ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፬


ምዕራፍ ፬

ኔፊ በጌታ ትዕዛዝ ላባንን ገደለ፣ እናም የነሀስ ሰሌዳዎቹን በብልሀት አገኘ—ዞራም ወደ ምድረበዳው በመሄድ ከሌሂ ቤተሰብ ጋር መደባለቅን መረጠ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ ለወንድሞቼ እንዲህ ስል ተናገርኩ፥ ተመልሰን ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ፣ እናም የጌታን ትዕዛዝ በመጠበቅ ታማኝ እንሁን፣ እነሆም እርሱ ከምድር ላይ ካለው ሁሉ ኃያል ነው፣ ከላባንና ከአምሳዎቹ ሰዎች፣ አዎን፣ ወይንም ከአስር ሺዎቹ እንኳ ለምን የበለጠ ኃያል አይሆንምን?

ስለዚህ እንሂድ፣ ልክ እንደ ሙሴ ጠንካሮች እንሁን፣ እነሆ እርሱ በእውነት የቀይ ባሕርን ውሃ ተናገረው፣ ውሃውም ወዲያና ወዲህ ተከፈለ፣ አባቶቻችንም በውስጡ ተሻግረው ከግዛት በደረቅ ምድር ወጡ፣ እናም የፈርዖን ሰራዊት ተከተሉትና፣ በቀይ ባሕር ውሃ ውስጥ ሰጠሙ።

አሁን እነሆ ይህ እውነት እንደሆነ አውቃችኋል፣ እናም ደግሞ መልአክ እንደተናገራችሁ ታውቃላችሁ፣ ስለዚህ፣ ልትጠራጠሩ ትችላላችሁን? እንሂድ ጌታ እኛን እንደአባቶቻችን ሊያድነን ላባንን እንደግብፃውያን ሊያጠፋ ይቻለዋል።

አሁን እነዚህን ቃላት በተናገርኩ ጊዜ፣ እንደተቆጡና አሁንም ማጉረምረማቸውን እንደቀጠሉ ነበር፣ ይሁን እንጂ እስከ ኢየሩሳሌም ግንብ ውጪ እስከደረስን ድረስ ተከተሉኝ።

እና ይህም በምሽት ነበር፤ እራሳቸውን ከግንቡ ውጪ እንዲደብቁ አደረኳቸው። እነርሱም ራሳቸውን ከደበቁ በኋላ እኔ ኔፊ ወደ ከተማው ሾለኩና፣ ወደ ላባን ቤት ሄድኩ።

እናም ማድረግ ያለብኝን ነገሮች ቀድሜ ሳላውቅ በመንፈስ ተመራሁ

ይሁን እንጂ፣ እኔም ወደፊት ሄድኩ፣ እናም ወደ ላባን ቤት እየቀረብኩ ስሄድ አንድ ሰው አየሁ፣ እና የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ስለነበረ ከፊቴ በመሬት ላይ ወድቆ ነበር።

እና ወደ እርሱ በመጣሁ ጊዜ ይህም ላባን እንደሆነ አወቅኩኝ።

የእርሱን ጎራዴ አየሁ፣ ከአፎቱም መዘዝኩት፣ የጎራዴውም መያዣ የተሰራው ከንፁህ ወርቅ ነበር፣ አሰራሩም እጅግ ያማረ ነበር፣ እናም ስለቱ በጣም ከከበረ ብረት መሆኑን አየሁ።

እናም እንዲህ ሆነ ላባንን እገድለው ዘንድ በመንፈስ ተገፋፋሁ፤ ነገር ግን በልቤ፣ በማንኛውም ጊዜ የሰው ደም አፍስሼ አላውቅም አልኩ። እና እኔ ተሸማቀቅሁና፣ እርሱን ላለመግደል ፈለግሁ።

፲፩ እናም መንፈስ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፥ እነሆ ጌታ እርሱን በእጆችህ አሳልፎ ሰጥቶሀል። አዎን፣ እኔም ደግሞ ሕይወቴን ሊወስድ እንደፈለገ አውቃለሁ፤ አዎን የጌታን ትዕዛዝ አያዳምጥም፤ እናም ንብረታችንንም ደግሞ ወስዷል

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ መንፈስ ለእኔ እንደገና እንዲህ አለኝ፥ ግደለው፣ ጌታ በእጆችህ አሳልፎ ሰጥቶሀልና፤

፲፫ እነሆ ጌታ ጻድቃዊ ዓላማውን ያሟላ ዘንድ ክፉዎችን ይገድላል። አንድ አገር እምነት በማጣት ከሚመነምንና ከሚሞት አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል

፲፬ እናም አሁን፣ እኔ፣ ኔፊ፣ እነዚህን ቃላት ስሰማ ጌታ በምድረበዳ እንዲህ ብሎ የተናገረኝን ቃላት አስታወስኩ፥ ዘርህ ትዕዛዛቴን እስከጠበቁ ድረስ በቃልኪዳኑ ምድር ላይ ይበለፅጋሉ

፲፭ አዎን ሕጉ ከሌላቸው በስተቀር በሙሴ ህግ መሰረት የጌታን ትዕዛዛት ሊጠብቁ እንደማይችሉ ደግሞ አሰብኩ።

፲፮ እናም እኔ ደግሞ ህጉ በነሀስ ሰሌዳው ላይ እንደተቀረፀም አውቃለሁ።

፲፯ እናም እንደገና ጌታ በትዕዛዙ መሰረት መዝገቦቹን አገኝ ዘንድ ላባንን በእጄ አሳልፎ የሰጠኝ ለዚህ ምክንያት መሆኑን አወቅሁ።

፲፰ ስለዚህ ለመንፈስም ድምፅ ታዘዝኩ፣ እና ላባንን የራሱን ፀጉር ይዤ በራሱ ጎራዴ አንገቱን ቆረጥኩት።

፲፱ እናም በራሱ ጎራዴ አንገቱን ከቆረጥኩ በኋላ፣ የላባንን ልብስ ወስጄ ለበስኩት፣ አዎን፣ አንድ ነገር ሳይቀር፣ እናም የእርሱን ጥሩር በወገቤ ላይ ታጠቅሁት።

ይህን ካደረግሁ በኋላ ወደ ላባን ግምጃ ቤት ተጓዝኩ። ወደ ላባን ግምጃ ቤት ስሄድ፣ እነሆም የግምጃ ቤቱን ቁልፍ የያዘውን የላባንን አገልጋይ አየሁ። እናም በላባን ድምፅ ወደ ግምጃ ቤቱ ከእኔ ጋር እንዲሄድ አዘዝኩት።

፳፩ እናም እርሱ የላባንን ልብስና ጎራዴውን በወገቤ መታጠቄን በማየቱ የእርሱ አለቃ መሰልኩት።

፳፪ እናም እርሱ አለቃው ላባን ሌሊቱን ከአይሁድ ሽማግሌዎች ጋር መሆኑን ስለሚያውቅ፣ ስለእነርሱ አነጋገረኝ።

፳፫ እናም እኔ ልክ ላባን እንደሆንኩኝ አስመስዬ ከእርሱ ጋር ተነጋገርኩ።

፳፬ እኔ ከግንቡ ውጭ ወደ ሚገኙት ታላላቅ ወንድሞቼ በነሀስ ሰሌዳ ላይ የተቀረፁትን ተሸክሜ መውሰድ እንዳለብኝ ተናገርኩት።

፳፭ እናም እኔ ደግሞ ሊከተለኝ እንደሚገባው አዘዝኩት።

፳፮ እርሱ የተናገርኩት ስለቤተክርስቲያን ወንድሞች መሰለው፣ እና እውነት እኔ የገደልኩትን ላባንን መሰልኩት፣ ስለዚህም ተከተለኝ።

፳፯ እናም እርሱ ከግንቡ ውጭ ወዳሉት ወንድሞቼ ስጓዝ ብዙ ጊዜ አይሁዶች ሽማግሌዎችን በተመለከተ ተናገረኝ።

፳፰ እናም እንዲህ ሆነ ላማን ባየኝ ጊዜ እጅግ ፈራ፣ እንዲሁም ልሙኤልና ሳምም። እናም እነርሱም ላባን ነው ብለው ስላሰቡ እኔንም የገደለኝና የእነርሱንም ህይወት የሚያጠፋ ስለመሰላቸው ከፊቴ ሸሹ።

፳፱ እናም እንዲህ ሆነ እኔም ጠራኋቸው፣ እናም ሰሙኝ፤ ስለዚህ ከፊቴ መሸሻቸውን አቆሙ።

እናም እንዲህ ሆነ የላባን አገልጋይ ወንድሞቼን ሲያይ መንቀጥቀጥ ጀመረና፣ ከእኔ ሸሽቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሊመለስ ፈለገ።

፴፩ እናም አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ በአቋሜ ግዙፍ በመሆኔና ከጌታም ጥንካሬን በማግኘቴ የላባንን አገልጋይ እንዳይሸሽ ያዝኩት።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ ጌታ ህያው እንደሆነ እኔም እስካለሁ ድረስ የእኔን ቃላት ከሰማ እንዲሁም ቃላታችንን ለመስማት ፈቃደኛ ከሆነ ሕይወቱን እኛ እንደምናተርፍለት ተናገርኩት።

፴፫ እናም እርሱ ከእኛ ጋር ወደ ምድረበዳ የሚሄድ ከሆነ መፍራት እንደሌለበት ልክ እንደ እኛ ነፃ ሰው እንደሚሆን በመሃላ ጭምር ተናገርኩት።

፴፬ እናም እኔ እንዲህ ብዬ ተናገርኩት፥ በእርግጥ ጌታ ይህን እንድናደርግ አዞናል፣ እናም የጌታንስ ትዕዛዛት በመጠበቅ መትጋት የለብንምን? ስለዚህ አንተ ወደ ምድረበዳ ወደ አባቴ የምትወርድ ከሆነ ከእኛ ጋር ትኖራለህ።

፴፭ እናም እንዲህ ሆነ ዞራም እኔ በተናገርኳቸው ቃላት ተበረታታ። ዞራም የአገልጋዩ ስም ነበር፤ እናም እርሱ ወደ ምድረበዳ ወደ አባታችን እንደሚሄድ ቃል ገባ። አዎን፣ ደግሞም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እርሱ ከእኛ ጋር እንደሚቆይ ማለልን።

፴፮ አሁን እርሱ ከእኛ ጋር እንዲቆይ የፈለግንበት ለዚህ ምክንያት ነበር፣ አይሁዶች እኛን እንዳያሳድዱን እናም እንዳያጠፉን በመፍራት ወደ ምድረበዳ መሸሸታችንን እንዳያውቁ ዘንድ ነው።

፴፯ እናም እንዲህ ሆነ ዞራም መሃላ ሲገባልን እርሱን በተመለከተ የነበሩን ፍርሃቶች አቆሙ።

፴፰ እናም እንዲህ ሆነ የነሀስ ሰሌዳዎችንና የላባንን አገልጋይ ወሰድንና፣ ወደ ምድረበዳው ሄድን፣ እንዲሁም ወደ አባታችን ድንኳን ተጓዝን።