2010–2019 (እ.አ.አ)
እርሱ እንደወደደን እርስ በርስ እንዋደድ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


እርሱ እንደወደደን እርስ በርስ እንዋደድ

በእውነት ፍቅር በማገልገል እና ይቅርታ በማድረግ፣ ለመፈወስ እና ፈተናችንን ለማሸነፍ ጥንካሬ ለመቀበል እንችላለን።

በመጨረሻው እራት፣ አዳኝ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ በማለት አዲስ ትእዛዝ ሰጣቸው፥

“እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።

“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”1

የአዳኝ ደቀ መዛሙርት ተጨማሪ ነገር፣ ታላቅ ነገር፣ እና በተጨማሪ መለኮታዊ የሆነ ነገር እንዲያደርጉ አዲስ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል። ይህ አዲስ ትእዛዝ እና ግብዣ “እንደወደድኋችሁ” በሚለው በዋናው ሀረግ በአጭር ይጠቃለላል።

ፍቅር ስራ ነው፤ ፍቅር አገልግሎት ነው።

“ፍቅር ጥልቅ የአምልኮ፣ የሀሳብ፣ እና የማፍቀር ስሜት ነው። ከሁሉም በላይ የሆነው እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ፍቅር ምሳሌ የሚገኘው መጨረዛ በሌለው የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ነው።”2 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”3 “ለእግዚአብሔር እና ለሰው ያለ ፍቅር የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ጸባይ ነው።”4

ባለፉት ከትንሽ አመታት፣ ታላቁ የልጅ ልጃችን ሆዜ አራት አመቱ ሆኖት ሳለ፣ ከባለቤቴ ጋር ይጫወት ነበር። እየሳቁ እና ጥሩ ጊዜ እያሳለፉ እያሉ፣ የልጅ ልጃችን እንዲህ ጠየቋት፣ “እማማ፣ ትወጂኛለሽን?”

እርሷም እንዲህ መለሰች “አዎን፣ ሆዜ፣ እወድሀለሁ።”

ከዚያም ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፥ “እንደምትወጂኝ እንዴት ታውቂአለሽ?”

ስለስሜቷ ገለጸችለት እናም ስላደረገችለት እና ለእርሱ ለማድረግ ፈቃደኛ ስለሆነችበት በሙሉ ነገረችው።

በኋላም ባላቤቴ ሆዜን እንዲህ አይነት ጥያቄ ጠየቀችው፣ በተጨማሪም ይህን ጥልቅ ጥያቄም ጠየቀችው፥ “እንደምትወደኝ እንዴት ታውቃአለህ?”

የዋህ ግን ልባዊ በሆነ መልስ፣ እንዲህ አላት፣ “እወድሻለሁ ምክንያቱም በልቤ ውስጥ ይሰማኛልና።” ሆዜ በዚያ ቀን እና ሁሌም ለአያቱ ያለው የፍቅር ጸባይ ፍቅር የስራ እና የጥልቅ ስሜት ጥማሬ እንደሆነ አሳይቷል።

ንጉስ ቢንያም እንዳስተማረው፥ “እናም እነሆ፣ ጥበብን ትማሩ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እናገራችኋለሁ፤ እናንተ ሰዎችን በምታገለግሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን እያገለገላችሁ እንደሆነ እርግጠኛ ትሆናላችሁ።”5

በተለያዩ ጉዳዮች ብዙ ስቃይ በሚገኝበት በዛሬ አለም ውስጥ፣ የሚያስቅ ስዕል ያለበት የእጅ ስልክ መልእክት መላክ ወይም ፎቶ “እወድሻለሁ” ከሚል ቃል ጋር መላክ ጥሩ እና ዋጋ ያለው ነው። ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ማድረግ የሚገባን የእጅ ስልኮቻችንን መተው፣ እናም በእጆቻችን እና በእግሮቻችን ታላቅ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት ያስፈልገናል። አገልግሎት የሌለው ፍቅር ስራ እንደሌለው እምነት ነው፤ በእርግጥም የሞተ ነው።

ፍቅር ይቅር ማለት ነው

የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር የሆነችው ልግስና፣6 አገልግሎት ለማድረግ እና ለመስጠት ከማነሳሳት በላይ ሁኔታም ምንም ቢሆንም ይቅርታ ለመስጠት ጥንካሬ እንዲኖረንም ታነሳሳናለች። የነካኝን እና ህይወቴን የቀየረውን አጋጣሚ ከእናንተ ጋር ልካፈል። ዛሬ በዚህ የሚገኙት የኩፐር ወላጆች ቴን እና ሼረን፣ በቤተሰባቸው ላይ ከዘጠኝ አመት በፊት የደረሰውን እንድካፈል ፈቃድ ሰጥተውኛል። የምናገረውም በቴድ፣ የኩፐር አባት፣ አስተያየት በኩል ነው፥

ነሀሴ 21 ቀን 2008 (እ.አ.አ) የትምህርት የመጀመሪያ ቀን ነበር፣ እናም የኩፐር ሶስት ወንድሞች፣ አይቭን፣ ጌረት፣ እና ሎገን ሁሉ በአውቶባስ ላይ ለመግባት በባስ ማቆሚያው አጠገብ ይጠብቁ ነበር። አራት አመት የነበረው ኩፐር በቢስክሌቱ ላይ ነበር፤ ባለቤቴ ሼረን በእገ ትሄድ ነበር።

ባለቤቴ በመንገዱ ተሻግራ ነበር እናም ኩበር ተሻግሮ እንዲመጣ ጠቆመችለት። በዚያም ጊዜ፣ መኪና በቀስታ መደ ግራኝ ዞረ እናም ኩፐርን ገጨው።

ጎረቤት ኩፐር በመኪና እንደተገጨ በስልክ ደውለው ነገሩኝ። እርሱን ለማየት ወዲያው ወደ አውቶቡስ ማቆሚያው በመንዳት ሄድኩኝ። ኩፐር በሳሩ ላይ ተኝቶ፣ ለመተንፈስ እየታገለ ነበር፣ ነገር ግን ምንም የሚታይ ጉዳት አልነበረውም።

በአጠገቡ ተንበረከኹኝ እና “መልካም ይሆናል። አይዞህ።” የሚሉ ማበረታቻዎችን አልኩት። በዚያ ጊዜ የከፍተኛ የክህነት ቡድን መሪ፣ ኔተን፣ ከባለቤቱ ጋር መጣ። እርሷም ኩፐርን የክህነት በረከት እንድንሰጠው ሀሳብ አቀረበች። በኩፐር ራስ ላይ እጆቻችንን ጫንን። በበረከቱ ምን እንዳልኩኝ አላስታውስም፣ ነገር ግን በአካባቢያችን ያሉትን ሌሎች በሙሉ አስታውስ ነበር፣ እናም በዚያም ጊዜ ነበር ኩፐር እንደሚሞት የተገነዘብኩት።

ኩፐር በሄሊኮፕተር ወደ ሆስፒታል በመብረር ሄደ፣ ነገር ግን ሞተ። የሰማይ አባት የምድር ሀላፊነቴ እንደተፈጸመ እና ኩፐር በእርሱ እንክብካቤ ስር እንዳለ እንደሚነግረኝ ተሰማኝ።

ከኩፐር ጋር በሆስፒታል የተወሰነ ጊዜ ለማሳለፍ ቻልን። በዚያ የሚሰሩት እርሱን አዘጋጁት እና እርሱን ለማቀፍና ደህና ሁን ለማለት እንድንችል አደረጉ እናም እስከፈለግነው ያህል ከእርሱ ጋር ጊዜ ለማሳለፍና እርሱን ለማቀፍ እንድንችል አደረጉ።

ወደቤት ስንመለስ፣ የምታዝነው ባለቤቴ እና እኔ ተመለካከትን እና መኪናውን ይነዳ ስለነበረው ልጅ ተነጋገርን። አናውቀውም ነበር፣ ምንም እንኳን በዎርዳችን ክልል ውስጥ፣ በአንድ መንገድ መሻገሪያ አካባቢ ቢኖርም።

ሁላችንም በሀዘን ተጥለቅልቀን ስለነበርን የሚቀጥለው ቀን በጣም አስቸጋሪ ነበር። ተንበረከኩኝ እና አቅርቤው ከማውቀው በላይ ልባዌ ጸሎት አቀረብኩኝ። የሰማይ አባት በአዳኝ ስም የሚያጥለቀልቀውን ሀዘን እንዲወስድልኝ ጠየቅኩት። እንዲህም አደረገ።

በዚያ ቀን በኋላም በካስማችን አመራር አንዱ አማካሪ፣ መኪናውን ይነዳ የነበረውን ወጣት ሰው እና ወላጆቹን በአማካሪያችን ቤት ውስጥ እንድንገናኝ አዘጋጀልን። ሼሮን እና እኔ ልጁ እና ወላጆቹ እስኪደርሱ ድረስ ጠበቅን። በሩ ሲከፈት፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኘናቸው። ኤጲስ ቆጶሴም በጆሮዬ እንዲህ አሾከሾኩልኝ፣ “ወደ እርሱ ሂድ።” ሼሮን እና እኔ እርሱን በትብብር አቀፍነው። ለብዙ ጊዜ በሚመስል ያህል አብረን አለቀስን። የደረሰው አደጋ እንደነበረ እንደምናውቅ ነገርነው።

እኛ እንዲህ ስሜት መኖራችን እና አሁንም እንዲሁ ማሰባችን፣ ለእኔ እና ለሼሮን ይህ ታዕምራታሚ ነበር። በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ትልቅ መንገድን፣ ግልፅ የሆነውን መንገድ፣ ብቸኛ የሆነውን መንገድ ለመውሰድና ይህን ወጣት ሰው ለማፍቀር ችለናል።

በሚቀጥሉትም አመቶች ውስጥም ከእርሱ እና ከቤተሰቡ ጋር ቅርብ ለመሆን ችለናል። የእርሱን አስፈላጊ ድርጊቶችን ከእኛ ጋር ተካፍሏል። ለሚስዮን በሚዘጋጅበትም ከእርሱ ጋር ወደ ቤተመቅደስ አብረን ለመሄድም ችለናል።7

ወንድሞችና እህቶች፣ ቴድ ያለጥርጥር የሰማይ አባታችን እንደሚወደን ያውቃል። ይቅርታ ማድረግ መቻል፣ እናም ከራሱ ላይ ሸከምን ማውረድ፣ ይቅርታ እንደማድረግ ጣፋጭ እንደሆነ ያውቃል። ይህም ጣፋጭነት የሚመጣው የታላቁ ምሳሌአችንን ምሳሌ በመከተል ነው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ አልማ ስለአዳኝ እንዳወጀው፣ “እናም በመከራ እናም በሁሉም ዓይነት ህመም እና ፈተናዎች መሰቃየቱን ይቀጥላል፤ የህዝቡን ህመምና በሽታ በራሱ ላይ ለመውሰድ የገባው ቃል ይፈፀም ዘንድ ይህ ይሆናል።”8

ወንድሞችና እህቶች፣ እንዴት የሚያስደንቅ የእውነተኛ ፍቅር እና ምህረት ታሪክ ነው። እኛም ሌሎችን ስናገለግል እና ምህረት ስንሰጥ፣ እንደዚህ ደስታ ለማግኘት እንችላለን። ጊዮርጊ፣ ሌላኛው የልጅ ልጃችን፣ በብዛት እንደሚለው፣ “ምን አይነት ቤተሰብ ነን?” እናም እንዲህ ይመልሳል፣ “እኛ ደስተኛ ቤተሰብ ነን።”

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እንዲህ በማለት እንደመከሩን፥ “ህይወታችንን እንፈትሽ እናም የአዳኝን ምሳሌ ደግ፣ አፍቃሪ፣ እና ለጋስ በመሆን ለመከተል እንወስን።”9

የሰማይ አባታችን እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንደሚወዱን እና እነርሱ እንደሚወዱን እርስ በርስ ስንዋደድ ለመስራት እንደሚረዱን ፈቃደኛ እንደሆኑ አውቃለሁ። በእውነት ፍቅር በማገልገል እና ይቅርታ በማድረግ፣ ለመፈወስ እና ፈተናችንን ለማሸነፍ ጥንካሬ ለመቀበል እንደምንችልም አውቃለሁ። ስለዚህ የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።