2010–2019 (እ.አ.አ)
ብርሃናችሁን አብሩ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ብርሃናችሁን አብሩ

ነቢያት እኛን፣ እህቶችን እየጠሩን ነው። ጻድቅ መሆን ትችላላችሁን? እምነታችሁን በግልጽ ትገልጻላችሁን? ብርሃናችሁን ታበራላችሁን?

ይህንን አታውቁ ይሆናል፣ ነገር ግን ፕሬዘደንት ሞንሰን እና እኔ መንታ ልጆች ነን። በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ በተወለድኩበት ዕለት፣ በተወለድኩበት ሰዓት፣ የ36 ዓመት ወጣት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን አዲሱ ሐዋርያ በመሆን ተሾሙ። ከእግዚአብሔር ነቢይ፣ ፕሬዘደንት ሞንሰን ጋር ያለኝን የግል ግንኙነቴን እወደዋለሁ።

ነቢያት ስለሴቶች እየተናገሩ ናቸው።1 በዚህ ስብሰባ ውስጥም ከተወሰኑት ቃላቶቻቸውን ትሰማላችሁ። ለጽሑፎቼ በፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል በተፃፈው አስገራሚ ትንቢት ወደ 40 ዓመት ገደማ  እመለሳለሁ። መስከረም 1979 (እ.አ.አ) ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ቤተክርስትያኗ የሴቶች አጠቃላይ ስብሰባ አድርገው ነበር። ፕሬዘደንት ኪምቦል ንግግራቸውን አዘጋጁ፣ ነገር ግን የስብሰባው ቀን ሲመጣ፣ ወደ ሆስፒታል ገቡ። በምትካቸውም ባለቤታቸውን ካሚላ አይሪንግ ኪምቦልን እሳቸውን በመተካት መልክታቸውን እንዲያነቡ ጠየቁ።2

ምስል
እህት ከሚሊያ ኪምባል በመስበኪያ ንግግር ሲያቀርቡ

እህት ኪምባልም የነብዪን ቃላት፣ አዳኝ ምጽአቱ ከመምጣቱ በፊት የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ሴቶች በዓለም መልካም ሴቶች ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ አነበበች። በንግግሩ ፍጻሜ ላይ እስካሁን ድረስ የምንነጋገርበት ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች የሚያነቃቃ ሃላፊነት ተሰጠ።

ፕሬዘዳንት ኪምቦል ካሉት ውስጥ ጥቂቱን ልጥቀስ፤

“በመጨረሻ ውድ እህቶቼ፣ ከዚህ በፊት ያልተነገረ ወይም ቢያንስ በዚህ መንገድ ያልተጠቀሰ አንድ ነገር ላርብላችሁ። በመጨረሻዎቹ ቀናት ወደ ቤተክርስቲያኗ የሚመጣው ዋነኛው እድገት አብዛኛዎቹ የዓለም መልካም ሴቶች … ወደ ቤተክርስቲያኗን በታላቅ ቁጥር ስለሚጎትቱ ነው። ይህም በተወሰነ ደረጃ የቤተክርስቲያኗ ሴቶች በህይወታቸው ውስጥ ጽድቅን እና ግልጽነትን የሚያንፀባርቅ እና የቤተክርስቲያኗ ሴቶች ከአለም ሴቶች እይታ ጋር በተለየ ሁኔታ እና በተለየ መልኩ—ደስ በሚያሰኝ መንገድ—ይታያሉ።

በዓለም ላይ ከሚገኙት እውነተኛ የሴት ጀግኖች መካከል ወደ ቤተክርስቲያን የሚገቡ ሴቶች ራስ ወዳድ ከመሆን ይልቅ ጻድቅ መሆንን የሚመርጡ ናቸው። እነዚህ እውነተኛ የሴት ጀግኖች ከመታየት ይልቅ ሃቀኛነትን የሚያራምድ እውነተኛ ትህትና አላቸው። …

“… የቤተክርስቲያኗ የሴት አርአያቶች የሚሆኑ በመጨረሻው ቀናት የቤተክርስቲያኗ በቁጥርም ሆነ በመንፈሳዊ እድገት ወሳኝ ኃይል ይሆናሉ።”3

ይህ እንዴት ያለ ትንቢታዊ ቃል ነው። ለማጠቃለል ያህል፥

  • በቀጣዮቹ ዓመታት ለቤተክርስቲያኗ የሚመጡትን ዋና እድገቶች የሚቀሰቅሱ የሴቶች ጥሩ ግንኙነት ይሆና።

  • የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሴቶች፣ የወጣት ሴቶች እና የህጻናት ክፍል ልጃገረዶች ከልብ፣ በታማኝነት፣ መልካም የሆኑ ከሌሎች እምነት ሴቶች የሚገነቡት ጓደኝነት በመጨረሻዎቹ ቀናት ቤተክርስቲያኗ እንዴት እያደገች እንደምትሄድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

  • ፕሬዘደንት ኪምባል እነዚህን ሴቶች ከሌላ እምነት የሆኑትን “የሴት ጀግኖች” ብለው ይጠሯቸዋል፣ እኚህም ሰዎች ከራስ ወዳድነት ይልቅ ጻድቃን ለመሆን ስለሚጨነቁ ንጹሕ አቋም በሰው ፌት ከመታየት የበለጠ ዋጋ እንዳለው ያሳዩናል።

በዓለም ዙሪያ ስራዬን በማከናውንበት ጊዜ ከብዙ ጥሩ ሴቶች ጋር ተገናኝቻለሁ። ጓደኝነታቸው ለእኔ ከፍተኛ ዋጋ አለው። ከጓደኞቻችሁና ከጎረቤቶቻችሁም መካከል ታውቀዋላችሁ። እነሱ አሁን የቤተክርስቲያኗ አባላት ሊሆኑም ወይም ላይሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን በጣም ወሳኝ በሆነ ጓደኝነት እንገናኛለን። የእኛን ክፍል እንዴት እንጫወታለን? ምን ማድረግ አለብን? ፕሬዘዳንት ኪምባል አምስት ነገሮችን ይገልጻሉ፤

የመጀመሪያው ፃድቅ መሆን ነው። ጻድቅ መሆን ፍጹማን መሆን ወይም ፈጽሞ ስህተት አንሰራም ማለት አይደለም። ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ውስጣዊ ግንኙነትን ማጎልበት፣ ከኃጢአቶቻችንም ሆነ ከስህተታችን በመመለስ እና ሌሎችን በነፃነት መርዳት ማለት ነው።

ንስሐ የገቡ ሴቶች የታሪኮችን ጎዳና ይለውጣሉ። ወጣት በነበረችበት ጊዜ የመኪና አደጋ ያጋጠማት፣ እና ከዚያም በህክምና መድሃኒቶች ሱሰኛ የነበረች አንድ ጓደኛ አለችኝ። በኋላ ላይ ወላጆቿ ተፋቱ። በአጭር የጓደኝነት ትስስር ውስጥ አረገዘች እና በሱሷም ቀጠለች። ግን አንድ ምሽት፣ የህይወቷን መመሰቃቀል እና መበጥበጥ ተመልክታ፣ “ይበቃል” ብላ አሰበች። እርሷን እንዲረዳ ወደ አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስ ጮኸች። ከእርሷ ከፍተኛ ችግር በላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠንካራ እንደሆነ እና በንስሀ መንገድ ላይ ስትጓዝ በእርሱ ጥንካሬ ላይ ለመመካት እንደምትችል ተማርኩኝ አለች።

ወደ ጌታ እና ወደ እርሱ መንገድ በመመለስ፣ የታሪኳን መንገድ እና የትንሽ ልጇን ታሪክ እና የአዲስ ባለቤቷን ታሪክ ቀየረች። ጻድግ ነች፤ ስህተት ለሰሩት እና ለመቀየር ለሚፈልጉት ሌሎች ልቧ የተከፈተ ነው። ልክ እንደ እኛ ሁሉ፣ እርሷ ፍጹም አይደለችም፣ ነገር ግን ንስሓ መግባትንና በመሞከር መቀጠል እንዳለባት ታውቃለች።

ሁለተኛው ግልጽ መሆን ነው። ግልጽ መሆን ማለት ስለ አንድ ነገር እና ለምን እንደሆነ ምን እንደሚሰማችሁ መግለጽ ማለት ነው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ፣ ክርስቲያንነትን ያቃለለ በፌስቡክ ድረ ገሴ ላይ የተለጠፈ ነገር ነበር። አነበብኩት እና ትንሽ ተበሳጭቼ ነበር፣ ነገር ግን ችላ ብዬ አለፍኩት። ነገር ግን፣ የእኛ የእምነት አባል ያልሆነች አንድ የማውቃት ሰው የራሷን ምላሽ ሰጠች። እንዲህም ጻፈች፥ “[ይህ] ኢየሱስ ከቆመበት አላማ በቀጥታ የተቃረነ ነው — እሱ…ለውጥ ፈላጊ ነበር … ምክንያቱም እርሱ ዓለምን እኩል አደረገ። … እርሱ አመንዛሪ(ዎችን) [አነጋገረ]፣ ከቀረጥ ሰብሳቢው ጋር አብሮ [በላ]… ብርቱ ያልሆኑ ሴቶች እና ልጆችን ጓደኛ አደረገ… [እንዲሁም] ስለ ጥሩው ሳምራዊ ታሪክ ሰጡልን። ይህም እውነተኛ ክርስቲያኖች በዓለም ላይ በጣም አፍቃሪ ሰዎች ለመሆን ጥረት ያደርጉ ዘንድ። ይህን ሳነብ፣ ለራሴ እንዲህ አሰብኩኝ፣ “ለምን ነው እንደዚህ የጻፍኩት?”

እያንዳንዳችን ለእምነታችን ምክንያቶችን በመግለፅ ረገድ የተሻለ መሆን አለብን። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምን ይሰማችኋል? ለምን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ትቆያላችሁ? መፅሐፈ ሞርሞን ቅዱስ መጻህፍት እንደሆነ ለምንድነው የምታምኑት? ሰላማችሁን የምታገኙት ከየት ነው? ነቢዩ በ 2017 (እ.አ.አ) መናገሩ ለምንድን ነው አስፈላጊ የሆነው? እርሱ በእርግጥ ነቢይ መሆኑን እንዴት ታውቃላችሁ? ከጓደኞቻችሁ ጋር፣ በዝግታ ውይይቶች፣ ከልጅ ልጆቻችሁ ጋር በምታደርጉት ውይይቶች ላይ፣ የምታውቁትን እና የሚሰማችሁን ስሜት በማህበራዊ ሚድያ ለመናገር ድምጻችሁን እና ኃይላችሁን ተጠቀሙ። ለምን እንደምታምኑ፣ ስሜቱ እንዴት እንደሆነ ንገራቸው፣ ጥርጣሬ አድሮባችሁ የሚያውቅ ከሆነ እንዴት እንደተወጣችሁት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንናንተ ምን ማለት እንደሆነ ንገሯቸው። ሐዋሪያው ጴጥሮስ እንዳለው፣ “አትፍሩ … ዳሩ ግን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት፤ በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ።”4

ሶስተኛው ግልጽ መሆን ነው። በዚህ ሃምሌ ወር በፍሎሪዳ ውስጥ በፓናማ ከተማ የባህር ዳርቻ ላይ የተከሰተውን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ።5 ሮቤርቶ ኡርስሪ ከሰዓት በኋላ ላይ ሁለቱ ወጣት ልጆቿን ከ 90 ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ውቅያኖስ ውስጥ ሲጮኹ አዩ። እነሱ ኃይለኛ በሆነ የባህር ውጀብ ተይዘው ወደ ባሕር ተወሰዱ። በአቅራቢያቸው የነበሩ ጥንዶች ልጆቹን ለማዳን ሞክረው ነበር፣ ነገር ግን እነርሱም በወጀቡ ተያዙ። የዩረስሬ ቤተሰብ አባላት በትግል የሚዋኙትን ለማዳን ወደ ውስጥ ዘለው ገቡ፣ እናም ወዲያውኑ ዘጠኝ ሰዎች በወጀቡ ተያዙ።

ገመዶች አልነበሩም። የሕይወት ጠባቂ አልነበረም። ፖሊሶች የማዳኛ ጀልባ ላኩ፣ ነገር ግን በውቅያኖስ ውስጥ ያሉ ሰዎቹ ለ20 ደቂቃዎች የሚሆን ሲታገሉ ቆይተው፣ እናም ተደክመውና በውኃው ውስጥ ሲደክሙና ሲንሸራተቱ ነበር። በባሕሩ ዳርቻ ላይ ከሚመለከቱት ሰዎች መካከል አንዷ ጄሲካ ሜ ሲሞን ነበረች ባለቤቷ የሰው ሰንሰለት ለመስራት አሰቡ። በባህር ዳር ያሉት ሰዎች እንዲረዷቸው ጮሁ፣ እናም ብዙ ሰዎችም እጆቻቸውን በማያያዝ ወደ ውቅያኖሱ ሄዱ። ጄሲካ እንደጻፈችው፣ “ከተለዩ ዘሮችና ጾታ የተውጣጡ ሰዎች እንግዳዎችን ለመርዳት ሲመጡ ማየት እጅግ በጣም አስገራሚ ነው!!”6 80 የሚሆኑ የሰው ሰንሰለት ተዘርግቶ ወደሚዋኙት ዘልቀው ተጓዙ። በዚያ አስደናቂ ጊዜ የሆነውን ይህን ምስል ተመልከቱ።

ምስል
የሚዋኙት ሰዎች የሰው ሰንሰለት ሲዘረጉ

በባሕሩ ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ የተለመደን መፍትሄዎችን ብቻ በማሰብ ሽባ ሆነው ቆሙ። ይሁን እንጂ አንድ ጥንዶች በሴኮንድ ውስጥ የተለየ አማራጭ መፍትሔን አስበው ነበር። ፈጠራ እና ፍጥረት መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። ቃልኪዳናችንን ስንጠብቅ፣ በባህላችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ ከሌሎች የተለየን ሊያደርግ ይችላል፣ ነገር ግን የተለያዩ መፍትሄዎችን፣ የተለያዩ አቀራረቦች፣ የተለያዩ አተገባበሮችን ለማሰብ እንድንነሳሳ ያደርገናል። ሁልጊዜ ከዓለም ጋር ለመመሳሰል አንችልም፣ ነገር ግን በአዎንታዊ መንገዶች የተለዩ መሆን ለሚቸገሩ ሰዎች የሕይወት መስመር ሊሆን ይችላል።

አራተኛው ልዩ መሆን ነው። ልዩ መሆን ማለት በደንብ ተለይቶ በሚታወቅ መልኩ መገለጽ ማለት ነው በባህር ዳርቻው ላይ ስለ ጄሲካ ሚ ሲሞንስ ታሪክ ልመለስ። የሰዎች ሰንሰለቱ ወደሚዋኙት እያደገ ሲሄድ መርዳት እንደምትችል አውቃለች። ጄሲካ ሜ እንዲህ አለች፣ “ትንፋሼን በመያዝ በቀላሉ የኦሎምፒክ የዋና ገንዳን እዞራለሁ! [ከውሃ ጅረት እንዴት መውጣት እንዳለብኝ አውቅ ነበር።] [እያንዳንዱን ዋናተኛ] ወደ ሰው ሰንሰለት ለማምጣት እንደምችል አውቄ ነበር”7 እሷና ባለቤቷ መንሳፈፊያውን ይዘው ዋናተኞቹ ጋር እስ ኪደርሱ በሰንሰለቱ ላይ በመዋኘት እናም አንድ በአንድ ተሸክመው ወደ የባህር ዳርቻ አመጧቸው። ጄሲካ ልዩ ችሎታ ነበረባት፤ ከውሃ ጅረት እንዴት አምልጣ መዋኘት እንዳለባት ታውቅ ነበር።

ዳግመኛ የተመለሰው ወንጌል በሚለይ መልኩ ተገልጿል። ነገር ግን እንዴት እንደምንከተል ልዩ ልንሆን ይገባል። ልክ ጄሲካ መዋኘትን እንደምትለማመድ፣ ከአደጋው በፊት ወንጌልን መኖራችንን እንለማመድ፣ ፍርሃት ሳይሰማን፣ ሌሎች በጅረቱ ሲነጠቁ እኛ ለመርዳት ጠንካራ እንሆናለን።

እናም በመጨረሻም፣ አምስተኛው በደስተኝነት ከአንድ እስከ አራት ያሉትን ማድረግ ነው። ደስተኛ መሆን ማንኛውም ነገር ሲከሰት የውሸት ፈገግታን በፊታችን ላይ መጥለፍ አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ህጎች ማክበር፣ ሌሎችን መገንባትና ከፍ ከፍ ማድረግ ማለት ነው።8 ሌሎችን ስንገነባ፣ የሌሎችን ሸክም ስናስወግድ ፈተናዎቻችን ሊወሰዱት በማይችሉበት መንገድ ህይወታችንን ይባርከናል። በፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ የተሰጠን ጥቅስ በየቀኑ ላይ በምችልበት ቦታ ላይ ተቀምጧል። እንዲህ አሉ፥ “በአሉታዊ በአፍራሽ አመለካከት … መገንባት አንችልም።” በብሩህ ተስፋዎች ከተመለከታችሁ፣ በእምነት ከሰራችሁ ነገሮች እንዲሁ ይከናወናሉ።9

ደስተኛና ብሩህ አመለካከት ስለመያዝ እንደ ምሳሌ የገለጽኳት ኤሊ የተባለች የ 13 ዓመት ልጅ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ቢተን ሮግ 2,900 ኪሎ ሜትር ርቃ ወደምትገኘው ወደ ሊዊዝያና ጓደኞቿን ርቃ መሄዷ ነው። ለ13 አመት ልጅ ወደ አዲስ ቦታ መዘዋወር ቀላል አይደለም። ኤልሳ መረዳት በሚቻል ምልኩ ቦታ ስለመቀየሩ እርግጠኛ አልነበረችም፣ ስለዚህ አባቷ በረከት ሰጣት። በበረከቱ መጀመሪያ ላይ፣ የእናቷ ስልክ በመልክት መጮህ ጀመሩ። በሉውዚያና የምትኖሩት ወጣት ሴቶች “ወደ ዎርዳችን ግቢ!”10 የሚል ርዕስ ያለው ፎቶ ላኩልኝ።

ምስል
ወጣት ሴቶች እንኳን ደህና መጣሽ የሚል ምልክት ይዘው

እነዚህ ወጣት ሴቶች ከእርሷ ጋር ሳይገናኙም ኤልሳን እንደሚወዱ ተስፋ ነበራቸው። የእነሱ ቅንነት ለኤልሳ በመጪው የቦታ ለውጥ ላይ አዎንታዊ አመለካከት ፈጥሮና ሁሉም ነገሮች መልካም እንደሚሆን ፀሎትዋን መለሰላታል።

ከደስተኛነት እና ብሩህ ተስፋ የሚመጣ ጉልበት እኛን ብቻ ሳይሆን በአካባቢያችን ያሉትን ሁሉ ይገነባል። በሌሎች እውነተኛን የደስታን ብርሃን ለማምጣት የምታደርጉት ትንሽ ነገር ፕሬዝዳንት ኪምቦል ያበሩትን ችቦ መያዛችሁን ያሳያል።

የፕሬዚዳንት ኪምለል ንግግር በተሰጠበት ወቅት የ15 ዓመት ልጅ ነበርኩ። ከ40 ዓመት በላይ የሆንነው ሰዎች ይህንን የፕሬዚዳንት ኪምቦልን ሃላፊነትን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተሸክመናል። አሁን የ 8 ዓመት ልጆችን፣ የ 15 ዓመት ልጆችን እና 20 አመት እና 35 አመት እድሜ ያላቸው ሰዎችን እመለከታለሁ፣ እናም ይህን ችቦ ለእናንተ አሳልፌ እሰጣለሁ። በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ የወደፊቱ መሪዎች ናችሁ፣ እናም ይህን ብርሃን ወደ ፊት ለማጓዝ እና የዚህን ትንቢት ፍፃሜ ለመፈጸም የእናንተ ሃላፊነት ነው። ከ 40 ዓመት በላይ የሆነው እጆቻችን ከእጃቸሁ ጋር በማጠላለፍ ከእናንተ ጥንካሬ እና ሀይልዎን እናገኛለን። ታስፈልጉናላችሁ።

ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 49:26–28 ውስጥ የተገኘውን ይህን ጥቅስ አዳምጡ። ምናልባትም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የተፃፈ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በዚህ ምሽት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት፣ ይህንን ቅዱስ ሥራ የግል ጥሪያችሁ እንደምታደርጉት ተስፋ አደርጋለሁ።

“እነሆ እላችኋለሁ፣ እኔ እንዳዘዝኳቸሁ አድርጉ፣ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ ንስሓ ግቡ፤ ለምኑ ይሰጣችሁማል፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል።

እነሆ እኔ እከተላችኋለሁ ከፊታችሁም እሆናለሁ፣ እኔም በእናንተ መካከል እሆናለሁ፣ እናንተም አትደናበሩም።

“እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ፈጥኜም እመለሰላሁ።”11

የእግዚአብሔርን ለጋስ ፍቅር ሊሰማችሁ በምትችሉበት ቦታ ራሳችሁን እንድታስገኙ እለምናችኋለሁ። ራሳችሁንከዚያ ፍቅር አስርቃችሁ ለማስገኘት አትችሉም። የእርሱ ፍቅር ሲሰማችሁ፣ እርሱን ስታፈቅሩ፣ ንስሀ ትገባላችሁ እናም ትእዛዛቱን ታከብራላችሁ። ትእዛዛቱን ስትጠብቁ፣ በስራው ሊጠቀምባችሁ ይችላል። የእርሱ ስራ እና ክብር ሴቶች እና ወንዶችን ሁሉ ወደ ዘለአለማዊ ህይወት ማምጣት ነው።

ነቢያት እኛን፣ እህቶችን እየጠሩን ነው። ጻድቅ መሆን ትችላላችሁን? እምነታችሁን በግልጽ ትገልጻላችሁን? የተለያችሁ እና ጉልህ መሆን ትችላላችሁን? ፈተናዎች ቢኖርባችሁም እንኳ ደስታችሁ መልካም እና ክቡር የሆኑ እና የእናንተን ጓደኝነት ለሚሹ ሰዎች የሚስብ ይሆናልን? ብርሃናችሁን ታበራላችሁን? ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ በፊት እንደሚሄድ እና በመካከላችን እንደሚሆን እመሰክራለሁ።

በተወደዱት በነቢዩ ቶማስ ኤስ ሞንሰን በተናገሩት ቃላት እደመድማለሁ ። “ውድ እህቶቼ፣ ይሄ የእናንተ ቀን ነው፣ ይህ የእናንተ ጊዜ ነው“12 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ፕሬዘደንት ብሬገም ያንግ፤ “[እህቶች] የሴቶች መረዳጃ ማህበር በተለያዩ አጥቢያዎች እንዲያደራጁ ይፍቀዱ። በመካከላችን ከፍተኛ ተሰጥዖ ያላቸው ሴቶች አሉን፣ እና በዚህ ጉዳይ ላይ እርዳታዎቻቸውን እንፈልጋለን። አንዳንዶች ይሄ በጣም ትንሽ ነገር ነው ብለው ያስቡ ይሆናል፣ ግን አይደለም፤ እናም እነዚህ እህቶች የንቅናቄው ዋና አካል እንደሆኑ ትገነዘባላችሁ” (in Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society [2011], 41)።

    ፕሬዝዳንት ሎሬንዞ ስኖው፤ “ከቅዱስ ክህነት ጎን ተገኝታችኋል፣ ዝግጁ ሆናችሁ… የእግዚአብሔርን መንግሥት ፍላጎቶች ለማራመድ የበኩላችሁን ለማድረግ፣ እናም በእነዚህ ስራዎች ስትካፈሉ፣ በእውነቱ ሥራው ድልን እና ጌታ ለታመኑ ልጆቹ በሚሰጣቸው ክብር እና ክብር ውስጥ ትካፈላላችሁ” (in Daughters in My Kingdom, 7)።

    ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምቦል፤ በዚህ “[በሴቶች መረዳጃ ማህበር] የጺዮንን ቤቶች ለማጠንከር እና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት የሚያስችል በሙሉነት ያልሞከርነው ሃይል አለ እናም እህቶች እና የክህነት [ወንድሞች] የሴቶች መረዳጃ ማህበር የእድገት ራዕይን እስኪረዱ ድረስ አይሟላም” (in Daughters in My Kingdom, 142)።

    ፕሬዘደንት ሃዋርድ ደብሊው ሃንተር፤ “እርስ በርስ እና ከወንድሞች ጋር በመቆም በኛ ዙሪያ ያሉ የክፋት ማዕበልን በመቋቋም እና የአዳኛችንን ስራ ለማራዘም ለቤተክርስቲያኗ ሴቶች መደገፍ በጣም ያስፈልጋል። … ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን፣ ቤተክርስቲያናችንን እና ማኅበረሰቦቻችንን ለማጠናከር የእኛን ሃይለኛ ተፅእኖ በመሆን እንድታገለግሉ እንጠይቃለን” (in Daughters in My Kingdom, 157)።

    ፕሬዘደንት ጎርደን  ቢ ሂንክሊ፤ “በዚህች ቤተክርስቲያን ሴቶች ጥንካሬና ታላቅ አቅም አለ። የአመራር እና ምሪት፣ የነጻነት መንፈስ እና የዚህም የጌታ መንግስት አካል በመሆን እና ከካህናት ጋር እጅ ለእጅ ተካፋይ በመሆን የበኩላችሁን ተግባር በማድረግ የሚመጣ ሀሴት አለ” (in Daughters in My Kingdom, 143)።

    ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን፤ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ቤሌ ስሚዝ ስፓፎርድን በመጥቀስ እንደጻፉት፤ “ከዛሬ ዓለም ጊዜ ሴቶች የበለጠ ተጽዕኖ ያሳደረ የለም። የእድል በሮች ከዚህ በላይ በሰፊው ተከፍቶላቸው አያውቅም። ይህ ለሴቶች የሚጋብዝ፣ አስደሳች፣ ፈታኝ እና ወሳኝ ጊዜ ነው። ሚዛንን ከጠብቀን በሽልማት የተሞላ፣ እውነተኛ የህይወት እሴቶችን የምንማርበት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በመምረጥ ጥበብ የተሞላበት ጊዜ ነው። [A Woman’s Reach (1974), 21]. ውድ እህቶቼ፣ ይሄ የእናንተ ቀን ነው፣ ይህ የእናንተ ጊዜ ነው”(“The Mighty Strength of the Relief Society፣” Ensign፣ Nov. 1997, 95)።

    ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን “የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እህቶቼን ወደፊት እንድሄድ እማጸናችኋለሁ! በቤታችሁ፣ በኅብረተሰባችሁ እና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፣ ከመቼውም በላይ ትክክለኛና አስፈላጊ የሆነውን ቦታዎን ይውሰዱ። የፕሬዚዳንት ኪምለልን ትንቢት እንድትፈጽሙ እማጸናለሁ። እናም ይህን ስታደርጉ፣ መንፈስ ቅዱስ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማታውቁት መንገድ የእናንተን ተፅዕኖ ከፍ እንደሚያደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ቃል እገባላችኋለሁ” (“A Plea to My Sisters,” Liahona, Nov. 2015, 97)።

  2. እህት ካሚላ ኪምባል የፕሬዘደንት ስፔንሰርን  ደብሊው ኪምባልን መልእክት በሚያነቡት ጊዜ ያለውን ቪዲዮ conference.lds.org ይመልከቱ፤ ደግሞም ስፔንሰርን ደብሊው. ኪምባል፣ “The Role of Righteous Women,” Ensign, ህዳር 1979 (እ.አ.አ)፣ 102–4 ይመልከቱ።

  3. ስፔንሰርን ደብሊው ኪምባልን፣ “The Role of Righteous Women,” 103–4; emphasis added.

  4. 1 ጴጥሮስ 3፥14–15

  5. ማኪንሊ ኮርብለይ “80 Beachgoers form Human Chain to Save Family Being Dragged Out to Sea by Riptide፣” July 12, 2017 (እ.አ.አ) ተመልከቱ።

  6. ጀሲካ ሜ ስመንስ፣ in Corbley፣ “80 Beachgoers Form Human Chain።”

  7. ጀሲካ ሜ ስመንስ፣ in Corbley፣ “80 Beachgoers Form Human Chain።”

  8. አልማ 41፥1034፥28ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 38፥27ሉቃስ 16፥19–25 ተመልከት።

  9. Teachings of Presidents of the Church: Gordon B. Hinckley (2016), 71.

  10. ከቨርጂኒያ ፒርስ ቤተሰብ የተሰጠ ማስታወሻ።

  11. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 49፥26–28

  12. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “The Mighty Strength of the Relief Society፣” 95።