2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?

መንፈስ ቅዱስ ያስጠነቅቃል፣ መንፈስ ቅዱስ ያጽናናል እናም መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል።

አንድ ሰኞ ምሽት ላይ በቅርብ ጊዜ፣ ባለቤቴ፣ ሌሳ፣ እና እኔ በአካባቢያችን የሚኖሩ አንድ ወጣት ቤተሰብ ቤት ቆም አልን። እዛ እያለን፣ የቤተሰብ የቤት ምሽት ዝግጅት ላይ የዘጠኝ ዓመት ልጃቸው ትምህርቱን ማዘጋጀቱን ነግረውን እንድንሳተፍ ጋበዙን። እርግጥም እኛ ቆየን!

የመግቢያ መዝሙር፣ ጸሎቱና የቤተሰብ ጉዳዮችን ተከትሎ፣ የዘጠኝ-ዓመቱም ልጅ፣ በእጅ ከተጻፈው ትምህርቱ ውስጥ ጥያቄን በማንበብ ጀመረ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል? ይህንን መጠየቁ ሁሉም ሐሳቦችን እና ግንዛቤዎችን እንዲያጋሩና ትርጉም ያለው የቤተሰብ ውይይት እንዲጀመር አደረገ። የእኛን አስተማሪ ትምህርት ዝግጅት እና በጣም ጥሩ ጥያቄው አስደነቀኝ፣ ውስጤን ደግሞና ደጋግሞ ነወጠኝ።

ምስል
በእጅ የተጻፈ የቤተሰብ የቤት ምሽት ትምህርት

ከዛን ጊዜ ጀምሮ፣ ራሴንም “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?” ብዬ መጠየቅ ቀጥልኩኝ። ይህም በተለይ በህጻናት ክፍል ውስጥ ሆነው ወደ ስምንት አመት ለሚሸጋገሩ እና ለጥምቀት ዝግጅት ላይ ላሉ እናም በቅርብ ጊዜ ለተጠመቁ እና መንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለተቀበሉ ህጻናት ተገቢ የሆነ ጥያቄ ነው። ይህም በቅርብ ለተቀየሩት ብዙ ሺህም የሚጠቅም ነው።

እያንዳንዳችንን፣ በተለይ በህጻናት ክፍል ውስጥ ላሉት ልጆች “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?” የሚለውን እንደታስቡ እጋብዛለሁ። ይህን ጥያቄ ሳሰላስል፣ ወዲያውኑ ከሕፃንነቴ ጀምሬ የነበረኝን አንድ ተሞክሮ ላይ አንጸባረኩኝ። ይህም ታሪክ ለቤተክርስቲያን ሽማግሌ ሮበርት ዲ ሄልስ የአስራ ሁለቱ ሃዋሪያት አባልነቴን ጥሪ ተከትሎ ነገርኳቸው እናም እሳቸውም ስለእኔ ሕይወት አስመልክቶ እንዲህ በማለት በቤተ ክርስቲያን መጽሔት አንቀጽ ውስጥ አካተዋል።1 ከእናንተ መካከል አንዳንዶቻችሁ ይህን ታሪክ ሰምታችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን ብዙዎች ላይሰሙ ይችላል።

እኔ የ 11 ዓመት ልጅ ሳለሁ አባቴ እና እኔ በቤታችን አቅራቢያ በሚገኘው ተራሮች ውስጥ በሞቃት የበጋ ቀን ለሽርሽር ወጣን። አባቴ ቁልቁለቱን መንገድ ሲወስድ፣ እኔ ጎንና ጎን ወዳሉት ከአንድ ትልቅ ዓለት ወደ ሌላ በመዝለል፣ በመንገዱ ጎን ቀጠልኩ። አንዱን ትልቅ አለት መውጣት አስቤ ወደ ቻፉ ላይ መጣር ጀመርኩኝ። ይህንን ሳደርግ፣ አባቴ ቀበቶዬን ይዞ ወደ ታች በፍጥነት በመጎተት “በዛ ድንጋይ ላይ አትውጣ።” ሲለኝ ተገርሜ ነበር። በመራመጃ መንገዱ ላይ ብቻ እንቆይ አለ።

ከደቂቃዎች በኋላ፣ ከፍ ካለው መንገድ ላይ ወደ ታች ስንመለከት፣ እኔ መውጣት አስቤ በነበረው ዓለት አናት ላይ ፀሐይ በመሞቅ ላይ ያለ ትልቅ የእባብ በማየታችን ተደነቅን።

ከዛም በኋላ፣ ወደቤት እየነዳን ባለበት ጊዜ፣ “አንተ እባብ እንደነበረ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?” በማለት እድጠይቅ አባቴ እየጠበቀ እንደሆነ አወኩኝ። ስለዚህም ጠየኩኝ፣ ጥያቄዬም ስለመንፈስ ቅዱስና መንፈስ ቅዱስ እንዴት ሊረዳን እንደሚችል እንድንወያይ መራን። በዚያ ቀን የተማርኩትን ነገር ረስቼ አላውቅም።

መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደረዳኝ ማየት ትችላላችሁን? ረጋ ያለውን፣የመንፈስ ቅዱስ ሹሹክታ ድምጽን አባቴ በመስማቱ በጣም ምስጋና አለኝ፣ ምክንያቱም ህይወቴን አድኗልና።

ስለ መንፈስ ቅዱስን የምናውቀው ነገር

በተጨማሪ “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?” የሚለውን ጥያቄ ከመመልከታችን በፊት፣ ጌታ ስለመንፈስ ቅዱስ ያሳወቀንን አንዳንዶቹን እንመልከት። መመልከት የምንችላቸው በርካታ የዘላለማዊ እውነቶች አሉ፣ ነገር ግን ዛሬ ሦስቱን ብቻ ላብራራ።

በመጀመሪያ፣ መንፈስ ቅዱስ የስላሴ ሦስተኛው አባል ነው። በእምነት የመጀመሪያ አንቀጽ ላይ ይህንን እውነት እንማራለን፤ “በዘላለማዊ አባት እግዚአብሄር፣ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን።”2

ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ በዘመናችን ቅዱስ ቃል ላይ እንደተገለጸው የመንፈስ አንድ ግለሰብ ነው። አብ ሥጋ እና እንደ ሰው ተጨባጭ የሆነ አጥንት እና አካል አለው፤ ወልድም ደግሞ እንዲሁ ነው፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሥጋና አጥንት ያለው አካል የለውም፣ ነገር ግን የመንፈስ ግለሰብ ነው። ይህም ባይሆን ኖሮ፣ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ዘንድ ባላደረ ነበር።”3 ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ አካል ካላቸው፣ እግዚአብሔር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ መልኩ፣ መንፈሳዊ አካል አለው ማለት ነው። ይህም እውነት መንፈስ ቅዱስ የተሰጠውን የምናቃቸውን ሌሎች ስሞች ያብራራል፣ እኚህም ቅዱስ መንፈስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ፣ የተስፋ ቃል፣ እናም አፅናኝ ናቸው።4

ሦስተኛ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እጅን በመጫን የሚመጣ ነው። ይህ ስርዓት፣ ጥምቀትን በመከተል፣ መንፈስ ቅዱስ ያለማቋረጥ ጓደኛችን እንዲሆን ብቁ ያደርገናል።5 ይህን ሥርዓት ለማከናወን፣ ብቁ የመልከጸዲቅ የክህነት ስልጣን ያለው የግለሰቡ ራስ ላይ እጁን በመጨን፣ ስሙን በመጥራት፣ የክህነት ስልጣኑን በመግለጽ፣6 እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ እርሱ ወይም እርሷ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል መሆኑን ያረጋግጣል፣ እናም አስፈላጊ የሆኑ ቃላትን ያክላል፤

መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?

ስለ መንፈስ ቅዱስ ሦስቱን ቁልፍ እውነቶች ከገመገምን በኋላ፣ ወደ መጀመሪያው ጥያቄ እንመለስ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዴት ይረዳችኋል?

መንፈስ ቅዱስ ያስጠነቅቃል

የልጅነቴን ተሞክሮ ቀድሜ እንደገለጽኩት፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊና መንፈሳዊ አደጋ ከማጋጠሙ በቅድሚያ ሊያስጠነቅቃችሁ ይችላሉ። በጃፓን የአካባቢ አመራር ውስጥ ሳገለግል፣ ስለ መንፈስ ቅዱስ አስፈላጊ ማስጠንቀቂያ ሚና እንደገና ተማርኩኝ።

በዚህ ጊዜ፣ የጃፓን ሰንዳይ የወንጌል ተልእኮ ፕሬዝዳንት ከነበሩት ከሬድ ታኬኦታ፣ ጋር በቁርኚት ሰራሁ። ከተለመደው የሚስዮን የለት ተግባሩ ውስጥ፣ ፕሬዚዳንት ታኬኦታ ከሚስዮኑ ደቡባዊ ክፍል ውስጥ ከሚስዮናውያን መሪዎች ጋር ስብሰባን አቀደ። ከስብሰባው የተወሰኑ ቀናት አስቀድሞ፣ ፕሬዝዳንት ታኬኦታ የሆነ ስሜት ተሰማው፣ በልቡ ውስጥ በዚያ ዞን ውስጥ ለሚገኙ መሪዎች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ሚስዮናውያንን እንዲሳተፉ ለመጋበዝ አሰበ።

እርሱ እቅዱን ባስታወቀ ጊዜ፣ እርሱም ይህን የተለየ ስብሰባ ለሚስዮናውያን መሪዎች ብቻ እንጂ ለሁሉም እንዳልሆነ አስታወሰ። ሆኖም ግን፣ የተለመደውን መንገድ ፈቀቅ አድርጎ መንፈስ የመራውን ሃሳብ ለመከተል ሲል፣ ሁሉንም ሚስዮናውያን፣ፉኩሺማ ከተማንም ጨምሮ በርካታ የባሕር ዳርቻዎች ከተሞች ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙትን ወደ ስብሰባ ጋበዘ። በቀጠሮውም ቀን፣ መጋቢት 11, 2011(እ.አ.አ)፣ ሚስዮናውያን በኮሪያማ መሃል ከተማ ውስጥ ለተስፋፋው የወንጌል ተልዕኮ ስብሰባ ላይ ተሰባሰቡ።

በስብሰባውም ላይ 9 ነጥብ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ሱናሚ በጃፓን ሰንዳይ ተልዕኮ የሚገኝበት ጃፓን ክልል መታው። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ በርካታ የባሕር ዳርቻ ከተሞች፣ ሚስዮናውያን የመጡበት አካባቢዎችን ጨምሮ፣ አሰቃቂ የህይወት ማጣትን ገጠማቸው። እናም የፉኩሺማ ከተማ በተከተለው የኑክሌር ክስተት መከራ ደርሶባቸዋል።

በዚያን ቀን ሚስዮናውያኑ ተሰብስበው የነበሩበት የመሰብሰቢያው ቤቱ በመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት ጉዳት ቢደርስበትም፣ የመንፈስ ቅዱስን መሪት በመከተል፣ ፕሬዚዳንት እና እህት ታቴኦካ እናም ሁሉም ሚስዮናውያን በደህና ተሰባሰቡ። ከሱናሜም እና ከኑክሌር መሰናከል አደጋ ከጉዳት ውጪ ነበሩ እናም ከውድመትም ርቀው ነበር።

የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ስትሰሙ፣ አብዛኛውን ጊዜ የጸጥታ እና የረጋ ስሜት ሲሰማችሁ፣ ከመንፈሳዊ እና ከአካላዊ አደጋ ሳታውቁት ልትጠበቁ ትችላላችሁ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ መንፈስ ቅዱስ ለአባቴና ለፕሬዚዳንት ታቴኦካ እንዳደረገ፣ እናንተን በማስጠንቀቅ ይረዳችኋል።

መንፈስ ቅዱስ ያስጠነቅቃል

“መንፈስ ቅዱስ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?” ለሚለው ጥያቄ በመልስ ለመቀጠል የአጽናኝ ሚናውን እንመርምር። በሕይወታችን ውስጥ ያልተጠበቁ ክስተቶች ሐዘን፣ ሥቃይ፣ እና ብስጭትን ያመጣሉ። ሆኖም ግን፣ ከነዚህ መከራ መካከል፣ መንፈስ ቅዱስ የእርሱ ወሳኝ ሚና ከሆነው ውስጥ አንዱ በማጽናናት እኛን ያገለግላል፣ በርግጥ ይህም ከስሙ አንዱ ነው። ከኢየሱስ ክርስቶስ ከሆኑት እነዚህ ሰላማዊ፣ የሚያበረታቱ ቃላት፣ ይህን ቅዱስ ሚና ይገልጻሉ፥ “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።”7

ይህንን ደግሞ በተጨማሪ ለማስረዳት፣ ከብዙ አመታት በፊት አንድ ቤተሰብ ከአምስት ወንዶች ልጆቻቸው ጋር ሎስ አንጀለስ፣ ካሊፎርኒያ፣ ዮ.ኤስ.ኤ. ወደ ትንሽ ከተማ የተጓዙ እውነተኛ ታሪክን አካፍላለሁ። ሁለቱ የመጀመሪያ ልጆች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርት መጫወት እና ጓደኞችን ማፍራት፣ ከመሪዎች እና ከአሰልጣኞች ጋር መቅረብን ጀመሩ፤ አብዛኛዎቹም የቤተክርስቲያን ታማኝ አባላት ነበሩ። እነዚህ ግንኙነቶች ታላቅ ወንድምየው ፈርናንና ታናሽ ወንድሙ ወደ ጥምቀት እንዲሄዱ ረድቷኛል።

ፈርናንዶ በኋላ ላይ ትምህርት ለመቀጠል እና የኮሌጅ ፉትቦል ለመጫዋት ከቤት ርቆ ሄደ። በቤተመቅደስ ውስጥም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፍቅረኛውን፣ ቤይሊን፣ አገባ። ፌርናንዶ እና ቤይሊ ትምህርታቸውን እንደጨረሱም፣ በጉጉት የመጀመሪያ ልጃቸውን-ሕፃን ሴት ልጅ ተጠባበቁ። ነገር ግን ቤት ለመቀየር ፌርናንዶን እና ቤይሊን ለመርዳት ቤተሰቦቻቸው በማገዝ ላይ ሳሉ፣ ቤይሊ እና እህቷ በበርካታ ተሽከርካሪዎች ዋና መንገድ ላይ ተጋጩ። የቤይሊን እና የህጻኗን ሴት ልጅም ሞቱ።

ምስል
ፈርናንዶና ቤይሊ

ነገር ግን የፈርናንዶ እንዲሁም የቤይሊ ወላጆች እና እህቶቿ ሐዘን ጥልቅ ቢሆንም፣ ወድያውኑ በተቃራኒ በውስጣቸው ያደረው ሰላምና መጽናናት የጠለቀ ነበር። አፅናኝ በመሆን ሚና ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በእርግጥም ይህ አስቸጋሪ በሆነ መከራ ጊዜ ፈርናንዶን አበረታቶታል። አደጋው ለደረሰባቸው ሁሉ የይቅርታ እና የፍቅር ስሜት እንዲሰጥ በቀጣይ ሰላም ፌርናንዶን መንፈስ ተናግሮታል።

የቤይሊ ወላጆች በአደጋው ​​ጊዜ እንደ ሚስዮናዊ ሆኖ ያገለግል የነበረውን ወንድሟን ደወሉለት። በደብዳቤ ስለሚወዳት እህቱ ከባድ ዜና ሲሰማ ስሜቱን ለቤተሰቡ እንዲህ ሲል ገለጸ፤ “በዚህ መከራ መካከል ድምፃችሁን በጣም በተረጋጋ ሁኔታ በመስማቴ ተገርሜ ነበር። ምን እንድምል አላውቅም። … ለማሰብ የምችለው ቢኖር ወደቤት ስመለስ እህቴ እዚያ አትገኝ እንደሆነ ነው። … ምንም ስህተት በሌላቸው በአዳኝ እና በእቅዱ ምስክሮች ተፅናንቼ ነበር። በማጠናበት እና በማስተምርበት ጊዜ እንባ እንዲቀረኝ የሚያደርገኝ መንፈስ ልቤን ማላው። ከዛም ተጽናናሁ እናም እማውቃቸው ነገሮች ታወሱኝ።”8

ለፌርናንዶ እና ቤይሊ ቤተሰብ እንዳደረገው፣ መንፈስ ቅዱስ እናንተን በማፅናናት ይረዳችኋል።

መንፈስ ቅዱስ ያስጠነቅቃል

መንፈስ ቅዱስ ስለአብ እና ወልድ እናም ስለእውነቶች በሙሉ ይመሰክራል።9 ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር፣ እንዲህ አለ፣ “ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝnb}… በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።”10

የመንፈስ ቅዱስን ጠቃሚ ሚና እና መስካሪነት ለመግለጽ፣ የፌርናንዶን እና የቤይሊን ታሪክ እቀጥላለሁ። ካስታወሳችሁ፣ ፈርናንዶ ወንድሙ ተጠምቀው እንደነበር አጋርቼ ነበር፣ ነገር ግን ወላጆቹ እና 3 ወጣት ወንድሞቹ አልተጠመቁም ነበር። እናም፣ ባለፉት ዓመታት ከሚስዮናውያን ጋር ለመገናኘት በርካታ ግብዣዎች ቢቀበሉም፣ እያንዳንዱ ጊዜ ቤተሰቡ ውድቅ አድርገው ነበር።

በቤይሊ እና በማኅፀን ውስጥ የነበረችው ውድ ልጇ በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፍ የፈርናንዶ ቤተሰብ ሃዘናቸውን አብዝቶ ነበር። ከፌርናንዶ እና ከቤይሊ ቤተሰብ በተለየ መልኩ፣ እነሱ ምንም መጽናናትን ወይም ሰላምን አላገኙም። የቤይሊ ቤተሰብ እና የራሳቸው ልጅ፣ ያላቸውን ከባድ ሸክም እንዴት ሊሸከሙ እንደቻሉ ሊገባቸው አልቻለም።

ከጊዜ በኋላ እነርሱም ልጃቸው ያለው እና እነርሱ የሌላቸው የኢየሱስ ክርስቶስ በዳግም የተመለሰው ወንጌል መሆኑን መደምደሚያ ላይ ደረሱ። ይህንን ከተገነዘቡ በኋላ፣ ቤተሰባቸውን ወንጌልን እንዲያስተምሩ ሚስዮናውያኑን ጋበዙ። ከዚህ የተነሳ፣ በብርታት ሲፈልጉት የነበረውን ጣፋጭ ሰላም እና የሚያረጋጋ መጽናናትን ያመጣላቸውን፣ ስለ የደስታ ታላቅ እቅድ የራሳቸውን ምስክርነት ተቀበሉ።

ምስል
የፈርናንዶ ቤተሰብ ጥምቀት

ቤይሊን እና በፅንስ ላይ የነበረችውን የልጅ ልጅ ካጡ ሁለት ወራት በኋላ፣ የፌርናንዶ ወላጆች እና ሁለቱ ታናናሽ ወንድሞቹ ተጠመቁ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት ማሪጋገጫን እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ተቀበሉ። የፈርናንዶ ታናሽ ወንድም ጥምቀቱን ስምንት አመት እስኪሞላው በጉጉት ይጠባበቃል። እያንዳንዳቸው መንፈስ ቅዱስ፣ ወንጌል እውነት መሆኑን እና ለመጠመቅ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንዲቀበሉ ፍላጎት እንዲኖራቸው ምስክርነት እንደሰጣቸው ይናገራሉ።

ወንድሞች እና እህቶች፣ መንፈስ ቅዱስ ለአባቴና ለፕሬዚዳንት ታቴኦካ እንዳደረገ፣ እናንተን በማስጠንቀቅ ይረዳችኋል።

ማጠቃለያ

አሁን በአጭሩ እንመልከት። የመንፈስ ቅዱስ እውቀት የሚያመጡልንን ሦስት የመገለጥ እውነታዎችን ዘርዝረናል። እነዚህ መንፈስ ቅዱስ የስላሴ ሦስተኛው አባል ነው፣ መንፈስ ቅዱስ የመንፈስ ግለሰብ ነው፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እጅን በመጫን የሚመጣ ነው። “መንፈስ ቅዱስ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?” ስለሚለውም ሶስት መልሶችን ለየን። መንፈስ ቅዱስ ያስጠነቅቃል፣ መንፈስ ቅዱስ ያጽናናል እናም መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል።

ስጦታውን ለማስቀረት ብቁ መሆን

ለመጠመቅ እና ለማረጋገጫ በዝግጅት ላይ ያላችሁ፣ በቅርብም ሆነ ቆይቶ ይህንን ያሟላችሁ፣ ለአካል እና ለመንፈስ ደህንነታችን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታን መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ትእዛዛትን ለመጠበቅ ጥረት በማድረግ፣ የግል እና የቤተሰብ ጸሎት በማድረግ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ፣ ከቤተሰብ ጋር እና ከወዳጆቻችን ጋር አፍቃሪ እና መሃሪ ዝምድናን በመሻት እንጀምራለን። አስተሳሰባችን፣ ድርጊታችንን፣ እና ቋንቋችንን ንጹህ አድርገን መጠበቅ አለብን። በቤት፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በተቻለን መጠን በቤተ መቅደስ ውስጥ የሰማይ አባታችን ማምለክ ይገባል። በመንፈስ ቅርብ ሁኑ፣ እናም መንፈስ ከእናንተ ጋር ቅርብ ይሆናል።

ምስክርነት

እኔ አሁን በግብዣ እና የእኔን እርግጠኛ ምስክርነት በመስጠት እዘጋለሁ። በህጻናት ክፍል በብዛት የሚዘመሩትን ቃላት በሙሉነት እንድትኖሩበት እጋብዛችኋለሁ። እርግጠኛ ነኝ ቃላቱን ያውቁታል፤ “አድምጡ፣ አድምጡ። መንፈስ ቅዱስ ይንሾካሾካል። “አድምጡ፣ የረጋውን ድምጽ አድምጡ።”11

ሽማግሌ እና ወጣት ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ እኔ አምላክ በመለኮታዊ ማንነታቸው ክብር ሕልውና እንዳላቸው ምስክር ይሰጣለሁ። እነርሱም አብ እግዚአብሔር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና መንፈስ ቅዱስ ናቸው። በወንጌል ሙሉነት ውስጥ የምንኖር የኋለኛው ቀን ቅዱሳን፣ ከምንቀበላቸው እድሎች መካከል አንዱ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደሆነ እመሰክራለሁ። መንፈስ ቅዱስ እናንተን እንደሚረዳ አውቃለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኝ እና ቤዛ እንደ ሆነ፣ እግዚአብሔር የሰማይ አባታችን እንደ ሆነ ልዩ ምስክርነቴን አክላለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።