2010–2019 (እ.አ.አ)
ወደ ማንስ እንሄዳለን?
ጥቅምት 2016 (እ.አ.አ)


ወደ ማንስ እንሄዳለን?

በስተመጨረሻ፣ እያንዳንዳችን ለአዳኝ ጥያቄ መልስ መስጠት አለብን፤ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?”

ከብዙ አመታት በፊት ቤተሰቤ እና እኔ የተቀደሰችዋን ምድር ጎበኘን። ከጉዟችን አንዱ ግልጽ ትውስታዬ፣ በተለምዶ የመጨረሻው የጌታ ማእድ የተደረገበት የኢየሩሳሌም የላይኛው ክፍል ነው።

በዛ ቦታ እንደቆምን፣ ዮሀንስ 17ትን አነበብኩላቸው፣ ይህም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ አባቱን ሲማጸን ያለበት ክፍል ነው፥

“... እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። …

“ከቃላቸው የተነሳ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አለምንም፤

“እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ እንደሆንክ።”1

ይህንን ቃላቶች ባነበብኩ ጊዜ ልቤ በጥልቅ ተነካ እናም ከቤተሰቤ ጋር እና ከሰማዩ አባቴ ጋር እናም ከልጁ ጋር አንድ ላይ እንድሆን በዛው ቅዱስ ቦታ ላይ በመጸለይ እራሴን አገኘሁት።

ከቤተሰቦቻችን፣ ከጓደኞቻችን፣ ከጌታ ጋር እናም በዳግም ከተመለሰው ቤተክርስቲያኑ ጋር ያለን ውድ ዝምድና ከሁሉም በላይ በህይወታችን ጠቃሚ ነው። እነዚህ ዝምድናዎች በጣም ጠቃሚ በመሆናቸው የተነሳ፣ እነርሱም መንከባከብ፣ መጠበቅ እና ማደግ ይገባቸውል።

ልብን ከሚሰብሩ ከቅዱሳን መጽሃፍት ታሪክ ውስጥ አንዱ የተከሰትው “አብዛኞቹ [የጌታ] ደቀ መዘምራን” የሱን ትምህርቶች ለመቀበል ከብዷቸው “ወደኋላ ተመለሱ እናም ከሱም ጋር አብረው አልተጓዙም።2

እነዚያም ደቀ መዛሙርት ሲሄዱ፣ ኢየሱስ ወደ አስራ ሁለቱ ዞረና እንዲህም ጠየቃቸው፣ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?”3

ጴጥሮስም እንዲህ አለ፥

“ጌታ ሆይ፣ ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ።

“እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምነናል፣ አውቀናልም።”4

በዚያች ቅጽበት፣ ሌሎች መቀበል ስላልቻሉት ነገር ላይ ትኩረት ሲያደርጉ፣ ሐዋርያቱ ግን ስላመኑት እና ስላወቁት ነገር ላይ ማተኮርን መረጡ፣ በዚህም ምክንያት ከክርስቶስ ጋር ቀሩ።

ከጊዜ በኋላ፣ በጴንጤቆስጤ በዓል ቀን, አስራ ሁለቱ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተቀበሉ። ስለ ክርስቶስ በሚሰጡት ምስክርነት ላይ ደፋር ሆኑ እናም የኢየሱስን ትምህርቶች በሙሉነት መረዳት ጀመሩ።

ዛሬ ምንም የተለየ አይደለም። ለአንዳንዶች፣ ለማመን እና ለመቅረት የሚጠይቀው የክርስቶስ ግብዣ ከባድ እንደሆነ ይቀጥላል--- ወይም ለመቀበል አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። አንዳንድ ደቀ መዛሙርት አንድ የተወሰነ የቤተክርስቲያን መመሪያ ወይም ትምህርት ለመረዳት ይቸገራሉ። ሌሎች ደግሞ በታሪካችን ውስጥ ወይም ባለፉት ሆነ በጊዜያችን ባሉ አንዳንድ አባላት እና መሪዎች ፍጹም ያለመሆን ስጋት ያድርባቸዋል። አሁንም ሌሎች ደግሞ በጣም የሚጠይቅ ሃይማኖት መኖር አስቸጋሪ ሆኖ ያገኙታል። በመጨረሻም፣ አንዳንዶች “መልካም ሥራን ለመሥራት ተዳክመዋል”5 በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች፣ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት በእምነታቸው ይወላውላሉ፣ ምናልባትም “ወደ ኋላ የተመለሱትን፣ ወደ ፊትም ከኢየሱስ ጋር ያልሄዱትን” ለመከተል በማሰብ።

ከእናንተ ማንም በእምነታችሁ የምታቅማሙ ከሆነ፣ ጴጥሮስ የጠየቀውን ተመሳሳይ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ “ወደ ማን [ትሄዳላችሁ]?” እናንተ ተሳታፊ ላለመሆን ወይም በዳግም የተመለሰውን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት ከመረጣችሁ፣ ወዴትስ ትሄዳላችሁ? ምንስ ታደርጋላችሁ? ከቤተ ክርስቲያን አባላት ጋር እና ከተመረጡ መሪዎች ጋር ”ከእንግዲህ ወዲህ ላለመራመድ” መወሰን አሁን ሊታይ የማይችል የረጅም ጊዜ ተፅዕኖ አለው። የተወሰነ መሠረተ ትምህርት፣ አንዳንድ ፖሊሲ፣ አንዳንድ ትንሽ ታሪክ ሊሆን ይችላል ከእምነታችሁ ጋር የሚቃረናችሁ፣ እናም ውስጣዊ ብጥብጥን ለመፍታት ብቸኛው መንገድ ከቅዱሳን ጋር ”ከእንግዲህ ወዲህ አለመራመድ” ሊሰማቸው ይችላል. እንደ እኔ ረጅም እድሜ የምትኖሩ ከሆነ፣ ነገሮች ራሳቸውን መፍቻ መንገድ እንዳላቸው እያወቃችሁ ትመጣላችሁ። አንድ በመንፈስ የተመራ ማስተዋል ወይም መገለጥ አንድ ጉዳይ ላይ አዲስ ብርሃንን ሊያፈስ ይችላል። የተመለሰው በዳግም የተመለሰው የአንዴ ክስተት አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን እንደሚቀጥል አስታውሱ።

በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተገለጡትን ታላቅ እውነቶች በጭራሽ አትተዋቸው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኙትን የክርስቶስ ትምህርቶችን ማንበብን፣ ማሰላሰልን እናም መተግበርን በጭራሽ አታቁሙ።

ጌታ የገለጠውን ለመረዳት በሐቀኛ ትጋታችሁ ወደ ጌታ እኩል ጊዜ ለመስጠት አትሰናከሉ። ውድ ጓደኛዬ እና የቀድሞ የሥራ ባልደረባዬ ሽማግሌ ኒል ኤ. ማክስዌል እንዳሉት ”አንድ ነገር እኛ ማብራራት ካልቻልን መብራራት አይቻልም ... ብለን ልናስብ አይገባም።”6

ስለሆነም በመንፈሳዊ አደገኛ የሆነውን የመተው ምርጫ ከማድረጋችሁ በፊት፣ ቆማችሁ እና በመጀመሪያ ደረጃ የኢየሱስ ክርስቶስን በዳግም የተመለሰውን ቤተ ክርስቲያን ምስክርነት የሰጣችሁን ነገር በጥንቃቄ እንደታስቡ አበረታታችኋለሁ። ቁሙና እዚህ የተሰማችሁን ስሜት እና ለምን እንደተሰማችሁ አስቡ። መንፈስ ቅዱስ ስለ ዘላለማዊ እውነት የመሰከረላችሁን ጊዜያት አስቡ።

እምነታችሁን በግል፣ በአፍቃሪ ሰማያዊ ወላጆች፣ ወደ ዘላለማዊ መገኛቸው እንድንመለስ የሚያስተምሩን የጋራ እምነት ያላቸውን ሰዎችን ለማግኘት ወዴትስ ትሄዳላችሁ?

ጥሩ ጓደኛ ስለሆነው አዳኝ፣ ለሃጥያታችሁ ብቻ ሳይሆን “በሁሉም አይነት ህመምና ፈተናዎች ” የተሰቃየው “በስጋ አንጀቱም በምህረት ይሞላ ዘንድ፣ በስጋ ህዝቡን ከድካሙ እንዴት እንደሚረዳ ያውቅ ዘንድ”7 እንደማምነው፣ የእምነትን ማጣትን ድካም ጨምሮ ስለተሰቃየው የት ሄዳችሁ ነው የምትማሩት?

ስለ ሰማያዊ አባታችን የዘላለማዊ ደስታ እና ሰላም እቅድ እናም በሚደንቁ አጋጣሚዎች፣ ትምህርቶች እናም ምሪቶች ለሟች እና ለዘላለማዊ ህይወታችን ያለውን እቅድ ለመማር ወዴት ትሄዳላችሁ? የመዳን እቅድ የሟች ህይወትን ትርጉም፣ ዓላማ፣ እና መመሪያ መስጠቱን አስታውሱ።

ጥልቅ የሆነና በመንፈስ በተመራ የቤተ ክርስቲያን አወቃቀር ውስጥ እናንተን እና ቤተሰቦቻችሁን በማገልገል ጌታን ለማገልገል በጥልቅ ቃል በገቡ ወንዶችና ሴቶች የት ሄዳችሁ ነው የምትማሩት እና የምትደገፉት?

ለናንተ ተጨማሪ የምክር፣ የመረዳት፣ የመጽናናት እናም ለጊዜአችን ችግሮች የምሪት ምንጭ ለመሆን በእግዚአብሄር የተጠሩ በህይወት ያሉ ነብያትንና ሃዋሪያትን ለማግኘት የት ነው የምትሄዱት?

እናንተ ከምትጋሯቸው እናም ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ለማሳለፍ የምትፈልጉትን እሴቶች እና መሥፈርቶች የሚኖሩ ሰዎችን ለማግኘት የት ነው የምትሄዱት?

በቤተ መቅደስ ውስጥ ስለሚሰጠው የማዳን ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች አማካኝነት የሚያስገኘውን ደስታ ተሞክሮ ለማግኘት የት ትሄዳላችሁ?

ወንድሞች እና እህቶች፣ የክርስቶስ ወንጌልን መቀበል እና መኖር ተፈታታኝ ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ እንደዚህ ነበር፣ እና መቼም እንዲሁ ይሆናል። ሕይወት ቁልቁለታማ እና አድካሚ የእግር መንገድ እንደሚወጡ ተጓዦች ሊሆን ይችላል። አልፎ አልፎ ትንፋሻችንን ለመሰብሰብ እና ፍጥነት ለመለወጥ የሚያስችል፣ መንገዳችንን ለማስላት እና ፍጥነታችንን ለማስተካከል መንገድ ላይ ለአፍታ መቆም ተፈጥሯዊ እና የተለመደ ነገር ነው። ሁሉም ሰው መንገድ ላይ ቆም የለበትም፣ ነገር ግን የእናንተ ሁኔታ ሲጠይቅ መቆሙ ምንም ስህተት አይደለም። እንዲያውም፣ ይህም በክርስቶስን ወንጌል ሕያው ውኃ ራሳቸውን ለማደስ አጋጣሚውን ሙሉ በሙሉ ለሚጠቀሙ ሰዎች አዎንታዊ ነገር ሊሆን ይችላል።

አንድ ሰው ርቆ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመልቀቅ ከመረጠ አደጋ ይመጣል።8 አንዳንድ ጊዜ መማር፣ ማጥናት እና ማወቅ እንችላለን፣ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ማመን፣ ተስፋ ማድረግ፣ እና እምነታችንን መጣል አለብን።

በስተመጨረሻ፣ እያንዳንዳችን ለአዳኝ ጥያቄ መልስ መስጠት አለብን፤ “እናንተም ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?”9 ሁላችንም ለዚህ ጥያቄ የራሳችንን መልስ መፈለግ አለብን። ለአንዳንዶች፣ መልሱ ቀላል ነው፣ ለሌሎች ደግሞ አስቸጋሪ ነው። እምነት ከሌሎች ይልቅ ለአንዳንዱ በቀላል ለምን እንደሚመጣ እንደማውቅ አላስመስልም። እኛ እነሱን ለማግኘት ካሻናቸው፣ መልሶች ሁልጊዜ እንዳሉ በማወቄ በጣም አመስጋኝ ነኝ ---በእውነተኛ ፍላጎት እና በጸሎት ልብ በሙሉ ዓላማ ፈልጉ ---እኛም በወንጌል መንገድ ላይ ስንቀጥል ለጥያቄዎቻችን መልሶች በመጨረሻ ላይ እናገኛለን። በአገልግሎቴ ውስጥ፣ ስተው እምነታቸው ከተሞከረ በኋላ የተመለሱ ሰዎችን አውቄአለሁ።

የእኔ ልባዊ ተስፋ ብዙ የእግዚአብሄርን ልጆች እንድንጋብዝና የወንጌል ጎዳና ላይ እንዲቆዩ እንዲሁም “ከፍሬዎች ሁሉ በላይ የሚፈለግ [የሆነውን] ፍሬ መካፈል እንዲችሉ” ነው።10

የእኔ ልባዊ ልመና እንድናበረታታ፣ እንድንቀበል፣ እንድንረዳ፣ እንዲሁም ከእምነት ጋር ትግል የሚያደርጉ ሰዎችን እንድናፈቅር ነው። ማንኛውንም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ፈጽሞ ችላ ማለት የለብንም። ሁላችንም በጎዳናው ላይ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ነን፣ እናም በተገቢው መልኩ እርስ በርሳችን አገልግሎት መስጠት ያስፈልገናል።

ልክ ወደ ወንጌሉ አዲስ የተለወጡትን በግብዣ መንፈስ ያለንን ክንዶች እንደምንከፍት ሁሉ፣ እንዲሁ ደግሞ ጥያቄዎች ያላቸውን እና በእምነት የተዳከሙትን ሰዎች መቀበል እና መደገፍ አለብን።

ሌላ የታወቀን ዘይቤ በመጠቀም፣ ማንኛውም ሰው “የጥንቷን የፅዮን መርከብ”፣ እግዚአብሔር እና ክርስቶስ በመቅዘፊያ ላይ የሆኑትን፣ ለመተው ካሰበ ቆሞ በጥንቃቄ ማሰብ አለበት።

ታላቅ አውሎ ነፋስና ማዕበል የጥንቷን መርከብ ቢገፏትም እንኳ፣ አዳኝ ሁልጊዜ ተሳፍሮ እንዳለና እናም ”ሰላም ይሁን” ብሎ አውሎ ንፋሱን ሊገስጽ ይችላል። እስከዚያ ጊዜ ድረስ፣ መፍራት የለብንም፣ እናም የማይናወጥ እምነት ሊኖረንና “እንኳ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት” መሆናቸውን ማወቅ ይገባናል።11

ወንድሞች እና እህቶች፣ እርሱ ቤተክርስቲያኑን ፈጽሞ እንደማይተወን እና እርሱ ከእኛ መካከል አንዳችንንም ፈጽሞ እንደማይተወን በጌታ ስም ቃል እገባላችኋለሁ። ለአዳኝ ጥያቄ እና ቃላት ጴጥሮስ የሰጠው ምላሽ አስታውሱ፥

“ጌታ ሆይ, ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ።

“እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምነናል፣ አውቀናልም።”12

“ በክርስቶስ እና ሁሉን በሚችለው ጌታ ስም ካልሆነ በስተቀር፣ ለሰው ልጆች ደህንነት ሊመጣ የሚችልበት ሌላ ምንም የተሰጠ ስም፣ መንገድ እና ዘዴ” 13 እንደሌለ እመሰክራለሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ዘመን ሐዋርያትና ነቢያትን እንደጠራ እና ቤተ ክርስተያኑን ከትምህርቶቿ ጋር እና ከትእዛዞቿ ጋር፣ የአለም ህዝቦች ንስሃ ካልገቡና ወደሱ ካልተመለሱ የሚያመጣውን “ዐውሎ ነፋስ፣ እና ቁጣ ጋር መጠጊያ እንዲኖረን” እንደመለሰ እመሰክራለሁ።14

በተጨማሪም ጌታ “ሁሉም ወደ እርሱ እንዲመጡ ይጋብዛል፣ ወደ እርሱ የሚመጡትን አይክድም፣ ጥቁርም ነጭም፣ ባሪያውንና ነጻውን፣ ሴትና ወንድን፣ እናም እምነተቢሶችንም ያስባል፣ እናም አይሁድም ሆኑ አህዛብ ለእግዚአብሄር አንድ እንደሆኑ” እመሰክራለሁ።15

ኢየሱስ፣ አዳኝ እና ቤዛ ነው፣ እኛም በወንጌል መንገድ ላይ ከቆየን እና የእርሱን ፈለግ ከተከተልን፣ ዳግም የተመለሰው ወንጌል ወደ ሰማይ ወላጆቻችን ፊት በደህና ይመራናል። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።