2010–2019 (እ.አ.አ)
የእናንተ ደስታ ሙሉ እንዲሆን
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


የእናንተ ደስታ ሙሉ እንዲሆን

ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉም ፈውስ፣ ሰላምና፣ ዘላላማዊ እድገት ምንጭ ነው።

ወንድሞችና እህቶች፣ ከእናንተ ጋር መሆን የሚያስደስት ነው። እናም ያም ከእናንተ ጋር ለመነጋገር የምፈልገው ርዕስ ነው—የደስታ ሙላትን ማግኘት።

የቅርብ አርእስተ ዜና ላይ እንዲህ ተብሎ ተነበበ “መቅሰፍት ህዝብንና አለምን አንቀጠቀጠ።”1 ከአውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ወደ ያልተለመደ ከፍተኛ ሙቀት እና ድርቅ፤ ከሰደድ እሳት እና ከመሬት መንቀጥቀጥ ወደ ጦርነት እና አስከፊ በሽታ፤ “ምድር በሙሉ በሁከት ውስጥ ያለ ይመስላል።”2

በሚሊየን የሚቆጠሩ ህዝቦች ተፈናቅለዋል፤ በቁጥር የማይገለጽ የሰው ልጆች ህይወት በእነዚህ ፈተናዎች ተናውጧል። በቤበተሰብ እና በማህረሰብ ውስጥ ያለ ግጭት እንዲሁም የውስጥ ፍርሃት ትግል፣ ጥርጣሬ፣ እናም ያልተሟላ ግምት ሽብር ውስጥ ይተወናል። ደስታን ለመስማት ይከብዳል ሌሂ ስላስተማረው የህይወት አላማ።3 በአንድ ወቅት ሁላችንም ይሄንን ጥያቄ ጠይቀናል፥ “ለሰላም ወዴት ነው የምዞረው? መጽናናቴ የት ነውን … ?”4 እኛ እናስባለን፣ “እንዴት ብለን ነው ደስታን የምናገኘው ምንም እንኳን ምድራዊ መከራዎች ውስጥ ብናልፍም?”

ይህ መልስ በጣም ቀላል ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ከአዳም ጊዜ ጀምሮ እውነት መሆኑን አረጋግጧል። ዘለቄታዊ ደስታ የሚመጣው በአዳኛችን ላይ ትኩረት ሲኖር ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናም እርሱ ባሳየን እና ባስተማረን ወንጌል መኖር። የበለጠ እምነትም ስለማግኘት፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስለማመን እናም ምሳሌውን ስለመከተል ስንማር እርሱ የሁሉም ፈውስ፣ ሰላምና፣ ዘላላማዊ እደገት ምንጭ እንደሆነ የበለጠ እየተገነዘብን እንመጣለን። እያንዳንዳችንንም ወደ እሱ እንድንመጣ ጋብዞናል፣5 ይህንን ግብዣ ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዲህ ብለው አስታውቀዋል “ማንኛውም ሰው መቀበል የሚገባው በጣም ወሳኝ ግብዣ።”6

ስለኢየሱስ ክርስቶስ መማር

እንዴት ነው ወደ እርሱ የምንመጣው? ባሳለፍነው ሚያዚያ፤ ፕሬዝዳንት ረስል ኤም ኔልሰን እና ሽመግሌ ረስል ኤም. ባላርድ “ህያው ክርስቶስ”ን7 እንድናጠና አበረታተውናል። ብዝዎቻችን ይህንን ስራ ተቀብለን ተባርከናል። ብዙም ሳይቆይ አንዷ የልብ ጏደኛዬ ለአዋቂ ልጆቿ የሰነድ ኮፒ ከወንጌል ስእል ጋር በማድረግ እያንዳንዱን ሃረግ ለመግለጽ ሰጥታቸዋለች። ልጆችዋ የልጅ ልጆችዋን እንዲያስረዷቸውና በቃላቸው እንዲይዙ አበረታታችዋለች። ከትንሽ ጊዜ በኃላ ጏደኛዬ ስድስት አመት የሆናትን የሴት ልጅ ልጇን ሌይኒ በመኮላተፍ በቃሏ የያዘችውን በጉጉትና በራስ መተማመን በተሞላበት የሚያሳየውን የቪድዮ ምስል አካፍላ ነበር። የስድስት አመት ልጅ ይህንን ማድረግ ከቻለች እኔም እችላለሁ ብዬ እኔም መገንዘብ ችያለሁ!

ምስል
“ህያው ክርስቶስ” የገመገመችው ሌይኒ

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮት በትኩረት እና በዝግጅት “ህያው ክርስቶስን” በትውስታ ባጠናሁ ጊዜ፤ ምስጋናዬና በአዳኛችን ላይ ያለኝ ፍቅር ይበልጥ ጨምሯል። መንፈስ የሚያነሳሳው ሰነዱ ላይ የሚገኘው እያንዳንዱ አእረፍተ ነገር ስብከት ይዟል እናም ስለእርሱ መለኮታዊ አስተዋጽኦ እና ምድራዊ ተልእኮ ግንዛብዬን አንጾታል። የተማርኩትና የተሰማኝ በዚህ የጥናት እና በጥልቅ ማሰብ ወቅት በእውነት ኢየሱስ “ ብርሃን፣ ህይወት፣ እና የአለም ተስፋ”8 መሆኑን አረጋግጦልኛል። Aእርሱን በማሞገስ በጥንት ቅዱሳት መጻህፍት እና በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የተጻፉት ወይም የተናገሩት “በዚህ ህይወት ወደደስታ እና በሚመጣው አለምወደ ዘለአለም ህይወት የሚመራው የእርሱ መንገድ ነው”9 ይላሉ።

በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ማድረግ

የክርስቶስን ህይወት እና አስተምሮት በብዙ መንገድ ስታጠኑ፤ በእርሱ ላይ ያላችሁ እምነት ይጨምራል። እሱ እንደሚያፈቅራችሁ እናም በፍጹም እንደሚረዳችሁ እያወቃችሁ ትመጣላችሁ። በ33 አመት የሟች ህይወቱ፣ እርሱ ተቃውሞን፣ አግልሎን፣ ስጋዊ ርሃብን፣ ጥማትን፣ እናም ድካምን፣10 ብቸኝነትን፣ ቃላዊና አካላዊ ጉስቁልናን፣ እናም መጨረሻ ላይ፣ በሃጥያተኞች እጅ በስቃይ ሞት ውስጥ አልፏል።11 በጌተሰማኔ የአታክልቱ ቦታ እናም በቀራንዮ መስቀል ላይ፣ የሁላችንንም ህመም፣ ስቃይ፣ ፈተና፣ በሽታ እና ድክመት ተሰምቶታል።12

በምንም ነገር ብንሰቃይ፣ እርሱ የፈውሳችን ምንጭ ነው። ማንኛውም ስቃይ አይነት ውስጥ ይለፉ፣ በአስደንጋጭ ሁኔታ መክሰር፣ ስር የሰደደ ህመም ወይም አካለ ስንኩል የሚያደርግ መቅሰፍት፣ የውሽት ክስ፣ ጭካኔ የበዛበት ጥላቻ፣ በሃጥያት ምክንያት ወይም ካለመረዳት የሚመጣ መንፈሳዊ ጉዳት በሙሉ በአለም አዳኝ ይድናሉ። ነገር ግን እርሱ ያለ ግብዣ አይገባም። እኛ ወደ እርሱ መምጣት ይኖርብናል እናም ታዕምራቱን እንዲሰራ መፍቀድ አለብን።

አንድ ውብ ጸደይ ቀን ንጹሕ አየር እንዲገባ በሬን ከፈትኩ። ትንሽዬ ወፍ በሮ ገባ ከዛ እዛ መሆን እንዳልፈለገ ተረዳ እና በሚያሳዝን ሁኔታ ክፍሉን በሙሉ በረረ። እየደጋገመም ወደ መስታወቱ መስኮት ለማምለጥ በረረ። ቀስ ብዬ ወደበሩ ለመምራት ሞከርኩ፣ ነግር ግን ፈራ እናም ሸመጠጠ። በመጨረሻም በመስኮቱም ጫፍ ላይ ባለው መጋረጃ ላይ በድካም ግራ በመጋባት አረፈ። የመጥረጊያ እንጨት በማምጣት ወፉ በፍርሃት ወዳአረፈበት ቦታ አስጠጋሁት። የመጥረጊያውን እራስ ከወፉ እግር ስር ሳስቀምጥለት መጥረጊያው ጭራሮ ላይ ወጣ። ቀሰ በቀስ በሩን ለመክፈት ተራመድኩ፤ መጥረግያውን ላለማንቀሳቀስ ይዤ። ልክ በሩ ጋር ስንደርስ፤ ወፉ በፍጥነት ወደ ነጻነት በረረ።

እንደ ወፉ፤ አንዳንዴ እኛም ለማመን እንፈራለን ምክያቱም የእግዛብሔርን ፍቅርንና እኛን ለመርዳት ያለውን ፍላጎት ስለማንረዳ ነው። ነገር ግን ስለ ሰማዩ አባት እቅድና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተልእኮ ስናጠና የእነሱ ኣላማ ለኛ ዘላለማዊ ደስታን እና እድገት መሆኑን እንረዳለን።13 ስንጠይቅ፣ ስንሻ፣ እናም ስናንኳኳ እኛን ለመርዳት ይደሰታሉ።14 እምነታችንን ስንለማመድ እና በትሕትና ለመልሳቸው ራሳችንን ስንገልጽ፤ ካለመንገዘባችንና ከማመንታት ነጻ እንወጣለን፤ እናም ወደ ፊት ማየት እንችላለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ምንጭም ነው። “በሰፊው እጆቹ እንድንደገፍ”15 ጋብዞናል እናም “መረዳት ከምንችለው በላይ የሆነን ሰላም”16 ቃል ገብቶልናል፣ ይህም ሰላም የሚመጣው የእርሱ መንፈስ ምንም ያህል በፈተና ብንከበብም እንኳን “ሰላምን ሲነግረን በሚሰማን ስሜት”17 ነው። የግል ትግሎች ቢሆኑም የቤተሰብ ችግሮች፣ ወይም የህብረተሰብ ጠንቅ፣ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የሚያመውን ነፍሳችንን ለመፈወስ ሀይል እንዳለው ስናምን ሰላም ይመጣል።

ምስል
ስንጀዛና ፖድቪንስኪ፣ በክሮኤሽያ የሚኖር አባል

ስኔጄዝና ፖድዪንስኪ በትንሽ ከሚቆጠሩ ቅዱሳን አባላኣት በካርሎቫክ ክሮኣትያ ውስጥ ያለች፣ በአዳኛችን ላይ ተደገፈች ባለፉት በስድስት ወራት ውስጥ ባለቤትዋንና ሁለቱንም ወላጆችዋን ባጣች ጊዜ። ሃዘን አደረባት ነገር ግን የቤተሰብ ዘላለማዊነት ምስክርነትዋ፣ ያላትን ሁሉ ቁጠባ ወደ ቤተ መቅደስ ለመጓዝ ተጠቀመች፤ ከወላጆችዋ እንዲሁም ከባለቤትዋ ጋርም ታተመች። ቤተ መቅደስ ውስጥ ያሳለፈችው ጊዜ ለሷ የህይወቷ ምርጥ ጊዜ መሆኑን አካፍላ ነበር። በኢየሱስ ክርስቶስ እናም በቤዣነቱ ባላት ጽኑ ምስክርነት ምክንያት ሰላምንና ፈውስን ሊሰማት ችሏል በሷ ዙርያ ላሉት ደሞ ጥንካሬን ሆናለች።

እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ከፈውስና ከሰላም በላይ ብዙ ስጦታዎችን ያመጣል። ፕሬዝዳንት ሄነሪ ቢ. አይሪንግ እንዳካፈሉት እንደ እናንተም፣ ጌታ ሰላም ሲያስፈልገኝ አፅናኚው እንዲጎበኘኝ ለላከልኝ ብዙ መነዶች ምስጋና አለኝ። ነገር ግን የሰማይ አባት ስለእኛ ምቾት የሚያስብ ብቻ ሳይሆን ደግሞም በተጨማሪ ስለእድገታችን ያስባል።”18

በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት፤ የመድሃኒት ስጦታና ትንሳኤ ምክንያት ንስሃን መግባት፣ መለወጥና፣ በዘለአለም ማደግ እንችላለን። ስንታዘዝ እሱ በሚሰጠን ሃይል ምክንያት እኛ ብቻችንን መሆን ከምንችለው በላይ መሆን እንችላለን። አሁን ሙሉ በሙሉ ላንገነዘብ እንችላልን ነገር ግን እያንዳንዳችን በክርስቶስ ላይ እምነታችን ሲጨምር የተሰማን ሁሉ የበለጠ ስለመለኮታዊ ማንነታችን እና አላማ ግንዛቤ ተቀብለናል፤ በእውቀታችንም አንድ አይንት ውሳኔ እንድንወስን።

ምንም እንዃን አለም “ወደ እንስሶች”19 ኩሬ ደረጃ ሊወረውን ቢሞክርም እግዛብሔር አባታችን መሆኑን ማወቃችን መለኮታዊ አቅማችንን እና ንጉሳዊ ቃልኪዳንን ያረጋግጥልናል። ምንም እንኳን አለም ይቺ ህይወት መውጫ እንደሌላት ቢነግረንም፤ የእግዛብሔር አንድያ ልጅ ማወቃችን እኛ እንድንድንና ትንሳኤን እንድናድርግ ተስፋን በመስጠት ቀላል አድርጎልናል።

ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የበለጠ ስንማር፤እምነታችን የበለጠ ያድጋል እናም በሚገባ ምሳሌውን መከተል እንፈልጋለን። ታላቁ ፍላጎታችን ትእዛዛቱን መጠበቅ ይሆናል። ልባችን እንደሱ የሌሎችን ስቃይ ለማስታገስ ይሻል፣ እኛ ያገኘነውን ሰላምና ደስታ እነሱ እንዲያገኙ እንሻለን።

ለምንድን ነው እሱ ያደረገውን ማድረግ ሃያል የሆነው? ምክንያቱም እምነታችንን ስራ ላይ ስናውል፣ መንፈስ ቅዱስ ዘላለማዊ እውነትን ይመሰክርልናል።20 ኢየሱስ ተከታዮቹን ትእዛዛቱን እንዲጠብቁ አዟቸው ነበር ምክንያቱም የእርሱን ምሳሌ ስንከተል መደሰት እንጀምራለን፣ በመንገዱ ስንቀጥል ሙሉ ደስታ ይኖረናል። እንዲህም ብሎ አስረዳ “እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ፣ ደስታዬ እናንተ ላይ እንዲሆን ነው፣ እናም ደስታችሁ ሙሉ እንዲሆን።”21

ምስክርነታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እና በወንጌሉ መደብአለት ላይ ነው የተመሰረተው? የህይወት ማእበል ሲጫነን በፍጥነት ከመፀሀፍ ላይ ወይም ከኢንተርኔት ላይ እርዳታ ለማግኘት እንመለከታለን? በችግር እና በመከራ ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እውቀት እና ምስክርነት ለማዳበር ጊዜ ስንወስድ ብዙ ውጤት እናገኛለን። እለት በእለት ቅዱሳን መጽሀፍትን ማንበብ እና የነብያትን ቃል ማሰላሰል፣ ትርጉም ያለው ጸሎት ማድረግ፣ በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን በሙሉ ሀሳብ መካፈል፣ አዳኙ እንደሚያደርገው አገልግሎት መስጠት እነዚህ እያንዳንዱ ቀላል ተግባራት ለደስተኛ ሀይወት ገንቢ ብሎኬቶች ይሆናሉ።

ደስታን የሚያመጣላችሁ ምንድን ነው? ከረዥም ቀን በኃላ የምትወዷቸውን ሰዎች አይን ማየት ነውን? በተፈጸመ ስራ መረካት? የአይናቸው ብርሃንን ማየት ነው ሸክማቸውን ስንካፈል? ልብ ውስጥ ጠልቆ የሚገባ የዝማሪ ቃል ነውን? የቅርብ ጏደኛ የሙገሳ ጭብጨባ? ስለበረከታችሁ ለማሰብ ጊዜ መውሰድ እና ለማካፈል መንገድ መፈለግ። ሌሎችን ለማገልገል ስትድርሱ እናም ጎረቤት ወይም በታላቅ ብጥብጥ ውስጥ ባለው አለም ላይ የሚገኙ ወንድምና እህቶቻችሁን ስታነሱ፤ ታላቅ ሰለም እናም ፈውስ እናም እድገት ይሰማችኃል።

ወደ እርሱ ኑ ሁኔታዎቻችሁ ምንም ቢሆን ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወታችሁ ማእከል ካደረጋችሁት ደስታን እንደምታገኙ እመሰክርላችኋለሁ። በእርግጥም “አንዱ እሱ ብቻ” 22 ነው መልሱ። በትጋት ጥናት፣ በእርሱ ታላቅ እምነት በማሳደግ፣ እና እንደ እርሱ ለመሆን በመጣር ኢየሱስ ክርስቶስን ለማወቅ ጊዜ ስጡ እናም ጊዜ ውሰዱ። ይህን ስናደርግ፣ እኛም፣ “እግዚአብሔር አቻ ለሌለው መለኮታዊው ልጁ ስጦታ ምስጋና ይሰጠው”23 በማለት እንነሳሳለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።