2010–2019 (እ.አ.አ)
የሁሉም ነገሮች እውነታ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


የሁሉም ነገሮች እውነታ

እያንዳንዳችን ጠንካራ ምስክርነትን ለማግኘት እና ለማቆየት አስፈላጊውን ነገር የማድረግ የግል ሀላፊነት አለብን።

እውነትን በሚያስተምረው መንፈስ ቅዱስ ጠንክረን እና ተባርከን እንደምንመለስ ተስፋ በማድረግ እና በማመን በዚህ ምሽት መጥተናል።1 ልናገር የምፈለገው ስለ የግል እውነትን ፍለጋችን ነው።

እንደ ወጣት፣ ስለቤተክርስቲያኗ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ። አንዳንድ ጥያቄዎቼ ቅን ነበሩ። ሌሎቹ ግን አልነበሩም እናም የሌሎችን ጥርጣሬ የሚያንጸባርቁ ነበሩ።

በብዛት በጥያቄዎቼ ላይ ከእናቴ ጋር እናወራ ነበር። ብዙዎቹ ጥያቄዎቼ ቅን እና ከልብ እንደነበሩ እንደተሰማት እርግጠኛ ነኝ። ብዙም ቅን ባልነበሩት እና በይበልጥ አከራካሪ በነበሩት ጥያቄዎች ትንሽ ቅር ተሰኝታ እንደነበር አስባለሁ። ሆኖም፣ ጥያቄዎች ስለነበሩኝ ዝቅ አታደርገኝም ነበር። ታዳምጥና ለመመለስ ትምክራለች። የምትችለውን ያህል ሁሉ ካለች በኋላ እና አሁንም እኔ ጥያቄዎች እንዳሉኝ ሲሰማት፣ እንዲህ አይነት ንግግር ትናገር ነበር፥ “ዴቪድ፣ ያ ጥሩ ጥያቄ ነው። መልስ ለማግኘት እየፈለክ፣ እያነበብክ እና እየፀለይክ ሳለህ፣ ለምንድን ነው ማድረግ እንዳለብህ የምታቃቸውን ነገሮች የማታደርገው እና ማድረግ የሌለብህን ነገሮችን ደግሞ ከማድረግ የማትቆጠበው?” ይሄ እውነትን ለማድረግ ባለኝ ፍለጋ ላይ መርህዬ ሆነ። በማጥናት፣ በፀሎት እና ትእዛዛትን በመጠበቅ፣ ለሁሉም አስፈላጊ ጥያቄዎቼ መልሶች እንዳሉ ተረዳሁ። ለአንዳንድ ጥያቄዎች፣ ቀጣይ እምነት፣ ትእግስት፣ እና መገለጥ እንደሚያስፈልግም ተረዳሁ።2

እምነት የማሳደግ እና መለስ የማግኘት ሀላፊነትን እማዬ በእኔ ላይ አደረገች። አስፈላጊ መልሶች የሚመጡት የሰማይ አባት በጠቆመው መንገድ በራሴ እውነትን ስፈልግ እንደሆነ እርሷ ታውቅ ነበር። እውነትን ማግኘት ያስፈልገኝ እንደነበር ታውቅ ነበር። በጥያቄዎቼ ቅን መሆን እና እውነት እንደሆኑ የማቃቸውን መተግበር እንደሚያስፈልገኝ ታውቅ ነበር። ማንበብ እና መፀለይ እናም መልሶችን ከጌታ ስሻ ታላቅ ትእግስትን ማሳደግ እንደሚያስፈልገኝ ታውቅ ነበር። ታጋሽ የመሆን ፍቃደኝነት እውነትን የመፈለግ ክፍል ነው እናም የጌታ እውነትን የመግለፅ ሂደት ክፍል ነው።3

ከጊዜያት በኋላ፣ እናቴ እያስተማረችኝ የነበረው እውነትን የመፈለግ የሰማይ አባትን መርህ መሆኑን አወኩ። እምነቴ አደገ፣ መልሶች መምጣት ጀመሩ፣ እና የሚስኦናዊ ጥሪን ተቀበልኩ።

በሚስኦኔ መጀመሪ ላይ፣ ቤተክርስቲያኑ እውነት እንደሆነች እና ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚአብሔር ነቢይ እንደነበር ማወቅ እንደነበረብኝ የተሰማኝ ወቅት መጥቶ ነበር። ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ በግልጽ የገለፁት ተሰምቶኝ ነበር፥ “ስለነዚህ ነገሮች ጠንካራ ምስክርነት ከሌላችሁ፣ እንዲኖራችሁ ማድረግ የሚያስፈልጋችሁን አድርጉ። በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜዎች የራሳችሁ ምስክርነት ማግኘታችሁ አስፈላጊ ነው፣ የሌሎች ምስክርነቶች የተወሰነ እርዳታ ነው የሚሰጣችሁና።”4 አስፈላጊ የነበረው ምን እንደሆነ አውቅ ነበር። መጽሐፈ ሞርሞንን በቅን ልብ፣ በሙሉ መሻት ማንበብ፣ እና እውነት እንደሆነ እግዚአብሔርን መጠየቅ ያስፈልገኝ ነበር።

በነብዩ ሞሮኒ አማካኝነት የሰማይ አባታችን የሰጠውን ድንቅ ቃል አዳምጡ፥ “እናም እነዚህን ነገሮች በምትቀበሉበት ጊዜ እነዚህ ነገሮች ሀሰት እንደሆኑ ዘለአለማዊ አባታችሁ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ስም እድትጠይቁት እመክራችኋለሁ፣ እናም በንፁህ ልባችሁ፣ ከእውነተኛ ስሜት በክርስቶስ አምናችሁ ከጠየቃችሁት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እውነቱን ይገልፅላችኋል።”5

በመጻሐፈ ሞርሞን ውስጥ ያለውን ለመቀበል፣ ማንበብ ያስፈልገኝ ነበር። ከመጸሐፉ መጀመሪያ ጀመርኩ እናም በየቀኑ አነበብኩ። አንዳንዶች ምስክርነት በፍጥነት ያገኛሉ። ለሌሎች፣ የበለጠ ጊዜ እና የበለጠ ፀሎት ይወስዳል እናም ምናልባት መጸሐፉን ብዙ ጊዜ ማንበብን ሊያካትት ይችላል። ቃል የተገባውን ምስክር ከማግኘቴ በፊት ሙሉ መጽሐፉን ማንበብ አስፈልጎኝ ነበር። ሆኖም፣ ስለእውነትነቱ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ገለጠልኝ።

በሚስኦናዊ መዝገቤ ላይ፣ እውነቱን በማወቅ ስላለው ደስታ እንዲሁም ስለተቀበልኩት ግላዊ ቁርጠኝነትን እና የልባዊነት አገላለፅን ተነተንኩ። እንዲህ ጻፍኩ፥ “የተቻለኝን ሁሉ ለማድረግ፣ በቀሪ ሕይወቴ መቶ በመቶ ለመጣር፣ ምንም ነገር ብጠየቅ ለማድረግ ለሰማይ አባቴ እና ለራሴ ቃል ገባሁ፣ ነገር ግን ለአሁኑ ቀሪ ሚስኦኔ አለ እናም ታላቅ ሚስኦን አደርገዋለሁ፣ መጥፎ ስሜት እንዳይሰማኝ ለማድረግ፣ ነገር ግን ለእኔ ሳይሆን፣ ለጌታ። ጌታን እወደዋለሁ፣ እና ስራውን እወዳለሁ፣ እና ያ ስሜት መቼም እንዳይተወኝ እጸልያለሁ።”

ያ ስሜት እንዳይተው ቋሚ እንክብካቤ እና ቀጣይነት ያለው ንሰሀ የመግባት እና ትእዛዛትን የመጠበቅ ጥረት እንደሚያስፈልግ አወኩ። ፕሬዘደንት ሞንሰን እንዳሉት፣ “ምስክርነት በእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥነት እና በየቀኑ ጸሎት እና የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት በኩል ህያው ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊ ነው።”6

በአመታት ውስጥ እውነቱን ለመሻት እና ምስክርነትን ለማግኘት የግል ጥረታቸውን እንዴት እንደጀመሩ ሚስዮናውያንን እና በአለም ዙሪያ ያሉ ወጣቶችን ጠየኳቸው። ባልተለያየ ምላሽ፣ ግላዊ ምስክርነት የማግኘት ጥረታቸው የጀመረው መጽሐፈ ሞርሞንን ከመጀመሪያው ጀምሮ ለማንበብ እና እውነት መሆኑን እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ግላዊ ውሳኔ በማድረግ እንደሆነ ምላሽ ሰጡኝ። ይህን በማድረግ፣ “በሌሎች ጥርጠሬ ከመመራት” ይልቅ “እራሳቸው ለመተግበር”7 ወሰኑ።

እውነትን ለማወቅ፣ ወንጌልን መኖር8 እና በቃሉ ላይ “መለማመድ”9 ይኖርብናል። የጌታን መንፈስ ላለመከልከል እንጠነቀቃለን።10 ንሰሀ፣ ትእዛዛትን በመጠበቅ ቁርጠኝነት ታጅቦ፣ የእያንዳንዱ ግለሰብ እውነትን የመፈለግ ወሳኝ ክፍል ነው።11 በእርግጥም፣ እውነትን ለማወቅ ሀጢአቶቻችንን “ሁሉን ለመተው” ፍቃደኛ መሆን ያስፈልገናል።12

“በማጥናት እና እንዲሁም በእምነት እውቀትን እንድንሻ” እና “የጥበብን ቃላት ከድንቅ መጽሐፍቶች ውስጥ እንድንሻ” ታዝዘናል።13 የእውነት ፍለጋችን በ“ምርጥ መጽሐፍት” እና በምርጥ ምንጮች ላይ ማተኮር አለበት። በጣም ከምርጦች ውስጥ ቅዱስ መጽሐፍት እና የህያው ነብያት ቃላት አሉ።

ጠንካራ ምስክርነትን ለማግኘት እና ለማቆየት የሚያፈልገውን ሁሉ እንድናደርግ ፕሬዘዳንት ሞንሰን እያንዳንዳችንን ጠይቀዋል።14 ምስክርነታችሁ እንዲዘልቅ እና እንዲጠነክር የሚያስፈልገው ምንድን ነው? እያንዳንዳችን ጠንካራ ምስክርነትን ለማግኘት እና ለማቆየት አስፈላጊውን ነገር የማድረግ የግል ሀላፊነት አለብን።

መልሶችን ከጌታ ለመቀበል የተቻለንን ስናደርግ አብሮም በትእግስት ቃልኪዳናችንን መጠበቅ እውነትን የመማር የእግዚአብሔር መርህ ነው። በተለይም ነገሮች ሲከብዱ፣ “በደስታና በትእግስት ለጌታ ፍቃድ መሰጠት”15 ሊጠበቅብን ይችላል። በትግስት ቃልኪዳንን መጠበቅ ትህትናችንን ያሳድጋል፣ እውነትን የማወቅ ፍላጎታችንን ጥልቅ ይሆናል፣ እና መንፈስ ቅዱስ “እንባረክበት፣ እንበለፅግበት፣ እናም እንጠበቅበት ዘንድ በጥበብ እንዲመራን”16 ያደርጋል።

ባለቤቴ፣ ሜሪ፣ እና እኔ ከልባችን የምንወዳት በአንዳንድ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች በአብዛኛው ህይወቷ ትግል ያለባት እህት አለች። ወንጌልን ትወዳለች፣ እና ቤተክርሰቲያኑን ትወዳለች ነገር ግን አሁንም ጥያቄዎች አሏት። በቤተመቅደስ ታትማለች፣ በቤተክርስቲያን ንቁ ተሳታፊ ነች፣ ጥሪዎችዋን ታሟላለች፣ እና ድንቅ እናት እና ሚስት ናት። በአመታት ቆይታ ውስጥ፣ እውነት እንደሆኑ የምታውቀውን ነገሮች ለማድረግ እና ስህተት እንደሆኑ ከምታውቃቸው ነገሮች ለመቆጠብ ሞክራለች። ቃልኪዳኖቿን ጠብቃለች እናም ፍለጋዋን ቀጥላለች። አንዳንዴ በሌሎች እምነት ላይ በመመርኮዟ አመስጋኝ ነበረች።

በቅርቡ፣ ኤጲስ ቆጶሷ እርሷን እና ባለቤትዋን ለማግኘት ጠየቀ። የቤተመቅደስ ስርአት ለሚያስፈልጋቸው ወኪል እንዲሆኑ የቤተመቅደስ ስራን እንዲቀበሉ ጠየቃቸው። ይሄ ጥሪ አስደነቃቸው፣ ነገር ግን ተቀበሉት እናም በጌታ ቤት ውስጥ አገልግሎታቸውን ጀመሩ። ወጣት ልጃቸው በቅርቡ በቤተሰብ ታሪክ ስራ ላይ ተሳትፏል እና የቤተመቅደስ ስርአት ያለተጠናቀቀላቸውን ቤተሰብ ስሞች አግኝቶ ነበር። በጊዜው እንደ ወኪል ሆኑ፣ ለእዚህ ሰው እ ለቤተሰቡ የቤተመቅደስ ስርአትን አከናወኑ። በመሰዊያው ተንበርክከው እና የማተም ስርአቱ እየተከናወነ ሳለ፣ ለብዙ ጊዜ ስትፈልግ የቆየችው ይህች ድንቅ እና ታጋሽ ሴት የግል መንፈሳዊ ተሞክሮ አገኘች በዛም ቤተመቅደስ እና በውስጡ የሚከናወኑት ስርአቶች እውነት እና እሙን እንደሆኑ ማወቅ ቻለች። እናቷን ደውላ ስለተሞክሮዋ ነገረቻት እናም አሁንም ጥቂት ጥያቄዎች ቢኖራትም፣ ቤተመቅደስ እውነት እንደሆነ፣ የቤተመቅደስ ስርአቶች እውነት እንደሆኑ፣ እናም ቤተክርስቲያኑ እውነት እንደሆነ እንደምታውቅ ነገረቻት። እናቷ ስለ አፍቃሪው፣ ታጋሹ የሰማይ አባት እና በትእግስት መፈለጓን ስለምትቀጥለው ሴት ልጇ በአመስጋኝነት አነባች።

በትግስት ቃልኪዳንን መጠበቅ የሰማይ በረከቶችን ወደ ህይወታችን ያመጣል።17

“በመንፈስ ቅዱስ ሀይል የሁሉንም ነገሮች እውነታ ታውቃላችሁ”18 በሚለው የጌታ ቃል ትልቅ መፅናናትን አግኝቻለሁ። ሁሉም ነገር ባናውቅም፣ እውነትን ማወቅ እንችላለን። መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ ለማወቅ እንችላለን። በእርግጥም፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን በዚህ ቀን ከሰዓት በኋላ እንዳስተማሩት፣ “በልባችን ‘ጥልቅ ቦታ’ ውስጥ [አልማ 13፥27 ተመልከቱ]፣ መፅሐፈ ሞርሞን is ያለጥርጣሬ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ይሰማናል” እኛም “በጥልቅ ተሰምቶን ከለዚያ ለአንድ ቀን ለመኖርም አንፈልግም።”19

እግዚአብሔር አባታችን እንደሆነ፣እንደሚወደን፤ እናም ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዳኛችን እና ቤዛችን ሞሆኑን ማወቅ እንችላለን። የእርሱ ቤተክርስቲያን አባል መሆን አስደሳች እንደሆነ እና የየሳምንት ቅዱስ ቁርባን መካፈል እኛን እና ቤተሰባችንን በመጠበቅ እንደሚረዳን ማወቅ እንችላለን። በቤተመቅደስ ስርአቶች አማካኝነት፣ ቤተሰብ በእውነትም ለዘለአለም አብረው መሆን እንደሚችሉ ማወቅ እንችላለን። የኢየሱስ ክርስቶስ የሀጢአት ክፍያ እና የንስሀ እና የቅር መባል በረከቶች እውነት እና እሙን እንደሆኑ ማወቅ እንችላለን። ውዱ ነብያችን፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ የጌታ ነብይ እንደሆኑ እና አማካሪዎቻቸው እናም አስራ ሁለቱ ሀዋርያቶች፣ ነብያት፣ ትንቢተኞች እና ገላጮች እንደሆኑ ማወቅ እንችላለን።

እነዚህ ሁሉ እውነት እንደሆኑ እናም ምስክርነቴን የማካፈለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።