2010–2019 (እ.አ.አ)
እርሱም ይጠናከር ዘንድ
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


እርሱም ይጠናከር ዘንድ

ለግርማዊ አገልግሎታቸው ለማዘጋጀት ሌሎችን ከፍ ለማድረግ ያለንን ጥሪአች ተነስተን እንድንቀበል ጸሎቴ ነው።

የእግዚአብሔር ክህነትን ከያዙ ጋር በዚህ ስብሰባ በመገኘቴ በረከት ይሰማኛል። የእነዚህ ጎልማሳ ሰዎች እና ወንድ ልጆች አምልኮ፣ እምነት፣ እና ራስ ወዳጅ ያልሆነ አገልግሎት የዚህ ዘመን ታዕምራት ነው። በዚህ ምሽት የምናገረው፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልብ በማገልገል አንድ ለሆኑት ለክህነት ተሸካሚዎች፣ ለወጣቶችና ለሸመገሉት ነው።

በክህነት ሀላፊነታቸው በብቁነት ለሚያገለግሉ የክህነት ባለስልጣኖች ሁሉ ጌታ ሀይሉን ይሰጣል።

ዊልፈርድ ዎድረፍ፣ እንደ ቤተክርስቲያኗ ፕሬዘዳንት፣ በክህነት ስልጣኖች ውስጥ ስለነበራቸው አጋጣሚ እንዲህ ገልጸዋል።

“በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስብከትን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማሁ። በሚቀጥለው ቀንም ተጠመቅኩኝ። … እንደ አስተማሪ ተሾምኩኝ። የሚስዮን አገልግሎቴም ወዲያው ተጀመረ። … በሚስዮን አገልግሎቴ በሙሉ ያሳለፍኩት እንደ አስተማሪ ነበር። … በጉባኤ እንደ ካህን ተሾምኩኝ። … እንደ ካህን ከተሾምኩኝ በኋላ ወደ ደቡብ አገር ለሚስዮን አገልግሎት ተላኩኝ። ያም በልግ 1834 (እ.አ.አ) ነበር። ከእኔም ጋር የአገልጋይ ጓደኛ ነበረ፣ እናም ያለ ኮረጆም ከረጢትም ነበር የጀመርነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮች ተጓዝን ወንጌልንም ሰበክን፣ እናም ለማረጋገጥ የማልችል ብዙ የጠመቅኳቸው ነበሩ፣ ምክንያቱም እኔ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ካህን ብቻ ነበርኩኝና። … እንደ ሽማግሌ ከመሾሜ በፊት ወንጌል በመስበክ ለጊዜ በጉዞ ላይ ነበርኩኝ። …

“[አሁን] Iለሀምሳ አራት አመታት የአስራ ሁለት ሐዋሪያት አባል ነበርኩኝ። ከዚያ እና ከሌሎች ቡድኖች ጋር ለ60 አመት እጓዝ ነበር፤ በዚህ ለተሰበሰቡት ይህን ለማለት እፈልጋለሁ፣ የአስተማሪ ሀላፊነት እያለኝ፣ እና በወይን አትክልት ስፍራ ላይ እንደ ካህን ሳገለግል፣ እንደ ሐዋርያ እንደነበረኝ ያህል በእግዚአብሔር ሀይል እደገፍ ነበር። ሀላፊነታችንን እስካከናወንን ድረስ በዚህ ምንም ለውጥ የለም።”1

ያም ለውጥ እንደሌለው የሚያሳይ መንፈሳዊ የመከሰት ሁኔታ በሀሳብ የቀረበው ጌታ የአሮናዊ ክህነትን እንደ መልከጸዴቅ ክህነት “ተጣባቂ” ብሎ በሚገልጽበት ነው።2ተጣባቂ የሚለው ቃል ትርጉም ሁለቱ የተያያዙ ናቸው የሚል ነው። ይህም ግንኙነት፣ በዚህ አለም እና ለዘለአለም፣ ክህነት ለመሆን ለሚችልበት ሀይል እና በረከት አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ይህ “ያለ መጀመሪያ ቀናት እና መጨረሻ አመታት ነውና።”3

ይህም ግንኙነት ቀላል ነው። የአሮናዊ ክህነት ወጣት ሰዎችን ለተጨማሪ ቅዱስ ታማኝነት ያዘጋጃቸዋል።

“የከፍተኛው፣ ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት፣ ሀይል እና ስልጣን በቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ በረከቶች ላይ ሁሉ ቁልፎችን መያዝ ነው—

“በተጨማሪም፣ የመንግስተ ሰማያትን ሚስጥራት ለመቀበል ልዩ መብት እንዲኖረው፣ ሰማያት ለእነርሱ እንዲከፈቱላቸው፣ ከበኩሩ ቤተክርስቲያንና ከአጠቃላይ ተሰብሳቢዎች ጋር እንዲገናኝ፣ እና ከእግዚአብሔር አብ እና ከአዲስ ኪዳን መካከለኛ ከሆነው ከኢየሱስ ጋር መገናኘትን እና በእነርሱም መገኘት ለመደሰት ነው።”4

እነዚያ የክህነት ቁልፎች በዚህ ጊዜ በሙሉ የሚጠቀምበት አንድ ሰው ነው፣ ይህም የጌታ ቤተክርስቲያን ፕሬዘደንት እና የሊቀ ካህናት መሪ ነው። ከዚያም፣ በፕሬዘደንቱ በመወከል፣ እያንዳንዱ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያለው ሰው በሁሉን ቻይ ስም ለመናገር እና ለመስራት ስልጣን እና ልዩ መብት በመንፈስ በረከት ይሰጠዋል። ለዚህ ሀይልም መጨረሻ የለውም። ይህም በህይወት እና በሞት፣ በቤተሰብ እና በቤተክርስቲያን፣ በእግዚአብሔር በራሱ ታላቅ ፍጥረት እና በዘላለም ስራው ጉዳይ ላይ የሚመለከት ነው።

ጌታ የአሮናዊ ክህነት ባለስልጣኖችን በእምነት፣ በሀይል፣ እና በምስጋና በግርማዊው የመልከ ጼዴቅ ክህነት ውስጥ እንደ ሽማግሌ እንዲያገለግሉ እያዘጋጀ ነው።

ለሽማግሌዎች፣ የክህነት አገልግሎታችሁን በሙሉ ለማከናወን ጥልቅ ምስጋና በጣም አስፈላጊ ነው። ከፍተኛ ክህነት የነበራቸው በክህነት ጉዞአችሁ ከፍ ለማድረግ እና ለማበረታታት ሲደርላችሁ የነበሩትን የዲያቆን፣ የአስተማሪ፣ ወይም የካህን ጊዜአችሁን ታስታውሳላችሁ።

የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያላቸው ሁሉ እንደዚህ አይነት ትዝታ አላቸው፣ ነገር ግን የምስጋና ስሜት በአመታት ትደበዝዝ ይሆናል። ተስፋዬ ይህን ስሜት ለማነሳሳት እና በዚህም ያላችሁን በሙሉ የተቀበላችሁትን አይነት እርዳታ እናንተ ለመስጠት እንድትችሉ የልብ ውሳኔ እንዲደረግ ለማድረግ ነው።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ በክህነት ሀይል ለመሆን የምችልበት እንዳለኝ ይመስል እንደተመለከኝ አስታውስ ነበር። ክህን እያለሁ አንድ እሁድ ጠራኝ። አንዳንድ የአጥቢያ አባላትን አብሬው እንድጎበኝ እንደሚፈልገኝ ነገርኝ። ለውጤታማነቱ እኔ በጣም አስፈላጊ እንደሆንኩኝ አይነት አስመሰለው። እኔ ለዚህ አስፈላጊ አልነበርኩም። በኤጲስ ቆጶስ አመራኡ ውስጥ በጣም ጥሩ አማካሪዎች ነበሩት።

ብዙ ገንዘብ የሌላቸው እና የተራቡ መበለትን ጎበኘን። ልባቸውን ለመንካት፣ የገንዘብ ወጪአቸውን እንዲቆጣጠሩ ለመጠየቅ፣ እና ራሳቸውን ለመንከባከብ ብቻ ሳይሆን ሌሎችን ለመርዳት ወደሚችሉበት ለመድረስ እንደሚችሉ የተስፋ ቃል ለመስጠት እንድረዳው ፈልጎ ነበር።

በሚቀጥለውም በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚኖሩ ሁለት ትትንሽ ሴት ልጆችን ለማፅናናትም ሄድን። ከዚያ ወጥተን ስንሄድም፣ በጸጥታ ኤጲስ ቆጶሱ እንዲህ አለኝ፣ “እነዚያ ልጆች ወደ እነርሱ እንደመጣን በምንም አይረሱም።”

በሚቀጥለው ቤት ውስጥ፣ እንዴት ተሳታፊ ያልሆነውን ሰው የአጥቢያ አባላት እንደሚፈልጉት በማሳመን ወደ ጌታ እንዲመጣ እንዴት እንደሚጋበዝ አየሁ።

ያም ኤጲስ ቆጶስ እይታዬን ከፍ ያደረገ እና በምሳሌ እንድሻሻል ያደረገኝ የመልከ ጼዴቅ ክህነት የያዘ ነበር። በጌታ አገልግሎት የትም ለመሄድ ሀይል እና በብርቱነት እንዲኖረኝ አስተማረኝ። ወደ ሽልማቱ ከሄደ ረጅም ጊዜ ሆኗል፣ ነገር ግን እርሱን አሁንም አስታውሳለሁ ምክንያቱም አጋጣሚ ያልነበረኝ የአሮናዊ ክህነት ያዝ በነበርኩበት እኔን ለማንሳት ደርሷልና። በኋላም፣ በእይታ ከነበረኝ በላይ፣ በወደፊት በታላቅ የክህነት ሀላፊነቶች መንገድ ላይ እንደተመለከተኝ አወቅኩኝ።

አባቴም እንዲህ አይነት ነገር ለእኔም አድርጎ ነበር። እርሱም ጥበባዊ እና የተለማመደ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያዥ ነበር። አንድ ጊዜ ስለ ምድር እድሜ የሳይንስ ወረቀት እንዲጽፍ በሐዋርያ ተጠይቆ ነበር። አንዳንዶች ምድር የሳይንስ መረጃ ከሚያሳየው በታች በጣም በእቅሜ የቀነሰች እንደሆነይ የሚያምኑ እንዳሉ በማወቅ፣ በጥንቃቄ ጻፈው።

አባቴ የጻፈውን ሰጥቶኝ እንዲህ ያለኝን አሁንም አስታውሳለሁ፣ “ሀል፣ ይህን ለሐዋሪያት እና ነቢያት መላክ እንደሚገባኝ ለማወቅ የመንፈስ ጥበብ አለህ።” ወረቀቱ ያለው ምን እንደነበር በብዙም ዓላስታውስም፣ ነገር ግን ራሴ ለማየት የማልችለውን መንፈሳዊ ጥበብ ለመተመለከተልኝ ለመልከ ጼዴቅ ክህነት ያዢ የተሰማኝ ምስጋና ለዘለአለም በውስጤ እይዘዋለሁ።

አንድ ምሽት፣ ከትንሽ አመታት በኋላ፣ እንደ ሐዋርያ ከተሾምኩኝ በኋላ፣ የእግዚአብሔ ነቢይ ጠሩኝ እናም ስለቤተክርስቲያኗ ትምህርት የተጻፈውን እንዳነብ ጠየቁኝ። የመፅሐፍ ምዕራፍን በማንበብ ምሽትን አሳልፈው ነበር። በመሳም እንዲህ አሉኝ፣ “ይህን ሁሉ ለመጨረስ አልቻልኩም። እኔ እየሰራሁ እያለሁ አንተ ማረፍ አይገባህም።” ከዚያም አባቴ ከአመታት በፊት የተጠቀመውን ቃላት ተጠቀሙ፥ “ሀል፣ ይህን ማንበብ የሚገባው አንተ ነህ። ይህን ለማተም ትክክለኛ እንደሚሆን አንተ ታውቀዋለህና።”

ያም የመልከ ጼዴቅ ባለስልጣኖች እይታን ከፍ የማድረግ እና ልበ ሙሉነት የመስጠት ንድፍ የመጣው በቤተክርስቲያኗ በተደገፈው የንግግር በአል ጊዜ ነበር። በ17 አመቴ፣ ለብዙ አድማጮች ንግግር እንዳደርግ ተጠይቄ ነበር። ከእኔ ምን እንደሚጠበቅ አላወቅኩም ነበር። ርዕስ አልተሰጠኝም ነበር፣ እና ስለዚህ ስለወንጌሉ ከማውቀው በላይ የሆነ ንግግር አዘጋጀሁኝ። ስናገርም፣ ስህተት እንደሰራሁ ተረዳሁ። ከተናገርኩኝ በኋላ፣ የወደቅሁ እንደሆንኩኝ የነበረኝ ስሜትን አሁንም አስታውሰዋለሁ።

የሚቀጥሉት እና የመጨረሻው ተናጋሪ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንቆ አባል ሽማግሌ ማቲው ኮንሊ ነበረ። ታላቅ ተናጋሪ ነበሩ—በቤተክርስቲያኗም የተወደዱ። በንግግር ማቅረቢያው አጠገብ ባለው መቀመጫዬ ላይ ሆኔ እሳቸውን ስመለከት አስታውሳለሁ።

በሀይለኛ ድምጽ ጀመሩ። ንግግሬ በታላቅ ጉባኤ ውስጥ እንደሚገኙ እንዲሰማቸው እንዳደረገ ተናገሩ። ይህን ሲሉም ፈገግ ብለው ነበር። የውድቀት ስሜቴ አልፎ ሄደ እናም አንድ ቀን እርሳሸው እንደሆንኩ የሚያስቡትን አይነት ለመሆን ልበ ሙሉነትም ተከተለ።

የዚያ ምሽት ትዝታም አሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ሲናገር በጥንቃቄ እንዳዳምጥ አሁንም ይመራኛ። ሽማግሌ ካውን ለእኔ ባደረጉት ምክንያት፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ሁልጊዜም እጠብቃለሁ። በብዛትም ቅር አይለኝም እናም በብዙ ጊዜም እገረማለሁ፣ እናም ሽማግሌ ካውሊ እንዳደረጉትም ፈገግ ማለትን ላቆመው አልችልም።

ወጣት ወንድሞቻችንን ብዚ ነገሮች በክህነት ውስጥ ከፍ እንዲሉ ይረዳቸዋል፣ ነገር ግን በክህነት አገልግሎታቸ የእግዚአብሔር ሀይልን እንዲጠቀሙበት እምነት እና ልበ ሙሉነት እንዲያድጉ እኛ ከምንረዳቸው በላይ ሀይል ያለው ምንም የለም።

ከሁሉም በላይ ታላቅ ስጦታ ባለው የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ ከፍ በመደረግ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ያም እምነት እና ልበ ሙሉነት አብሮአቸው የሚቆይ አይደለም። በእነዚህን ሀይሎች መጠቀም በክህነት ተጨማሪ ልብድ ባላቸው በሚመጡት በብዙ የልበ ሙሉነት አገላለጽ የሚያድጉ መሆን አለባቸው።

የአሮናዊ ክህነት ተሸካሞዎች ደግሞም የየቀኑ እና እንዲሁም የየሰዓቱ ማበረታቻዎች እና ማስተካከያዎች ከጌታ ራሱ በመንፈስ ቅዱስ በኩል መቀበል ያስፈልጋቸውል። ያም ለእነርሱ የሚገኘው እነርሱ ለዚህ ብቁ ለመሆን ሲመርጡ ነው። ይህም እነርሱ በሚያደርጉት ምርጫ ላይ የሚመካ ነው።

ለዚህ ነው የታላቁ የመልከ ጼዴቅ ክህነት መሪው የንጉስ ቤንያምን ቃላት በምሳሌ እና በምስክርነት ማስተማር ያለብን።5 እነዚህም ክህነቱ የእርሱ በሆነው በጌታ ስም የተነገሩ የፍቅር ቃላት ናቸው። ንጉስ ቢንያም የጌታን ማበረታቻ እና ማስተካከያ ለመቀበል ንጹን በመሆን ለመቆየትከእኛ ምን እንደሚጠበቅብን አስተምሪ ነበር።

“እናም በመጨረሻም፣ ኃጥያት ልትፈፅሙ የምትችሉባቸውን ነገሮች ሁሉ ልነግራችሁ አልችልም፤ ምክንያቱን መቁጠር የማልችለው ብዙ መንገዶችና ዘዴዎች ስለሚኖሩ ነው።

“ነገር ግን ይህን ያህል ልነግራችሁ እችላለሁ፣ እራሳችሁን፣ ሀሳባችሁንና፣ ቃላችሁን፣ እናም ድርጊታችሁን የማታስተውሉና፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የማትጠብቁ፣ እናም የሚመጣውን ጌታችንን በተመለከተ የሰማችሁትን እስከ ህይወታችሁ መጨረሻ በእምነት የማትቀጥሉ ከሆናችሁ፣ መጥፋት ይገባችኋል። እናም አሁን፣ ሰው ሆይ፣ አስታውስ፣ እናም አትጥፋ።”6

የጻድቅ ጠላት ፍላጻዎች እንደ መጥፎ ንፋስ በጣም በምናፈቅራቸው ወጣት ካህናት ላይ እየተላኩ እንዳሉ እናውቃለን። ለእኛ እነርሱም ራሳቸውን የሔላማን ልጆች ብለው እንደጠሩት እንደ ጎልማሳ ጀግኖች ይመስሉናል። እንደ እነዚያ ወጣት ጀግኖችም፣ ንጉስ ቢንያም እንዲያደርጉ ባበተታታቸው መንገድ ራሳቸውን በደህንነት ከጠበቁ፣ ለመዳን ይችላሉ።

የሔላማን ወንድ ልጆች በምንም አልተጠራጠሩም። በጀግንነት ተዋጉ እናም አሸናፊ ሆኑ ምክንያቱም የእናታቸውን ቃላት አምነው ነበርና።7 የምታፈቅር እናት እምነት ሀይልም እንረዳለን። እናቶች ዛሬ ለወንድ ልጆቻቸው ታላቅ ድጋፌ ይሰጣሉ። እኛ ባለ ካህናትም ስንቀየር ወደ ወንድሞቻቸን በመድረስ እንድናጠናከር ላለን ሀላፊንት መልስ ለመስጠት በልብውሳኔ በማድረግ በዚያ ድጋፌ ላይ መጨመር እንችላለን፣ እናም አለብን።8

ጸሎቴም እያንዳንዱ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ በጌታ የተሰጠውን እድል እንዲቀበል ነው።

“እናም በመካከላችሁ አንዱ ሰው በመንፈሱ ጠንካራ ቢሆን፣ በቅንነት እንዲታነጽ፣ ደግሞም ጠንካራ ይሆን ዘንድ፣ ከእርሱ ጋር ደካማ የሆነውን ይውሰድ።

“ስለዚህ፣ ከእናንተ ጋር በአነስተኛው ክህነት የተሾሙትን ውሰዱ፣ እናም ቀጠሮም ያድርጉ፣ እናም መንገድንም እንዲያዘጋጁላችሁ፣ እናም እናንተ ራሳችሁ ልታከናውኑት የማትችሉትን ቀጠሮ ያሟሉላችሁ ዘንድ በፊታችሁ ስደዷቸው።

“እነሆ፣ ይህም በቀደሙት ጊዜያት ሐዋሪያቴ ቤተክርስቲያኔን የገነቡበት መንገድ ነው።”9

እናንተ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚ የክህነት መሪዎች እና አባቶች ታዕምራት ለመስራት ትችላላችሁ። የታማኝ ካህናት ሰልፍን ወንጌልን ለመስበክ ያለን ጥሪ በሚቀበሉ እና በልበሙሉነት ይህን በሚያከናውኑ ወጣቶች ለሞምላት ጌታን ለመርዳት ትችላላችሁ። ከፍ ያደረጋችኋቸውን እና በታማኝነት እንዲቆዩ፣ በቤተመቅደስ እንዲያገቡ፣ እና በተራም ሌሎችን ከፍ እንዲያደርጉ እና እንዲያዘጋጁ ያበረታታችኋቸውን ታያላችሁ።

ይህም አዲስ የመሳተፊያ ፕሮግራም፣ የተሻሻለ ማስተማሪያዎች፣ ወይም የተሻለ የህዝብ መተላለፊያ ዘዴ አያስፈልገውም። አሁን ካላችሁ ጥሪ በላይ ምንም አያስፈልገውም። የክህነት መሀላ እና ቃል ኪዳን ሀይል፣ ስልጣን፣ እና መመሪያ ይሰጣችኋል። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍል 84ውስጥ የሚገኘውን የክህነት መሀላ እና ቃል ኪዳን ወደ ቤት ሄዳችሁ በጥንቃቄ እንድታጠኑት ጸሎቴ ነው።

ተጨማሪ ወጣት ወንዶች እንደ አሮናዊ የክህነት ተሸካሚ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በሚቀይር ሀይል ለማስተማር እንደቻሉት እንደ ዊልፈርድ ዎድረፍ አይነት አጋጣሚ እንዲኖራቸው ሁላችንም ተስፋ አለን።

ለግርማዊ አገልግሎታቸው ለማዘጋጀት ሌሎችን ከፍ ለማድረግ ያለንን ጥሪአች ተነስተን እንድንቀበል ጸሎቴ ነው። እኔን ከፍ ላደረጉትን እና ሌሎችን እንዴት እንደማፈቅር እና ከፍ እንደማደርግ ላሳዩኝ በልቤ በሙሉ አመሰግናቸዋለሁ።

ፕሬዘደንት ቶምስ ኤስ.ሞንሰን የክህነት ቁልፎችን በሙሉ በምድር ላይ አሁን እንደያዙ እመሰክራለሁ። በህይወት ሁሉ አገልግሎታቸው እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ ሌሎችን ከፍ የማድረግ ምሳሌ እንደነበሩም እመሰክራለሁ። እኔን ከፍ ላደረጉኝ እና ሌሎችን እንዴት ከፍ እንደማደርግ ስላሳዮኝም የግል ምስጋና አለኝ።

እግዚአብሔር አብ ህያው ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህችም ቤተክርስቲያኑ እና መንግስቱ ናት። ይህም የእርሱ ክህነት ነው። ስለዚህም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በኩል ለራሴ አውቃለሁ። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።