2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈሱ ከእናንተ ጋር እንዲሆን
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


መንፈሱ ከእናንተ ጋር እንዲሆን

የመንፈስን ድምፅ፣ ለእናንተ በደግነት የተላከውን፣ ትሰሙ ዘንድ በልቤ በሙሉ እጸልያለሁ።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በጌታ ሰንበት፣ በቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ጉባኤ፣ በዚህ የትንሳኤ ወቅት እናንተን ለማነጋገር ላለን እድል ምስጋና ይሰማኛል። የሰማይ አባታችንን፣ የእኛ ቤዛ ለመሆን ወደ ምድር በፈቃደኝነት ለመጣው፣ ለውድ ልጁ ስጦታ አመሰግናለሁ። ለኃጢያቶቻችን ክፍያ ማድረጉን እና በትንሳኤ መነሳቱን በማወቄም ምስጋና አለኝ። በየቀኑ፣ በኃጢያት ክፍያው ምክንያት፣ ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ጋር ለመኖር አንድ ቀን ከሞት እንደምነሳ በማወቄ የተባረኩኝ ነኝ።

እነዚያን ነገሮች የማውቀው ማንኛችንም እነርሱን ለማወቅ በእምንችልበት ብቸኛ መንገድ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ አዕምሮዬ እና ልቤ እውነት እንደሆኑ—አንዴ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ጊዜ—ተናግሯል። ያም የማያቋርጥ መፅናኛ ያስፈልገኛል። ሁላችንም የመንፈስ ማረጋገጫ የሚያስፈልገን አሳዛኝ ድርግቶች ያጋጥሙናል። ይህም አንድ ቀን ከአባቴ ጋር በሆስፒታል ውስጥ በቆምኩበት ጊዜ ተሰምቶኛል። እናቴ ትንሽ ጥልቀት ያላቸው ትንፋሽዎችን ስትወስድ—እናም አለመውሰዷን ተመለከትን:: ፊቷን ስንመለከት፣ ህመሟ ሲሄድ ፈገግ ትል ነበር። ከትንሽ ጸጥተኛ ግዜ በኋላ፣ አባቴ በመጀመሪያ ተናገረ። እንዲህ አለ፣ “አንድ ትንሽ ልጅ ወደ ቤት ሄዳለች።”

በጸጥታ ነበር ያለው። ሰላም ያለው ይመስል ነበር። እውነት እንደሆነ የሚያውቀውን ነበር የተናገረው። የእማዬን ነገሮች በእርጋታ መሰብሰብ ጀመረ። ለበርካታ ቀናት የተንከባከቡትን ነርሶች እና ዶክዎች ለማመስገን ወደ ሆስፒታሉ መተላለፊያ ወጣ::

በዚያ ጊዜ የተሰማውን፣ የሚያውቀውን፣ እና ያደረገውን ለመድረግ አባቴ የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት ነበረው። ብዙዎች እንደተቀበሉት እርሱም ቃል ኪዳኖችን ተቀብሏል፥ “መንፈሱ ሁልግዜም ከእነርሱ ጋር ይሆን ዘንድ” (ት. እና ቃ. 20፥79)።

የእኔ ተስፋ ዛሬ እናተ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ያላችሁን ፍላጎት እና ችሎታ መጨመር ነው። አስታውሱ፣ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ሦስተኛው አባል ነው። አብ እና ወልድ ከሞት የተነሱ ሰዎች ናቸው። መንፈስ ቅዱስ የመንፈስ ሰው ነው። (ት. እና ቃ. 130፥22፣ 79 ተመልከቱ።) እርሱን ለመቀበል እና በልባችሁና በአዕምሮአችሁ ለመቀበል የእናንተ ምርጫ ነው።

ይህን መለኮታዊ በረከት የምንቀበልበት መንገድ በየሳምንቱ ሲነገሩ በምንሰማቸው ግን ምናልባት ሁልጊዜም በልባችን እና በአዕምሮአችን የማይዘልቁ በነበሩት ቃላት እንሰማቸዋለን። መንፈሱ ወደ እኛ እንዲላክ ዘንድ አዳኝን “ሁልጊዜ ማስታወስ” እና “ትእዛዛቱን መጠበቅ” አለብን (ት. እና ቃ. 20፥77)።

ይህ የአመት ጊዜ የአዳኝን መስዋዕት እና ከመቃብር በሙት መነሳቱን እንድናስታውስ ይረዳናል። አብዛኛዎቻችን የእነዚያ ትዕይንቶች ምስሎች በትዝታችን እንይዛቸዋለን። አንድ ጊዜ በኢየሩሳሌም መቃብር ቦታ ላይ ከባለቤቴ ጋር ቆሜ ነበር። ብዙዎች የተሰቀለው አዳኝ ከሞት እንደተነሳ ሰው እና እንደ ህያው እግዚአብሔር ከዚህ መቃብር እንደወጣ ያምናሉ።

በዚያ ቀን የነበረው አክባሪው መሪም በእጁ እየጠቆመ እንዲህ አለን፣ “ኑ፣ ባዶ የሆነውን መቃብር ተመልከቱ።”

ለመግባት አጎነበስን። በግድግዳው አጠገብ የድንጋይ ጠረጴዛ አየን። ነገር ግን በአእምሮዬ ሌላ ስዕል መጣ፣ በዚያ ቀን እንዳየነው አይነት እውነተኛ የሆነ። ይህችም በሐዋሪያት በመቃብሩ አጠገብ የተተወችው ማሪያም ነበረች። ያንንም ነበር መንፈስ እዛ እንደነበርኩኝ ያህል በግልፅ እንዳይ እና በዓዕምሮዬ ውስጥ እንድሰማ የፈቀደልኝ፥

“ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤

“ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።

“እነርሱም፣ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። “እርስዋም፣ ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው።

“ይህንም ብላ ወደ ኋላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቀችም።

“ኢየሱስም፣ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት። ጌታ ሆይ፣ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።

“ኢየሱስም። ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ። ረቡኒ አለችው፤ ትርጓሜውም፣ መምህር ሆይ ማለት ነው።

“ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት” (ዮሀንስ 20፥11–17)።

በመቃብሩ ማሪያም የተሰማትን እና ሁለቱ ሐዋሪያት በኤመስ መንገድ ላይ ከሞት ከተነሳው አዳኝ ጋር፣ ከኢየሩሳሌም የሚጎበኝ መስሏቸው፣ ሲራመዱ የተሰማቸውን ትንሽም እንዲሰማኝ ፈቃድ እንዳገኝ እጸልያለሁ፥

“እነርሱ፣ ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት። ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ።

“ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው

“ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ።

“እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ። (ሉቃስ 24፥29–32)።

ከ70 አመታት በፊት እገኝበት በነበረው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ከእነዚያ አንዳንድ ቃላቶች ተደግመው ነበር። በእነዚያ ቀናት የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ የነበረው በምሽት ነበር። ውጪ ጨለማ ነበር። ጉባኤው እነዚህን የተለመዱ ቃላት ዘምሯል። ለብዙ ጊዜ ሰምቻቸው ነበር። ነገር ግን በአንድ ልዩ ምሽት የነበረኝ ስሜት ነው የሚቆይ ትዝታ የሰጠኝ። ወደ አዳኝ እንድቀርብ አደረገኝ። ምናልባት እነዚህን ቃላት ስደግም፣ ይህም ወደ ሁላችንም ይመጣ ይሆናል፥

ከእኔ ጋር ሁን፤ ምሽት ነውና፣

ቀኑ አልፎ ሄዷል፤

የምሽት ጥላ ወድቋል፤

ምሽት እየመጣ ነው።

በልቤ ተቀባይ ተጋባዥ፣

በቤቴ ከእኔ ጋር ሁን።

ከእኔ ጋር ሁን፤ ምሽት ነውና፣

ከእኔ ጋር ዛሬ ትጓዛላህ

በውጤ ያለውን ልቤን አቃጥሎታል፣

ከአንተን ሳናግርህ።

ቅን ቃላቶች ነፍሴን ሲሞሉ

እናም በጎንህ ስታደርገኝ።

አዳኝ ሆይ፣ በዚህ ምሽት ከእኔ ጋር ሁን፤

እነሆ፣ ምሽት ነውና።

አዳኝ ሆይ፣ በዚህ ምሽት ከእኔ ጋር ሁን፤

እነሆ፣ ምሽት ነውና።1

ከድርጊቶች ትዝታ በላይ ውድ የሚሆነው መንፈስ ቅዱስ ልባችንን የሚነካበት እና የእርሱ የእውነት ተከታታይ ማረጋገጫ ትዝታ ነው። ከአይናችን ከማየት በላይ፣ ወይም ምናስታውሳቸው የተነገሩ ወይም የተነበቡ ቃላይ በላይ ውድ የሚሆኑት፣ ከጸጥተኛ የመንፈስ ድምፅ ጋር የሚመጡት ስሜቶች ናቸው። በብዛትም ባይሆን፣ በኤመስ መንገድ ላይ የነበሩት ተጓዦች እንደተሰማቸው፣ በልብ ለስላሳ መንደድ፣ ተሰምቶኛል። በብዛትም፣ የብርሃን እና የጸጥታ ማረጋገጫ ስሜት ነው።

ታላቅ ዋጋ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ጓደኝነት ቃል ኪዳን እንዳለን፣ እናም እንዴት ይህን ስጦታ ለማግኘት የምንችልበትን እውነተኛ መመሪያዎች አሉን። እነዚህ ቃላት በጌታ በተሾመ አገልጋይ እጆቹ በራሳችን ላይ ተጭነው ተባሉ፥ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበል።” በዚያ ጊዜ፣ እናንተ እና እኔ እርሱ እንደሚላክ ማረጋገጫ ይሰጠናል ነገር ግን ሀላፊነታችን፣ በህይወታችን ሁሉ፣ የመንፈስ አገልግሎትን ለመቀበል ልባችንን ለመክፈት መምረጥ ነው።

የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አጋጣሚ መመሪያን ይሰጣል። የጀመረው እና አገልግሎቱን የቀጠለው የራሱ ጥበብ ለሚያደርጋቸው ነገሮች ብቁ እንዳልሆኑ በመወሰን ነበር። በእግዚአብሔር ፊት ትሁት ለመሆን መረጠ።

ቀጥሎም፣ ጆሴፍ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ መረጠ። እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠው በማመን ጸለየ። መልሱ የመጣው ወጣት ልጅ እያለ ነው። እነዚያ መልእክቶች የመጡት እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑን እንዴት ለመመስረት እንደሚፈልግ ለማወቅ ባስፈለገው ጊዜ ነበር። መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ በሙሉ አፅናናው እና መራው።

አስቸጋሪ ሲሆንም የመንፈስ መነሳሻዎችን አከበረ። ለምሳሌ፣ ከምንም ጊዜ በላይ በሚፈልጋቸው ጊዜ አስራ ሁለቱን ወደ እንግሊዝ እንዲልክ የተሰጠውን መመሪያ ተሰጠው። ላካቸው።

በእስር ቤት እያለ እና ቅዱሳን በመጥፎ ሁኔታ በሚሳደዱበትም ጊዜ ከመንፈስ እርማትን እና ማፅናኛን ተቀበለ። እናም እስከሞት የሚያመጣ አደጋ እንደሚያጋጠው ቢያውቅም ወደ ካርቴጅ በሚጓዝበትም ጊዜ ታዛዥ ነበር።

ነቢዩ ጆሴፍ ለእኛ እንዴት የሚቀጥሉ የመንፈስ መመሪያዎችን እና መፅናኛዎችን ከመንፈስ ቅዱስ እንደምንቀበል ምሳሌ ሰጠን።

በመጀመሪያ የመረጠው በእግዚአብሔር ፊት ትሁት መሆንን ነበር።

ሁለተኛውም በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት መጸለይ ነበር።

ሶስተኛውም በትክክል ታዛዥ መሆን ነበር። ታዛዥነት በፍጥነት መሄድም ሊሆን ይችላል። ይህም መዘጋጀትም ሊሆን ይችላል። ወይም በትእግስት ለተጨማሪ የመንፈስ መነሳሻ መጠበቅም ሊሆን ይችላል።

አራተኛውም የሌሎችን ፍላጎቶች እና ልቦች እና ለጌታ እንዴት እንደምንረዳቸው ለማወቅ መጸለይ ነው። ጆሴፍ በችግር ላሉት ቅዱሳን በእስር ቤት እያለ ጸለየ። የእግዚአብሔር ነቢያት ሲጸልዩ፣ ለመንፈስ መነሳሻ ሲጠይቁ፣ መመሪያ ሲቀበሉ፣ እና በዚህም ሲሰሩ ለማየት እድል ነበረኝ።

በብዛት ጸሎታቸው ለሚያፈቅሯቸው እና ለሚያገለግሏቸው ሰዎች እንደሆነም ተመልክቻለሁ። ለሌሎች ያላቸው ሀሳብ ልባቸው የመንፈስ መነሳሻን ለመቀበል እንዲከፈቱ የሚያደርግ ይመስላሉ። ያም ለእናንተ እውነት ሊሆን ይችላል።

የመንፈስ መነሳሻ ለጌታ ሌሎችን እንድናገለግል ይረዳናል። ይህን በአጋጣሚዎቻችሁ አይታችሁታል፣ እኔም እይቼዋለሁ። ኤጲስ ቆጶሴ አንዴ እንዳሉኝ—ባለቤቴ በራሷ ህይወት ውስጥ በችግር ላይ እያለች—”በዎርድ ውስጥ እርዳታ ስለሚያስፈልገው ሰው በምሰማበት ጊዜ፣ ለመርዳት ወደዛ ስደርስ፣ ባለቤትህ ከእኔ በፊት እዛ አገኛታለሁ። ይህን እንዴት ነው የምታደርገው?”

እርሷም በጌታ መንግስት ውስጥ እንደሆኑት ሌሎች ታላቅ አገልጋዮች ናት። የሚያደርጉት ሁለት ነገሮች ያሉ ይመስላሉ። ታላቅ አገልጋዮች መንፈስ ቅዱስ ለእነርሱ ቋሚ ጓደኛ እንዲሆንላቸው ብቁ ሆነዋል። እናም የክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ለሆነው ለልግስና ስጦታ ብቁ ሆነዋል። እነዚያ ስጦታዎች፣ ሌሎችን በጌታ ፍቅር ምክንያት ሲያገለግሉ፣ በውስጣቸው አድገዋል።

ጸሎት፣ በመንፈስ መነሳሳት፣ እና የጌታ ፍቅር አብረው እንዴት የሚሰሩበት መንገድ የተገለጸልኝ በእነዚህ ፍጹም ቃላት ነበር፥

“ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።

“እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤

“እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።

ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

“ገና ጥቂት ዘመን አለ ከዚህም በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።

እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።

“ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ” (ዮሀንስ 14፥14–21)።

አብ በዚህ ጊዜ ስለእናንተ፣ ስለስሜታችሁ፣ እና በአካባቢያችሁ በሙሉ ስላሉት መንፈሳዊ እና ምድራዊ ፍላጎቶች እንደሚያውቅ የግል ምስክሬን እሰጣችኋለሁ። አብ እና ወልድ ስጦታው ላላቸው፣ በረከቶችን ለሚጠይቁ፣ እና ለዚህም ብቁ ለመሆን ለሚፈልጉት መንፈስ ቅዱስን እንደሚልኩም ምስክሬን እሰጣለሁ። አብ ወይም ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ በግድ በህይወታችን ውስጥ አይገቡም። ለመምረጥ ነጻ ነን። ጌታ ለሁሉም ነገሯል፥

“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

“እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።

“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ” (ራዕይ 3፥20–22)።

የመንፈስን ድምፅ፣ ለእናንተ በደግነት የተላከውን፣ ትሰሙ ዘንድ በልቤ በሙሉ እጸልያለሁ። ልባችሁንም እርሱን ለመቀበል ትከፍቱት ዘንድ እጸልያለሁ። በእውነት ፍላጎት እና በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ለመንፈስ መነሳሻ ከጠየቃችሁ፣ ይህን በጌታ መንገድ እና በእርሱ ጊዜ ትቀበሉታላችሁ። እግዚአብሔር ለወጣቱ ጆሴፍ ይህን አድርጓል። ዛሬም ለህያው ነቢያችን፣ ለፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ ይህን ያደርጋል። እናንተን በሌሎች የእግዚአብሔር ልጆች መንገድ ላይ ለእርሱ እንድታገለግሏቸው አስቀምጧችኋል። ይህን የማውቀው በአይኔ ባየሁት ብቻ ሳይሆን ግን ከሁሉም በላይ ሀይለኛ በሆነ መንፈስ በልቤ ባሾካሸከው ነው።

በአለም አቀፍ ለሚገኙት ለእግዚአብሔር ልጆች በሙሉ እና በመንፈስ አለም ላሉት ልጆቹ አብ እና ውድ ልጁ ያላቸው ፍቅር ተሰምቶኛል። የመንፈስ ቅዱስ መፅናናት እና መመሪያም ተሰምቶኛል። እናንተም መንፈስ ሁልጊዜም እንደጓደኛ የሚገኝበትን ደስታ እንዲኖራችሁ እጸልያለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “Abide with Me; ’Tis Eventide,” Hymns, no. 165.