2010–2019 (እ.አ.አ)
በጌታ እመኑ እና አትደገፉ
ሚያዝያ 2017 (እ.አ.አ)


በጌታ እመኑ እና አትደገፉ

እርሱን በማወቅ በአዳኝ ህይወታችንን መካከለኛ ለማድረግ እንችላለን፣ እና እርሱም መንገዳችንን ይመራል።

በእስያ ስጓዝ፣ ውድ እህት ወደእኔ መጣች። አቀፈችኝ እና እንዲህ ጠየቀችኝ፣ “ይህወንጌል እውነት እንደሆነ እውነታዊ እምነት አለሽን?” ውድ እህት፣ ይህ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ። ጌታን አምናለሁ።

ምሳሌ 3፥5–6፣ ይህን ምክር እናነባለን፥

“በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤

“በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”

ይህ የቅዱስ መጻህፍት ጥቅሰት ከሁለት መገሰጽ፣ ከማስጠንቀቂያ፣ እና ከአስገራሚ ቃል ኪዳን ጋር የሚመጣ ነው። ሁለት ማስጠንቀቂያዎች “በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን” እናም “በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ።” ማስጠንቀቂያው፥ “በራስህም ማስተዋል አትደገፍ።” እናም አስገራሚው ቃል ኪዳን፥ “እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።”

መጀመሪያ ማስጠንቀቂያውን እንወያይበት። በስዕል የሚታእው የምናሰላስልበት ብዙ ይሰጠናል። ማስጠንቀቂያው “አትደገፍ” በሚለው ቃል ነው—“በራስህም ማስተዋል አትደገፍ።” በእንግሊዘኛ ሊን የሚባለው ቃል በሰውነት ወደ ጎን ማዘንበል ወይም ወደ አንድ በኩል መሄድ የሚል ትርጉም አለው። እኛ በስጋ ወደ አንድ ጎን ወይም ወደሌላ ስንደገፍ፣ ከመሀከል እንወጣለን፣ ከሚዛን ውጪ ነን፣ እናም እንደፋለን። እኛ በመንፈስ ወደምንረዳው ስንደገፍ፣ ከጌታ በመራቅ እናዘነብላለን። ስንደገፍ፣ ከመሀከል እንወጣለን፣ ከሚዛን ውጪ ነን፣ በክርስቶስ ላይ አናተኩርም።

እህቶች፣ አስታውሱ፣ ከዚህ ህይወት በፊት፣ ከአዳኝ ጋር ቆመን ነበር። በእርሱ አመንን። በሰማይ አባታችን ለተገለጸው የደስታ እቅድ እኛን ድጋፍ፣ ቅንዓት፣ እና ደስታ በድምጻችን አሳየን። አልተደገፍንም። በምስክራችን ተዋጋን፣ እና “ራሳችንን ከእግዚአብሔር ሀይሎች ጋር አንድ አደረግን፣ እናም እነዚያ ሀይሎችም ድል አደረጉ።”1 በመልካምና በጥፉ መካከል ያለው ይህ ጦርነትወደ ምድር መጥቷል። እንደገናም እንደ ምስክር ለመቆም እና በጌታ እምነታችንን የመጣል ቅዱስ ሀላፊነት አለን።

እንዲህም መጠየቅ ያስፈገናል፥ እንዴት በመካከል ለመሆን እና በራሴ ግንዛቤ ላለመደገፍ እችላለሁ? የአለምድምጾች የሚጎትቱ ሲሆኑ እንዴት የአዳኝን ድምፅ ለማወቅ እና ለመከተል እችላለሁ? በአዳኝ ማመንን እንዴት ለማሳደግ እችላለሁ?

እውቀታችንን እና በአዳኝ የምናምንበትን የምናሳድግበት ሶስት መንገዶች በሀሳብ ላቅርብ። እነዚህ መርሆች አዲስ እንዳልሆኑ፣ ግን መሰረታዊ እንደሆኑ ታገኛላችሁ። እነዚህ በእያንዳንዱ የመጀመሪያ ክፍል የተዘመሩ፣ በወጣት ሴቶች ትምህርቶች የሚስተጋቡ፣ እና ለሴቶች መረዳጃ ማህበር ጥያቄዎች መልሶች ነበሩ። እነዚህ በመካከል የሚገኙ—እና የማይደገፉ—መርሆች ናቸው።

መጀመሪያ፣ “የክርስቶስን ቃል [ስንመገብ]፤ እነሆ የክርስቶስ ቃል ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች በሙሉ ይነግራችኋልና”2፣ ክርስቶስን ለማወቅ እና እርሱን ለማመን እንችላለን።

ከብዙ ወራት በፊት፣ የቤተሰብ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ላይ ነበርን። ስናነብም ሁለት አመት የነበረው የልጅ ልጄ በእኔ ጭን ላይ ተቀምጦ ነበር። በወንድ ልጄ ቤተሰብ ጉብኝት በመደስት፣ በሙሉ አያትነት ሁኔታ ላይ ነበርኩኝ።

የቅዱስ መጻህፍት ጥናት ፈጽመን፣ መፅሀፌን ዘጋሁ። የልጅ ልጄ የመኝታ ጊዜ ቅርብ እንደሆነ አወቀ። በሰማይ አይነት አይኑ ከፍ ብሎ ተመለከተ እና ዘለአለማዊ እውነት ተናገረ፥ “ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት፣ ናና።”

ምስል
የእህት ኮርዶን የልጅ ልጅ

መልካም እና የማይቀየር ወላጅ የሆነው ልጄ እንዲህ አስጠነቀቀኝ፣ “እማ፣ ደካማ አገናኝ አትሁኝ። ወደ መኝታ የማይሄድበትን እየፈለገ ነው።”

ነገር ግን የልጅ ልጄ ለተጨማሪ ቅዱስ መጻህፍት ሲጠይቅ፣ ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍትን አነበብን። ተጨማሪ ቅዱሳት መጻህፍት አዕምሮአችንን አብራሩ፣ ነፍሳችንን መገቡ፣ ጥያቄዎቻችንን መለሱ፣ በጌታ ያለንን እምነት አሳደጉ፣ እናም ህይወታችንን በእርሱ መካከለኛ ለማድረግ ረዱን። “እናንተ ትጠቀሙ ዘንድ እነርሱን በትጋት መፈተሽን አንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።”3

ሁለተኛ፣ ጌታን ለማወቅ እና እርሱን በጸሎት በኩል ለማመን እንችላለን። ለእግዚአብሔራችን ለመጸለይ መቻል እንዴት ታላቅ በረከት ነው። “በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ።”4

እንደ ሀብት የምመለከታቸው የጸሎት ውድ ትዝታዎች አሉኝ። በኮሌጅ በነበረኝ አንድ የበጋ ሽርሽር ጊዜ፣ በቴክሳስ ውስጥ ስራ አገኘሁኝ። ቨርን ብዬ በፍቅር ስም በሰጠኋት በአሮጌ መኪናዬ ከአይደሆ ወደ ቴክሳስ ለመሄድ ለብዙ መቶ ማይሎች መንዳት ነበረብኝ። ቨርን እስከ ጣራ ድረስ ተሞልታ ነበር፣ እናም ለአዲስ ጀብዱ ተዘጋጅቼ ነበር።

ከበር ስወጣ፣ ውድ እናቴን አቀፍኩኝ እና እንዲህ አለችኝ፣ “ከመሄድሽ በፊት እንጸልይ።”

ተንበረከክን እና እናቴ መጸልይ ጀመረች። ከሰማይ አባት ጋር ለደህንነቴ ተማለደች። አየር ለማቀዝቀዝ ለማይችለው መኪናዬ፣ መኪናዋ እንደሚያስፈልግባት እንድትሰራ ጸለየች። በበጋ በሙሉ መላእክት ከእኔ ጋር እንዲሆኑ ጠየቀች። እርሷም ጸለየች፣ እና ጸለየች፣ እናም ጸለየች።

ከዚያ ጸሎት የመጣው ሰላም በጌታ እንዳምን እና በራሴ ማስተዋል እንዳልደገፍ ማበረታቻ ሰጠኝ። በዚያ በጋ ባደረኳቸው ብዙ ውሳኔዎች ጌታ መንገዴን መራው።

የሰማይ አባትን በጸሎት የመቅረብጸባይ ሲኖረን፣ አዳኝን ለማወቅ እንችላለን። እርሱን ለማመን እንጀምራለን። ፍላጎታችን እንደ እርሱ ይሆናል። ለራሳችን እና ለሌሎች በእምነት ከጠየቅን የሰማይ አባት በፈቃደኛነት ለመስጠት የተዘጋጀውን በረከቶች ለማግኘት እንችላለን።5

ሶስተኛ፣ ጌታን ለማወቅ እና ሌሎችን ስናገለግል እርሱን ለማመን እንችላለን። የሚቀጥለውን ታሪክ የምካፈለው በሚያስፈራ እና ህይወትን በሚያስፈራራ በሽታ ላይ የአገልግሎት መርሆን ለመረዳት በቻለችው በኤሚ ራይት ፈቃድ ነው። ኤሚ እንዲህ ጻፈች፥

“በጥቅምት 29፣ 2015 (እ.አ.አ)፣ ነቀርሳ እንዳለኝ ተነገረኝ። ከነቀርሳዬ የምድንበት 17 ፐርሰንት እድል እንዳለኝ አወኩኝ። የመዳን እድል ጥሩ አልነበረም። ለህይወቴ እምደምታገል አውቄ ነበር። ለራሴ ብቻ ሳይሆን፣ ከሁሉም አስፈላጊ ለሆነው ለቤተሰቤ ያለኝን በሙሉ ለመስጠት ወሰንኩኝ። በታህሳስ፣ የራኢዳሲዮን መድሀኒት መውሰድ ጀመርኩኝ። የነቀርሳ መድሀኒቶች ብዙ ጉዳቶች እንዳሉት አውቅ ነበር፣ ነገር ግን ሰው እንደዚህ ያህል ታምሞ በህይወት ለመኖርም እንደሚችል አላውቅም ነበር።

“በአንድ ጊዜ፣ የራኢዳሲዮን መድሀኒት የህይወት መብትን የሚተላለፍ ነው ብዬ አወጅኩኝ። ባለቤቴን በቃኝ ብዬ ነገርኩት። አቆመዋለሁ! ወደ ሆስፒታል አልመለስም። በጥበቡም፣ የልብ ውዴ በትእግስት አዳመጣኝ እና ከዚያም እንዲህ መለሰ፣ ‘እንግዲህ፣ የምናገለግለውን አንድ ሰው እናገኛለን።’”

ምን አለ? ባለቤቱ ነቀርስ እንዳላት እና አንድ ተጨማሪ የማስታወቅ ስሜት ወይም አንድ በጣም የሚያም ግዜ ለማሳለፍ እንደማልችል አያውቅምን?

ኤሚ እንዲህ በመግለጽ ቀጠለች፥ “የበሽታዬ ምክቶች እየባሱ ሄደው፣ እንደምትኖር፣ እንደምትተነፍስ ሰው ለማከናወን የምችለው በወር አንድ ወይም ሁለት “የሚሻሉ” ቀናት ብቻ ይኖሩኝ ነበር። በእነዚያ ቀናት ነው ቤተሰባችን የማገልገል መንገድ የምናገኘው።”

በእነዚያ አንድ ቀን፣ የኤሚ ቤተሰብ ለሌሎችም በራኢዳሲዮን መድሀኒት የሚረዱ ነገሮችን፣ የሚያስደስቱ እና የበሽታ ምልክትን የሚረዱ ነገሮች የተሞሉትን ነገሮች አሳልፈው ሰጡ። ኤሚ ለመተኛት ሲያስቸግራት፣ የሌላን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ መንገዶችን አሰበች። አንዳንድ መንገዶች ትልቅ ነበሩ፣ ነገር ግን ብዙዎቹ የሚያበረታቱ እና የፍቅር ትንሽ መልእክቶች ወይም የስልክ መልእክቶች ነበሩ። ህመሟ ታላቅ ሆኖ ለመተኛት በማትችልበት በእነዚያ ምሽቶች፣ በመኝታ ሆና ለሞቱት ትውልዶቿ መከናወን የሚያስፈልጉትን ስርዓቶች በአይፓዷ ትፈትሽ ነበር። በታዕምራት ህመሟ ይቀንሳል፣ እናም ለመፅናት ችላ ነበር።

ኤሚ እንደመሰከረችው፣ “አገልግሎት ህይወቴን አዳነኝ። ወደፊት ለመሄድ ጥንካሬን በመጨረሻ ያገኘሁት በአካባቢዬ ያሉትን ሰዎች ስቃል ለመቀነስ በምጥርበት ባገኘሁት ደስታ ነው። በታላቅ ደስታ እና በተስፋ ለአገልግሎት ስራችን በጉጉት መመልከት ጀመርኩኝ። እስከዚህ ድረስ ይህም የሚያስደንቅ ነበር። መላጣ፣ በመርዝ የታመመች፣ እና ለህይወቷ የምትታገለው ‘አሁን ሁሉም ስለእኔ ነው’ ብላ ለማሰብ መብት አላት ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ቢሆንም፣ ስለራሴ፣ ስለጉዳዬ፣ ስለስቃዬና ህመሜ ሳስብ፣ አለሙ የጨለመ እና የሚያስጨንቅ ይሆናል። ትኩረቴ ወደሌሎች ሲዞር፣ ብርሀን፣ ተስፋ፣ ጥንካሬ፣ ብርቱነት፣ እና ደስታ ይኖራል። ይህም የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ደጋፊ፣ ፈዋሽ፣ እና የሚያስችል ሀይል ነው።”

ኤሚ እርሱን ስታውቅ ጌታን ማመን ጀመረች። በራሷ ማስተዋል ላይ በትንሽም ብትደገፍ፣ የአገልግሎት ሀሳብን ትጥል ነበር። አገልግሎት ህመሟንና ስቃይን እንድትቋቋም እና በዚህ የቅዱስ መጻህፍት ጥቅሰት እንድትኖር አስቻላት፥ “እናንተ ሰዎችን በምታገለግሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን ብቻ እያገለገላችሁ [ናችሁ]።”6

ኢየሱስ ክርስቶስ አለምን አሸንፏል። በእርሱም ምክንያት፣ በእርሱ መጨረሻ በሌለው የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ በመጨረሻም ሁሉም መልካም እንደሚሆን በማወቅ ከሁሉም ታላቅ የሆነ የእምነት ምክንያት አለን።

እህቶች፣ እያንዳንዳችን ጌታን ለማመን እና ላለመደገፍ እንችላለን። እርሱን በማወቅ በአዳኝ ህይወታችንን መካከለኛ ለማድረግ እንችላለን፣ እና እርሱም መንገዳችንን ይመራል።

በምድር ያለነው በእርሱ ለማመንና “እዚህ አለሁ፣ እኔን ላከኝ”7 በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያውጅበት አብረነው እንድንቆመ የፈቀደልንን ለማሳየት ነው።

ምስል
ክርስቶስ እና ፍጥረት

ውድ እህቶቼ፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንደመሰከሩት፣ “ቃል የተገቡልን በረከቶች ከመመዘን በላይ ናቸዋ። የሀይለኛ ዝናብ ዳመና ቢሰበሰብም፣ ዝናብም ቢፈስብን፣ የወንጌል እውቀታችን እና ለሰማይ አባታችንና ለአዳኛችን ያለን ፍቅር ያፅናናናል እናም ይደግፈናል ... በቅንነት ስንራመድም። … በዚህ አለም ያለ ምንም ነገር ሊያሸንፈን አይችልም።”8

በውድ ነቢያችን ምስክርነትም የራሴን እጨምራለሁ። የሰማይ አባታችንን እና አዳኛችንን ካመንን እና በራሳችን ማስተዋል ካልተደገፍን፣ መንገዳችንን ይመራሉ እናም የምህረት ክንድን ወደ እኛ ይዘረጋሉ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻ፥ በሚያዝያ 1፣ 2017፣ እህት ኤስፒን ከመጀመሪያ ክፍል አጠቃላይ አመራር እንደ መጀመሪያ አማካሪ ሀላፊነት ተለቅቀው ነበር።