2010–2019 (እ.አ.አ)
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እሱን ባየው ጊዜ ወደደው
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እሱን ባየው ጊዜ ወደደው

በማንኛውም ጊዜ እናንተ ከባድ ነገር እንድታደርጉ የተጠየቃችሁ መስሎ ከተሰማችሁ፣ ጌታ እናንተን እንደሚያያችሁ፣ እንደሚወዳችሁ ሁኔታውን ትታችሁ እርሱን እንድትከተሉት እየጋበዛችሁ መሆኑን አስቡ።

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት፣ በዋሽንግተን በስፖኬን ሚሲዮን ውስጥ እንድናስተዳድር ከባለቤቴ፣ ጃኪ ጋር፣ ተጠራሁ። በጣም ብዙ አስደናቂ ወጣት ሚስዮናውያን ጋር የመሥራት ኃላፊነቱ በፍርሃት እና በደስታ ድብልቅ ስሜት ይዘን ወደ የአገልግሎት ቦታው ደረስን። ከብዙ የተለያየ አስተዳደግ የመጡ ናቸው እናም በፍጥነት ልክ እንደ የራሳችን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሆኑ።

አብዛኞቹ ድንቅ መልካም ስራ ቢሰሩም፣ ጥቂቶቹ ግን የጥሪያቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ጋር ትግል ነበራቸው። አንዱ ሚስዮናዊም እንዲህ ብሎ ሲነግረኝ አስታውሳለሁ፣ ‘’ፕሬዝደንት፣ ሰዎችን አልወድም።” በርካቶች ደግሞ ጥብቅ የሆነውን የሚስዮናዊ ደንቦችን መከተል ፍላጎት እንዳልነበራቸው ነገሩኝ። ከመታዘዝ የሚመጣውን ደስታ ገና ላልተማሩት ሚስዮናውያን ልባቸውን ለመለወጥ ምን ማድረግ እችል ዘንድ ተጨነኩኝ እናም አሰብኩኝ።

አንድ ቀን በዋሽንግተን-አይዳሆ ድንበር ላይ በውበት በተጠቀለሉ የስንዴ መስኮች መሃል በምነዳበት ጊዜ፣ የተቀዳ የአዲስ ኪዳን አዳምጥ ነበር። ታዋቂውን የሃብታሙን ወጣት ልጅ የዘላለም ህይወት ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለበት አዳንኝን ለመጠየቅ ስለመጣው ታሪክ ሳዳምጥ፣ ያልተጠበቀ ነገር ግን ጠንካራ የግል ራአይ አሁን ቅዱስ ትውስታ የሆነልኝን ተቀበልኩኝ።

ኢየሱስ ትእዛዛቱን የነገረውን እና ወጣቱም ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ እንደጠበቃቸው ሲመልስ ከሰማሁ በኋላ፣ የአዳኝን የረጋ እርማት አዳመጥኩኝ፥ “አንድ ነገር ጐደለህ፥ … ያለህን ሁሉ ሽጠህ...ና፥ ተከተለኝ።”1 ነገር ግን እጅግ ባስገረመኝ ሁኔታ፣ ይልቁንስ ፈጽሞ ከዚህ በፊት ሰምቼው ወይም አንብቤው የማላቅ የመሰለኝን ጥቅሶች ውስጥ ስድስት ቃላትን ሰማሁ። እነዚህ ጥቅሶች በቅዱስ መጽሃፍ ውስጥ የታከሉ ያህል ነበር የመሰለኝ። በመንፈስ መሪነት አማካኝነት በዛ ጊዜ ስለተገለጠው መረዳት ተደነኩኝ።

ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩብኝ እነዚህ ስድስት ቃላት ምን ነበሩ? እነዚህን ተራ የሚመስሉ ቃላት ለመለየት ትችሉ እንደሆነ ለማየት አዳምጡ፣ በሌሎች የወንጌል መዝገቦች ውስጥ ሳይሆን ነገር ግን በማርቆስ ወንጌል ላይ ብቻ ነው የሚገኘው፥

“አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ... የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።

“እናም እየሱስ እንዲህ አለው፣ …

“ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አታታልል፥ አባትህንና እናትህን አክብር አለው።

“እርሱም መልሶ … ፣ መምህር ሆይ፥ ይህን ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ አለው።

ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና፣ አንድ ነገር ጐደለህ፥ ሂድ፥ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፥ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፥ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፥ ተከተለኝ አለው።”2

“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እሱን ባየው ጊዜ ወደደው

እኔም ይህን ቃላት ስሰማ፣ በጣም ግልጽ የሆነ ምስል ጌታችን ቆሞ ይህንን ወጣት ሲመለከተው ታየኝመመልከት ስንል—በጥልቅ በማየት ጥሩነቱን እንዲሁም ደግሞ አቅሙን በመገንዘብ፣ እንዲሁም ከሁሉ የሚበልጠውን የሚያስፈልገውን ማስተዋል ነው።

ከዚያም በቀላሎቹ ቃላት—ኢየሱስ ወደደው። ለዚህም መልካም ወጣት ሰው ያለ መጠነ ሰፊ ፍቅርና ርኅራኄ ተሰማው፣ እናም በዚህም ፍቅር ምክንያት እናም ባለው በፍቅሩ ኢየሱስ ከእርሱ ይበልጥ ጠየቀው። እንደዚህ ባለ ፍቅር በመታቀፍ እንዲሁም በጣም ከባድ የሆነ ነገር ንብረቱን ሽጦ ለደሆች እንዲሰጥ እስኪጠየቅ ድረስ ይህ ወጣት ምን እንደተሰማው በአይምሮዬ ሳልኩኝ።

በዛ ቅጽበት፣ መቀየር የሚያስፈልጋቸው የኛ የተወሰኑት ሚስዮናውያን ብቻ ልብ እንዳልሆነ አወኩኝ። የኔም ልብ ጨምሮ ነበር። ከአሁን በኋላ ጥያቄውም እንዲህ የሚል አልነበረም “እንዴት ነው አንድ የተበሳጨ የሚስዮን ፕሬዘደንት በትግል ላይ ያለን ሚስዮናዊ የተሻለ ጠባይ እንዲገዛ የሚያደርገው?” ይልቁንስ፣ ጥያቄው “ እንዴት ነው እኔ በክርስቶስ ፍቅር ተሞልቼ፣ አንድ ሚስዮናዊ ለመለወጥ መሻት እንዲኖረው በእኔ በኩል የእግዚአብሔርን ፍቅር ሊሰማቸው የሚችለው?” የሚል ነው። እንዴት አድርጌ እሱን ወይም እሷን ጌታ ወጣቱን ባለሃብት በተመለከተበት አይን፣ በርግጥ ምን እያደረጉ ባሉበት ወይም በሌሉበት ሳይሆን በማንነታቸው እናም ምን መሆን በሚችሉበት መመልከት እችላለሁ? እንደ አዳኝ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

“በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እሱን ባየው ጊዜ ወደደው።”

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ በአንዳንድ የታዛዥነት ገጽታዎች ላይ ችግር ካለበት ወጣት ሚስዮናዊ ጋር ጉልበት ለጉልበት ስንበረከክ፣ በልቤ ውስጥ ታማኝ የሆነ ውይም የሆነችን ወደሚሲዮን አገልግሎት ለመምጣት ባላቸው መሻት ላይ የተገበሩ ወጣትን ተመለከትኩኝ። ከዚያም እንደ አንድ የለሰለሰ ወላጅ ስሜት እንዲህ ማለት ቻልኩኝ፥3 “ሽማግሌ ወይም እህት፣ ባልወድህ ኖሮ፣ ባገልግሎትህ ላይ ስለሚከሰቱት ነገሮች ግድ አይሰጠኝም ነበር። ነገር ግን እወድሃለሁ፣ እናም ስለምወድህ፣ ማን ለመሆን ስለምትችለው እቆረቆራለሁ። ስለዚህ ላንተ ከባድ የሆኑትን ነገሮች እንድትቀይር እና ጌታ መሆን የሚፈልግህን እንድትሆን እጋብዝሃለሁ።

እያንዳንዷ ጊዜ ከሚስዮናውያን ጋር ቃለ መጠየቅ ሳደርግ፣ በመጀመሪያ የልግስና ስጦታ እንዲኖረኝ እና እያንዳንዱን ኤልደር እና እህት ጌታ እንደሚያያቸው ማየት እንድችል ጸለይኩኝ።

ከዞን ጉባኤዎች አስቀድሞ፣ አንድ በአንድ እህት ፖልመር እና እኔ ሚስዮናውያን ሰላምታ ስንሰጥ፣ እቆምና ዓይኖቻቸውን በጥልቀት እመለከት ነበር፣ ያለ ቃላት ቃለ መጠየቅ በማድረግ—እናም ከዚያን ያለ ውድቀት በታላቅ ፍቅር ለነዛ ውድ የእግዚአብሄር ወንድ እና ሴት ልጆች ተሞላሁ።

በዚህ እጅግ ግላዊ ተሞክሮ ብዙ ሕይወት ለዋጭ የሆነ ትምህርትን ከማርቆስ ምእራፍ 10 ተማርኩኝ። እያንዳንዳችንን ይረዳናል ብዬ ከማምነው ትምህርቶች መካከል አራቱ የሚከተሉት ናቸው፤

  1. ሌሎችን በገዛ ዓይናችን ሳይሆን፣ ጌታ እንደሚመለከታቸው ለማየት ስንማር ለእነርሱ ያለን ፍቅር እና እነርሱን ለመርዳት ያለን ፍላጎት ያድጋል። በራሳቸው ላይ የማይመለከቱትን እምቅ ችሎታ እንመለከታለን። በክርስቶስ ፍቅር በድፍረት ለመናገር አትፍሩም ምክንያቱም “ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላልና።“4 እናም ለማፍቀር አስቸጋሪ የሆኑት አብዝተው ፍቅር እንደሚያስፈልጋቸው በማስታወስ ፈጽሞ ተስፋ አንቆርጥም።

  2. በብስጭት ወይም በቁጣ ካደረግነው ምንም ትምህርት ወይም መማር ፈጽሞ አይከሰትም፣ እና ፍቅር በሌለበት ልብ መለወጥ አይችልም። እኛ እንደ ወላጆች፣ አስተማሪዎች፣ ወይም መሪዎች ባለን ሚና ላይ እርምጃ ስንወስድ፤ እውነተኛ ትምህርት በመተማመን ብቻ እንጂ በማውገዝ ስሜት ውስጥ አይከሰትም። ቤታችን ሁልጊዜ ለልጆቻችን ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንጂ የጥላቻ አካባቢ መሆን የለበትም።

  3. አንድ ልጅ፣ ጓደኛ፣ ወይም የቤተሰብ አባል እኛ ባስቀመጥነው ደረጃ መኖር ሲያቅተው ፍቅር መነጠቅ የለበትም። እያዘነ በሄደው ሀብታሙ ወጣት ምን እንደደረሰባት ባናውቅም ነገር ግን ቀላል መንገድ ቢመርጥም እንኳ ኢየሱስ በፍጹም እንደወደደው እርግጠኛ ነኝ። ምናልባት ከጊዜ በኋላ በሕይወት ውስጥ፣ ንብረቱ ባዶ ሲሆን፣ ጌታ በተመለከተው ጊዜ፣ በወደደው ጊዜ፣ እናም እንዲከተለው የጋበዘውን ብቸኛ ተሞክሮ አስታውሶ እርምጃ ወስዶ ይሆናል።

  4. እርሱ እኛን ስለሚወደን፣ ጌታ ከእኛ ብዙ ይጠብቃል። ትሑት ከሆንን፣ ጊታ ንስሃ እንድንገባ፣ መስዋትን እንድንሰጥ፣ እና እንድናገለግል የሰጠውን ግብዣዎች ለሱ ፍጹም ፍቅር ማስረጃ እንዲሆን እንቀበላለን። ከሁሉም በኋላ፣ የንስሐ ግብዣ የምሕረት እና የሰላም ድንቅ ስጦታን የማግኘት ግብዣ ነው። ስለሆነም፣ “ የጌታን ቅጣት አታቅልል ... በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና።”5

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አሁን በማንኛውም ጊዜ ከባድ ነገር እንድታደርጉ የተጠየቃችሁ መስሎ ከታያችሁ፣ —መጥፎ ልማድን ወይም ሱስን እንድትተዉ ስትጠየቁ፣ የአለምን ነገር እንድትተዉ ፤ሰንበት በመሆኑ የምትወዱትን ተግባር እንድትተዉ ስትጠየቁ፣ ያስቀየማችሁን ይቅር እንድትሉ ስትጠየቁ፣ ጌታ እናንተን እንደሚመለከታችሁእንደሚወዳችሁ ነገሮችን እንድትተዉና እንድትከተሉት እንደሚጋብዛችሁ አስታውሱ። ተጨማሪ ነገሮችን እንድታደርጉ እናንተን አፍቅሮ ስለጋበዛችሁ አመስግኑት።

ስለ አዳኛችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እመሰክራለሁ፣ እናም እሱ እጁን በያንዳንዳችን ትከሻ ላይ የሚያስቀምጥበትን፣ እኛን በመመልከት በፍጹም ፍቅሩ የሚከበንን ቀን በጉጉት እጠብቃለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።