2010–2019 (እ.አ.አ)
ጉዞው ቀጥሏል!
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ጉዞው ቀጥሏል!

ወደሰማይ አባታችን መጓዝ ከህይወታችን ሁሉ አስፈላጊ የሆነ ጉዞ ነው።

ከአንድ መቶ ሰባ ዓመታት በፊት ብሪገም ያንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሶልት ሌክ ሸለቆን በማየት “ይህ ትክክለኛ ቦታ ነው!” በማለት አወጀ።1 ቦታውን ያውቅ ነበር ምክንያቱም ጌታ ገልጾለት ነበርና።

በ1869 (እ.አ.አ) ከ70,000 የሚበልጡ ቅዱሳን ተመሳሳይ ጉዞን አደረጉ። በቋንቋ፣ በባህል እና በብዛት ልዩነቶች ቢኖሩም ስለ አብ፣ ስለ ወልድ እና ስለ መንፈስ ቅዱስ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መመለስ እና ለአዳኝ ዳግም ምጽአት ለመዘጋጀት የሰላምን፣ ደስታ እና የውበት ቦታን ጽዮንን የመገንባት ፍላጎት ነበራቸው።

ምስል
ጄን ማኒንግ ጄምስ

በዩታ ከመጡ ከነዚህ የመጀመሪያ ቅዱሳን መካከል ጁማን ማኒንግ ጀምስ ነው —ነፃ የወጣ የባሪያ ሴት ልጅ፣ ወደ ተመለሰው ቤተክርስትያን የተለወጠች፣ እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን የተሸከመች አስገራሚ ደቀ መዝሙር ነበረች። እህት ጄምስ በ 1908 (እ.አ.አ) በ87 ዓመቷ እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ ታማኝ የኋለኛው ቀን ቅዱስ ሆና ቆይታለች።

እንዲህም ጻፈች፥ “እዚህ ልናገር እፈልጋለሁ፣ ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደምታስተምረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ያለኝ እምነቴ ዛሬም ጠንካራ ነው፣ ከተቻለም ከተጠመኩበት ቀንም በላይ ብርቱ ነው። አስራቶቼንና መሥዋዕቶቼን እከፍላለሁ፣ የጥበብ ቃልን እጠብቃለሁ፣ በጊዜም ወደመኝታም ሄጄ በማለዳም እነሳለሁ፣ ለሁሉም ጥሩ ምሳሌ ለመሆን በደካማው መንገዴ እሞክራለሁ።”2

እህት ጄምስ እንደ ሌሎቹ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጺዮንን በደሟ በላቧ እና እንባዎቿ ብቻ የገነባች ሳይሆን፣ በህይወቷ የወንጌል መርሆችን በምትችለው መጠን በመኖር የጌታን በረከቶች ፈለገች እናም በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እሱን ከልብ ለሚፈልጉ ሰዎች ታላቅ ፈዋሽ በሆነው እምነትን ያዘች።

የቀድሞዎቹ ቅዱሳን ፍጹማን አልነበሩም፣ነገር ግን እኛ አሁን ቤተሰቦችን የምንገነባበት መሰረት እና ቃል ኪዳናቸውን የሚወዱ እና የሚጠብቁ ማኅበረሰብን አቋቋሙ፣ ለእየሱስ ባለን መሰጠት እና በቅርብ እና በሩቅ ያሉትን ለመርዳት ያለን ፈቃደኛ ጥረት በአለም ዙሪያ በተለያዩ የዜና አምዶች ተዘግቧል።3

ፕሬዘደንት አይሪንግ፣ በሚክሲኮ፣ ቴክሳስ፣ እና ሌሎች ቦታዎች ለሚያገለግሉት ብዙ ሺህ የቢጫ ሸሚዝ መላዕክቶችም ምስጋናዬን ልጨምር።

መስራች አባቶቻችንንና እናቶቻችንን ጨምሮ ከእኛ በፊት ከነበሩት ጋር ያለንን ግንኙነት ካጣን በጣም ውድ የሆኑ ሀብቶችን እናጣለን። ላለፉት ጊዜያት ስለ “እምነት በእያንዳንዱ እርምጃዎቼ” ተናግሬአለሁ እናም ወደፊትም እቀጥላለሁ ምክንያቱም መጪው ትውልዶች በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና በዳግም በተመለሰው የእርሱ ወንጌል ተመሳሳይ እምነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ስለማውቅ ነው። 4

የኔም መስራች ቅድመ አያቶቼ እና እናቶቼ የእጅ ጋሪን ከጎተቱ፣ ሰረገላን በመንዳት እና በእግር በመጓዝ ወደ ዩታ ከገቡ መካከል ናቸው። ልክ እንደ እህት ጄን ማኒንግ ጄምስ የእራሳቸውን ጉዞ ሲጀምሩ በእያንዳንዱ እርምጃቸው ላይ ጠንካራ እምነት ነበራቸው።

የእነሱም የለት ተለት ማስታወሻ ደብተር ስለ መከራቸው፣ ረሃባቸው እና ህመማቸው የሚገልጽ፣ እንዲሁም በእግዚአብሄር እና በዳግም በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ ያላቸውን ምስክርነት የተሞሉ ናቸው።

እነሱ ጥቂት ዓለማዊ እቃዎች ነበሯቸው ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ካገኙት የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ታላቅ በረከቶችን አግኝተው ነበር። በተቻላቸው ጊዜ በግፍ የተደቆሱትን በማንሳት የታመሙትን እና እርስ በርስ እና በእግዚአብሔር የክህነት ስልታን ባረኩ።

በካሽ ቫሊ ዩታ የሚገኙት እህቶች በሴቶች መረዳጃ ማህበር መንፈስ ውስጥ “የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት በአንድነት በመስራት” አገልግለዋል።5 ቅድመ አያቴ ማርጋሬት ማክኒል ባላርድ ባለቤታቸው ሄንሪ፣ ኤጲስ ቆጶስ በነበሩበት ጊዜ ለ 40 ዓመታት ከጎናቸው አገልግለዋል። ማርጋሬት ለ 30 አመታት በአጥቢያው ውስጥ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዘደንት ነበሩ። ድሆችን፣ ታማሚዎችን፣ እና ባሏ የሞተባትን እና ወላጅ አልባ የሆኑትን ወደ ቤታቸው ወስደዋል፣ እናም ንጹህ የቤተመቅደሳቸውን ልብሶች አንስተውም ለሙታን አልብሰዋል።

ምንም እንኳን ታሪካዊውን የ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሞርሞን ፈር ቀዳጆችን ጉዞ ማስታወስ አስፈላጊ ቢሆንም፣ “በእያንዳንዱ እርምጃ ላይ እምነታችንን” በማሳየት እያንዳንዳችን “የሕይወት ጉዞ ሁሉ መቀጠሉን” ማስታወስ አለብን።

ምስል
አባላት በክልላቸው በሚገኙ ቡድኖች ተሰበሰቡ

አዳዲስ አማኞች ከአሁን በኋላ በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሰፈራ ፈር ቀዳጆች ለመሆን አይሰበሰቡም። በምትኩ፣ አማኞች የሰማይ አባታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚሰግዱበት ወደ አካባቢያቸው ጉባኤዎች ይሰበሰባሉ። በዓለም ዙሪያ ከተቋቋሙት ከ 30,000 በሚበልጡ ጉባኤዎች ውስጥ ሁሉም በራሳቸው ጽዮን ይሰበሰባሉ። ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚጠቁሙት “ይህች ልበ ንጹ፣ ጽዮን ናት።”6

በህይወት መንገድ ስንራመድ፣ “ጌታ [ያዘዘንን] ሁሉንም ነገሮች ለማድረግ እንትጋ” መሆኑን ለማየት እንፈተናለን።7

ብዙዎቻችን ወደ ግላዊ መፈጸምና ወደ መንፈሳዊ ብርሃን ወደሚመሩ በሚያስደንቅ የግኝት ጉዞ ላይ ነው ያለነው። አንዳንዶቻችን ግን ለሐዘን፣ ለኃጥያት፣ ለጭንቀት፣ እና ለተስፋ መቁረጥ በሚዳር ጉዞ ላይ ነን ያለነው።

በዚህም ሃሳብ ውስጥ እባካችሁን እራሳችሁን ጠይቁ፤ የመጨረሻ መድረሻችሁ ምንድነው? የእግር እርምጃዎቻችሁ ወደየት ነው የሚያመሩት? እናም እርምጃዎቻችሁ አዳኝ ቃል ወደገባው “ወደበረከት ብዛት” ነውን የሚያመራው?8

ወደ ሰማይ አባታችን የሚያመራው ጉዞ በህይወታችን ውስጥ ካሉ ጉዞዎች በጣም አስፈላጊው ጉዞ ነው፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ እና በየዓመቱ በእሱ እና በተወደደው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችንን ስንጨምር ይቀጥላል

የእኛ የሕይወት ጎዳና በየትኛው መንገድ እንደሚወስደን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። የኢየሱስን ምክር ለደቀመዛሙርቱ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ እንደሰጠው ንቁ በመሆን መታዘዝ አለብን፤ “ንገረን፣ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?

“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ ማንም ሰው[ሴትንም የሚለውን ጨምራለሁ] እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።”9

ዛሬ የቤተክርስቲያኗ መሪዎችን ቀድመው የሰጡትን ምክር እደግማለሁ።

  • ወንድሞች እና እህቶች፣ የክርስቶስን ትምህርት ንጹህ አድርጋችሁ ጠብቁ እናም ትምህርቱን በሚለውጡ ሰዎች በምንም አትታለሉ። የአብ እና ወልድ ወንጌል ለዚህም የመጨረሻው ዘመን ነቢይ በጆሴፍ ስሚዝ በዳግም መመለሱን ተመልክተናል።

  • ያልተሾሙ እና/ወይም ለቤተክርስቲያኗ ጥሪ ያልተለዩ እና በቤተክርስቲያኗ አባላት በጋራ ስምምነት እውቅና ያልተሰጣቸውን አታዳምጡ።10

  • በዛሬው ጊዜ ሐዋርያት እና ነቢያት ያላወቁትን ወይም የማይረዱትን የመሠረተ ትምህርት ጥያቄዎች ምስጢራዊ ምላሽ አለን የሚሉ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችን፣ ወይም ግለሰቦችን ልብ በሉ።

  • ሀብታን ታገኛለህ በሚል ዘዴዎች የሚያስቱትን አትሰሙ። አባሎቻችን በጣም ብዙ ገንዘብ አጥተዋል፣ ስለዚህ ተጠንቀቁ።

በአንዳንድ ቦታዎች፣ ብዙዎች የኛ ሰዎች ከዕይታ በላይ እና ፈውስን እና ድጋፍን እናቀርባለን በሚሉ ውድ እና አጠያያቂ ልምዶች ላይ ምስጢራዊ ዕውቀትን በመፈለግ ላይ ናቸው።

ከአንድ ዓመት በፊት የተሰጠ የቤተክርስትያን መግለጫ እንዲህ ይላል፤ “የቤተክርስቲያኑ አባላት በገንዘብ ተዓምራዊ ፈውስ ለማድረግ ወይም ልዩ ስልት እንዳላቸው ከሚናገሩት በአግባቡ ከተሾሙት የክህነት ተሸካሚዎች የማዳን ኃይል ውጪ በማንኛውም ቡድን ውስጥ ስለመሳተፍ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እናሳስባለን።”11

የቤተክርስቲያኗ መተዳደሪያ መጽሃፍ እንደሚመክረው፥ “አባላት በሥነ ምግባር ወይም በህጋዊ መልኩ አጠያያቂ የሆኑ የሕክምና ወይም የጤና ተግባራትን መጠቀም የለባቸውም። የአካባቢያዊ መሪዎች የጤና ችግር ያለባቸው አባላት በአገራቸው ውስጥ ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማማከር እንዳለባቸው ይንገሩ።”12

ወንድሞችና እህቶች፣ እንዲህ ዓይነቶቹ ድርጊቶች ለስሜት የሚያማልሉ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻ በመንፈሳዊም ሆነ በአካል ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ።

ለፈር ቀዳጅ ቅድመ አያቶቻችን፣ ነጻነት እና በራስ መተማመን አስፈላጊዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የማኅበረሰብነት ስሜታቸው በጣም አስፈላጊ ነበር። አብረው በመስራት በጊዜያቸው ያሉትን አካላዊ እና ስሜታዊ ችግሮች ለማሸነፍ እርስ በርሳቸው ይደጋገፉ ነበር። ለወንዶቹ የክህነት ጉባኤ ነበር፣ እና ሴቶች በሴቶች መረዳጃ ማህበር ይገለገሉ ነበሩ። እነዚህ ውጤቶች በዘመናችን አልተለወጡም።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የክህነት ቡድኖች ለአባሎቻችን መንፈሳዊ እና ጊዜያዊ ደህንነት ያቀርባሉ።

ወደ ሰማይ አባት እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰላም መመለስ እንድትችሉ “በእያንዳንዱ እርምጃዎቻችሁ እመኑ” በወንጌልም መንገድ ላይ ቆዩ። ጌታ የኛ ውድ አዳኛችን ነው። አለምን የዋጀው እሱ ነው። የእርሱን ቅዱስ ስም ማክበር እና በምንም በክንቱ አለመጠቀም፣ ሁልጊዜም ትእዛዛቱን ለማክበር መጣር ይገባናል። እንዲህ ካደረግን, ይባርከናል እናም በደህንነት ወደቤት ይመራናል።

ድምጼን ለምትሰሙ ሁሉ፣ ማንኛውንም ዛሬ በራሳቸው ጉዞ ላይ ያሉትን በመንገዳቸው ውስጥ የትም ቢሆኑ፣ እንድትቀበሏቸው እና በእቅፋቸሁ ውስጥ እንድታደርጓቸው እጋብዛለሁ።

ከተመለሰው ወንጌል የተሻለ፣ ከተቀበልነው እና ከኖርነው፣ ዘለአለማዊ ደስታን እና ሰላምን፣ ዘለአለማዊ ህይወትንም ጭምር ቃል የሚገባ በረከት በላይ ማንም ሰው ሊያካፍል እንደማይችል እባካችሁ አስታውሱ። የእኛን ጉልበት፣ ጥንካሬ፣ እና ምስክርነት ሚስዮኖቻችንን የእግዚአብሔርን ልጆች እንዲመሩ ለመርዳት፣ ለማስተማር እና ለማጥመቅ ለመርዳት እንጠቀምባቸው።

የእግዚአብሔር ልጆች በርኅራኄ መቀበል አለብን እና የዘረኝነት፣ የጾታ እና ብሔራዊ ስሜት ጭፍን ጥላቻን ማስወገድ ይኖርብናል። በዳግም የተመለሱት የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በረከቶች በእውነትም ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ እንደምናምን ይነገር።

“ጉዞው መቀጠሉን” እመሰክራለሁ፣ እና በወንጌል ጎዳና ላይ እንድትጓዙ ፣ ወደ እግዚአብሄር ልጆች ሁሉ በፍቅር እና ርህራሄ ውስጥ በመድረስ፣ ልባችንን ንጹህ እና እጆቻችን ንፁህ እንዲሆኑ ለማድረግ የሰማይ አባታችንን እና ውድ ልጁን በእውነት ለሚወዱ ሁሉ እየጠበቃችሁ ያለውን “የበረከት ብዛት” መቀበል እንድንችል ሁላችሁንም እጋብዛለሁ፣ ለዚህም በትሁት የምጸልየው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።