2010–2019 (እ.አ.አ)
ከመጠን ያለፈ ዋጋ
ጥቅምት 2017 (እ.አ.አ)


ከመጠን ያለፈ ዋጋ

ሁልጊዜም የመንፈስ ብቁነታችንን እውነት በማረጋገጥ፣ የመንፈስ ቅዱስን አስደሳች ማሾክሾክ ለማግኘት እንችላለን።

በምዕራብ አፍሪካ የሴራ ሊዮንን አገር እየጎበኘሁ ሳለ፣ በቃስማ የህጻናት መሪ ሲመራ በነበረው ስብሰባ ላይ ተሳተፍኩ። ማሪያማ በግሩም ፍቅር፣ ፀጋ፣ እና መተማመን በመምራቷ፣ ለረጅም ጊዜ የቤተክርስቲያን አባል እንደሆነች ለመገመት ቀላል ነበር። ይሁን እንጂ ማሬያማ በቅርብ ጌዜ ወደ ቤተክርስቲያን የተቀላቀለች ነች።

ምስል
ማርያምና ሴት ልጇ

ታናሽ እህቷ ቤተክርስቲያኗን ተቀላቀለች እና ማሪያማ ከእሷ ጋር የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ክፍል እንድትካፈል ጋበዘቻት። ማሪያማ በመልእክቱ እጅግ ተደነቀች። ትምህርቱም በንጽህና ሕግ ላይ ነበር። ሚስዮናውያን ተጨማሪ ያስተማሯት ዘንድ ጠየቀች እናም ብዙም ሳይቆይ የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ምስክርነትን አገኘች። በ 2014 እ.ኤ.አ ተጠመቀች እና ሴት ልጇም ባለፈው ወር ተጠመቀች። አስቡት፣ ለማሪያማ መለወጥ መንገድ የሆኑ ሁለት መሠረታዊ ትምህርቶች የንጽህና ህግ እና ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ናቸው፣ ሁለቱም ነጥቦች ዓለም ብዙውን ጊዜ የማይጠቅም፣ ጊዜ ያለፈበት፣ ወይም ተጨባጭ እንዳልሆነ ያስባሉ። ነገር ግን ማሪያማ እራሷን ወደ ብርሃን እንደተሳበች የእሳት እራት እንደነበረች መሰከረች “ወንጌልን ባገኘሁ ጊዜ እራሴን አገኘሁ” አለች። መለኮታዊ በሆኑት መርሆዎች የማንነቷን ዋጋ አወቀች። እንደ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ዋጋዋ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ተገልጦላት ነበር።

አሁን ደግሞ ከህንድ የሲኝ እህታማሞች የሆኑትን እንገናኝ። ራኑ፣ በቀኝ ጥግ ላይ የምትገኘው፣ ቤተክርስቲያን ከተቀላቀሉ ከአምስት እህቶች መካከል አንዷ የሆነችው፣ እነዚህን ሀሳቦች አጋርታለች፤

ምስል
የሲንግ እህቶች

ስለ ቤተክርስቲያኗ መማር ከመጀመሬ በፊት፣ ልዩ እንደሆንኩ አላሰብኩም ነበር። ማኅበረሰቤ እና ባህሌ እኔ እንደ ግለሰብ ዋጋ ያለኝ መሆኔን አላስተማሩኝም፣ በዚህም ውስጥ ካሉ ከብዙ ሰዎች መካከል አንዷ ነበርኩኝ። ወንጌልን ስማር እና የሰማይ አባታችን ሴት ልጅ መሆኔን ሳውቅ፣ ይህም ለወጠኝ። በድንገት ልዩ ስሜት ተሰማኝ፣ በእርግጥም እግዚአብሔር ፈጠረኝ እናም ነፍሴን እና ሕይወቴን በዋጋ እና በአላማ ፈጠራት።

ወንጌልን በህይወቴ ውስጥ ከማግኘቴ በፊት፣ ሁልጊዜ ለየት ያልኩ ሰው እንደሆንኩ ለሌሎች ለማስረዳት እሞክር ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሴት ልጅ መሆኔን እውነቱን ከተማርኩ በኋላ፣ ለማንም ሰው እራሴን ማስረዳት አላስፈለገኝም። ልዩ መሆኔ ታወቀኝ። “… በፍሱም ማንም አይደለሁም ብላችሁ አታስቡ።”

ፕሬዘደንት ቶማስ  ኤስ ሞንሰን እነዚህን ቃላት በመጥቀስ በፍጹም ሁኔታ ገልጸውታል፤ “የነፍስ ዋጋ ሰው እንደ አምላክ የመሆን ችሎታው ነው።”1

ምስል
ታያና

በቅርብ ቀን ይህን ተመሳሳይ እውነት የተረዳች ሌላ ወጣት ሴት በማግኘት ተባርኬ ነበር። የእሷ ስም ታይአና ትባላለች። በሶልት ሌክ ሲቲ በህፃናት ሆስፒታል ውስጥ ተገናኘኋት። ታይአና በሃይስኩል ትምህርት ቤት የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳለች የነቀርሳ በሽተኛ መሆኗ ታወቀ። ከጥቂት ሳምንታት ከመሞቷ በፊት ለ18 ወራት ያህል በጀብዶነት ተጋፈጠች። ታይአና በብርሃን እና በፍቅር የተሞላች ነበረች። ተላላፊ በሆነው ፈገግታዋ እና የሷ መለያ በሆነው ሁለቱን አውራ ጣቷን ከፍ በማድረግ ትታወቃለች። ሌሎች “ለምን ታይአና አንቺን?” ብለው ሲጠይቁ, መልሷም “ለምንድነው እኔ የማይገባኝ?” ነበር። ታይአና በጣም ለምትወደው እንደ አዳኝ ለመሆን ፈልጋለች። በጉብኝታችን ጊዜ ታይአና መለኮታዊ ዋጋዋን እንደተረዳች ተማርኩ። የእግዚአብሔር ሴት ልጅ መሆኗን በማወቋ ከመጠን በላይ የሆነውን ፈተናዋን በቀናነት እንድትጋፈጥ ሰላምና ደፍረትን ሰጥቷታል።

የማሪያማ፣ ሬኑ እና ታይአና የሚያስተምሩን መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዳችን መለኮታዊ ዋጋችንን እንደሚያረጋግጥ ነው። በእውነት የእግዚአብሔር ሴት ልጅ መሆናችሁን ማወቁ በእያንዳንዱ የሕይወታችሁ ገጽታ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል እና በየቀኑ በምታቀርቡት አገልግሎት ውስጥ ይመራችኋል። ፕሬዘደንት ደብሊው. ኪምባል በነዚህ ድንቅ ቃላት ገልጸውታል፤

“እግዚአብሔር አባታችሁ ነው። ይወዳችኋል። እሱ እና የሰማይ እናታችሁ ከምንም በላይ ለናንተ ዋጋን ይሰጣሉ። …እናንተ ልዩ ናችሁ። ልዩ፣ የዘላለም ህይወት ባለቤትነት የሚሰጣችሁ ከዘላለማዊ ልቦና የተሰራችሁ ናችሁ።

“እንደ አንድ ግለሰብ ስላላችሁ ዋጋ ምንም ጥርጣሬ በአእምሮአችሁ አይኑር። የወንጌል ዋናው አላማ ለእያንዳንዳችሁ በሙሉ አቅማችሁ ወደ ዘለአለማዊ እድገትና ወደ አምላክነት እንድትደርሱ እድል ለመስጠት ነው።”2

በሁለት ጠቃሚ ቃላቶች መካከል ያለውን ልዩነት መመልክት አስፈላጊነት እጠቁማለሁ፤ የማንነት ዋጋ እና ብቁነት። አንድ አይደሉም። የመንፈሳዊ የማንነት ዋጋ ማለት አለም እንደሚሰጠን ዋጋ ሳይሆን የሰማይ አባት እንደሚሰጠን ዋጋ እራሳችንን መተመን ማለት ነው። እዚህ ምድር ላይ ከመድረሳችን በፊት የእኛ የማንነት ዋጋ ተወስኗል። “የእግዚአብሔር ፍቅር ገደብ የለውም፣ ለዘላለምም ይጸናል።”3

በሌላ መንገድ፣ ብቁነት በመታዘዝ የሚገኝ ነው። ኃጢአት ከሠራን፣ ብቁነታችንያነሰ ቢሆንም ነገር ግን የማንነታችን ዋጋ በፍጹም አነስተኛ አይደለም! ንስሀ መግባታችንን እንቀጥላለን እናም በማንነታችን ልክ እንደ ኢየሱስ ለመሆን እንጥራለን። ፕሬዘደንት ብሬገም ያንግ እንዳስተማሩት፤ “በምድር ላይ ካሉት በጣም ዝቅተኛ መንፈስ …፣ የዓለሞችን ዋጋ ያለው ነው።”4 ምንም ይሁን ምንም፣ ሁልጊዜም በሰማያዊ አባታችን ፊት ዋጋ አለን።

ምንም እንኳን ይህ ድንቅ እውነት ቢኖርም፣ ብዙዎቻችን ስለእራሳችን አፍራሽ ሀሳቦች ወይም ስሜቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያታገልን እንገኛለንን? እኔ ይህ ያጋጥመኛል። ቀላል ወጥመድ ነው። ሰይጣን የሁሉም ውሸቶች አባት ነው፣ በተለይ የእኛን መለኮታዊ ተፈጥሮና ዓላማን በተመለከተ በተሳሳተ መንገድ በሚገለጥበት ጊዜ። ስለ ራሳችን አሳንሰን ማሰብ አይጠቅመንም። ይልቁንም ወደኋላ ይይዘናል። በተደጋጋሚ እንደተማርነው፣ “ያለእናንተ ስምምነት ማንም የዝቅተኝነት ስሜት እንዲሰማቸሁ ሊያደርግ አይችልም።5 የእኛን የከፋውን ማንነት ከሌላኛው ሰው ጥንካሬ ጋር ማወዳደር ማቆም እንችላለን። “ማወዳደር የደስታ ሰራቂ ነው።”6

በተቃራኒው፣ ንጹህ ሃሳቦች ሲኖሩን ጌታ እኛ በእርግጠኝነት በልበ ሙሉነት፣ እራሳችንን እስከማወቅ ድረስ ልበ ሙሉነት እንደሚባርከን ያረጋግጥልናል። ቃላቱን ለማክበር የተሻለ ወሳኝ ጊዜ የለም። “ንጽህና አሳባችሁን እንዲሸፍን አድርጉ” አለ። “ልበሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት ጠንካራ ይሆናል፣ እናም … መንፈስ ቅዱስ ቋሚ ጓደኛህ ይሆናል።”7

ጌታ ይህን ተጨማሪ እውነት ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ገልጦለታል፣ “ከእግዚአብሔር ለተቀበለው፣ ከእግዚአብሄር መሆኑን ያመልክት፣ እናም ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቁ ሆኖ በመቀበሉም ደስታ ይሰማው።”8 መንፈሱ ሲሰማን፣ ይህ ጥቅስ እንደሚያብራራው፣ የሚሰማን ነገር ከሰማይ አባታችን የሚመጣ እንደሆነ እናውቃለን። እኛን ስለባረከን እንገነዘባለን እናም እናመሰግነዋለን። ለመቀበል ብቁዎች በመሆናችን ደስተኞች እንሆናለን።

በአንድ ማለዳ ጠዋት መጽሐፍ ቅዱስን እያነበብን እንዳለህ አድርገን እናስብ እናም የምታነቡትም ሁሉ እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ በሹክሹክታ ይናገራል። መንፈስን ማስተዋል ትችላላችሁን እናም የእርሱን ፍቅር የተሰማችሁ እና ለመቀበል የተገባችሁ በመሆናቸው ደስተኞች ትሆናላችሁን?

እናቶች፣ ከአራት ዓመቱ ልጃችሁ አጠገብ ጋር የመኝታ ጸሎቱን በሚያደርግበት ጊዜ ትንበረከኩ ይሆናል። ስታዳምጡም ልዩ ስሜት ይወራችኋል። ሙቅ እና ሰላም ይሰማችኋል። ስሜቱ አጭር ነው፣ ነገር ግን በዚያ ቅጽበት እናንተ ለመቀበል ብቁ እንደሆናችሁ ትገነዘባላችሁ። በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ መገለጥ ሁሌ አያጋጥመንም፤ ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ጣፋጭ ሹክሹክታ ማጣጣም እንችላለን እናም የመንፈሳዊ ማንነታችንን እውንነት እናረጋግጣለን።

ጌታ በእኛ ዋጋ እና በታላቅ የእሱ የኀጢአት መስዋዕት መካከል ያለውን ግንኙነት አብራርቷል፤

“የነፍሶች ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ መሆኑን አስታውሱ፣

“እነሆ፣ መድኃኒታችሁ ጌታ በሥጋ ሞትን ተሰቃየ፣ ስለሆነም የሁሉንም ህመም ተሸከመ፣ ሁሉም ሰው ንስሃ እንዲገባ እና ወደ እርሱ ዘንድ መምጣት ይችል ዘንድ።”9

እህቶች፣ እሱ ባደረገልን ነገር ምክንያት፣ “ከእርሱ ጋር ወዳጃዊ ትስስር አለን።”10 እንዲህም አለ፣ “አባቴም በመስቀል እሰቀል ዘንድ ልኮኛል እናም ከዛም በኋላ በመስቀል ላይ ከተሰቀልኩ በኋላ እንዲሁ ሰዎችን ሁሉ ወደ ራሴ አመጣ ዘንድ።”11

ንጉሥ ቢንያምም ከአዳኝ ጋር ያለውን ጥብቅ ግንኙነት አብራርቷል፤ “እናም እነሆ፣ በፈተናና በስጋዊ ህመም፣ በርሃብ፣ በጥማትና፣ በድካም፤ ከሞት በስተቀር ሰው ሊሰቃይበት ከሚችለው የበለጠም ይሰቃያል፤ እነሆም ለህዝቡ ክፋትና እርኩሰት ጭንቀቱ እጅግ ታላቅ ሆኖ፣ ደሙም ከእያንዳንዱ የሰውነቱ ቀዳዳ ይፈሳል።”12 ያም ስቃይ እና የዚያ ስቃይ ውጤቶች ልባችንን በፍቅር እና ምስጋና ይሞላሉ። ሽማግሌ ፖል ኢ. ኮሊከር እንዳስተማሩት፣ ወደ አለም የሚጎትቱንን እንቅፋቶች ስናስወግድ እናም እሱን ለመሻት ነጻ ምርጫችንን ስንጠቀም፣ ወደ እርሱ የሚጎትተንን ለሰማዩ ሃይል ልባችንን እንከፍታለን።”13 ለአዳኝ ያለን ፍቅር እና ለእኛ ስላደረገልን ነገር ለድክመቶች፣ እራስን መጠራጠር፣ ወይም ለመጥፎ ልማዶች ከምንሰጠው ጉልበት የላቀ ከሆነ በህይወታችን ስቃይ የሚያመጡትን ነገሮች ያስወግድልናል። እርሱ ከእራሳችን ያድነናል።

ደግሜ ስገልጽ፣ የአለም መጎተቻው በአዳኝ ላይ ከሚኖረን እምነት የበለጠ ጠንካሬ ከሆነ፣ ሁልጌዜ የአለም መጎተት ይጸናል። በአሉታዊ አመለካከቶቻችን ላይ ካተኮርን እና ዋጋችንን ከተጠራጠርን፣ አዳኝ ላይ ከመጣበቅ ይልቅ፣ የመንፈስ ቅዱስ ስሜትን ለመቀበል የበለጠ አስቸጋሪ ይሆናል።

እህቶች፣ ስለ ማንነታችን ግራ አይግባን! መለኮታዊ ማንነታችንን ለማስታወስ እና ለመቀበል መንፈሳዊ ጥረት ከማድረግ ይልቅ በመንፈስ ቸልተኛ መሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ቢሆንም፣ በተለይ በዚህ የኋለኛው ቀናት ውስጥ ይህን ተግባር ችላ ማለት አንችልም። እህቶች፣ “በክርስቶስ [የታመናችሁ ሁኑ፤ … ክርስቶስ ከፍ [ያድርገን]፣ እናም ስቃዩ፣ እናም ሞቱ፣ … እናም ምህረቱ እናም ፅናቱ፣ እናም ለክብሩ እናም ለዘለዓለማዊ ህይወት ያለው ተስፋ ለዘለዓለም [በአዕምሮአችን] ይኑር።”14 አዳኝ ወደ ከፍተኛ ቦታ ከፍ እንደሚያደርገን፣ ማን መሆናችንን ብቻ ሳይሆን ወደ እርሱ ከምናምነው በላይ እንድምንቀርብ በግልጽ ለማየት እንችላለን። በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።