2010–2019 (እ.አ.አ)
የሰማያዊ ብርሀን ተሸካሚዎች
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


የሰማያዊ ብርሀን ተሸካሚዎች

እንደ እግዚአብሔር ክህነት ተሸካሚዎች እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች፣ እናንተ የብርሀን ተሸካሚዎች ናችሁ።

ቴምብር ለመግዛት በፖስታ ቤት የተሰለፉ ሽማግሌ ሰው ነበሩ። በችግር እንደሚራመዱ አንድ ወጣት ሴት ተመለከተችና ጌዜ የማይፈጁበት መንገድ ለማድረግ በማሽን ቴምብሩን ለመግዛት የሚችሉበትን ለማሳየት ሀሳብ አቀረበችላቸው። ሽማግሌውም ሰም እንዲህ አሉ፣ “አመሰግናለሁ፣ ግን ለመጠበቅ እፈልጋለሁ። ማሽኑ ስለ አጥንት መገጣጠሚያ በሽታዬ አይጠይቀኝም።”

አንዳንዴ ስለችግራችን ከሰዎች ጋር መነጋገር ይረዳል።

ህመም፣ ሀዘን፣ እና በሽታ ሁላችንም የምንካፈላቸው አጋጣሚዎች ናቸው—የአደጋ፣ የስቃይ፣ እና የመጥፎ እድል ጊዜዎች በነፍሳችን ውስጣዊ ማከማቻ ውስጥ ተደባብረው ብዙ የትዝታ ቦታዎችን ሊወስዱ ይችላሉ።

ስለሰውነታችን ደህንነት በሚመለከት፣ በእድሜ መግፋትን እና በሽታን የስጋዊ ጉዞ ክፍል ነው ብለን ተቀብለናል። ሰውነትን የሚረዱትን ባለሙያዎች ምክር እንፈልጋለን። በስሜት ጭንቀት ወይም በአዕምሮ በሽታ ስንሰቃይ፣ እንደነዚህ አይነት በሽታዎችን የሚያክሙ ባለሙያዎችን እርዳታ እንፈልጋለን።

ስጋዊ እና ስሜታዊ ፈተናዎች በዚህ ስጋዊ ህይወት እንደሚያጋጥሙን፣ መንፈሳዊ ፈተናዎችም ያጋጥሙናል። ብዙዎቻችን ምስክርነታችን በብሩህ የሚነዱበት ጊዜዎች በህይወታችን አጋጥመውናል። ደግሞም የሰማይ አባት የራቀን የሚመስልበት ጊዜዎችን አጋጥመውናል። የመንፈስ ነገሮችን እንደ ሀብት የምንመለከትባቸው ጊዜዎች አሉ። ደግሞም ዋጋቸው የቀነሰ ወይም ጠቀሜታው የቀነሰ እንደሆነ የሚመስልባቸውም ጊዜዎች ይኖሩም ይሆናል።

ዛሬ ስለመንፈሳዊ ደህንነት—ከሚረጋው ስለመፈወስና በንቁ፣ መንፈሳዊ ደህንነትን ስለመራመድ ለመናገር እፈልጋለሁ።

መንፈሳዊ ህመም

አንዳንዴ መንፈሳዊ ህመም የሚመጣው በኃጢያት ወይም በስሜታዊ ቁስል ነው። አንዳንዴ መንፈሳዊ መሰበር የሚመጣው ቀስ በቀስ ስለሆነ ምን እንደሚከሰት ለማወቅ አንችልም። ደለል እንዳለው ድንጋይ አይነት፣ መንፈሳዊ ህመም እና ሀዘን በጊዜ ሂደት ይገነባሉ፣ ለመሸከም በጣም ከባድ እስከሚመስል ድረስ በመንፈሳችን ይከብዋዳል። ለምሳሌ፣ ይህ ለመድረስ የሚችለው በስራ፣ በቤት፣ እና በቤተክርስቲያን ያሉን ሀላፊነቶች በጣም ከባድ ሆነው የወንጌልን ደስታ ማየት ባለመቻላችን ነው። ምንም ተጨማሪ ለመስጠት እንደማንችል ወይም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ማክበር ከጥንካሬአችን በላይ ነው ብለን ይሰማን ይሆናል።

ነገር ግን በመንፈሳዊ ፈተናዎች እውነት ስለሆኑ ለመፈወስ አይቻሉም ማለት አይደለም።

በመንፈስ ለመፈወስ እንችላለን።

በጥልቅ መንፈሳዊ ቁስልም ቢሆን እንኳ፣ አዎን፣ ለመፈወስ የማይችሉ የሚመስሉትም፣ ሊፈወሱ ይችላሉ፡

ውድ ጓደኞቼ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የመፈወስ ሀይል በጊዜያችን የሌለ አይደለም።

የአዳኝ የሚፈውስ አነካካት በቀናችን ልክ በእርሱ ዘመን እንዳደረጋቸው ህይወቶችን ለመቀየር ይችላል። እምነት ከኖረን፣ እጆቻችንን ይዞ፣ ነፍሶቻችንን በሰማያዊ ብርሀነና ፍወሳ በሞምላት፣ የተቀደሱ ቃላትን ይናገረናል፣ “ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ።”1

ጭለማ እና ብርሀን

የመንፈሳዊ ህመማችንን ምክንያቱ ምንም ቢሆንም፣ ሁሉም አንድ የጋራ ነገር አላቸው፥ የመለኮታዊ ብርሀን አለመገኘት።

ጭለማ በግልጽ ለማየት ያለንን ችሎታ ይቀንሳል። በአንድ ጊዜ ግልጽ የነበረውን እይታችንን እንዲደበዝዝ ያደርጋል። በጭለማ ውስጥ ስንሆን፣ መልካም ያልሆነ ምርጫዎችን የማድረጋችን እድል የሰፋ ነው ምክንያቱም በመንገዳችን አደጋዎችን አናይምና። በጭለማ ውስጥ ስንሆነ፣ ተስፋ እንቆርጣለን ምክንያቱም በቀጥታ ከቀጠልን የሚጠብቁንን ሰላም እና ደስታ ለማየት አንችልምና።

ብርሀን፣ በሌላ በኩል፣ ነገሮች በእውነት እንደሆኑ እንድናይ ያስችለናል። በእውነት እና በስህተት ላይ፣ በአስፈላጊው እና በተራው ላይ በማስተዋል ለመለየት ያስችለናል። በብርሀን ውስጥ ስንሆን፣ በእውነተኛው መርሆች ላይ የተመሰረቱ ጻድቅ ምርጫዎችን እናደርጋለን። በብርሀን ውስጥ ስንሆን፣ “ፍጹም የተስፋ ብርሀን”2 ይኖረናል ምክንያቱም ስጋዊ ፈተናችንን በዘለአለማዊ አስተያየት እንመለከተዋለንና።

ከአለም ጥላ ስንወጣ እና ወደ ዘለአለማዊው የክርስቶስ ብርሀን ስንገባ በመንፈስ መፈወስን እናገኛለን።

የብርሀን ትምህርታዊ መሰረት ስንረዳና ስንጠቀምበት፣ በእያንዳንዱ ጎን እና እጅ በኩል ከሚያስጨንቀውን ወይም ከሚያስቸግረውን መንፈሳዊ በሽታ በተጨማሪ መከላከያ ይኖረናል፤ በሚሻል ሁኔታ እንደ ሀይለኛ፣ ብርቱ፣ ተንከባካቢ፣ እና ትሁት የቅዱስ ክህነት ተሸካሚዎች፣ እንዲሁም እንደ እውነተኛ አገልጋዮች እና እንደውዱና ዘለአለማዊ ንጉሳችን ደቀመዛሙርቶች፣ ለማገልገል እንችላለን።

የአለም ብርሀን

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለው፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም።”3

ይህ ምን ማለት ነው?

ይህም በቀላል፥ በትህትና ኢየሱስ ክርስቶስን የሚከተል የእርሱ ብርሀን ያጋጥመዋል እናም ይካፈላል። እናም ያ ብርሀን በጣም ታላቅ የሆነውን ጭለማ እስከሚበትን ድረስ ያድጋል።

ይህም ከአዳኝ የሚፈነጠቅ ሀይል፣ ጠንካራ ተፅዕኖ አለ ማለት ነው። ይህም “ከእግዚአብሔር ፊት የሀለንተናን ስፋት እስኪሞላ ድረስ”4 ይመጣል። ይህ ሀይል ህይወታችንን ስለሚያብራራል፣ ከፍ ስለሚያደርጋል፣ እናም ስለሚያበራ፣ ቅዱሳት መጻህፍት በብዛት ይህ ብርሀን ብለው ይጠሩታል፣ ነገር ግን ይህም ደግሞ በመንፈስ እና በእውነት ስም ይጠራል።

በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች እንደምናነበው “የጌታ ቃል እውነት ነው፣ እናም እውነት የሆነውም ብርሀን ነው፣ እናም ብርሀን የሆነውም መንፈስ ነው፣እንዲሁን የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ።”5

ይህም ታላቅ አስተያየት—ብርሀን መንፈስ ነው፣ ይህም እውነት መሆኑ እና ያም ብርሀን ወደዚህች አለም በሚመጡ እያንዳንዱ ነፍስ ላይ ማብራቱ—አስፈላጊ እንደሆነው ተስፋ የሚሰጥም ነው። የክርስቶስ ብርሀን ያብራራል እናም የመንፈስን ድምፅ ለሚሰሙት በሙሉ ይሞላል።6

የክርስቶስ ብርሀን ሁለንተናን ይሞላል።

ምድርንም ይሞላል።

እናም እያንዳድኑን ልብ ይሞላል።

“እግዚአብሔር ለሰው ፊት [አያደላም]።”7 የእርሱ ብርሀን ለሁሉም የሚገኝ ነው—ለትልቁም ይሁን ለትንሹ፣ ለሀብታሙም ይሁን ለደሀው፣ መብት ላለውም ይሁን ለሌለው።

አዕምሮአችሁን እና ልባችሁን የክርስቶችን ብርሀን ለመቀበል ከከፈታችሁ እና በትህትና አዳኝን ከተከተላችሁ፣ ተጨማሪ ብርሀን ትቀበላላችሁ። ጭለማ ከህይወታችሁ እስከሚወገድ ድረስ፣ በመስመር ላይ መስመር፣ በዚህም ትንሽ እና በዚያም ትንሽ፣ ተጨማሪ ብርሀንና እውነት በነፍሳችሁ ትሰበስባላችሁ።8

እግዚአብሔር አይኖቻችሁን ይከፍታል።

እግዚአብሔር አዲስ ልብ ይሰጣችኋል።

የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ብርሀን፣ እና እውነት የሚያንቀላፉ ነገሮች እንዲነቁ ያደርጋል፣ እናም እናንተም ወደ ህይወት አዲስነት በኢየሱስ ክርስቶስ በድጋሚ ትወለዳላችሁ።9

ጌታ ቃል እንደገባው፣ “እና ወደ ክብሬ ዐይኖቻችሁ ቢያተኩሩ፣ ሰውነታችሁ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፣ እና በእናንተም ምንም ጭለማ አይኖርም፤ እና ብሩህ የሆነ ሰውነትም ሁሉንም ነገሮች ይረዳል።”10

ይህም ለመንፈስ በሽታ የመጨረሻ መድሀኒት ነው። ጭለማ በብርሀን ፊት ይጠፋል።

የመንፈሳዊ ጭለማ ምሳሌ

ነገር ግን፣ እግዚአብሔር ብርሀኑን እንድናቅፍ አያስገድደንም።

ጭለማ የሚመቸን ከሆንን፣ ልባችን መቀየሩ የማይመስል ነው።

ለውጥ እንዲኖር፣ ብርሀኑን በቅልጥፍና ማስገባት ያስፈልገናል።

እንደ አውሮፕላን አብራሪነት በምድር ላይ ስበር፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት ወብት እና ፍጹምነት እደነቅ ነበር። በልዩም በምድር እና በጸሀይ መካከል ያለው ግንኙነት ያስደንቀኝ ነበር። ጭለማ እና ብርሀን እንዴት መገኘታቸው የሚያስደንቅ ትምህርት እንደሆነ አስብበታለሁ።

ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በየ24 ሰዓት ውስጥ ማታ ወደ ቀን እናም ቀን ወደ ማታ ይቀይራል።

ስለዚህ፣ ማታ ምንድን ነው?

ምሽት ከጥላ በላይ ምንም አይደለም።

በማታ ጭለማም፣ ጸሀይ ብርሀኗን ማብራት አታቆምም። እንደ ሁልጊዜም ታበራለች። ነገር ግን የምድር ግማሽ በጨለማ ውስጥ ናት።

የብርሀን አለመገኘት ጨለማን ይፈጥራል።

የማታ ጨለማ ሲመጣ፣ ተስፋ አንቆርጥም እናም ጸሀይ ጠፍታለች ብለን አናስብም። ጸሀይ የለችም ወይም ሞታለች ብለንም አንገምትም። በጥላ ላይ እንዳለን፣ ምድር በመዞር እንደምትቀጥል፣ እናም በመጨረሻም የጸሀይ ብርሀን እንደገና እንደሚደርሰን ተረድተናል።

ጨለማ ብርሀን እንደሌለ የሚያመለክት አይደለም። በብዚ ጊዜ፣ ይህም ብርሀን በማይቀበልበት ቦታ ውስጥ ነን ማለት ነው። በቅርቡ የጸሀይ በጨረቃ ኋላ በተደበቀችበት ጊዜ፣ ብሩህ በሆነው በጸሀይማ ቀን ውስጥ ጨረቃዋ በፈጠረችው ጥላ ውስጥ ለመገኘት ብዙዎች ጥረት አደረጉ።

በጣም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ፣ መንፈሳዊ ብርሀን በእግዚአብሔር ፍጥረታት ላይ ለማብራት ትቀጥላለች። ሰይጣን ጥላን ለመስራት ወይም ራሳችን በምንሰራው ጥላ ውስጥ እንድንገባ ሁሉንም ጥረቶች ያደርጋል። በራሳችን ብርሀን እንድንደብቅ ይገፋፋናል፤ ወደ ጨለማው ዋሻም እንድንገባ ይገፋናል።

የመንፈስ ጨለማ በፊት በብርሀን ይራመዱ እና በጌታ ይደሰቱ በነበሩት ላይ የመርሳት መጋረጃን ይዘረጋል። ይህም ቢሆን፣ በታላቅ ጨለማ ጊዜ፣ “ጌታ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው”11 ብለን ስንጸልይ እግዚአብሔር የትሁት ልመናችንን ይሰማል።

በአልማ ቀናት መንፈሳዊ ነገሮችን ለመቀበል የሚታገሉ ብዙ ነበሩ፣ እናም “ባለማመናቸው ምክንያት” የእግዚአብሔር ብርሀንና እውነት ወደ ነፍሳቸው ለመግባት አልቻሉም፤ “ልባቸውም ጠጥሮ ነበር።”12

እኛ የብርሀን ተሸካሚዎች ነን

ወንድሞች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን መለኮታዊ ብርሀን እና እውነት ለማየት በትክክለኛ ቦታ መገኘታችን የእኛ ሀላፊነት ነው። ጨለማ ሲሆን እና ምድር የጨለመች ስትመስል፣ በክርስቶስ ብርሀል ለመራመድ፣ ትእዛዛቱን ለማክበር፣ እና በድፍረት የእርሱን እውነትነት እና ታላቅነት ለመመስከር ለመምረጥ እንችላለን።

እንደ እግዚአብሔር ክህነት ተሸካሚዎች እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች፣ እናንተ የብርሀን ተሸካሚዎች ናችሁ። መለኮታዊ ብርሀኑን እንደሚንከባከቡ የሚያደርጉትን ነገሮች በማድረግ ቀጥሉ። “ብርሃናችሁን ከፍ አድርጉ”13 እናም ይህን አይተው እናንተን እንዲያደንቁ ሳይሆን፣ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”14

ውድ ወንድሞቼ፣ ብርሀንን እና ፍወሳን ለሰማይ አባት ልጆች ለማምጣት እቅድ በጌታ እጆች መሳሪያዎች ናችሁ። ምናልባት በመንፈስ የታመሙትን ለመፈወስ ብቁ እንደሆናችሁ አይመሰማችሁም—በእርግጥም የፖስታ ቤት ሰራተኛ በአጥንት ህመን ለመርዳት ብቁ እንደማይሆነው አይነት። ምናልባት የራሳችሁ የመንፈስ ፈተናዎች አሉባችሁ። ይህም ቢሆን፣ ጌታ ጠርቷችኋል። እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት ስልጣን እና ሀላፊነት ሰጥቷችኋል። በቅዱስ ክህነቱ ሀይል ብርሀን ወደ ጨለማ ለማምጣት እና የእግዚአብሔር ልጆችን ከፍ ለማድረግ የመንፈስ ስጦታ ሰጥቷችኋል። እግዚአብሔር “የቆሰለውን ነፍስ የሚፈውሰው”15 ቤተክርስቲያኑን እና ውድ ወንጌሉን በዳግም መልሷል። የመንፈሳዊ ደህንነት፤ ከመቆም ለመዳን እና ወደ ንቁ፣ መንፈሳዊ ደህንነት ለመግፋት መንገድንም አዘጋጅቷል።

በትሁት ጸሎት ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር በምታቀርቡበት ጊዜ ሁሉ፣ ብርሀኑ ያጋጥማችኋል። ቃሉን እና ፍላጎቱን በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ በምትፈልጉበት እያንዳንዱ ጊዜም፣ ብርሀኑ እየጎላ ይመጣል። እርዳታ የሚፈልግ በምታዩበት እና በፍቅር ለመድረስ የራሳችሁን ምቾት በመስዋዕት በምታስቀምጡበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ብርሀኑ ይስፋፋል እናም ያድጋል። ፈተናዎችን ስታስወግዱ እና ንጹህነትን በምትመርጡበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ይቅርታ በምትፈልጉበት ወይም በምትሰጡበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ስለእውነት በደፋርነት በምትመሰከሩበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ ብርሀን ጨለማን ያሸሻል እናም ብርሀንና እውነት የሚፈልጉ ሌሎች ወደዚህ ይሳባሉ።

በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ፣ በቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛ ላይ፣ በጸሎት በሚሰላሰልበት በጸጥተኛ ጊዜ፣ በቤተሰባችሁ መሰብሰብ፣ ወይም በክህነት አገግሎት ስራ ለእግዚአብሔር እና ለሰዎች አገልጎት በምትሰጡበት ያሉ ስለ የግል አጋጣሚያችሁን አስቡ። ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች፣ እና በልዩም ብርሀን ከሚፈልጉት ወጣቶቻችን ጋር እነዚህን ጊዜዎች ተካፈሉ። ከእናንተ፣ በጭለማ በተሸፈነ አለም ውስጥም፣ ይህ ብርሀን ከተስፋ እና ከመፈወስ ጋር እንደሚመጣ እነርሱ መስማት ያስፈልጋቸዋል።

የክርስቶስ ብርሀን ተስፋ፣ ደስታ፣ እና ከማንኛውም መሰረታዊ ቁስል ወይም ህመም መፈወስን ያመጣል።16 ይህ የሚያነጥር ተፅዕኖ የሚያጋጥማቸው በአለም ብርሀን እጆች መሳሪያዎች ይሆናሉ እናም ለሌሎች ብርሀን ይሰጣሉ።17 ንጉም ላሞኒ የተሰማውን ይሰማቸዋል፥ “ይህ ብርሃን በነፍሱ ውስጡ እንደዚያ ያለን ደስታ አምጥቷል፤ የጨለማው ዳመና ተበትኗል፣ እናም የዘለዓለማዊው ህይወት ብርሃን በነፍሱ ውስጡ ተቀጣጥሏል።”18

ውድ ወንድሞቼ፣ ውድ ጓደኞቼ፣ የዘለአለም ህይወት ብርሀኑ በውስጣችን ብሩህ እስኪሆን እና ምስክራችን በጨለማ መካከልም ቢሆን ልበ ሙሉና ጠንካራ እስኪሆኑ ድረስ ጌታን መፈለጋችን አስፈላጊ ነው።

እንደ ሁሉን ቻይ አምላክ ክህነት ተሸካሚዎች እና ሁልጊዜም እንደ ሰማያዊ ብርሀን ደስተኛ ተሸካሚዎች እጣ ፈንታችሁን ለማሟላት ውጤታማ እንድትሆኑ ጸሎቴና በረከቴ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።