2010–2019 (እ.አ.አ)
የማስተዋወቂያ ንግግር
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


የማስተዋወቂያ ንግግር

“የጌታን ስራ በውጤታማነት ለማከናወን የመልከ ጼዴቅ ክህት ሸንጎአችንን በታላቅ ለውጥ ማደራጀታችንን እናስተዋውቃለን።

ወንድም ሆልምስ፣ ለአስፈላጊው መልእክትዎ አመሰግናለሁ።

ውድ ወንድሞች፣ ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን እና ሽማግሌ ሮበርት ዲ. ሔልስበጣም ይናፍቁናል። ነገር ግን “በጌታ ስራ ወደፊት እንገባለን።”1

ቅዱስ ክህነትን ለሚሸከው እያንዳንዱ ሰው ታላቅ ምስጋና አለኝ። “እያንዳንዱ ሰው የአለም አዳኝ በሆነው በጌታ እግዚአብሔር ስም ይናገር ዘንድ”2 ፍላጎት ላለው ለቤዛችን ተስፋ ናችሁ። እርሱ ሁሉም የተሾሙ ልጆቹ፣ “እምነት ደግሞም በአለም [በሙሉ] ይጨምር ዘንድ፣”3 ለእርሱ ወኪል እንዲሆኑ፣ ለእርሱ እንዲናገሩ፣ እና በአለም አቀፍ ያሉትን የእግዚአብሔር ልጆች እስከመጨረሻ እንዲባርኩ ይፈልጋል።

አንዳንዶቻችሁ ቤተክርስቲያኗ ለብዙ ትውልዶች ተደራጅባ በነበረችበት ውስጥ ታገለግላላችሁ። ሌሎች ቤተክርቲያኗ አዲስ በሆነችበት ታገለግላላችሁ። ለአንዳንዶች፣ አጥቢያዎቻችሁ ትልቅ ናቸው። ለሌሎች፣ ቅርንጫፎቻችሁ ትንሽ እና ርቀታችሁ ረጅም የሆነ ነው። የግል ጉዳያችሁ ምንም ቢሆን፣ እያንዳንዳችሁ ለመማርና ለማስተማር፤ ሌሎችን ለማፍቀርና ለማገልገል መለኮታዊ ሀላፊነት ያላችሁ የክህነት ሸንጎ አባል ናችሁ።

በዚህ ምሽት፣ የጌታን ስራ በውጤታማነት ለማከናወን የመልከ ጼዴቅ ክህት ሸንጎአችንን በታላቅ ማደራጀታችንን እናስተዋውቃለን። በእያንዳንዱ አጥቢያ ውስጥ፣ ሊቀ ካህናት እና ሽማግሌዎች በአንድ የሽማግሌዎች ሸንጎ ይቀላቀላሉ። ይህም ለውጥ ክህነት የሚሸከሙት ሌሎችን ለማገልገል ያላቸውን ችሎታ በይበልጥ ለማሳደግ ይችላል። ሽማግሌ ለመሆን የሚችሉትም በዚያ ሸንጎ ተቀባይነትን እና ጓደኝነትን ያገኛሉ። በእያንድዳንዷ ካስማዎች፣ የካስማ አመራር የካስማ ሊቀ ካህናት ሸንጎን በመምራት ይቀጥላሉ። ነገር ግን የዚያ ሸንጎ አደራደር የሚመሰረተው፣ በቅርብ እንደሚገለጸው፣ አሁን በሚገኙት የክህነት ጥሪዎች ላይ ነው።

የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ አባላት ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እና ሽማግሌ ሮናልብ ኤ. ራዝባንድ አሁን ስለእነዚህ አስፈላጊ ለውጦች በተጨማሪ ያስተምሩናል።.

እነዚህ ለውጦች ለብዙ ወራት ሲጠኑባቸው ነበሩ። ለአባላቶቻችን የምንንከባከብበትን መንገድ እና ከእነርሱ ጋር የነበረንን ግንኙነት በሀተታ የምናቀርብበትን የማሻሻል አስፈላጊነት ተሰምቶን ነበር። ይህን በደንብ ለማድረግ፣ ጌታ ለቅዱሳኑ ለሚፈልገው የፍቅር አገልግሎት እና ድገፋ ዘንድ የክህነት ቡድኖቻችንን ታላቅ መመሪያዎች ለመስጠት እነርሱን ማጠናከር ያስፈልገናል።

እነዚህ ማስተካከያዎች በጌታ የተነሳሱኡ እንደሆኑ እመሰክራለሁ። እነዚህን በተግባር ስናውል፣ ከዚህ በፊር ከነበርነው በላይ ውጤታማ እንሆናለን።

በሁሉም ሀይለኛ እግዚአብሔር ስራ ላይ ያለን ነን። ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! እኛም የእርሱ ትሁት አገልጋዮች ነን! ሀላፊነታችንን ስንማር እና ስናከናውን እግዚአብሔር እናንተ ወንድሞችን እንዲባርክ የምጸልየው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።