2010–2019 (እ.አ.አ)
የአምልኮት በረከቶች
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


የአምልኮት በረከቶች

ለመንፈሳዊ ህይወታችን አምልኮ ዋና እና አስፈላጊ ነው። ልንጓጓው፣ ልንፈልገው እና ለመሞከር የምንጥረው ነገር ነው።

የእርሱ ጉብኝት

በቅዱሳን መፅሐፍት ውስጥ ተፅፎ ያለ አንዱ ድንቅ ተሞክሮ አዳኙ ከሞት እና ከትንሳኤው በኋላ በአሜሪካ ያሉትን ህዝብ ሔዶ መጎብኘቱ ነው። ህዝቡ ታላቅ ጥፋትን ከመቀበላቸው የተነሳ “ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ እንድትለወጥ”1 አደረገ። የነዛ ክስተቶች በዝገብ እንደሚያመለክተው ከድንገተኛው ጥፋት በኋላ ህዝቡ ያለማቋረጥ እንዳነቡ2 እና በጥልቅ ሀዘናቸው ሰዓት ፈውስን፣ ሰላምን እና መዳንን ተራቡ።

አዳኝ ከሰማይ ሲወርድ፣ ሰዎቹ ሁለት ጊዜ በእግሩ ላይ ወደቁ። የመጀመሪያው ጊዜ የተከሰተው እርሱ በመለኮታዊ ስልጣን ካስተዋወቀ በኋላ ነበር፤

“እነሆ ነብያት ወደ ዓለም ይመጣል ብለው የመሰከሩልኝ እኔ እየሱስ ክርስቶስ ነኝ።

“እና እነሆ እኔ የዓለም ብርሀን እናም ህይወት ነኝ።”3

የነበሩትን በመጋበዝ ተነሱ እና ወደ እኔ ኑ እናም ደግሞ የችንካሩ ምልክት በእጆ እም በእግሮቼ ላይ ትዳስሱ ዘንድ እጃችሁንም በጎኔ አስገቡት ስለዚህ እኔ የእስራኤል አምላክ መሆኔንም እናም የምድር ሁሉ አምላክ መሆኔን እናም ለዓም ሀጢያም መገደሌን ታውቃላችሁ። …

እናም ሁሉም በሄዱ እናም ለየራሳቸው በመሰከሩ ጊዜ በአንድነት እንዲህ ሲሉ ጮሁ፡

“ሆሳዕና! የሀያሉ አምላካችን ስም የተባረከ ይሁን!4

ከዛም ለሁለተኛ ጊዜ በኢየሱስ እግር ስር ወደቁ።” ነገር ግን እንደተማርነው በዚህ ጊዜ እርሱን በማምለክ አላማ ነበር።”5

በአሁን ጊዜ

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በምዕራብ አሜሪካ አንድ ካስማ እንድጎበኝ ተመድቤ ነበር። የተለመደ እሁድ፣ በተለመደው ማምለኪያ ቦታ እናም የተለመዱት የቤተክርስሪያን አባላት ነበሩ። ሰዎች ወደ ማምለኪያው ቦታ ሲገቡ እና በስነስረዓት ወደ ክፍት መቀመጫወች ሲያቀኑ አየሁ። በመጨረሻው ሰከንድ፣ ማሾክሾክ በመላ አዳራሹ አስተጋባ። እናቶች እና አባቶች— አንዳንዴ በከንቱ —ሀይል የተላበሱትን ልጆች ዝም ለማሰኘት ሞከሩ። የተለመደ ነው።

ነገር ግን፣ ስነስረዓቱ ከመጀመሩ በፊት በመንፈስ የተነሳሱ ቃላት ወደ አይምሮዬ መጡ።

እነዚህ አባሎች ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ወይም ተናጋሪዎችን ለማዳመጥ ብቻ አይደለም የመጡ።

የመጡት ለጥልቅ እና ለበለጠ ጠቃሚ ምክንያት ነው።

ለማምለክ መጥተዋል።

ስብሰባው እንደቀጠለ ከታዳሚው ውስጥ የተለያዩ አባላትን ተመለከትኩ። የሰማይ የሚመስል ገፅታ፣ የአክብሮት እና የሰላም ባህሪ ነበራቸው። የሆነ ነገራቸው ልቤን አሞቀው። እነርሱ የዛን እለት እሁድ የነበራቸው ተሞክሮ ለየት ያለ ነበር።

እያመለኩ ነበር።

ሰማይን እያጣጣሙ ነበር።

ከፊታቸው ማየት እችል ነበር።

ከእነርሱ ጋር አወደስኩ እናም አመለኩ። እና ይህንን ሳደርግ መንፈስ ለልቤ ተናገረ። እናም በዛ ቀን፣ ስለራሴ ስለ እግዚአብሔር እና ትክክለኛ አምልኮ በህይወታችን ላይ ስላለው ሚና አንድ ነገር ተማርኩ።

አምልኮ በየቀን ህይወታችን ውስጥ

በቤተክርስቲያን ጥሪ ውስጥ ማገልገልን በተመለከተ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ለየት ያሉ ናቸው። አንዳንዴ ግን ስራን ከመስራት ብቻ እየቆጠርነው፣ ስራችንን በልማዳዊ ድግግሞሽ እናደርገዋለን። አንዳንዴ ስብሰባዎቻችን ላይ ስንገኝ ወይም በመንግስቱ ግልጋሎታችን ላይ ቅዱስ የሆኑ የአምልኮ ነገሮች ሊጎለን ይችላል። እና ያለዚያ ደግሞ፣ መነጻፀር ከማይችለው የአፍቃሪው የሰማይ አባት ልጆች በመሆናችን ከምናገኘው ማለቂያ የሌለውን መንፈሳዊ አጋጣሚ ጎሎናል።

ድንገተኛ፣ የደስታ አጋጣሚ ከመሆን በራቀ መልኩ አምልኮ አስፈላጊ ነው እናም ለመንፈሳዊ ህይወታችን ማዕከል ነው። ልንጓጓው፣ ልንፈልገው እና ለመሞከር የምንጥረው ነገር ነው።

አምልኮ ምንድን ነው?

እግዚአብሔርን ስናመልክ፤ ስነሰርአት በተሞላበት ፍቅር፣ በትህትና እናም በአድንቆት ወደ እርሱ እንቀርባለን። ሃያል ንጉስ፣ የህዋ ፈጣሪ፣ ተወዳጅ እናም ዘላለማዊ አፍቃሪ አባታችን መሆኑም እንቀበላለን።

እናከብረዋለን እናም እናወድሰዋለን።

እራሳችንንም ለእርሱ እንሰጣለን።

ልባችንንም ሀያል በሆነ ጸሎት ከፍ እናረጋለን፣ ቃሉንም ዋጋ እንሰጠዋለን፣ በጸጋው ደስ ይለናል፣ እናም በታማኝነት እርሱን ለመከተል እራሳችንን እንሰጣለን።

በኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ህይወት ውስጥ እግዚአብሔርን ማምለክ አስፈላጊ ነገር ሲሆን እኛ በልባችን እርሱን መቀበል ሳንችል ስንቀር፣ በምክክራችን ላይ፣ በቤተክርስትያን ውስጥ፣ እናም በቤተመቅደስ ውስጥ በከንቱ እንፈልገዋለን።

እውተኛ ተከታዮቹ “ቀን እና ማታ የጌታን ስም እየጠሩ— ሰማይንና፣ ምድርን፣ባህርን እናም የውሃን ምንጭ የሰራውን ወደ ማምለክ ይሳባሉ።”6

ምናልባትም ከእኛ በጣም ከማይለዩ ሰዎች—አጋጣሚ፣ ባህሪ መለኮታዊ አመልኮ—ሌሎች እንዴት እንደሚያመልኩ በማጤን ብዙ መማር እንችላለን።

አድንቆት፣ ምስጋና፣ እናም ተስፋ

በ19ኛው ክፍለ ዘመን በመጀመርያው ክፍል፤ በክርስትያኑ አለም እግዛብሔር ሰውን አሁንም ያናግራል የሚለውን ሃሳብ ትተውታል። ነገረ ግን በጸደዩ 1820 ላይ ትሁቱ አርሶ አደር ወንድ ልጅ ጫካ ውስጥ ገብቶ ተንበርክኮ ከጸለየ በኃላ ያ ለዘላለም ተቀየረ። ከዛች ቀን በኃላ በሚጥለቀለቅ አስደናቂ ህልም፣ ራዕይ፣ እንዲሁም ሰማያዊ ገጽታ ምድርን አጠባት፤ ዝርያዋን ደግሞ ስለ እግዛብሔር ተፈጥሮ እና መለኮት እናም እሱ ከሰው ጋር ስላለው ግኑኝነት ድንቅ የሆነ እውቀትን ተለገሰች።

ኦሊቨር ካውድሪ እነዛን ቀናቶች “መቼም የማይረሱ” ብሎ ገለፀ። … ምን አይነት ሀሴት! ምን አይነት አስገረሚ የሆነ! ምን አይነት ድንቅ ነገር!”7

የኦሊቨር ቃላቶች የመጀመርያ የመለኮታዊ ንጉሳዊ የሆነ የአድንቆት ስሜት እንዲሁም ታላቅ የሆነ ምሰጋናን ሀሳብን ይገልጻል።

ሁል ጊዜም በተለይ ደግሞ በሰንበት ቀን፣ አስደናቂ የሆኑ አድሎች አሉን ገረሚ እና ድንቅ ሰማያዊ ልምዶች እንዲሁም ለቸርነቱ እንዲሁም መግለጽ ከምንችለው በላይ ለሚያሳየን ምህረቱ ምስጋናን ለማቅረብ ልዩ እድል አለን።

ይህ ደግሞ ወደ ተስፋ ይመራናል። እነዚህ ናቸው የመጀመርያዎቹ የአምልኮ ስርአቶች።

ብርሃን፣እውቀት፣ እና እምነት

በዛ በተባረከው በ ፔንቴቆስጥ ቀን መንፈስ ቅዱስ በእየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዘምራኑ ላይ በብርሃንና በእውቀት እየሞላቸው በልባቸው እና በአእምሩአቸው ውስጥ ገብቶ ነበር።

እስከዛች ቀን ድረስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እርግጠኛ አልነበሩም። ለአዳኙ ተከታዮች ኢየሩሳአሌም በጣም አደገኛ ስፍራ ሆነች እናም እነሱም እጣ ፈንታቸው ምን እንደሆነ ያስቡ ነበር።

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ልባቸውን በሞላበት ሰአት፤ ጥርጣሬ እና ግትርነትም ከእነርሱ ጠፋ። በመጠቀው የእውነተኛ አምልኮ ተሞክሮ አማካኝነት፣ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ሰማያዊ ብርሃንን ይቀበላሉ፣ እውቀትንም እናም የታነጸ ምስክርነት ይኖራቸዋል። ይህ ደግሞ ወደ እምነት አምርቷል።

ከዛም ሰኣት አንስቶ፣ ሐዋርያቶቹና ቅዱሳኖቹ በውሳኔ በመመራት ተገበሩ። ክርስቶስ ኢየሱስን ለአለም ሁሉ በቆራጥነት ሰበኩ።

በመንፈስ ስናመልክ፣ በነፍሳችን ላይ ብርሃንና እውነትን እንጋብዛለን፤ይህ ደግሞ እምነታችንን ያጠነክራል። እነዚህም ለእውነተኛ አምልኮ አስፈላጊ ስርዓቶች ናቸው።

ደቀ መዛሙርትነት እና ልግስና

ከመጸሀፈ ሞርሞን ላይ ትንሹ አልማ በራፁ አመፅ ከመጣበት ስቃይ ከዳነ በኃላ ተመልሶ በፊቱ እዳልነበረ እንማራለን። በድፍረት “በምድር ሁሉ ተጓዘ … እና በሁሉም ሰዎች መካከል … ፣ ያለመድከም በቤተክርስቲያኑ ላይ የፈጠረውን ውድመት እያደሰ።”8

ሀያሉ እግዛብሔርን በቀጣይነት ማምለኩ የብርቱ ደቀመዛሙርትነት ቅርፅን ያዘ።

እውነተኛ አምልኮ ቅን እና ታማኝ የሆነውን ተወዳጁ አስተማርያችንን እና አዳኛን ተከታይ ወደ መሆን ይቀይረናል። እንቀየራለን እናም የበለጠ እርሱን እየመሰልን እንመጣለን።

የበለጠ የምንረዳ እንዲሁም አሳቢዎች እንሆናለን። የበለጠ ይቅርባዮች እንሆናለን። የበለጠ ወዳጆች እንሆናለን።

ሌሎችን እየጠላን፣ፊት እየነሳን ወይም እያንቋሸሽን እግዚብሔርን እንወዳለን ማለት የማይቻል ነገር መሆኑን እንረዳለን።9

እውነተኛ አምልኮ ቆራጥ በሆነ የደቀመዝሙር መንገድ እንድንሄድ ብርታት ይሰጠናል። ይህ ደግሞ ወደ የማይቀየር ልግስና ይመራል። እነዚህ በጣም አስፈላጊ የሆኑ የአምልኮ ስርአቶች ናቸው።

ወደ በሩ በምስጋና ግቡ።

ወደዛ ወደ ተለመደው የሰንበት ማለዳ፣ በዛ በማምለኬያ ስፍራ በዛ በተለመደ ካስማ ዞር ብዬ ሳስብ ለዘላለም ህይወቴን የሚባርከው ያ ለየት ያለው መንፈሳዊ ተሞክሮ ዛሬም ልቤን ይነከዋል።

ምንም እንኳ የጊዜያችን፣ የጥሪያችን እና የሀላፊነታችን ምርጥ አስተዳዳሪ ብንሆንም፤ —ምንም እንኳ ፍፁም ግለሰብ፤ ቤተሰብ ወይም መሪ የሚያደርጉን ዝርዝሮችን ብናሟላም፤ በምህረት የተሞላው አዳኛችንን፣ የሰማይ ንጉስ፣ እናም የተከበረው እግዚአብሔርን ማምለክ ባንችል፣ የወንጌሉ ሀሴት እና ሰላም እያመለጠን እንደሆነ ተማርኩ።

እግዚአብሔርን ስናመልከው፣ ልክ ጥንት በአሜሪካ እንደነበሩት ህዝቦች እናውቀዋለን እናም በተመሳሳይ አክብሮት እንቀበለዋለን። መረዳት በማይቻል የመደነቅ ስሜት እንቀርበዋለን። በእግዚአብሔር መልካምነት በምስጋና እንደነቃለን። ስለዚህም፣ ተስፋን እናገኛለን።

ነፍሳችንን በብርሀን እና በእውነት የሚሞላውን የእግዚአብሔር ቃል እናሰላስላለን። በመንፈስ ቅዱስ ብርሀን ብቻ መታየት የሚቻለውን መንፈሳዊ ጉብኝትን እንገነዘባለን።10 በዚህም እምነትን እናገኛለን።

ስናመልክ መንፈሳችን ይታደሳል እናም በተወዳጁ በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ አርአያ ለመከተል ቃል እንገባለን። እና ከዚህ ውሳኔ፣ ልግስናን እናገኛለን።

ስናመልክ፤ ወደተባረከው እግዚአብሔር ጠዋት፣ ቀን እና ማታ ልባችንን በምስጋና እናፈሳለን።

በማምለኪያ ስፍራችን፣ በቤታችን፣ በቤተመቅደስ እና በሁሉ ስራችንን ያለማቋረጥ—እሱን እንቀድሰዋለን እናከብዋለን።

ስናመልክ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ፈዋሽ ሀይል ልባችንን እንከፍታለን።

ህይወታችን የአምልኮ ምልክት እና መገለጫ ይሆናል።

ወንድም እና እህቶቼ መንፈሳዊ ተሞክሮዎች አካባቢያችን ከሚካሄዱ ነገሮች ጋር ምንም አይገናኝም እና በልባችን ከሚካሄዱ ነገሮ ጋር ግን በሁሉም ነገር ይገናኛል። እውነተኛ አምልኮ የተለመደ የቤተክርስቲያ ስብሰባዎችን ወደ ለየት ወዳለ መንፈሳዊ ድግስ እንደሚቀይር ምስክርነቴ ነው። ህይወታችንን ያዳብርልናል፣ አረዳዳችንን ያሰፋልናል እና ምስክርነታችንን ያጠነክርልና። ልባችን ወደ እግዚአብሔር ሲያደላ፤ ልክ የጥንቱ መዝሙረ ዳዊት እንዳለው “ወደ ደጁ፣ ወደ አደባባዮቹ በምስጋና እንገባለን፤ ስለእርሱ አመስጋኝ ነን፣ እናም ስሙን እንባርካለን።

“እግዚአብሔር ቸር፣ ምህረቱም ለዘለአለም፣ እውነቱም ለልጅ ለልጅ ነውና።”11

በእውነት እና ከልብ በመነጨ አምልኮ አማካኝነት በተስፋ፣ በእምነት እና በልግስና እንፈካለን እንዲሁም እንበስላለን። በዚህ ሂደት ውስጥ ህይወታችንን በመለኮታዊ ትርጉም፣ ሁሌም በሚኖር ሰላም እና ዘላለማዊ ደስታ የሚያበራውን ሰማያዊ ብርሀን ወደ ነፍሳችን እንሰበስባለን።

የአምልኮ በረከት ያ ነው። ይህንም በትህትና የምመሰክረው በቅዱሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ ነው።