ምዕራፍ ፱
ኔፊ በሁለት የተካፈሉ መዝገቦችን ሰራ—እያንዳንዳቸው የኔፊ ሰሌዳዎች ይባላሉ—ትልልቆቹ ሰሌዳዎች አለማዊውን ታሪክ ይዘዋል፤ ትንንሾቹም ቅዱሳን ነገሮችን። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እና አባቴ ሀበልሙኤል ሸለቆ፣ ውስጥ በድንኳን ሲኖር፣ እነዚህን ነገሮች ሁሉና፣ በእነዚህ ሰሌዳዎች ላይ ሊፃፉ የማይችሉትን፣ ብዙ ትላልቅ ነገሮችን አየ፣ እንዲሁም ሰማ፣ ተናገረም።
፪ እናም አሁን፣ እነዚህን ሰሌዳዎች በተመለከተ እንደተናገርኩት፣ እነሆ እነርሱ የህዝቤን ታሪክ በሙሉ የፃፍኩባቸው ሀሰሌዳዎች አይደሉም፤ የእኔን ህዝቦች ታሪክ በሙሉ የፃፍኩባቸው ሰሌዳዎች ኔፊ የሚል ስም ሰጥቻቸዋለሁ፤ ስለዚህ፣ እነርሱ በእኔ ስም የኔፊ ሰሌዳዎች ተብለው ይጠራሉ፤ እናም እነዚህ ሰሌዳዎች ደግሞ የኔፊ ሰሌዳዎች ተብለው ይጠራሉ።
፫ ሆኖም፣ እኔ ለተለየ ሀዓላማ ስለህዝቦቼ ለአገልግሎት ታሪክ በእነዚህ ሰሌዳዎች በመቅረፅ እንድፅፍ ከጌታ ትዕዛዝ ተቀብያለሁ።
፬ ሀበሌሎቹም ሰሌዳዎች ላይ የንጉሶቹን የንግስ ታሪክ፣ እናም የጦርነትና የእኔ ህዝቦች ፀብ መቀረፅ አለበት፤ ስለዚህ እነዚህ ሰሌዳዎች በይበልጥ ስለአገልግሎት የሚቀረጹበት፤ እናም ሌሎች ሰሌዳዎች ስለንጉሶቹ ንግስና የእኔ ህዝቦች ፀብና ጦርነቶች የሚቀረጹበት ናቸው።
፭ ስለዚህ ጌታ እነዚህ ሰሌዳዎች ሀለብልህ ዓላማው እንድሰራው አዘዘኝ፣ ይህንም አላማ እኔ አላውቀውም።
፮ ነገር ግን ጌታ ሁሉንም ነገሮች ከመጀመሪያ ጀምሮ ሀያውቃል፤ ስለዚህ፣ ሁሉንም የእርሱን ስራዎች በሰው ልጆች መካከል ለመፈፀም መንገድ ያዘጋጃል፤ እነሆም፣ የእርሱ ቃላት በሙሉ የሚያሟላበት ሁሉም ለኃይል አለው። እናም ይህ ነው። አሜን።