተጠቀሱ ቁጥሮችን እንዳነብ ጠየቁኝ። የሚቀጥለውን ድምጼን ከፍ አድርጌ አነበብኩኝ፥

“እንሆ እርሱ ለሀጢያቶቹ ንሰሀ የገባ ይቅር ተብሏል እና እኔ ጌታ ዳግም አላስታውሳቸውም።

“በዚህ ሰው ንሰሀ መግባቱን ታውቃላችሁ እነሆ ይናዘዛቸዋል እናም ይተውታልም።”3

አንብቤ ስጨርስ ቀና ብዬ ያየሁትን የፕሬዝዳንት ሊንድበርግ በፍቅር የተሞላ ፈገግታ መቼም አረሳውም። በስሜት እኔ ቅዱስ ቁርባን መካፈሌን መጀመር እንዳለብኝ እንደሚሰማው ነገረኝ። ከቢሮውም እንደወጣሁ መግለፅ የማይቻል ደስታ ተሰማኝ።

እንደዚህ ያለ ደስታ የንሰሀን ውጤት ነው። ንሰሀ የምትለው ቃል “ካለፈ በኋላ ማስተዋልን” ያሳስባል እናም ለውጥን” ያመላክታል።4 በሲውድን ቋንቋ ቃሉ omvänd ነው፣ ይህም “ በቀላሉ ዞሮ መመለስ” ማለት ነው።5 የክርስቲያን ፀሀፊ ሲ. ኤስ. ሊውስ ስለመቀየር መንገዶች እና አስፈላጊነት ጽፏል። ንስሀ የሚቀጥለውን ያካትታል ሲል ገልጻል፥ “ወደ ትክክለኛው መንገድ ዳግም መመለስን የተሳሳተ ድምር ማስተካከል ይቻላል ይህም ሊሆን የሚችለው ስህተቱ እስኪገኝ ድረስ በቀላሉ በመመለስ ብቻ ነው እናም ከስህተቱ ጀምሮ እንደገና በመስራት ነው እንጂ መቼም ቀጥሎ በመሄድ አይደለም”6 ባህሪያችንን መቀየር እና ወደ “ትክክለኛው መንገድ” መመለስ የንሰሀ አንድ አካል ናቸው፣ ግን ግማሽ አካል ብቻ ናቸው። እውነተኛ ንሰሀ ማለት ልባችንን እና ፍቃዳችንን ወደ እግዚአብሔር መመለስ እና ኃጢያትን በይፋ መተውን ያካትታል።7 በሕዝቅኤል ላይ እንደተብራራው “ንሰሀ ማለት ከኃጢያት ተመልሶ ፍርድን እና ቅንን ማድረግ መያዣውንም መመለስ በህይወትም ትዕዛዝ መሄድ፣ ምንም ኃጢያትንም አለመስራት ነው።”8

ሆኖም ግን ያልተሟላ መግለጫ ነው። ንሰሀን ቀላል የሚያደርገውን ሀይል፣ የአዳኛችን የሀጢያት ክፍያ በስነስረዓት አይገልፀውም። እውነተኛ የሀጢያት ክፍያ በጌታ በክርስቶስ ላይ አምነትን ያካትታል፣ እኛን እሱ እንደሚቀይረን እምነት፣ እኛን ይቅር እንደሚለን እምነት እና ጥፋቶችን እንድናስወግድ እንደሚረዳን ማመን። ይህን አይነት እምነት የእርሱን የኃጢያት ክፍያ በህይወታችን ላይ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ያደርጋል። “ከዛም በኃላ ስንገነዘብ” እባ በአዳኙ እርዳታ “ስንመለስ” በእርሱ ቃልኪዳኖች ተስፋ ይሰማናል እና የእይቅር ባይነቱም ደስታ ይሰማናል። ያለአዳኙ በንሰሀ የሚመጣው ተስፋማነት እና ደስተኛነት ይጠፋሉ፣ እናም በቀላሉ አሳዛኝ የባህሪ ማስተካከያ ብቻ ይሆናል። ነገር ግን በእርሱ ላይ እምነትን በማዳበር ወደ እርሱ ይቅር ማለት ብቃት እና ችሎታ መቀየር እንችላለን።

ፕሬዝዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር ይህንን ተስፋማ የንሰሃን ቃልኪዳንን በሚያዚያ 2015 (እ.አ.አ) በዚህ መጨረሻ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያረጋግጡልናል። በግማሽ ክፍለ ዘመን በሐዋሪያነት አገልግሎቱ ካገኘው አውቀት የተጠለለ ብዬ የማስበውን የአዳኙን ፈዋሽ ሀይል የሆነውን የሀጢያት ክፍያ ገልጾታል። ፕሬዝዳንት ፓከር እንዲህ አሉ፥ የሀጢያት ክፍያው ምንም አይነት ዱካ ወይም ምንም የሚያያዘውን ነገር አይተውም። የተጠገው ተጠግኗል። … ይፈውሳል እናም የተፈወሰውም እንደተፈወሰ ይቀራል።”9

ሲልም ቀጠለ፥

“እያንዳዳችን የራሱ የሚያደርገን የሀጢያጥያት ክፍያ ምንም ጠባሳን አይዝም። ይህም ማለት ምንም ብናደርግ ወይንም የትም ሆነን ቢሆንም ወይም በምን አይት መልኩ ቢሆንም አንድነገር የተከሰተው በእውነት ንሰሀ ከገባን አዳኙ ለእኛ እንደሚሰቃይ ቃል ገብቶልናል። እናም እርሱም ሲሰቃይ ያንን ይደመድመዋል …

“የሀጢያት ክፍያው ማንኛውንም እድፍ ምንም ከባድ ቢሆንም ምንም ያህል ጊዜ በያልፈውም ወይም ምንም ያህል ቢደጋገም እድፉን ያነፃዋል።”10

የአዳኙ የሀጢያት ክፍያ ለእኔ እና ለእናንተ ለመዘርጋት ስፋት እና ጥልቀት ስፍር የለውም። ነገር ግን መቼም በላያችን ላይ እንደ ግዴታ አይጣልብንም ። ነብዩ ሊሀይ እንዳብራራው በበቂሁኔታ ከተማራችሁ በኃላ የሁሉም ሰው ታላቅ አማላጅ በሆነው “መልካምን ከክፉ ለማወቅ”11 “ነፀነትን እና ዘላለማዊ ህይወትን ወይንም እስርን እና ሞትን ለመምረጥ ነጻ ነን።”12 በሌላ ቋንቋ ንሰሀ ምርጫ ነው።

አንዳንዴ ለየት ያለ ምርጫን ልንመርጥ እንችላለን እናም እናደርጋለን። አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ምርጫዎች ትክክለ ያልሆኑ ላይመስሉ ይችላሉ ነገር ግን በትክክል ንሰሀ እንዳንገባ ያደርጉናል እናም ትክክለኛውን ንሰሀን እንዳንከተል ያግደናል። ለምሳሌ ሌሎች ላይ ለማሳበብ ልንመርጥ እንችላለን። እንደ 12 አመቴ በጎትበርግ፣ ስቲፋን ላይ ማሳበብ እችል ነበር። በመጀመሪያ ደረጃ እሱ ነው ትል እርችቱን እና ክብሪት ይዞ ወደ ቤተክርስቱያን የመጣው። ነገር ግን በሌሎች ማሳበብ ትክክል ቢሆንም እንኳ። የራሳችንን ባህሪ እንድንሸፍን ያደርገናል። ይህን በማድረግ የራሳችን ድርጊት ሀላፊነት ወደሌሎች ሰዎች እናደርጋለን። ሀላፊነት ወደ ሌላ ሰው ሲዘዋወር ለመተግበር ያለንን ችሎታ እና አስፈላጊነት እናጠፋለን። የራሳችንን ድርጊት ማድረግ ከሚችል ወኪል እራሳችንን ወደ ምስኪን ተጠቂ እንቀይራለን።13

ንሰሀን ከሚያግዱ ሌላኛው ምርጫ የራሳችንን ጥፋት መቀነስ ነው። በጎትበርግ በርችቱ አደጋ ማንም ሰው አልተጎዳም ዘለቄታዊነት ያለው ጥፋትም አልደረሰም ስብሰባውም ተካሂዶ ነበር። ንሰሀ ለመግባት ምንም ምክንያት የለም ለማለት ቀላል ነበር። ነገር ግን ስህተታችንን መቀነስ ምንም እንኳ ወዲያው ግልጽ ውጤት ባይኖረውም ለመለወጥ ያለውን መነሻሻም ያሶግደዋል። ይህ አስተሳሰብ ስህቶቻችን እንዲሁም ሀጢያቶቻችን ዘላላማዊ ውጤት እንዳላቸው ለማየት እንዳንችል ያደርጉናል።

ግን እግዚአብሔር ምንም ብናደርግ ስለሚወደን ሀጢያታችን ምንም አይደለም ብለን እንድናስብ ይስበናል። ኒሆር ለዛራሄምላ ሰዎች ሲል ያስተማረውን “ሁሉም የሰው ዘር በመጨረሻው ዘመን መዳን አለባቸው መፍራትም መንቀጥቀጥም አይገባቸውም እናም በመጨረሻም ሁሉም ሰው ዘላለማዊ ህይወት ሊኖረው ይባል።”14 ለማመን ሊፈትነን ይችላል። ይህ አታላይ ሰሃብ ውሸት ነው። እግዚአብሐር ይወደናል። ሆኖም ግን እኛ ምናደርገው ነገር ለእሱና ለእኛ ያሳስበዋል እንዴት መሆን እንዳለብን ግልፅ የሆነ መመሪያዎች ሰጥቶናል እነዚህን ትዕዛዛት ብለን እንጠራቸዋለን የእሰን ድጋፍ እና የእኛ ዘላለማዊ ህይወት በእኛ ባህሪ ይወሰናል ይህም በትህትና እውነተኛ ንሰሀን በፍቃደኝነት መሻትን ያካትታል።15

በተጨማሪ፣ እግዚአብሔርን ከትዕዛዛቱ ለመለየት ስንመርጥ ያለትክክለኛ ንሰሀ እንጓዛለን። ከዚህ በኃላ ቅዱስ ቁርባን ቅዱስ ባይሆን ንሮ ለጎትበርግ የቅዱስ ቁርባን ስነስረዓት የርችቱ ረባሽ ሽታ አያሳስብም ነበር። እግዚአብሔር የትዕዛዛት አመንጪ መሆኑን በሀጣናዊ ባህሪያቶች እንዳንሽር እንዳንዘርዝ ልንጠነቀቅ ይገባል። እውነተኛ ንሰሀ የአዳኙን መለኮታዊነት እና የእርሱን የኃለኛውን ቀን ስራ እውነተኛነት መገንዘብን ይጠይቃል።

ሰበብ ከመፈለግ ይልቅ ንሰሀን እንምረጥ። በንሰሀ አማካኝነት፣ እንደ ጠፋው ልጅ፣16 ወደ እራሳችን መምጣት እንችላለን እና ወደ ዘላለማዊ የድርጊታችን ጠቋሚ መመልከት። ሀጢያታችን እዴት ዘላለማዊ ደስታችን ላይ ተጽዕኖ እንዳለው ስንረዳ እውነተኛ ንሰሀ የገቡ ሰዎች መሆን ብቻ ሳይሆን የተሻልንም ለመሆን እንጥራለን። ፈተናዎች ሲያጋጥሙን በዊሊያም ሼክስፒር ቃላቶች እራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን፥

የምፈልገውን ማገኝ ከሆነ፣ ምን ድል ይኖረኛል?

ህልም፣ እስትንፋስ፣ የሞላ ደስታ።

ማነው የአንድ ደቂቃ ደስታን ለሳምንት ለቅሶ የሚገዛ?

ወይስ አንድ አሻንጉሊት ለማግኘት ዘላለማዊነት እንሸጣለን?17

ለአሻንጉሊት ብላችሁ የዘላለማዊነትን እይታ ካጣችሁ ንሰሀ ለመግባት መምረጥ እንችላለን። በክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ ምክንያት ሌላ እድል አለን። በምሳሌም፣ ምክርን በመቃወም የገዛነውን መጫወቻ እናስወግድ እናም የዘለአለም ተስፋን እንቀበል። እንዳብራራው፣ “ሁሉም ሰው ንሰሀ እንዲገባና ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ እነሆ አዳኛችሁ በስጋ ሞትን ተሰቃየ ስለዚህ የሰዎችን ህመም በሙሉ ተሰቃየ።”18

የሀጢያታችንን ዋጋ ስለከፈለ እየሱስ ክርስቶስ ይቅር ማለት ይችላል።19

ቤዛችን ካለው መወዳደር ከማይችለወል ፍቅር፣ ምህረት እና ርህራሄ የተነሳ ይቅር ማለትን ይመርጣል።

አዳኛችን ይቅር ለማለት ይፈልጋል ምክንያቱም ይህ ከእርሱ መለኮታዊ ባህሪ አንዱ ነውና።

እናም፣ እንደ መልካም እረኛነቱ፣ ንስሀ ለመግባት ስንመርጥ ደስተኛ ነው።20

ለድርጊታችን እግዚአብሔራዊ ፀፀት ሲሰማን21 ንሰሀ ለመግባት ስንመርጥ ወዲያውኑ አዳኙን ወደ ህይወታችን እንጋብዘዋለን። ነብዩ አሙሌክ እንዳስተማረው ኑ እና ከዚበላይ ልባችሁን አታጠጥሩ እነሆ የደህንነታችሁ ቀን እና ጊዜ አሁን ነው ስለዚህ ንሰሀ ከገባችሁ እና ልባችሁን ካላጠጠራችሁ ወዲያውኑ የመዳን እቅዱ ወደ እናንተ ይመጣል።22 ለድርጊቶቻችን እግዚአብሔራዊ ፀፀት ሊሰማን ይችላል በተመሳሳይ የአዳኙን እርዳታ ስለሚኖረን ደስታ ሊሰማን ይችላል።

ንሰሀ መግባታችን በራሱ የወንጌሉ ጥሩ ዜና ነው!23 የወንጀለኝነት ስሜት ይወገዳል።24 በደስታ መሞላት እንችላለን፣ ለጢያታችን መሰረየት እንቀበላለን እና የህሊና ሰላምም ማግኘት እንችላለን።25 ከተስፋ መቁረጥ ስሜት እና ከሀጢያት በርነት ነፃመሆን እንችላለን። በእግዚአብሔር ድቅ ብርሀን በመሞላት “ህመም ላይሰማን” ይችላል።26 በአዳኙ ምክንያት ንሰሀ መግባት ቀላል ብቻ ሳይሆን ደስ የሚያሰኝ ነው። ከርችቱ ክስተት በኃላ በቅርንጫፉ ፕሬዝዳንት ቢሮውስጥ የተሰማኝ ስሜት እስካሁን ትዝ ይለኛል። ይቅር እንደታባልኩ አውቄ ነበር። የወንጀልኛነት ስሜቴ ጠፋ የደስታ ስሜቴ ተነሳ እናም ልቤ ብርሀን ተሰማው።

ወንድሞች እና እህቶች ይህንን ጉባኤ ስንጨርስ በህይወታችሁ ውስጥ የበለጠ ደስታ እንዲሰማችሁ እጋብዛትኃለሁ፤ ደስታ የእሱስ ክርስቶስ የሀጢያት ክፍያ እውነት ከመሆኑ እውቀት፤ ደስታ በአዳኙ ችሎታ፣ ፍቃደኝነት እና ይቅር ለማለት ካለው ፍላጎት እንዲሁም ደስታ ንሰሀ ለመግባት ከመምረጥ። የአዳኙን መመሪያ እንከተል “በደስታ ውሀውንም ከመድሀኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።”27 ካለፈ በኃላ ሀጢያታችን መተው ልባችንን እና ፍቃዳችን አዳኙን ለመከተል ለማዞር እንምረጥ። የህያውነቱን እውነታ እመሰክራለሁ። እኔ ተወዳዳሪ ስሌለውን የርህራሄውን፣ ምህረቱ እና ፍቅሩ ምስክር እና ተቀባይ ነኝ። የሚያድነው የኃጢያት ክፍያው አሁን የእናንተ እንዲሆን–እና በተደጋጋሚም በህይወታችሁ በሙሉ፣28 ለእኔ እንደነበረው፣ እንዲሆንላችሁ እጸልያለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሽማግሌ ፐር ጎስታ ማልም (1948–2016) ከ2010 (እ.አ.አ) እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ እንደ አጠቃላይ ባለስልጣን አገልግለዋል። በጆንኮፒንግ፣ ስዊድን ቢወለዱም፣ እርሳቸው እና ባለቤታቸው፣ አገንታ፣ የኖሩት በጎትንቦርግ፣ ስዊድን ነበር። በጥቅምት 2010 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ንግግራቸው፣ ሽማግሌ ማልም ደግሞም ስለ ጎትንብርግ ትዝታቸውን ተናግረው ነበር። (see “Rest unto Your Souls,” Liahona, ህዳር 2010 (እ.አ.አ) 101–2)።

  2. ምንም እንኳን ስቲፋን የጓደኛዬ ትክክለኛው ስሙ ባይሆንም ታሪኩ የተነገረው ፍቃድ በመቀበል ነው።

  3. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 58፥42–43

  4. የግሪክ ምታኖ የሚለው ቃል ካለፈ በኃላ ማስተዋል ማለት ነው (ሜታ በኃላ ለውጥ ደግሞ ኖውዮ ማስተዋል ኖውስ አእምሮ የፍሬ ነገሮች ነፀብራቅ ነው። (see James Strong, The New Strong’s Expanded Exhaustive Concordance of the Bible [2010], Greek dictionary section, 162)።

  5. የእኔ omvänd. Om ትርጉም እንደ “በዙሪያ” ተብሎ ትርጉም ሊኖረው ይችላል። Vänd “መዞር” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

  6. C. S. Lewis, The Great Divorce (1946), 6. በመፀሀፉ መግቢያ ላይ ሊዊስ እዲህ አለ አንዳንዶች ከሰማይን እና ከሲኦል አንዱን ወይም ሌላኛውን ከመምረጥ ይልቅ ሁለቱን አንድ ለማድረግ ይጥራሉ። እሱ እደዚህም ይላል አንዳንዶቻችን እድገት ወይም ማስተካከያ ወይም ማሻሻያ ክፋትን ወደ ጥሩ ይቀይራል ብለን እናስባለን። ይህ አይነቱ እምነት አደገኛ ስህተት ነው ብዬ እወስደዋለሁ። እኛ የእያንዳንዱ መንገድ መስመር ከተከተልናቸው ሁሉም ቀስ በቀስ በመቀራረብ በመጨረሻ ወደ አንድ መአከል ወደ ሚመጣበት አለም አይደለም የምንኖረው። …

    ትክክል ያልሆነን መንገድን የመረጡ ሁሉ ይጠፋሉ ብየ አላስብም፤ ነገርግን የነሱ መዳን ግን ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመልሶ መምጣትን ያካትታል። ክፉን መፍታት እንችላለን ነገር ግን ወደ ጥሩ ነገር መሻሻል አይችልም። ጊዜ አይፈውሰውም። ትንሽ በትንሽ የድግምት ቁስል መፈወስ አለበ ካልሆነ አይሆንም” (5–6)።

  7. See Bible Dictionary, “ንስሀ” ይመልከቱ።

  8. ሕዝቅኤል 33፥14–15

  9. የፕሬዝዳንት ቦይድ ኬ. ፓከር በሚያዝያ 2005 (እ.አ.አ) ጉባኤ ጋር በማበር በነበረው የአመራር ስብሰባ ላይ የሰጡት ምስክርነት አልታተመም። እነዚህ ንግግሮች በጊዜው ከተያዘ የግል ማስታወሻ ላይ የተወሰዱ ናቸው።

  10. ቦይድ ኬ. ፓከር “የደህንነት እቅድ፣” Liahona፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)።

  11. 2 ኔፊ 2፥5

  12. 2 ኔፊ 2፥27

  13. 2 ኔፊ 2፥26 ይመልከቱ።

  14. አልማ 1፥4። ኒሆር እና ተከታዮቹ ስለንስሀ አያምኑም ነበር (አልማ 15፥15 ተመልከቱ)።

  15. ረስል ኤም. ኔልሰን፣ “Divine Love፣” Liahona፣ የካቲት 2003 (እ.አ.አ) ይመልከቱ።

  16. ሉቃስ 15፥17 ይመልከቱ፤ በተጨማሪ ቁጥር 11–24 ይመልከቱ።

  17. ውልያም ሼክስፒር The Rape of Lucrece, lines 211–14።

  18. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 18፥11

  19. ኢሳይያስ 53፥5 ይመልከቱ።

  20. አልማ 5፥21፣ 27ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥-13 ይመልከቱ።

  21. እውነተኛ ንሰሀ “እግዚአብሔራዊ ፀፀትን” ያካትታል (2 ቆሮንጦስ 7፥10)። ሽማግሌ ኤም. ራስል እንዲህ ብለው አስተማሩት፥ “መንገዳቸውን ለሳቱ ሰዎች አዳኙ መመለሻ መንገድ አዘጋጅቷል። ነገር ግን ያለህመም አይሆንም። ንሰሀ ቀላል አይደለም ጊዜ ይወስዳል፤ የሚያም ጊዜ።” (“Keeping Covenants,” Ensign, May 1993, 7). ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስካት በተጨማሪ እንዳስተማሩት፣ “አንዳንድ ጊዜ የንሰሀ እርምጃዎች መጀመሪያ ላይ ከባድ እና ህመም ያለባቸው ይሆናሉ” (“Finding Forgiveness,” Ensign, May 1995)። እግዚአብሔራዊ ፀፀት እ ህመም በንሰሀ ሂደት ውስጥ ሲካተቱ በጊዜ ሂደት የሚመጣው ውጤት ለሀጢያት ምህረት ማግኘት ስሜት ደስ የሚያሰኝ ነው።

  22. አልማ 34፥31፤ አተኩሮት ተጨምሯል።

  23. Bible Dictionary, “Gospels” ይመልከቱ።

  24. ኢኖስ 1፥6

  25. ሞዛያ 4፥3 ይመልከቱ።

  26. ሞዛያ 27፥29

  27. ኢሳይያስ 12፥3

  28. ሞዛያ 26፥29–30 ተመልከቱ። እግዚአብሔር በነጻ ምሀርት ለመስጠት ቃል ቢገባም፣ አዳኝ በምህረት ንስሀ መግባትን ቀላል እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት በፍላጎት ማጥፋት በእግዚአብሔር ፊት አስቀያሚ ነው (ዕብራውያን 6፥4–610፥26–27)። ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንዳሉት፥ “በድሮ መጥፎ ምርጫ ያደረጉትን ለማስወገድ ለሚፈልጉት ለማንኛቸውም የሚያስደስት ዜና ያለው ጌታ ደካማነትን ካመጸው በተለየ ሁኔታ እንደሚመለከት ማወቅ ነው። ግን ንስሀ የማይገባ አመጽ ቅጣት እንደሚኖረው ቢያስጠነቅቅም፣ ጌታ ስለደካማነት ሲናገር፣ ይህን የሚለው በምህረት ነው” (“Personal Strength through the Atonement of Jesus Christ,” Liahona, Nov. 2013, 83)።