ቅዱሳት መጻህፍት
፩ ኔፊ ፮


ምዕራፍ ፮

ኔፊ ስለ እግዚአብሔር ነገሮች ፃፈ—የኔፊ ዓላማ ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ መጥተው እንዲድኑ ማስረዳት ነው። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

እና አሁን እኔ፣ ኔፊ፣ የአባቶቼን የትውልድ ሀረግ በዚህ የመዝገቤ ክፍል አልፅፍም፣ በማንኛውም ጊዜ ቢሆን በዚህ በምፅፍበት ሰሌዳ ላይ አልፅፈውም፤ አባቴ ባቆየው መዝገብ ላይ ተፅፏልና፤ ስለዚህ በዚህ ሥራ ውስጥ አልፅፈውም።

እኛ የዮሴፍ ትውልዶች ነን ማለት ብቻ ይበቃኛል።

ሁሉንም የአባቴን ነገሮች በመፃፍ ጥንቁቅ መሆኔ ልዩነት አያመጣም፣ በእነዚህ ሰሌዳ ላይ መፃፍ አይችሉምና፣ እኔ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለመፃፍ ቦታውን እፈልገዋለሁና።

ሙሉ አላማዬም ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ፣ ወደ ይስሀቅ አምላክና፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ እንዲመጡና እንዲድኑ ለማሳመን ነውና።

ስለዚህ፣ ለዓለም አስደሳች የሆኑትን ነገሮች እኔ አልፅፍም፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔርና ከዓለም ላልሆኑት የሚያስደስቱ ነገሮችን እፅፋለሁ።

ስለዚህ ሰሌዳዎቹን ለሰው ልጆች ዋጋ በሌላቸው ነገሮች እንዳይሞሏቸው ለዘሮቼ ትዕዛዝን እሰጣለሁ።