2010–2019 (እ.አ.አ)
የእምነት መሰረቶች
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


የእምነት መሰረቶች

ልመናዬም መስዋዕትን እንድናደርግ እና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መሰረቶቻችንን ለማጠናከር የሚያስፈልገው ትህትና እንዲኖረን ነው።

ይህ አስደናቂ አጠቃላይ ጉባኤ ነበር። በእውነትም ተናፅተናል። የአጠቃላይ ጉባኤ ዋና እቅድ ቢኖር፣ በእግዚአብሔር አብ እና በአዳኛችን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እምነትን መገንባት ነው።

ንግግሬ የሚሆነው በዚያ እምነት መሰረቶች ላይ ነው።

እንደ ብዙ ብቁ የሆኑ አላማዎች፣ የግል መሰረቶች የሚገነቡት አንድ ደለልን፣ አንድ አጋጣሚን፣ አንድ ፈተናን፣ አንድ መሰናከልን፣ እና አንድ ውጤታማነትን በተራ በማለፍ ነው። በጣም የሚወደደው የግል አጋጣሚ የህጻን ልጅ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ይህን ማየት የሚያስደንቅ ነው። በፊት ላይ የሚያተው—የልብ ውሳኔ፣ የደስታ፣ የመደንገጥ፣ እና የማከናወን—ውድ አመለካከት የሚያነሳሳ ክስተት ነው።

በቤተሰባችን ውስጥ፣ በደንብ የሚታወስ እንደዚህ አይነት የሆነክስተት አለ። ታናሹ ወንድ ልጃችን አራት አመት ሲሆነው፣ ወደቤት ገባ እና በደስታ ለቤተሰቡ በታላቅ ኩራት እንዲህ ብሎ አሳወቀ፥ “አሁን ሁሉንም ለማድረግ እችላለሁ። ማሰር፣ መንዳት እና መቆለፍ እችላለሁ።” ጫማውን ለማሰር፣ ሶስት ጎማ ያለው ቢሽክሌቱን መንዳት፣ እና ካፖርቱን መቆለፍ እንደሚችል እንደሚነግረን ገባን። ሁላችንም ሳቅን ግን ለእርሱ በጣም ታላቅ የሆኑ ያከናወናቸው ነገሮች እንደሆኑ ተረዳን። እርሱ በእውነትም እንደደረሰ እና እንዳደገ አስቦ ነበር።

የአካል፣ የአዕምሮ፣ እና የመንፈስ እድገት ብዙ አንድነት አላቸው። የሰውነት እድገት በቀላሉ የሚታይ ነው። የምንጀምረው በህጻን እርምጃዎች እና ቀን በቀን፣ አመት በአመት፣ በማደግ የመጨረሻ የሰውነት ቁመታችን ላይ እንደርሳለን። ለእያንዳንዱ ሰው እድገት የተለያየ ነው።

ታላቅ አትሌትን ወይም የሙዚቃ ተጫዋችን ስንመለከት፣ ያ ሰው ታላቅ ስጦታ ያለው ነው እንላለን፣ በአብዛኛው ጊዜ ይህም እውነት ነው። ነገር ግን አፈጻጸሙ በብዙ አመቶች ዝግጅት እና መለማመድ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። አንድ በጣም ታዋቂ ጸሀፊ፣ ማልከም ግላድዊል፣ ይህን የ10 ሺህ ሰአታት ህግ ብሎ ጠርቶታል። በአትሌትነት፣ በሙዚቃ ጨዋታ፣ በትምህርት ብቁነት፣ በልዩ የስራ ሙያዎች፣ በህክምና ወይም በህግ ባለሙያነት፣ ዘወትር እንዲህ ያህል ልምምዶች አስፈላጊ እንደሆኑ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል። ከተመራማሪ ባለሙያዎች አንዱ እንዳለው “በማንኛውም ነገር የአለም ታዋቂ ባልሙያ ለመሆን የ10 ሺህ ሰዓቶች ልምምድ አስፈላጊ ነው።”1

ብዙ ሰዎች ከፍተኛውን የሰውነት እና የአዕምሮ ችሎታን ለማግኘት ዝግጅት እና ልምምድ አስፈላጊ እንደሆነ አውቀዋል።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በተጨማሪ የአለማዊ ትምህርትን በሚያቅፍ አለም ውስጥ፣ የበለጠክርስቶስን መሰል ወደመሆን የሚጸና እምነት የሚመራ መሰረትን ለመመስረት አስፈላጊ የሆነውን መንፈሳዊ እድገት ላይ አነስተኛ ትኩረት ተደርጓል። ልብ በሚማርክ መንፈሳዊ መረጃ ጊዜዎች ላይ ትኩረት እንሰጣለን። እነዚህም በልባችን እና በአዕምሮአችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ልዩ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን የሚመሰክርበት እንደሆነ የምናውቅበት ውድ ጊዜዎች ናቸው። በእነዚህ ድርጊቶች እንደሰታለን፤ በምንም መንገድ መቀነስ የለባቸውም። ነገር ግን ለሚጸና እምነት እና የመንፈስ ቅዱስ የማይቀየር ግንኙነት እንዲኖር፣ ከሰውነት እና ከዓዕምሮ እድገት ጋር የሚመሳሰል የግል የሀይማኖት ስነስርዓት ጸባይን የሚተካ ምንም ነገር የለም። እንዳንዴ የህጻን እርምጃን ከሚያመሳስሉ በእነዚህ አጋጣሚዎች መገንባት ይገባናል። ይህን የምናደርገው ለቅዱስ ቁርባን ስብሰባ፣ ለቅዱሳት መጻህፍት ጥናት፣ ለጸሎት፣ እና በጥሪ ለማገልገል ቆራጥ ውሳኔ ሲኖረን ነው። በቅርቡ ለ13 ልጆች አባት ለነበረው የሙት ታሪክ ላይ፣ እርሱ “ለየቀኑ ጸሎት እና የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት የነበረው ታማኝነት በልጆቹ ላይ ታላቅ ተፅዕኖ ኖሮት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማይነቃነቅ የእምነት መሰረት ሰጥቷቸዋል”2 በማለት ሀተታ ተሰጥቷል።

በ15 አመቴ የነበረኝ አጋጣሚ ለእኔ መሰረት ነበር። ታማኟ እናቴ በህይወቴ ውስጥ የእምነት መሰረት እንዲኖረኝ ለመርዳት በጀግንነት ሞክራለች። በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ፣ በመጀመሪያ ክፍል፣ በወጣት ወንዶች፣ እና በሴምነሪ ተሳተፍኩኝ። መፅሐፈ ሞርሞንን አንብቤአለሁ እና ሁልጊዜም በግሌ እፀልይ ነበር። ውዱ ታላቅ ወንድሜ የሙሉ ጊዜ ሚስዮን አገልግሎትን ለመቀበል በሚያስብበት ጊዜ በቤተሰባችን ውስጥ አስደናቂ ድርጊት መጣ። ድንቁ አባቴ፣ ተሳታፊ ያለሆነ የቤተክርስቲያኗ አባል፣ ትምህርቱን እንዲቀጥል እና በሚስዮን እንዳያገለግል ፈለገው። ይህም ያለመስማማት ምክንያት ሆነ።

ከወንድሜ ጋር በነበረ የሚያስደንቅ ውይይት፣ እርሱ በአመስት አመት የሚበልጥ ነገር እና ውይይቱን መርቷል፣ በሚስዮን የሚያገለግልበት ውሳኔ የሚወሰነው በሶስት ጉዳዮች እንደሆነ አጠቃለልን፥ (1) ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ነውን? (2) መፅሐፈ ሞርሞን እውነት ነውን? (3) ጆሴፍ ስሚዝ የዳግም መመለስ ነቢይ ነውን?

በዚያ ምሽት በልብ ስጸልይ፣ መንፈስ የእነዚህ ሶስት ጥያቄዎች እውነተኝነትንን አረጋገጠልኝ። በህይወቴ በሙሉ የማደርጋቸው እያንዳንዱ ውሳኔዎች በእነዚህ ሶስት ጥያቄዎች መልስ ላይ የተመሰረቱ እንደሚሆኑ ተገነዘብኩኝ። በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አስፈላጊ እንደሆነም ተረዳሁ። ስለዛም ጊዜ ሳስብ፣ መጀመሪያ በእናቴ ምክንያት፣ በዚያ ምሽት የመንፈስ ማረጋገጫን ለማግኘት መሰረቶች ተጥለው እንደነበረ አወቅኩኝ። ምስክርነት ያለው ወንድሜ በሚስዮን ለማገልገል ወሰነ እና በመጨረሻም የአባቴን ድጋፍ አገኘ።

መንፈሳዊ መመሪያ የምንቀበለው በሚያስፈልግበት ጊዜ፣ በጌታ ሰዓት እና በእርሱ ፈቃድ በኩል ነው።3 መፅሐፈ ሞርሞን፥ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት በጣምጥሩ ምሳሌ ነው። በቅርቡ የመፅሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያ እትምን አይቼ ነበር። ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉሙን ያጠናቀቀው በ23 አመቱ ነበር። ስለድርጊቱ እና በትርጉም ስለተጠቀመባቸው መሳሪያዎች አንዳንድ ነገሮች እናውቃለን። በ1830 (እ.አ.አ) በመጀመሪያ እትም ውስጥ፣ ጆሴፍ አጭር መግቢያ ጨመረ እናም “በእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል”4 በኩል እንደተተረጎመ በግልጽ አወጀ። ለትርጉም የረዱት፣ የገላጭ ድንጋዮች፣ ኡሪም እና ቱሚምስ? እነርሱ አስፈላጊ አልነበሩምን፣ ወይስ ጆሴፍ የበለጠ ቀጥተኛ ራዕይ ለመቀበል አስፈላጊ የሆነውን እምነት እስከሚለማመድ ድረስ በቢስክሌት ላይ እንዳለ የማሰልጠኛ ጎማዎች ነበሩ?5

ምስል
የ1830 (እ.አ.አ) የመፅሐፈ ሞርሞን መሸፈኛ
ምስል
የ1830 (እ.አ.አ) የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ

የሰውነት ወይም የአዕምሮ ችሎታን ለማግኘት የተደጋገመና የዘለቀ ጥረት እንደሚያስፈልግ፣ ለመንፈሳዊ ጉዳይም እንዲህ አይነትም እውነት ነው። ነቢዩ ጆሴፍ ሰሌዳዎችን ለመቀበልለመዘጋጀት ከአንድ ጎበኚ፣ ከመሮኒ፣ አንድ አይነት መልእክት ለአራት ጊዜ ተቀበለ። በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች በየሳምንቱ መሳተፍ በሙሉ ያለረዳናቸው የመንፈስ አንደምታ አለው። ቅዱሳት መጻህፍትን—አንዳንዴ ከማንበር—በየጊዜው ማሰላሰል ጥልቀት የሌለው መረጃን ህይወትብ በሚቀይር እምነታችንን በሚያሳድግ ለመቀየር ይቻላል።

እምነት የሀይል መሰረት ነው። በምሳሌ ላብራራላችሁ፥ እንደ ወጣት ሚስዮን፣ ታላቅ የሚስዮን ፕሬዘደንት6 በታላቅ ተፅዕኖ ባለው ሁኔታ ለ12 አመት ደም መፍሰስ ስለነበረባት እና ያላትን በሙሉ ሊያድኗት በማይችሉ ሀኪሞች ስላጠፋች ሴት በሉቃስ 8 ውስጥ ከሚገኘው ታሪክ ጋር አስተዋወቀኝ። እስከዚህ ቀን ድረስ የምወደው የቅዱስ መጻህፍት ጥቅስ ነው።

እርሷ የአዳኝን ልብስ ጫፍ እንኳ ከነካች እንደምትፈወስ እምነት እንደነበራት ታስታውሳላችሁ። ይህን ስታደርግ፣ ወዲያው ተፈወሰች። ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብሮ ይሄድ የነበረው አዳኝ፣ “የዳሰሰኝ ማን ነው?” አለ።

የጴጥሮስ መልስም ሁሉም አብረው እየሄዱ ከእርሱ ጋር እየተገፋፉ እንደሆነ ነበር።

“ኢየሱስ ግን፣ አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ።”

ዋናው ቃል ሀይል ነው። በስፓኒሽ እና በፖርቱጋልኛ፣ ይህም እንደ “ሀይል” ተተርጉሟል። ነገር ግን ይህም ቢሆን፣ አዳኝ አላያትም፤ እርሷ በምትፈልገው ላይ አላተኮረም። ነገር ግን እምነቷ እንዲህ ሆኖ የልብስ ጫፍን በመንካት ከእግዚአብሔር ልጅ የመፈወስ ሀይል ለመሳብ ቻለች።

አዳኝ ለእርሷ እንዲህ አላት፣ “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ።”7

ይህን ታሪክ በጎልማሳ ህይወቴ በሙሉ አሰላስዬዋለሁ። ወደ ወዳጅ የሰማይ አባት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የምናደርገው የግል ጸሎታችን እና ልመናችን እኛ ለመረዳት ከምንችለው በላይ የሆኑበረከቶች በህይወታችን ውስጥ ለማምጣት እንደሚችሉ ተገነዘብኩኝ። የእምነት መሰረት፣ ሴቷ ያሳየቸው አይነት እምነት፣ የልባችን ታላቅ ፍላጎት መሆን ይገባዋል።

ቢሆንም፣ የእምነት የመጀመሪያ መሰረት፣ እንዲሁም ከመንፈስ ማረጋገጫ ጋር፣ ፈተናዎች አያጋጥሙንም ማለት አይደለም። ወደ ወንጌል መቀየር ችግሮቻችን በሙሉ መፍትሄ ያገኛሉ ማለት አይደለም።

የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ እና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የተመዘገቡት ራዕዮች የእምነት መሰረቶችን የመመስረት እና እያንዳንዱ ሰው የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች መቋቋምን የሚያሳዩ ግሩም ምሳሌዎችን ይዘዋል።

የከርትላንድ ቤተመቅደስ መፈጸም የቤተክርስቲያኗ በሙሉ መሰረት ነበር። ይህም የተከናወነው በመንፈስ መፋሰስ፣ በትምህርት መገለፅ፣ እና ቤተክርስቲያኗን ለመመስረት አስፈላጊ ቁልፎችን በዳግም በመመለስ ነበር። በጴንጠቆስጤ ቀን የጥንት ሀዋሪያት እንዳደረጉት፣ ብዙ አባላት ከከርትላንድ ቤተመቅደስ መመረቅ ጋር የተገናኙ አስደናቂ የመንፈስ አጋጣሚዎችን አገኙ።8 ነገር ግን፣ በህይወታችን እንደሚሆነው፣ እነርሱ ወደፊት ሲገፉ ፈተናዎች ወይም ችግሮች አያጋጥሟቸውም ማለት አይደለም። ነፍሳቸውን የሚፈትን በዩናይትድ ስቴት ውስጥ በነበረው የገንዘብ ችግር—የ1837 መሸበር—ያጋጥማቸው እንደነበር የመጀመሪያው አባላት አያውቁም ነበር።9

ከዚህ የገንዘብ ችግር ጋር የተያያዘ አንድ የፈተና ምሳሌ የነበረው የዳግም መመለስ ታላቅ መሪዎች አንዱ የነበረው የሽማግሌ ፓርሊ ፒ. ፕራት አጋጣሚ ነበር። እርሱ የመጀመሪያ የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባል ነበር። በ1837 (እ.አ.አ) መጀመሪያ ውስጥ፣ ውድ ባለቤቱ፣ ታንክፉል፣ የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለደች በኋላ ሞተች። ፓርሊ እና ታንክፉል ለከተጋቡ ወደ 10 አመት ቀርበው ነበር፣ እናም የእርሷ መሞት በጣም አሳዝኖት ነበር።

ከትንሽ ወር በኋላ፣ሽማግሌ ፕራት ቤተክርስቲያኗ አጋጥሟት ከምታውቀው ጊዜዎች ሁሉ በላይ አስቸጋሪ በነበረው ራሱን አገኘ። በብሔራዊ ቀውስ መካከል፣ የክልል የገንዘብ ጉዳይ—በተጨማሪም የምድር ግምት እና በጆሴፍ ስሚዝ እና በሌሎች የቤተክርስቲያን አባላት የተገኙ የገንዘብ ድርጅቶች መታገል—አለመግባባትን እና ጠብን በከርትላንድ ውስጥ ፈጠረ። የቤተክርስቲያኗ መሪዎች በግል ህይወታቸው ጥበባዊ የሆኑ የምድር ውሳኔዎችን አላደረጉም ነበር። ፓርሊ ብዙ ገንዘብ ጠፋበት እናም ለጊዜም ከነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ጋር ተጣልቶ ነበር።10 ጆሴፍን በመንቀፍ ጻፈ እናም እርሱን እንደሚቃወም ከመስበኪያው ተናገረ። በተመሳሳይ ሰዓት፣ ፓርሊ በመፅሐፈ ሞርሞን እና በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች በማመን እንደሚቀጥልም ተናገረ።11

ሽማግሌ ፕራት ሚስቱን፣ መሬቱን፣ እና ቤቱን አጥቶ ነበር። ፓርሊ፣ ለጆሴፍ ሳይነግር፣ ወደ ምዙሪ ሄደ። በዚያ መንገድ ላይ እያለ፣ በድንገት አብረው ከሚያገለግሉት ወደ ከርትላንድ እየተመለሱ ካሉ ሐዋሪያት ከቶማስ ቢ. ማርሽ እና ከዴቪድ ፓትን ጋር ተገናኘ። በቡድኑ ውስጥ ስምምነት በዳግም እንዲመለስ ታላቅ ፍላጎት ተሰማቸው እና ፓርሊ ከእነርሱ ጋር እንዲመለስ አሳመኑት። ከጆሴፍ ስሚዝ እና ከቤተሰቡ በላይ ያጡ ማንም እንደሌሉ ተረዳ።

ፓርሊ ነቢዩን ፈልጎ አገኘ፣ አለቀሰ፣ እናም ያደረገው ትክክል እንዳልሆነ ተናዘዘ። ባለቤቱ፣ ታንክፉል፣ ከሞተች በኋላ ባለፉት ወራት ውስጥ፣ ፓርሊ “በጨለመ ዳመና ስር” ነበር እናም በፍርሀት እና በንዴት ተሸንፎ ነበር።12 ጆሴፍ፣ ተቃውሞና ፈተና ላይ መታገል ምን ይመስል እንደነበር በማወቅ፣ ለእርሱ በመጸለይና በመባረክ፣ፓርሊን “በግልፅ ይቅር አለው።”13 ፓርሌና በታማኝነት የቀሩ ሌሎች ከከርትላንድ ፈተናዎች ጥቅም አገኙ። በጥበብ ጨመሩ እናም በተጨማሪ ልዑል እና ምግባረ መልካም ሆኑ። አጋጣሚም የእምነታቸው መሰረት ክፍል ሆነ።

ፈተና በጌታ የታዘነባቸው ወይም በረከቱ የሚወሰድባቸው ሁኔታ እንደሆነ መመልከት አይገባም። በሁሉም ነገሮች ተቃራኒ መኖር ለዘለአለም የሰለስቲያል እጣ ፈንታ የሚያዘጋጅ የሚያነጥር እሳት ክፍል ነው።14 ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በልብርቲ እስር ቤት ውስጥ እያለ፣ ለእርሱ የተሰጡት የጌታ ቃላት ሁሉንም አይነት ፈተናዎች—በተጨማሪም ጭንቀቶች፣ በሀሰት መከሰስ—ገለጹለት እናም እንዲህ አጠቃለሉ፥

“የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊው ብትከፍትብህ፣ ልጄ ሆይ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ።

የሰው ልጅ ከሁሉም በታች ወርዷል። አንተ ከእርሱ ታልቅ ነህ?”15

ጌታ፣ ለጆሴም ስሚዝ በሰጠው በዚህ መመሪያ ውስጥ፣ ደግሞም የእርሱ ቀናት የታወቁ እንደሆኑ እና ከዚያ በታች እንደማይቀነሱ ግልፅ አደረገለት። ጌታም እንዲህ ፈጸመ፣ “ሰው ማድረግ የሚችለውን አትፍራ፣ እግዚአብሔር ለዘለአለም ከአንተ ጋር ነውና።”16

ከዚያስ የእምነት በረከቶች ምን ናቸው? እምነት ምን ያከናውናል? ዝርዝሩ መጨረሻ የሌለው ነው፥

ኃጢያቶቻችን በክርስቶስ እምነት ምክንያት ይሰረያል።17

እምነት ያላቸው በሙሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግንኙነት አላቸው።18

ደህንነት የሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በማመን በኩል ነው።19

ጥንካሬ የምንቀበለው በክርስቶስ ባለን እምነት መሰረት ነው።20

በክርስቶስ ደም ልብሳቸውን ካላጠቡት በስተቀር ማንም ወደ ጌታ እረፍት ለመግባት አይችልም።21

ጸሎቶች መልስ የሚያገኙት በእምነት መሰረት ነው።22

በሰዎች መካከል እምነት ከሌለ፣ እግዚአብሔር በመካከላቸው ታዕምራትን ለመስራት አይችልም።23

በመጨረሻም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እምነት ለዘለአለም ደህንነታችን እና ከፍተኛነት አስፈላጊ መሰረት ነው። ሔላማን ለልጆቹ እንዳስተማርው፣ “አስታውሱ፣ አዳኝ በሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ ዓለት መሰረታችሁን መገንባት እንዳለባችሁ … ፣ እርግጠኛ መሰረት በሆነው ሰዎች ከገነቡበት ሊወድቁበት በማይችሉበት [ነው]።”24

በዚህ ጉባኤ ለመጡት የእምነት መሰረቶች ምሽግ ምስጋና አለኝ። ልመናዬም መስዋዕትን እንድናደርግ እና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መሰረቶቻችንን ለማጠናከር የሚያስፈልገው ትህትና እንዲኖረን ነው። ስለእርሱም እርግጠኛ ምስክር የምሰጣችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. Malcolm Gladwell, Outliers: The Story of Success (2008), 40. የአዕምሮ ዶክተር ዳንኤል ለቪትንን ሲጠቅስ።

  2. Obituary of Bryant Hinckley Wadsworth, Deseret News, Jan. 15, 2017, legacy.com/obituaries/deseretnews.

  3. 2 ኔፊ 28፥30 ተመልከቱ። ስለጉዳዩ ወይም ከዚህ ጋር ስለተያያዙ መሀሰሮች ሁሉ በሙሉ እውቀቶችን አልተቀበልንም። የሚመጡት ሲያስፈልጉ ነው፥ በሥርዓት ላይ በሥርዓት፣ በትእዛዝም ላይ ትእዛዝ።

  4. የመፅሐፈ ሞርሞን የመጀመሪያው እትም፣ 1830 (እ.አ.አ) የታተመው፣ ውስጥ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደጻፈው፣ “ይህን በእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል እንደተረጎምኩት እነግራችኋለሁ” (የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያን ተመልከቱ [1830])። ከዚያ በሚቀጥሉት የመፅሐፈ ሞርሞን እትሞች ውስጥ እንደዚህ አይነት ሀረጎች ተጨምረው ነበር፥ “ሰሌዳዎች ለጆሴፍ ስሚዝ ተሰጥተው ነበር፣ እርሱም እነዚህን በእግዚአብሔር ስጦታ እና ሀይል ተረጎማቸው” (የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያን ተመልከቱ [2013])።

  5. ኦርሰን ፕራት ጆሴፍ ስሚዝ አዲስ ኪዳንን በሚተረጉምበት ብዙ ጊዜዎች ተገኝቶ እንደነበር እና በዚያ ስራ መሳሪያ እንዳልተጠቀመ እንዳየ ያስታውስ ነበር። “ጆሴፍ፣ ሀሳቡን እንዳነበበ አይነት፣ ቀና አለ እና ጌታ ኡሪም እና ቱቲምን የሰጠው በመንፈስ መነሳሳት ልምምድ በሌለበት ጊዜ እንደሆነ ገለጸ። ነገር ግን አሁን በጣም አድጎ የመንፈስ ርራን ይገነዘባል፣ እናም የዚያ መሳሪያ አያስፈልገውም” (“Two Days’ Meeting at Brigham City, June 27 and 28, 1874,” Millennial Star, Aug. 11, 1874, 499; see also Richard E. Turley Jr., Robin S. Jensen, and Mark Ashurst-McGee, “Joseph the Seer,” Liahona, Oct. 2015, 10–17)።

  6. የሚስዮን ፕሬዘደንት፣ የጀርመን አጠቃላይ ባለስልጣን የነበሩ፣ ሽማግሌ ማሪዮን ዲ. ሀንክስ ነበሩ።

  7. ሉቃስ 10፥43–48 ይመልከቱ።

  8. የሐዋሪያት ስራ 2 ይመልከቱ።

  9. ሞዛያ 2፥36–37 ተመልከቱ፤ ደግሞም ሔንሪ ቢ. አይሪንግ፣ “Spiritual Preparedness: Start Early and Be Steady,” Liahona, Nov. 2005, 38: “ስለዚህ፣ የህይወት ታላቁ ፈተና በህይወት ማዕበሎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንደምናዳምጥ እና እንደምናከብር ነው። ይህም ማዕበልን ለመፅናት አይደለም፣ ግን በመጥፎ ማዕበል ጊዜ ትክክለኛውን ለመምረጥ ነው። እናም በህይወት የሚያሳዝነው በፈተናው መውደቅ ነው እናም በዚህም ወደ ሰማይ ቤታችን በግርማ ለመመለስ ብቁ መሆንን መውደቅ ነው።

  10. See Terryl L. Givens and Matthew J. Grow, Parley P. Pratt: The Apostle Paul of Mormonism (2011), 91–98; volume introduction and introduction to part 5, The Joseph Smith Papers, Documents, Volume 5: October 1835–January 1838, ed. Brent M. Rogers and others (2017), xxviii–xxxi, 285–93.

  11. See “Letter from Parley P. Pratt, 23 May 1837,” in The Joseph Smith Papers, Documents, Volume 5: October 1835–January 1838, 386–91.

  12. See “History of John Taylor by Himself,” 15, in Histories of the Twelve, 1856–1858, 1861, Church History Library; Givens and Grow, Parley P. Pratt, 101–2.

  13. See The Autobiography of Parley P. Pratt, ed. Parley P. Pratt Jr. (1874), 183–84.

  14. 2 ኔፊ 2፥11 ይመልከቱ።

  15. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 122፥7–8

  16. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 122፥9

  17. ኢኖስ 1፥5–8 ይመልከቱ።

  18. ጄሮም 1፥4 ይመልከቱ።

  19. ሞሮኒ 10፥26፣ 38 ይመልከቱ።

  20. አልማ 14፥26 ተመልከቱ።

  21. 3 ኔፊ 27፥19 ተመልከቱ።

  22. ሞሮኒ 7:26 ተመልከቱ።

  23. ኤተር 12፥12 ተመልከቱ።

  24. ሔላማን 5፥12