2010–2019 (እ.አ.አ)
በእግዚአብሔር መቆየት እና የተሰበረውን መጠገን
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


በእግዚአብሔር መቆየት እና የተሰበረውን መጠገን

ክርስቶስ ከአብና ከእርስ በራስ ወደ አፍቃሪ ጓደኝነት እኛን ለማምጣት ሀይል አለው።

እውቀታችንን እና ለሰማይ አባት ታዛዥነታችንን ዝልቅ ለማድረግ ሁልጊዜ መቀጠል ያስፈልገናል። ከእርሱ ጋር ያለን ግኑነት ዘለአለማዊ ነው። እኛ የእርሱ ውድ ልጆች ነን፣ እናም ያም አይቀየርም። በዚህ ህይወትና በሚመጣው አለም ሊሰጠን በጣም የሚፈልገውን በረከቶች እንደሰትባቸው ዘንድ እኛ፣ እንደ ልጆቹ፣ ወደ እርሱ እንድንቀርብ በጋበዘን እንዴት በሙሉ ልባችን ለመቀበል እንችላለን?

ጌታ ለጥንት እስራኤል እንዳለው እና ለእኛ እንደሚለው፣ “በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።”1 አብ እንደሚናገረው በመናገር ለእኛ ለምን “አንተም ከእኔ ጋር ሁን፣ እና እኔም ከአንተ ጋር፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር ተራመድ” አለን?2 ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ የደስታችን እና የእድገት ውጤት ይኖረዋል።

በምድር ያለነው ለመማርና ለማደግ ነው፣ እናም ከሁሉም በጣም አስፈላጊ የሚሆነው መማር እና ማደግ የሚመጣው ከሰማይ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት ነው። ከእነርሱ ጋር ካለን ታማኝ ግንኙነት ጋር አምላካዊ እውቀት፣ ፍቅር፣ ሀይል እና ሌሎችን የማገልገል ታላቅ ችሎታ ይመጣል።

“እግዚአብሔር ስለራሱ የገለጸውን ሁሉ ለመማር ሀላፊነት አለን።”3 እግዚአብሔር አብ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ምድርን ለእድገታችን እንዲፈጥር እንዳዘዘ፣ የሰማይ አባት ልጁን ለደህንነታችን የፍትህን ዋጋ እንዲከፍል እንደሰጠው፣ እናም የአብ የክህነት ሀይል እና የወልድ ቤተክርስቲያን ከአስፈላጊ ስርዓቶች ጋር ለበረከቶቻችን በዳግም እንደተመለሱ መረዳት ያስፈልገናል። ለደስታችን እና እድገታችን በእነዚህ ዝግጅቶች የፍቅር ጥልቀት እንዳሉ ይሰማችኋልን? የሰማይ አባት የደህንነት እቅድ እኛ የወንጌሉን ህግጋትና ስርዓቶች ማክበር እና የዘለአለም ህይወትን ማግኘት እና በዚህም እግዚአብሔር እንደሆነው ለመሆን እንደሆነ ማወቅ ያስፈልገናል።4 ይህም የሰማይ አባት የሚያቀርብልን እውነተኛው እና ዘለአለማዊው ደስታ ነው። ሌላ ምንም እውነተኛ እና ዘለአለማዊ ደስታ የለም።

ፈተናችን ከደስታ መንገዳችን ጎትቶ ልያስወጣን ይችላል። ፈተናዎች ወደ መንበርከክ ሳይሆን ወደ ሀሳብ መሳብ ሲመሩን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን የእምነት ግንኙነትን ለማጣት እንችላለን።

ይህም ግጥም ቀደም ተከተላችንን ማመዛዘን ያስፈልገናል፥

አንዳንድ ነገሮች አስፈላጊ ናቸው; አንዳንድ ነገሮች አይደሉም።

ጥቂት ነገሮች ይቆያሉ፣ ግን ብዙ ነገሮች አይቆዩም።5

እህቶች፣ ለእናንተ ዋጋ ያለው ምንድን ነው? ለእናንተ የሚቆይ የሚሆንላችሁ ምንድን ነው? ለአብ በመቆየት ታላቅ ዋጋ ያለው ቢኖር ከእርሱ መማራችን፣ ራሳችንን ትሁት ማድረጋችን፣ እና በምድር አጋጣሚዎቻችን ለእርሱ ታዛዥ በመሆን መቆየታችን ነው። እርሱ ራስ ወዳጅነታችንን ወደ አገልግሎት፣ ፍርሀታችንን ወደ እምነት እንድንቀይር ይፈልገናል። እነዚህ የሚቆዩ ጉዳዮች በጣም ሊፈትኑን ይችላሉ።

ይህም ከስጋዊ ግድባችን ጋር፣ አብ ማፍቀር በጣም አስቸጋሪ በሚሆንበት እንድናፈቅረው፣ ማገልገል የሚመችበት በማይሆንበት እንድናገለግል፣ ይቅርታ ማድረግ ነፍስን የሚያስቸግር በሚሆንበት ይቅርታ እንድናደርግ የሚጠይቀን አሁን ነው። እንዴት? እንዴት ይህን እናደርጋለን? በቅንነት፣ በልጁ ስም፣ የጌታን እርዳታ እንጠይቃለን፣ እናም በኩራት የራሳችንን ፍላጎት ባለማስገባት ነገሮችን በእርሱ መንገድ እናደርጋለን።

ምስል
ውሀ ማንቆርቆሪያ

ፕሬዘደንት ኤዝራ ታፍት ቤንሰን የውስጣችንን እቃ ስለማጽዳት ሲናገሩ ስለራሴ ኩራት ተረድቻለሁ።6 ራሴን እንደ ውሀ ማንቆርቆሪያ ተመልክቻለሁ። የዘቀጠውን ኩራት ከማንቆርቆሪያ ውስጥ እንዴት ለማውጣት እችላለሁ? በግል ራሳችንን ትሁት ለመሆን መግፋት እና ሌሎችን ለመውደድ ማስገደድ፣ ቅን ያልሆነ፣ ባዶ የሆነ፣ እና የማይሰራ ነው። ኃጢያቶቻችን እና ኩራት በእኛእና የፍቅር ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከሰማይ አባታችን መካከል ክፍተት ወይም ልዩነት ይፈጥራል።

የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ብቻ ነው ከኃጢያታችን የሚያጸዳን እናም ልዩነትን የሚዘጋው።

በሰማይ አባታችን ፍቅር ክንዶች እና መመሪያዎች ለመከበብ እንፈልጋለን፣ እና ስለዚህ የእርሱን ፈቃድ መጀመሪያ እናደርጋለን እናም በተሰበር ልብ ክርስቶች የሚያጸዳ ውሀ በመያዣችን ላይ እንዲያፈስ እንለምናለን። መጀመሪያ ጠብ በጠብ ይመጣ ይሆናል፣ ግን ስንፈልግ፣ ስንጠይቅ፣ስንታዘዝ በብዛት ይመጣል። ይህ ህያው ውሀ ሊሞላን ይጀምራል፣ እናም በፍቅሩ ተሞልተን፣ የነፍስ መያዣችንን ለመገልበጥ እና በውስጡ ያለውን ለመፈወስ፣ ለተስፋ፣ እና ቦታ ያለው ለመሆን ጥማት ጋላቸው ጋር እንካፈላለን። የውስጥ እቃችን ሲጸዳ፣ የምድር ግንኙነታችን ለመፈወስ ይጀምራሉ።

ለእግዚአብሔር ዘለአለማዊ እቅድ ክፍል ለመስጠት የግል እቅዳችንን በመስዋእት መስጠት አስፈላጊ ነው። ለአብ የሚናገረው አዳኝ እንደለመነን፣ “ወደ እኔ ቅረቡ እና እኔም ወደ እናንተ እቀርባለሁ”7 ወደ አብ መቅረብ እውነቱን በቅዱሳት መጻህፍት በኩል መማር፣ የነቢያትን ምክር መከተል፣ እና እርሱን በፍጹም ለማድረግ መጣር ማለት ነው።

ክርስቶስ ከአብና ከእርስ በራስ ወደ አፍቃሪ ጓደኝነት እኛን ለማምጣት ሀይል እንዳለው እንረዳለን? እርሱ፣ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል፣ ስለዚህ ግንኙነት ጥልቅ አስተያየት ሊሰጠን ይችላል።

አንድ የጀመሪያ ትምህርት አስተማሪ ከ11 አመት ወንዶች ክፍል ጋር ስለነበረው ሀይለኛ አጋጣሚ ነገረኝ። ጅሚ ብዬ የምጠራው አንደኛው በክፍሉ ውስጥ መመሪያ የማይከታተል ብቸኛ ነበር። አንድ እሁድ፣ አስተማሪው የሚያስተምረውን እንዲያስቀምጥ እና ጅሚን ለምን እንደሚወደው ለመንገር የመንፈስ ምሪትን አገኘ። ለዚህ ወጣት ሰው ስላለው ምስጋና እና በእርሱ ስላለው እምነት ተናገረ። ከዚያም የክፍሉ አባላት ስለጅሚ የሚወዱትን ነገሮች እንዲነግሩት ጠየቃቸው። የክፍል አባላት፣ አንድ በአንድ፣ ጅሚ ለምን ለእነርሱ ልዩ እንደሆነ ሲነግሩት፣ ልጁ ጭንቅላቱን ዝቅ አደረገ እና እምባዎች በፊቱ ላይ ፈሰሱ። አስተማሪው እና ክፍሉም ወደ ጅሚ ብቸኛ ልብ መሻገሪያ ድልድይ ሰሩ። ቀላል ፍቅር፣ በታማኝነት ሲገለጽ፣ ለሌሎች ተስፋና ዋጋ ይሰጣል፡ ይህንም “ክፍተቱን መጠገን” ብዬ እጠራዋለሁ።

በአፍቃሪ ከሞት በፊት አለም ውስጥ የነበረው ህይወታችን፣ ምናልባት፣ ለእውነተኛ፣ የሚቆይ ፍቅር በዚህሽ ምድር በጕት እንድንፈልድ አድርጎን ይሆናል። ፍቅር ለመስጠት እና ለማፍቀር በመለኮት የተነደፍን ነን፣ እናም ጥልቁ ፍቅር የሚመጣው ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ስንሆን ነው። መፅሐፈ ሞርሞን እንደሚጋብዘን፣ “በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ከ[እግዢአብሔር ጋር] ታረቁ።”8

ኢሳይያስም የጾም ህግን በታማኝነት ስለሚኖሩበት እና በዚህም በትውልዳቸውም “የክፍተቱ ተጋኞች” ስለሆኑት ተናግሯል። እነዚህም ኢሳይያስ “የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ”9 ብሎ ቃል የገባባቸው ናቸው። በተመሳሰለ መንገድም፣ አዳኝ በእኛ እና በሰማይ አባት መካከል ያለውን ክፍተት፣ ወይም ርቀት፣ ይጠግናል። እርሱም፣ በታላቁ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕቱ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅር የምንካፈልበት እና በግል ህይወታችን “የፈረሱ ስፍራዎችን” በፍቅር የሚጠግንበት መንገር ከፍቶልናል። በእርስ በራስ መካከል ያለውን የስሜት ልዩነት መፈወስ የእግዚአብሔር ፍቅርን ከፍጥረታችን ራስ ወዳጅነት እና የመፍራት ስሜታችንን በስማዕት ከማድረግ ጋር ማዋሀድ ያስፈልገዋል።

በአንድ በሚታወስ ምሽት፣ አንድ ዘመድ እና እኔ በፖለቲካ ጉዳይ ላይ አልተስማማንም። በፍጥነት እና በሙሉ ያልኩትን በመሰባበር፣ የቤተሰብ አባላት በሚሰሙበት ትክክል እንዳልሆንኩኝ አሳወቀችኝ። ሞኝ እና መረጃ እንደሌለኝ ተሰማኝ—ምናልባትም ነበርኩኝ። በዚያ ምሽት ለመጸለይ ስንበረከክ፣ ይህች ዘመድ እንዴት አስቸጋሪ እንደነበረች በፍጥነት ገለጽኩለት! በመናገርም ቀጠልኩኝ። ምናልባት በምተችበት ለትንሽ ሳቆም፣ እና መንፈስ ቅዱን የእኔን ትኩረት ለማግኘት ጊዜ በማግኘትኑ ምክንያት፣ በሚቀጥለው “ምናልባት እንድወዳት ትፈልገኛለ” ስል ራሴን ስሰማ ደነገጥኩኝ። እርሷን ማፍቀር? እንዲህ በማለት ለመጸለይ ቀጠልኩኝ፣ “እንደት ላፈቅራት እችላልሁ? በፍጹም የምወዳት አይመስለኝም። ልቤ ጠጣር ነው እና ስሜቴ ተጎድቷል። ላደርገው አልችልም።”

ከዚያም፣ በእርግጥም በመንፈስ እርዳታ፣ እንዲህ ስል አዲስ ሀሳብ መጣልኝ፣ “ግን የሰማይ አባት፣ አንተ ታፈቅራታለህ። እርሷን አፈቅር ዘንድ፣ ለእርሷ ያለህን የፍቅር ትንሽ ክፍል ትሰጠኛለህን?” የተከፋኝ ስሜት ለሰለሰ፣ ልቤም ለመቀየር ተጀመረ፣ እናም ይህችን ሰው በልዩ ለመመልከት ጀመርኩኝ። እግዚአብሔር እንዳላት የሚያየው የእርሷን እውነተኛ ዋጋ ማየት ጀመርኩኝ። ኢሳይያስ እንደጻፈው፣ “እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት [ጠገነ]፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም [ፈወሰ]።”10

ከጊዜም በኋላ በመካከላችን የነበረው ልዩነት ተዘጋ። ነገር ግን የተቀየረ ልቤን ባትቀበልም፣ ለመወደድ አይችሉም ብለን የምናስባቸውንም የእርሱን እርዳታ ከጠየቅን የሰማይ አባት እንድናፈቅር እንደሚያስችለን ተማርኩኝ። የአዳኝ የኃጢያት ክፍያ ከሰማይ አባታችን ለሚመጡት ለሚቀጥለው የልግስና ፍሰት መግቢያ ነው። ለሁሉም ልግዝና ይኖረን ዘንድ ይህን ፍቅር በዚህ ለመቆየት መምረጥ ይገባናል።

ልባችንን ለአብና ወልድ ስንሰጥ፣ አለማችንን እንቀይራለን—በአካባቢያችን ያሉ ጉዳዮች ባይቀየሩም፡ ወደ ሰማይ አባት እንቀርባለን እናም የክርስቶስ እውነተኛ ደቀመዛሙር ለመሆን የምንጥርበትን የእርሱ ለስላሳ ተቀባይነት ይሰማናል። የምንለይበት፣ ልበ ሙሉነታችን፣ እና እምነታችን ይጨምራል።

በልባችን ሀይል ሁሉ ለዚህ ፍቅር እንድንጸልይ ሞርሞን ነግሮናል እና ይህም ከምንጩ፣ እንዲሁም ከሰማይ አባት ይሰጠናል።11 ከዚያም በኋላ ብቻ ነው የምድራዊ ግንኙነቶች ክፍተት ጠጋኞች ለመሆን የምንችለው።

የአባታችን መጨረሻ የሌለው ፍቅር፣ ወደ ክብሩና ደስታው እኛን ለማምጣት፣ ወደ እኛ ይደርሳል። አንድያ ልጁን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን፣ በእርሱና በእኛ መካከል በስፋት የተከፈተውን ክፍተትን ለመጠገን ሰጥቶናል። ከሰማይ አባት ጋር እንደገና መገናኘት ለሚቆይ ፍቅር እና ለዘለአለማዊ እቅድ አስፈላጊ ነው። ምን በእውነት አስፈላጊ እንደሆነ ለመማር፣ እርሱ እንደሚያፈቅረው ለማፍቀር እና እንደእርሱ በመሆን ለማደግ በአሁን ከእርሱ ጋር ግንኙነትን ማድረግ ይገባናል። ከሰማይ አባት እና ከአዳኝ ጋር ያሉን ታማኝ ግንኙነቶች ለእነርሱ እና ለእኛ በዘለአለም አስፈላጊ ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።