2010–2019 (እ.አ.አ)
“ሰላሜን እሰጣችኋለሁ”
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


“ሰላሜን እሰጣችኋለሁ”

ጌታ ትቷቸው ሊሄድ ሲል ለደቀመዛሙርቱ የሰላም ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ለእኛም እንደዚህ አይነት ቃል ኪዳን ሰጥቶናል።

ውድ እህቶቼ፣ በዚህ ምሽት መእግዚአብሔር መንፈስ ተባርከናል። ከሀይለኛ መሪ እህቶች የተሰጡ የተነሳሱ መልእክቶች እና መዝሙር እምነታችንን አጠናክረዋል እናም ከአፍቃሪው የሰማይ አባታችን ጋር የገባነውን ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የመጠበቅ ፍላጎታችንን አሳድገዋል። ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለን ፍቅር እና ለእርሱ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት ያለን ምስጋና ሲጨምሩ ተሰምተውናል።

የዚህ ምሽት መልእክቴ ቀላል ነው። በዚህ ምሽት ሰላም ሁላችንም ተሰምቶናል። ሁላችንም እንደዚህ አይነት ሰላም በውስጣችን፣ በቤተሰባችን ውስጥ፣ እና በአካባቢያችን ከሚገኙ ሰዎች ጋር እንዲሰማን እንፈልጋለን። ጌታ ትቷቸው ሊሄድ ሲል ለደቀመዛሙርቱ የሰላም ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ለእኛም እንደዚህ አይነት ቃል ኪዳን ሰጥቶናል። ነገር ግን ሰላም የሚሰጠው በራሱ መንገድ እንጂ በአለም መንገድ አይደለም። ሰላም የሚልክበትን መንገድ እንዲህ ገልጿል፥

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሀንስ 14፥26–27)።

የሞዛያ ልጆች ወደ ላማናውያን በሚስዮናቸው ሲሄዱ ያ የሰላም ስጦታ አስፈልጓቸው ነበር። የስራቸውን ታላቅነት በመረዳት በትንሽ ጭንቀት፣ መረጋገጫ ለማግኘት ጸለዩ። እናም “ጌታ በመንፈሱ ጎበኛቸውና፣ እንዲህ አላቸው፥ ተፅናኑ። እነርሱም ተፅናኑ።” (አልማ 17፥10፤ ደግሞም አልማ 26፥27 ተመልከቱ)።

በጊዜም፣ እናንተ ያልተረጋገጠ እና ከፍ ያለ የሚመስል ፈተና ሲያጋጥማችሁ ሰላምን ትፈልጉ ይሆናል። የሞዛያ ልጆች ለሞሮኒ ያስተማረውን ትምህርት ተምረዋል። ይህም ለሁላችንም መመሪያ ነው፥ “ሰዎች ወደ እኔ የሚመጡ ከሆነ ድክመታቸውን አሳያቸዋለሁ። ሰዎች ትሁት እንዲሆኑ ድካምን እሰጣቸዋለሁ፤ እናም ፀጋዬም እራሳቸውን በፊቴ ዝቅ ላደረጉ ሁሉ በቂ ነው፤ እነርሱም በፊቴ እራሳቸውን ዝቅ ካደረጉ፣ እናም በእኔም እምነት ካላቸው፣ ከዚያም ደካማ የሆኑትን ለእነርሱ ጠንካራ እንዲሆኑ አደርጋለሁ።” (ኤተር 12፥27)።

መሮኒ እንዳለው “እነዚህን ቃላቶች ስሰማ፣” እርሱም “ተፅናና” (ኤተር 12፥29)። እነርሱም ለሁላችንም መፅናኛ ለመሆን ይችላል። ድክመታቸው የማያዩ አያድጉም። ድክመታችሁን ማወቅ በረከት ነው፣ ምክንያቱም ትሁት እንድትሆኑ እና እናንተን ጠንካራ ለማድረግ ሀይል ወዳለው አዳኝ ለመዞር እንድትቀጥሉ ይረዳችኋልና። መንፈስ እናንተን ማፅናናት ብቻ ሳይሆን በፍጥረታችሁ ውስጥ የኃጢያት ክፍያ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራበት ነው። ከዚያም ደካማ ነገሮች ጠንካራ ይሆናሉ።

እናንተም በጊዜ እምነታችሁ በሰይጣን ይፈተናል፤ ይህም ለሁልም ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቶች ሁሉ ይደርሳል። ለእነዚህ ጥቃቶች ያላችሁ መከላከያ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጓደኛችሁ መጠበቅ ነው። ለነፍሳችሁ መንፈስ ሰላም ይናገራል። በእምነት ወደፊት እንድትሄዱ ይገፋፋችኋል። እናም የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሀን እና ፍቅር የተሰማችሁን እነዚያን ጊዜዎች ትዝታመልሶ ያመጣላችኋል።

መንፈስ ከሚሰጣችሁ ውድ ስጦታዎች አንዱ ማስታወስ ይሆን ይሆናል። “እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል [ጌታም የነገራችሁን] ሁሉ ያሳስባችኋል”” (ዮሀንስ 14፥26)። ትዝታው ለጸሎት፣ የክህነት ስርዓት ለመቀበል፣ የምስክርነታችሁ ማረጋገጫ መልስ፣ ወይም የእግዚአብሔርን የሚመራ እጅ በህይወታችሁ ውስጥ ያያችሁበት ጊዜ ይሆናል። ምናልባት ወደፊት በሚመጡት ቀናት ጥንካሬ ሲያስፈልጋችሁ፣ መንፈስ በዚህ ምሽት ያላችሁን ስሜት ያመጣላችሁ ይሆናል። ይህም እንዲሆን እጸልያለሁ።

መንፈስ ወደ አዕምሮዬ የሚያመጣው አንድ በትዝታ ቢኖር በብዙ አምት በፊት በአውስትሪያ ስለነበረ የአንድ ምሽት ቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ነበር። ይህም በባቡር መንገድ ስር ነበር። በእንጨት ወንበር ላይ የተቀመጡ ደርዘን ሰዎች ብቻ ነበሩ። አብዛኛዎቹ ሴቶች፣ አንዳንድ ወጣት እና አንዳንድ ያረጁ፣ ነበሩ። ለነዚህ ትንሽ ተሰብሳቢዎች ቅዱስ ቁርባን ሲተላለፍ አንዳንድ የምስጋና እምባዎች አይቼ ነበር። ለእነዚያ ቅዱሳን አዳኝ ያለው ፍቅር ተሰማኝ፣ እነርሱም ተሰማቸው። ነገር ግን በደንብ የማስታውሰው ታዕምራት ቢኖር የብረት መሸሸጊያውን እየሞላ ውስጥ በግልጽ ይታይ የነበረውን ብርሀን ነበር። ምሽት ነበር እና ምንም መስኮት አልነበረም፣ እና ግንክፍሉ በሙሉ እንደ ከሰዓት በኋላ የጸሀይ ብርሀን በርቶ ነበር።

የመንፈስ ቅዱስ ብርሀን በዚያ ምሽት ብሩህና በብዛት የሚገኝ ነበር። እናም ብርሀኑን ያስገባውም መስኮት በጌታ ፊት ለኃጢያታቸው ይቅርታ ለመጠየቅ እና እርሱን ሁልጊዜ ለማስታወስ የልብ ውሳኔ ባደረጉት የነዚያ ትሁት ቅዱሳን ልብ ነበር። በዚያ ጊዜ እርሱን ለማስታወስ ከባድ አልነበረም፣ እናም የዚያ ቅዱስ አጋጣሚ ትዝታዬ እርሱን እና የኃጢያት ክፍያውን ከዚያ በሚቀጥሉ አመታት ለማስታወስ ቀላል አደረገልኝ። በዚያ ቀን መንፈስ ከእኛ ጋር እንደሚሆነና በዚህም የብርሀንና ሰላም ስሜት እንደሚያመጣልን የተገባልን የቅዱስ ቁርባን ጸሎት ቃል ኪዳን ተሟላ።

እንደ እናንተም፣ ጌታ ሰላም ሲያስፈልገኝ አፅናኚው እንዲጎበኘኝ ለላከልኝ ብዙ መነዶች ምስጋና አለኝ። ነገር ግን የሰማይ አባት ስለእኛ ምቾት የሚያስብ ብቻ ሳይሆን ደግሞም በተጨማሪ ስለእድገታችን ያስባል። “አፅናኚ” መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ከሚጠራበት ስሞች አንዱ ብቻ ነው። ሌላው ይህ ነው፥ እናም አሁን፣ እውነት፣ እውነት፣ እልሀለሁ፣ ወደ መልካም፣ ... በሚመራው መንፈስ ላይ እምነትህን አድርግ” (ት. እና ቃ. 11፥12)። በአብዛኛው ጊዜ፣ ወደ መልካሙ የሚመራችሁ የእግዚአብሔርን ተፅዕኖ እንዲያገኙ ሰውን በመርዳት ነው።

በእርሱ ጥበብ፣ ጌታ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ በድርጀቶች እና በክፍሎች ውስጥ አብርቶ አምጥቷችኋል። ይህን ያደረገው መልካም የምታደርጉበትን ለማሳደግ ነው። በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ፣ ሌሎችን በእርሱ ስም የማገልገል ሀላፊነት አላችሁ። ለምሳሌ፣ እናንተ ወጣት ሴት ከሆናችሁ፣ በኤጲስ ቆጶሳችሁ ወይም በወጣት ሴቶች መሪያችሁ “ተሳታፊ ላለመሆን” ብለን በምንጠራው የሆኑትን ሎራል እንድትጋብዙ ትጠየቁ ይሆናል። እናንተ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የወጣት ሴቶች መሪ ከሚያውቋት በላይ ታውቋት ይሆናል። በቤት ወይም በትምህርት ቤት ወይም በሁለቱ ችግር እንዳላት ታውቁ ይሆናል። መሪዎቻችሁ እርሱን እንድትረዱ ለምን ስሜት እንደነበራቸው አያውቁም ይሆናል፣ ነገር ግን ጌታ ያውቃል፣ እናም ይህን ስራ በመንፈሱ ማነሳሻ በኩል ይመራል።

በጥረታሁ ውጤታማነት ለማግኘት በእናንተ እና እንድታድኑ በተላካችኋት የወጣት ሴት ልብ ውስጥ የመቀየር ታዕምራት ይስፈልገዋል—እና ያም የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት ያስፈልገዋል። ተሳታፊ ያልህነችውን ሎራል መንፈስ እንደሚያያት እንድትመለከቷት ይፈቅድላችኋል። ጌታ ልቧን እና ልባችሁን ያውቃል፣ እናም የልብ መቀየር አጋጣሚዎች እንዳሉም ያውቃል። ትህትናን፣ ምህረትን፣ እና ፍቅርን ለማነሳሳት በመንፈሱ ሁለታችሁንም ለመጎብኘት ይችላል።

ያም መንፈስ የእናንተ ወደ መንጋው እንድትመለስ ለመጋበዝ አስፈላጊ የሆኑትን ቃላይ፣ ስራዎች፣ እና ትዕግስት ለማነሳሳት ይችላል። እናም ለማፍቀርና የጠፋችውን በግ በሰላምታ ለመቀበል፣ በዚህም ስትመለስ ቤት እንዳላት እንዲሰማት ዘንድ፣ በሎራል ክፍል ውስጥ ያሉትን የመንጋን ልብ ለመንካት ይችላል።

እንደ እግዚአብሔር ሴቶች ቡድን መልካም ለማድረግ ያላችሁ ሀይል የሚመካው በእናንተ መካከል በሚገኘው አንድነት እና ፍቅር በኩል ነው። በመንፈስ ቅዱስ በኩል የሚመጣ ሌላም የሰላም ስጦታ አለ።

አልማ ይህን ተረድቷል። ለዚህም ነው ህዝቡን “አንዱ ከሌላኛው እንዳይጣላ፣ ነገር ግን አንድ እምነትና፣ አንድ ጥምቀት ይዘው፣ በአንድ ዓይን እንዲተያዩ፣ ልባቸው በአንድ ላይ በአንድነትና፣ አንዱ ሌላኛውን ባለው ፍቅር እንዲጣበቁ” የለመነው (ሞዛያ 18፥21)።

መንፈስ በክፍላችንና በቤተሰባችን ውስጥ እንዲገኝ ዘንድ አንድነት አስፈላጊ ነው። ነገር ግን እናንተ ልክ እኔ በልምምድ እንደማውቀው እንደዚያ አይነት ፍቅር ለመጠበቅ አስሸጋሪ ነው። ይህም ስሜታችንን ለማራራት እና አይናችንን ለመክፈት የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት ያስፈልገዋል።

አንድ ሰባት ወይም ስምንት አመት የነበረ ወንድ ልጃችን በመኝታው ላይ በሀይል ዘልሎ የሚሰብረው ይመስለን የነበረበትን ጊዜ እስታውሳለሁ። ተናድጄ ነበር፣ እናም ወዲያው ቤቴን ለማስተካከል ሞከርኩኝ። በትንሹ ትከሻው ልጄን ያዝኩት እና አይኖቻችን በሚገናኙበት ድረስ ከፍ አደረኩት።

መንፈስ ቃላትን በአዕምሮዬ ጨመራቸው። ጸጥተኛ ቢሆንም ጠንካራ የሆነ ድምፅ ልቤን ነካት። “የያዝከው ታላቅ ሰው ነው።” በቀስታ ወደ መኝታው መለስኩት እና ይቅርታ ጠየኩን።

አሁን እርሱ መንፈስ ቅዱስ ከ40 አመት በፊት ያሳየኝ ታላቅ ሰው ሆኗል። ጌታ እርሱ እንደሚያየው የእግዚአብሔር ልጅን እንዳይ መንፈስ ቅዱስን በመላክ ስላዳነኝ ዘለአመላዊ ምስጋና ይሰማኛል።

በቤተሰባችን እና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የምንፈልጋቸው አንድነት የሚመጣው እርስ በራስ ስንመለከታተት ወይም እርስ በራስ ስንተሳሰብ የምናየውን መንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ እንዲኖረው በመፍቀድ ነው። መንፈስ የክርስቶስ ንጹህ ፍቅርን ያያል። ሞርሞን ልግስናን ለመግለፅ የተጠቀመባቸውን ቃላት አድምጡ። ያን ስሜት የተሰማችሁበትን ጊዜ አስታውሱ፥

“ልግስና ይታገሳል፣ እናም ደግ ነው፣ እናም አይቀናም፣ እናም በኩራት አይወጠርም፣ የራሷን አትፈልግም፤ በቀላሉ አይቆጣም፣ ክፉ አያስብም፣ እናም በመጥፎ ስራ አይደሰትም፣ ነገር ግን በእውነት ይደሰታል፣ ሁሉንም ነገሮች ይታገሳል፣ በሁሉም ነገሮች ያምናል፣ ሁሉንም ነገሮች ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉም ነገሮች ይፀናል።

“ስለዚህም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞች [እኔም እህቶችን እጨምራለሁ]፣ ልግስና ከሌላችሁ ከንቱዎች ናችሁ፣ ልግስና አትወድቅምና። ስለሆነም ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነውን ልግስናን ያዙ፤ ሁሉም ነገሮች መውደቅ አለባቸውና—

“ነገር ግን ልግስና ንፁህ የክርስቶስ ፍቅር ነው፣ እናም እስከዘለዓለም ይፀናል፤ እናም በመጨረሻው ቀንም እርሱን የያዘ መልካም ይሆንለታል።

“ስለሆነም የተወደዳችሁ [እህቶቼ]፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ፣ እርሱ እንደሆነ እናየዋለንና፣ እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደእርሱ እንሆን ዘንድ፣ ይህም ተስፋ ይኖረን ዘንድ፣ ልክ እርሱ ንጹህ እንደሆነ እኛም ንጹህ እንሆን ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ።” (ሞሮኒ 7፥45–48)።

ያም የሰማይ አባታችሁ ለእናንተ ለውድ ሴት ልጆቹ ያለው አላማ ነው። ይህም የራቀ አላማ ይመስላችሁ ይሆናል፣ ነገር ግን ከእርሱ አስተያየት፣ እናንተ ከዚህ የምትርቁ አይደላችሁም። ስለዚህ እናንተን ለማፅናናት፣ ለማበረታታት፣ እና ለመቀጠል ለማነሳሳት ይጎበኛችኋል።

አብ እንደሚያውቃችሁ—ፍላጎታችሁን እና ስማችሁን እንደሚያውቅ—እንደሚወዳችሁ፣ እና ጸሎታችሁን እንደሚሰማ እርግጠኛ የሆነ ምስክሬን እተውላችኋለሁ። ውዱ ልጁ ወደ እርሱ እንድትመጡ እየጋበዛችሁ ነው። እናም እነርሱም እናንተንና በእነርሱ ስም ሌሎችን ለመርጋት በምትጥሩበት እንዲረዳችሁ መንፈስ ቅዱስን ይልካሉ።

በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያ፣ የምንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት በነፍሳችሁ ላይ የሚቀድስ እና የሚያነጻ ውጤት ይኖረዋል። ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመተው ጌታ ቃል የገባውም ሰላም ይሰማችኋል። ከዚያም ሰላም ጋር ብሩህ ተስፋ እና ለአብ እና መንግስቱን በምድር ላይ በህያው ነቢያት ለሚመራው ለውድ ልጁ ያለ የብርሀንና ፍቅር ስሜት ይመጣል። የምመሰክረው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።