2010–2019 (እ.አ.አ)
ንጹህ ፍቅር፡ የእያንዳንዱ እውነትኛ ደቀመዝሙር ምልክት
ሚያዝያ 2018 (እ.አ.አ)


ንጹህ ፍቅር፡ የእያንዳንዱ እውነትኛ ደቀመዝሙር ምልክት

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ማእከል ያደረገው አብ እና አዳኝ ለእኛ ባላቸው ፍቅር ላይ እናም ለእነርሱ እና እርስ ለእርሳችን ባለን ፍቅር ላይ ነው።

ፕሬዘዳንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰንን እንወደዋለን እናም እንናፍቀዋለን፣እንዲሁም ፕሬዘዳንት ኔልሰንን እንወደዋለን እናም እንደግፈዋለን። ፕሬዘዳንት ኔልሰን በልባችን ውስጥ የተለየ ቦታ አለው።

ጣት አባት በነበርኩ ጊዜ፣የአምስት አመት እድሜ ላይ የነበረው፣ትንሹ ወንድ ልጃችን፣አንድ ቀን ከትምህርት ቤት መጣና እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት፣ “አባዬ የሚሰራው ስራ ምን አይነት ስራ ነው?’’ ከዚያም አዳዲስ የክፍል ጓደኞቹ ስለ አባቶቻቸው ስራዎች መከራከር እንደጀመሩ አብራራ። አንዱ አባቱ የከተማው ፖሊስ የበላይ አለቃ እንደሆነ ተናገረ፣ሌላኛው ደግሞ በኩራት አባቱ የአንድ ትልቅ ድርጅት ዋና አለቃ እንደሆነ አወጀ።

እናም ስለ እሱ አባት ሲጠየቅ፣ ወንድ ልጄ በቀላሉ እንዲህ አለ፣“አባቴ ቢሮ ውስጥ ኮምፒተር ላይ ነው ሚሰራው።” ከዚያ፣ የሰጠው መልስ ትናንሸ ጓደኞቹን እንዳልሳበ ተረዳ፣ እንዲህ ብሎ ጨመር አደረገበት፣ “እናም በነገራችን ላይ፣ አባቴ የጠፈር አለማት ዋና አለቃ ነው።”

እንደማስበው ከሆነ ያ የውይይታቸው መቋጯ ነበር።

ለሚስቴ እንዲህ ብዬ ነገርኳት፣ “ስለ መዳን እቅድ እና ሃላፊው ማን እንደሆነ በጥልቀት ሰፋ አድርገን እሱን የምናስተምረበት ሰዓት ነው።”

ነገር ግን ልጆቻችንን ስለ መዳን እቅድ እያስተማርን በሄድን ቁጥር፣ የፍቅር እቅድ መሆኑን እየተማሩ በመጡ ሰዓት ለሰማይ አባት እና ለአዳኝ ያላቸው ፍቅር አደገ። የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ማእከል ያደረገው አብ እና አዳኝ ለእኛ ባላቸው ፍቅር ላይ እናም ለእነርሱ እና እርስ ለእርሳችን ባለን ፍቅር ላይ ነው።

ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድ እንዳሉት፤ “ከዘለአለም ሁሉ የመጀመሪያው ታላቅ ትእዛዝ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን፣ ሀይል፣ አዕምሮ፣ እና ጥንካሬ ማፍቀር ነው—ያም ታላቁ የመጀመሪያ ትእዛዝ ነው። ነገር ግን ከዘለአለም ሁሉ የመጀመሪያው ታላቅ እውነት እግዚአብሔር እኛን በሙሉ ልቡ፣ ሀይሉ፣ አዓምሮው፣ እና ጥንካሬው እንደሚያፈቅረን ነው። ያ ፍቅር የዘላለማዊነት የመሰረት ድንጋይ ነው፣ እናም የቀን ተቀን ሕይወታችን የመሰረት ድንጋይ መሆን አለበት።”1

የለት ከለት ኑሮዋችን አለት መሰረት መሆን፣ከእያንዳንዱ እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ንጹህ ፍቅር ይጠበል።

ሞርሞን እንዳስተማረው፣ “ስለሆነም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ በልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታዮች ሁሉ ላይ በሚያፈሰው በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ በኃይል ከልባችሁ ወደ አብ ፀልዩ።”2

በርግጥም ፍቅር የእያንዳንዱ እውነትኛ ደቀመዝሙር ምልክት ነው።

እውነትኛ ደቀመዛሙርት ማገልገልን ይወዳሉ። አገልግሎት የእውነተኛ ፍቅር እና በጥምቀት ወቅት የገቡት ቃልኪዳን መገለጫ እንደሆነ ያውቃሉ።3 በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው ጥሪ ወይም በማህበረሰብ ውስጥ ድርሻ ምንም ይሁን ምን፣ጐታን እና እርስ ራሳቸውን የመውደድ እና የማገልገል የሚያድግ መሻት ይሰማቸዋል።

እውነትኛ ደቀመዛሙርት ይቅር መለትን ይወዳሉ። የአዳኝ ቤዛነት የእያንዳንዳችንን ሃጢያቶች እና ስህተቶች ሁሉ እንደሚሸፍን ያውቃሉ። የከፈለው ክፍያ “ሁሉን ያጠቃለለ ክፍያ” እንደሆነ ያውቃሉ። መንፈሳዊ ግብሮች፣ክፍያዎች፣ኮምሽኖች፣ ወይም ከሀጢያቶች፣ ከስህተቶች፣ እናም ከተሳሳቱ ተግባራቶች ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ሁሉ ተሸፍነዋል። እውነተኛ ደቀ መዛሙርቶች ይቅርታ ለመስጠት እና ይቅርታ ለመጠየቅ ፈጣን ናቸው።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ይቅር የማለት ጥንካሬ ለማግኘት የምትቸገሩ ከሆነ፣ ሌሎች እናንተ ላይ ያደረጉትን ነገር አታስቡ፣ ነገር ግን አዳኝ ለእናነተ ያደረገውን አስቡ፣ እናም በቤዛው ፈዋሽ በረከቶች ሰላምን ታገኛላችሁ።

እውነትኛ ደቀመዛሙርት በልባቸው ሰላምን ይዘው እራሳቸውን ለጌታ አሳልፈው ይሰጣሉ። ትሁት እና የሚገዙ ናቸው ምክንያቱም እሱን ይወዳሉ። በሚያደርገው ነገር ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን እንዴት እና መች እንደሚያደርግም ፍቃዱን ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል እምነት አላቸው። እውነትኛ ደቀመዛሙርት እውነተኛ በረከቶች ሁሌም እነሱ የሚፈልጉት ነገር ሳይሆን ነገር ግን ጌታ ለእነሱ የሚፈልገው ነገር እንደሆነ ያውቃሉ።

እውነትኛ ደቀመዛሙርት ጌታን ከአለም አስበልጠው ይወዳሉ እናም በእምነታቸው ጠንካራ እና የማይነቃነቁ ናቸው። በሚቀያየር እና ግራ በተጋባ አለም ውስጥ ጠንካራ እና ጽኑ ሆነው ይቆያሉ። እውነትኛ ደቀመዛሙርት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽን መስማትን ይወዳሉ እናም በአለም ድምጽ ግራ አይጋቡም። እውነትኛ ደቀመዛሙርት “በቅዱስ ስፍራዎች ላይ መቆም”4 ይወዳሉ እናም የሚቆዩበትን ስፍራን ቅዱስ ማረግን ይወዳሉ። የትም ይሂዱ ይት፣ የጌታን ፍቅር እና ሰላም ወደ ሌሎች ልቦች ማምጣትን ይወዳሉ። እውነትኛ ደቀመዛሙርት የጌታን ትእዛዛት መታዘዝ ይወዳሉ፣ እናም የሚታዘዙትም ጌታን በመውደዳቸው ምክንያት ነው። ቃልኪዳናቸውን ሲወዱ እና ሲጠብቁ፣ ልቦቻቸው ይታደሳል እናም ትክክልኛ ተፈጥሯቸው ይቀየራል።

ንጹህ ፍቅር የእያንዳንዱ እውነትኛ ደቀመዝሙር ምልክት ነው።

ስለ ንጹህ ፍቅር ከእናቴ ተማርኩ። የቤተክርስቲያን አባል አልነበረችም።

ከብዙ አመታት በፊት፣ በካንሰር ህመም ስትስቃይ የነበረችውን፣ እናቴን ጎበኘዋት። ልትሞት እንደነበረ አውቅ ነበር፣ ነገር ግን እየተሰቃየች ስለነበር አሳስቦኝ ነበር። አንዳችም ነገር አላልኩም፣ ነገር ግን ጠንቅቃ ስለምታቀኝ፣ እንዲህ አለችኝ፣ “እንዳሳሰበክ እመለከታለሁ።”

ከዛም ያስገረመኝ ነገር፣ ድክም ባለ ድምጽ እንዲህ ጠየቀችኝ፣ “እንዴት እንደምጸልይ ማስተማር ትችላለህን? ለአንተ መጸለይ እፈልጋለሁ። ‘የተወደድክ የሰማይ አባት’ ተብሎ እንደሚጀመር አውቃለሁ፣ ነገር ግን ከዛ በኋላ ምን ልበል?”

ከአልጋዋ ጎን ተንበርክኬ እናም ለእኔ ጸለየችልኝ፣ ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ ፍቅር ተሰማኝ። ቀላል፣ እውነተኛ እና ንጹህ ፍቅር ነበር። ስለ መዳን እቅድ ምንም ባታቅም፣ በልቧ ውስጥ እናት ለወንድ ልጅዋ ያላት ፍቅር እቅድ አይነት የራሷ የሆነ የግል የፍቅር እቅድ ነበራት። በህመም ውስጥ ነበረች፣ ለመጸለይ እነኳን አቅም አጥታ ስትታገል ነበር። ድምጿን እራሱ በግድ ነበር የምሰማው፣ ነገር ግን በርግጥም ፍቅሯ ተሰምቶኛል።

እንደዚህ ማሰቤን አስታውሳለሁ፣“በእንደዚህ ታላቅ ህመም ውስጥ ያለ ሰው እንዴት ስለሌላ ሰው ይጸልያል? እስዋ ነበር የሚያስፈልጋት።”

ከዚያ መልሱ ወደ አእምሮዬ በግልጽ መጣ፤ ንጹህ ፍቅር። እኔን በጣም ከመውደዷ የተነሳ ስለ ራሷ ረሳች። በጣም በአስቸጋሪ ሰዓቷ፣ ከራሷ አስበልጣ ወደደችኝ።

አሁን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ይህንን አይደል አዳኝ ያደረገው? በርግጥም፣ ዘላለማዊ በሆነ እና መጣም በተለቀ ምልከታ። ነገር ግን በታላቅ ህመሙ መሃል፣ በዛች ማታ በአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ ማሰብ መሸከም ከሚችለው በላይ እየተሰቃየ፣ እሱ ነበር እርዳታ የሚያስፈልገው። ነገር ግን በስተመጨረሻም፣ ስለ ራሱ ረሳና ሙሉ ክፍያ እስኪከፍል ድረስ ለኛ ጸለየልን። ያንን እንዴት ሊያደርች ቻለ? ለአባት እሱን የላከው እና እንዲሁም ለኛ ባለው ንጹህ ፍቅር ምክንያት። ከራሱ በላይ አባቱን እና እኛን ወዶናል።

ላላደረገው ነገር ነው የከፈለው። ላልፈጸመው ሃጢያት ነው የከፈለው። ለምን? ንጹህ ፍቅር፡ ሙሉ ክፍያውን በመክፈሉ፣ ንሰሀ የምንገባ ከሆነ፣ የከፈለበትን በረከቶች ለእኛ ለመስጠት የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ ነበር። ለምንድነው ይህንን ያቀረበው? እንደገና፣ እና ሁልጊዜም፣ ንጹህ ፍቅር።

ንጹህ ፍቅር የእያንዳንዱ እውነትኛ ደቀመዝሙር ምልክት ነው።

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዳሉት፥ “አሁን፣ በዛሬው እለት፣ የቤተሰቦቻችን አባሎች፣ ጓደኞቻችንም፣ ቀለል ያለ ትውውቅም፣ ወይም ሙሉ ለሙሉ እንግዳም ቢሆኑም እንኳ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ፍቅርን ለመግለጽ እንጀምር። በየጠዋቱ ስንነሳ፣ በመንገዳችን ላይ ለሚመጡ ማናቸውም ነገሮች በፍቅር እና በበጎነት ለመመለሰ እንወስን።”5

ወንድሞች እና እህቶች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የፍቅር ወንጌል ነው። ታላቁ ትእዛዝ ስለ ፍቅር ነው። ለእኔ፣ስለ ፍቅር ብቻ ነው። ልጁን ለእኛ የሰዋው፣ የአባት ፍቅር ነው። ሁሉን ለእኛ የሰዋው፣ የአዳኝ ፍቅር ነው። ለእርሱ ወይም ለእርሷ ልጆች ማንኛውንም ነገር የሚሰጡት፣ የእናት እና የአባት ፍቅር። በዝምታ ለሚያገለግሉ እና ለአብዛኛዎቻቸን የማይታወቁት ነገር ግን በጌታ በደንብ የታወቁት ሰዎች ፍቅር። ሁሉንም እና ሁሌም ይቅር የሚሉት ፍቅር። ከሚቀበሉት በላይ የሚሰጡ ሰዎች ፍቅር።

የሰማይ አባቴን እወደዋለሁ። አዳኜን እወደዋለሁ። ወንጌልን በጣም እወደዋለሁ። ይህችን ቤተክርስቲያን በጣም እወዳታለሁ። ቤተሰቤን እወደዋለሁ። ይህን ድንቅ ህይወት እወደዋለሁ። ለእኔ፣ስለ ፍቅር ብቻ ነው።

ይህ የአዳኝን ትንሳኤ የምናስታውስበት ቀን ለእያንዳንዳችን የመንፈሳዊ ዳግመ እድሳት ይሁንልን። ይህ ቀን በፍቅር የተሞላ ህይወት፣ “የእለት ተእለት ኑሮዋችን የመሰርታችን አለት መጀመሪያ ይሁንልን።”

የእያንዳንዱ እውነተኛ ደቀመዛሙርት ምልክት በሆነው በንጹህ የክርስቶስ ፍቅር ልቦቻችን ይሞሉ። ይህ ፀሎቴ ነው በእየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።