2010–2019 (እ.አ.አ)
እስከ መጨረሻ የጸናው፣ እርሱም ይድናል።
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


እስከ መጨረሻ የጸናው፣ እርሱም ይድናል።

ለምናምነው እና ለምናውቀው ታማኝ እንሁን።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ አንዳንድ ስሜቶቼን እንድገልፅ ለተሰጠኝ እድል በጣም አመሰግናለው።

ከጥቂት አመታት በፊት፣ እኔና ባለቤቴ በሶልት ሌክ ሲቲ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ታሪክ ቤተ-መዘክር አሳታፊ በልጆች ትርዒት የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተን ነበር። በስነ ስርዓት መጨረሻ ላይ፣ ፕሬዝደንት ቶማስ ስ. ሞንሰን ወደ እኛ በመራመድ፣ እጆቻችንን እየጨበጡ፣ “ፅኑ፣ ድል ተደርጋላችሁ” አሉን—ሁላችንም የምንናረጋግጠው በርግጥም እውነታ የለውና ጥልቅ ትምህርት።

ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳረጋገጠልን “እስከ መጨረሻ የሚፀና ግን እርሱ ይድናል።”1

መፅናት ማለት “ምንም እንኳን ፈተና፣ተቃውሞ ወይም መከራ ብኖርም፣ ለእግዚአብሔር ትዕዛዘት በመሰጠት ፀንቶ መቆየት ነው።”2

ኃይለኛ መንፈሳው ተሞክሮዎች የነበራቻው እና ታማኝ አገልግሎት የሰጡ እንኳ እስከ መጨረሻ ከልፀኑ አንድ ቀን ልተፉና ወደ ተሳትፎ አልባነት ልቀየሩ ይችላሉ። “ይህ በእኔ ላይ አይደርስም” የምለውን ዓረፍተ ነገር ሁልጊዜ አጥብቀን በአእምሮችንና በልባችን እንጠብቀው። “ይህ በእኔ ላይ አይደርስም” የሚለውን ዓረፍተ ነገር ሁልጊዜ አጥብቀን በአእምሮችንና በልባችን እንጠብቀው።

ኢየሱስ በቅፍርናሆም ሳስተምር ሳለ “ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፣ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም።

“ኢየሱስም ለአስራ ሁለቱ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን? አለ”3

ከእርሱ ጋር ቅዱስ ቃል ኪዳን ለገባናው ሁላችንንም ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትወዳላችሁን?” ብሎ ዛሬ እንደምጠይቀን አምናለው።

የዘላለም ሕይወት ለእኛ ያያዘውን በጥልቀት በማሰላሰል ስምዖን ጵጥሮስ እንዳለው፥ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማንስ እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ።”4

ለምናምነው እና ለምናውቀው ታማኝ እንሁን። በእውቀታችን መሠረት እኛ ባልኖርን፣ እንለውጠው። በኃጢአታቸው የሚጸኑ ኃጢአተኞች፣ እናም ንስሀ የማይገቡ፣ ንስሃ ለመግባት፣ ይቅርታን ለማግኘት እና በዘለአለማዊ በረከቶች ሁሉ ለመባረኩ ያላቸውን አጋጣሚ በጣም አደጋ ላይ በመጠል፣ ሰይጣንም ለራሱ እስክወስዳቻው ድረስ ወደ ጥልቀት እና ወደ ቆሻሻነት ውስጥ ሰምጠዋል።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ካቆሙ ሰዎች ብዙ ምክንያቶችን ሰምቻለሁ እናም በዚህ ምድር ላይ የምናደርገውን የጉዞአችንን ትክክለኛውን ራዕይ አጥተዋል። እንዲያስቡበት እና እንዲመለሱ መከርኳቸው፣ ምክንያቱም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ማንም ሰበብ ለማቅረብ እንድማይችል አምናለሁ።

ስንጠመቅ “የኢየሱስ ክርስቶስን ስም [በራሳችን] ለመውሰድ፣ እስከ መጨረሻው እርሱን በቁርጠኝነት ለማገልገል”5 በመስማማት ከአዳኝ ጋር ቃል ኪዳኖችን ገብተናል።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ላይ መገኘታችን እርሱን ለማገልገል፣ ለመንፈሳዊ ጥንካሬያችን እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችንን ለመሳደግ፣ ቁርጠኝነታችንን መገምገም የምንችልበት ቁልፍ ከሆኑ መንገዶች መካከል አንዱ ነው።

ቅዱስ ቁርባንን መከፈል በሰንበት ቀን የምናከናውነው በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ጌታ ይህን ስና ስርዓት ለሐዋርያቱ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ አብራርቷል። በአሜሪካ አህጉርም ተመሳሳይ ነገር አድርጓል። በዚህ ስነ-ስርአት ውስጥ የምንሳተፍ ከሆነ፣ ሁልጊዜ እርሱን እንደምናስታውሰው ለአብ ለምስክርነት እንደምሆን እና መንፈሱ ከእኛ ጋር እንደሚሆን ቃል እንደገባልን ይነግረናል።6

ታናሹ አልማ ለልጁ ሺብሎን በሰጠው ትምህርት፣ ለቃል ኪዳኖቻችን ታማኝ ሆነን እንድንጸና የሚረዱን ብልህ ምክሮች እና ማስጠንቀቂያዎች እናገኛለን፥

“አንተ በኩራት እንዳልሞላህ አረጋግጥ፤ አዎን፣ በራስህ ጥበብም ሆነ፣ በጉልበትህ እንደትማትመካ አረጋግጥ።

“ግልፅነትን ተጠቀም፣ ነገር ግን ሀያልነትን አትጠቀም፤ እናም ደግሞ በፍቅር ትሞላ ዘንድ፣ ስሜትህን በሙሉ ተቆጣጠር፤ ከስራ ፈትነት እንድምትሸሽም አረጋግጥ።”7

ከጥቂት አመታት በፊት፣ በእረፍት ጊዜ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ በጀልባ ለመሄድ ፈለግሁ። ጀልባን ተከራየሁና፣ በደስታ ተሞልቼ ወደ ባሕሩ ገባሁ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ ማዕበል ጀልባውን ገለበጣው። በጣም ከፍተኛ ጥረት፣ በአንድ እጅ መቅዘፊያውን እና በሌላ እጄ ጀልባን በመያዝ፣ አቀማመጤን እንድገና ማግኘት ቻልኩኝ።

ጀልባውን ለመቅዘፍ እንደገና ሞክሬ ነበር፣ ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጀልባውን እንደገና ተገለበጠ። እኔ በእምቢተኝነት ያለ ጥቅም እሞክር ነበር። ስለጀልባ አካሄድ የተረዳ አንድ ሰው ዛጎሉ ተሰንጥቆ ካያኩ በውሃ ሞልቶ፣ ይህም ያልተረጋጋና ለመቆጣጠር የማይቻል አድርጎት ልሆን ይችላል አለኝ። ጀልባውን ወደ ባሕሩ ዳርቻ በመጎተት መሰኪያውን አነሳሁት በእርግጠኝነትም ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወጣ።

አንዳንድ ጊዜ ከኃጢአቶች ጋር በህይወት ስንኖር፣ እንደ ጀልባ ቀዳዳ የእኛን መንፈሳዊ እድገት እደሚያግዱ አስባለሁ።

በኃጢአታችን ውስጥ የምንጸና ከሆነ፣ ከጌታ ጋር የገባነውን ቃል ኪዳን እንረሳለን ይሁን እንጅ እነዚያ ኃጢአቶች በህይወታችን ውስጥ የሚፈጥሩትን ሚዛን አልባነት ምክንያቱም መቆየታችንን እንቀጥላለን።

በጀልባው ውስጥ እንዳሉት ስንጣቄዎች ሁሉ በህይወታችን ውስጥ ያሉት ስንጣቄዎችም መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ኃጢያቶች ከሌሎች በላይ ንስሀ ለመግባት ብዙ ጥረቶች ያስፈልገዋል።

ስለዚህ ራሳችንን መጠየቅ አለብን፥ ስለ አዳኝ እና ስለ ስራው ያለን አመለካከት የት ይገኛለ? እኛስ እንደ ጴጥሮስ በለ ሁኔታ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንክዳለን? ወይስ ከአዳኙ ከተቀበለው “ታላቅ ተልዕኮ” በኋላ የነበረውን አመለካከት እና ቁርጠኝነት ውሳኔ የላቀ ደረጃ ላይ ደርሰን ይሆን?8

ትእዛዛቱን በሙሉ ለመታዘዝ ጥረት ማድረግ እና ለመጠበቅ ለእኛ ከባድ ለሆኑት ነገሮች ትኩረት መስጠት አለብን። ጌታ ከጎናችን በመሆን፣ በሚያስፈልገን ጊዜ እና በድክመት ጊዜ ይረዳናል፣ እናም ልባዊ ፍላጎትን ካሳየን እና በተግባር ላይ የምናውል ከሆነ፣ “ደካማ የሆኑ ነገሮች ጠንካራ እንዲሆኑ”9 ያደርጋል።

ታዛዥነት ኃጥአትን ለማሸነፍ ጥንካሬ ይሰጠናል። በተጨማሪም የእምነታችን መከራ፣ ብዙውን ጊዜ ውጤቱን ሳናውቅ እንድንታዘዝ የሚጠይቅ መሆኑን መረዳት አለብን።

እስከመጨረሻ ለመፅናት የሚያግዝንን ቀመር (ዘዴ) አቀርባለሁ፥

  1. በየዕለቱ፣ መጸለይና ቅዱሳን መጻህፍትን መንበብ።

  2. በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን በተሰበረ ልብና በተዋረደ መንፈስ መክፈል።

  3. አስራት እና በየወሩ የጾም በኩራትን ክፈሉ።

  4. በየሁለት ዓመቱ—በየዓመቱ ለወጣቶች—የቤተመቅደስ ማረጋገጫን ማሳደስ።

  5. በህይወታችን በሙሉ፣ በጌታ ሥራ ውስጥ ማገልግል።

የወንጌሉ ታላቅ እውነቶች አዕምሮአችንን ያፅኑ፣ እናም በዚህ ህይወት የባህር ውስጥ ጉዞዎቻችን ደህንነት ለመጉዳት ከሚችሉ ስንጣቄዎችም እራሳችንን እንጠብቅ።

በጌታ መንገድ ስኬት ዋጋ አለው፣ እናም ያንን ለማግኘት የሚቻለው ብቸኛው መንገድ ዋጋውን መክፈል ነው።

ታላቅ የስርየት መስዋዕቱን በማጠናቀቅ፣ አዳኛችን እስከ መጨረሻው ድረስ በመፅናቱ ምንኛ አመስጋኝ ነኝ።

ለኃጢአቶቻችን፣ ለሥቃዮቻችን ለጭንቀቶቻችን፣ ለስቃዮች፣ ለሕመሞችና ለፍርሃቶቻችን ተሠቃይቷል፣ እንዲንጸናና ላልተመሸነፉት የተያዘውን አክሊል ማግኘት እንድንችል እናም እንዴት እኛን መርዳት፣ ማነሳሳት፣ ማፅናናት፣ ማጠናከር እንዳለበት ያውቃል።

ሕይወት ለእያንዳንዳችን የተለየች ናት። ሁላችንም የሙካራ ጊዜ፣ የደስተኝነት ጊዜ፣ የመወሰን ጊዜ፣ እንቅፋቶችን የማሸነፍ ጊዜ እና አጋጣሚዎችን የመጠቀም ጊዜ አለን።

የግል ሁኔታዎቻችን ምንም ይሁን ምን፣ የሰማይ አባታችን ያለማቋረጥ “እወዳችኋለሁ። እደግፋችኋለሁ። እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። ተስፋ አትቁረጡ። ንስሃ ግቡና እኔ ባሳየኋችሁ መንገድ ጽኑ። እናም በሰማይ ቤታችን ውስጥ በድጋሚ እንደምንተያይ እርግጠኛ ነኝ” ብሎ እንደምናገር እመሰክራለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣አሜን።