የመጀመሪያው የኔፊ መጽሐፍ

፩ ኔፊ 

የሌሂና የሚስቱ የሳርያ፣ እንዲሁም የእርሱ አራት ልጆች (ከበኩር ጀምሮ) ላማን፣ ልሙኤል፣ ሳምና፣ ኔፊ ተብለው የሚጠሩት መዝገብ። ጌታ ሌሂን ከኢየሩሳሌም ምድር እንዲወጣ አስጠነቀቀው፣ ምክንያቱም እርሱ የህዝቡን ክፋት በተመለከተ ስለተነበየ እነርሱ ህይወቱን ሊያጠፉ ፈለጉ። ከቤተሰቡም ጋር የሶስት ቀን ጉዞ ወደ ምድረበዳ አደረገ። ኔፊ የአይሁዶችን መዝገብ ለመውሰድ ወንድሞቹን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ምድር ተመለሰ። ስለስቃያቸው ታሪክ። እነርሱም የእስማኤልን ሴት ልጆች አገቡ። ቤተሰቦቻቸውንም ይዘው ወደ ምድረበዳ ሄዱ። በምድረበዳ ውስጥ የነበራቸው ስቃያቸውና መከራቸው። የጉዞአቸውም አቅጣጫ። ወደ ትልቁ ውሃ መጡ። የኔፊ ወንድሞች በእርሱ ላይ አመፁ። እርሱም እነርሱን ዝም አሰኛቸው፣ እና መርከብን ሰራ። የቦታውንም ስም ለጋስ ብለው ጠሩት። ታላቁን ውሃ ተሻግረው ወደ ቃል ኪዳን ምድር ቀጠሉ። ይህ በኔፊ አመዘጋገብ መሰረት ነው፣ ወይም በሌላ አነጋገር እኔ፣ ኔፊ፣ ይህን ታሪክ ፃፍኩ።
ምዕራፍ ፩

ኔፊ የእርሱን ሕዝብ የሕይወት ታሪክ መመዝገብ ጀመረ—ሌሂ የእሳት አምድ በራዕይ አየ እናም ከትንቢት መጽሐፍም አነበበ—እግዚአብሔርንም አወደሰ፣ የመሲህን መምጣት አስቀድሞ ተናገረ፣ እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ጥፋት ተነበየ፣ በአይሁዶች ስደት ደረሰበት። ፮፻ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

ሌሂ ቤተሰቡን በቀይ ባሕር በኩል ወደ ምድረበዳ ወሰደ—ንብረታቸውንም ተዉ—ሌሂ መስዋዕትን ለጌታ አቀረበ፣ እናም ወንዶች ልጆቹን ትዕዛዛትን እንዲጠብቁ አስተማረ—ላማን እና ልሙኤል በአባታቸው ላይ አጉረመረሙ—ኔፊ ታዛዥና በእምነትም የሚፀልይ ነው፣ ጌታም እርሱን ተናገረው እና በወንድሞቹም ላይ እንዲገዛ ተመረጠ። ፮፻ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

የሌሂ ወንዶች ልጆች የነሀስ ሰሌዳዎቹን ለማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ—ላባን ሰሌዳዎቹን አልሰጥም አለ—ኔፊ ወንድሞቹን ገሰፀ እና አበረታታ—ላባን ንብረታቸውን ቀማቸው እናም ሊገድላቸውም ሞከረ—ላማንና ልሙኤል ኔፊንና ሳምን መቷቸው፣ እናም መልአክ ገሰፃቸው። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ኔፊ በጌታ ትዕዛዝ ላባንን ገደለ፣ እናም የነሀስ ሰሌዳዎቹን በብልሀት አገኘ—ዞራም ወደ ምድረበዳው በመሄድ ከሌሂ ቤተሰብ ጋር መደባለቅን መረጠ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

ሳርያ በሌሂ ላይ አጉረመረመች—በወንዶች ልጆቻቸው መመለስ ሁለቱም ተደሰቱ—መስዋዕትም አቀረቡ—የነሀስ ሰሌዳዎቹ የሙሴን እና የነቢያትን ፅህፈቶች ይዘዋል—ሰሌዳዎቹ ሌሂ ከዮሴፍ ትውልድ መሆኑን ያሳያሉ—ሌሂ ስለዘሮቹና ሰሌዳዎቹን ስለመጠበቅ ተነበየ። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ኔፊ ስለ እግዚአብሔር ነገሮች ፃፈ—የኔፊ ዓላማ ሰዎችን ወደ አብርሃም አምላክ መጥተው እንዲድኑ ማስረዳት ነው። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፯

የሌሂ ወንዶች ልጆች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እስማኤልንና ቤተሰቦቹን አብረዋቸው እንዲጓዙ ጋበዙአቸው—ላማንና ሌሎቹ አመፁ—ኔፊ ወንድሞቹን በጌታ እምነት እንዲኖራቸው መከራቸው—በገመድ አሰሩት እናም የእርሱን ጥፋት አቀዱ—በእምነት ሀይል እርሱ ነፃ ሆነ—ወንድሞቹ ይቅርታን ጠየቁ—ሌሂና አብረውት የነበሩትም የሚቃጠለውን መስዋዕት አቀረቡ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

ሌሂ ስለ ሕይወት ዛፍ ራዕይ አየ—ከፍሬውም ተካፈለና ቤተሰቦቹም እንደዚያው እንዲያደርጉ ፈለገ—የብረት በትር፣ የጠበበና የቀጠነ መንገድና ሰዎችን የሚጋርደውን የጨለማ ጭጋግ ተመለከተ—ሳርያ፣ ኔፊና፣ ሳም፣ ፍሬውን ተካፈሉ፣ ላማንና ልሙኤል ግን ተቃወሙ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፱

ኔፊ በሁለት የተካፈሉ መዝገቦችን ሰራ—እያንዳንዳቸው የኔፊ ሰሌዳዎች ይባላሉ—ትልልቆቹ ሰሌዳዎች አለማዊውን ታሪክ ይዘዋል፤ ትንንሾቹም ቅዱሳን ነገሮችን። ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

ሌሂ አይሁዶች በባቢሎናውያን በምርኮ እንደሚወሰዱ ተነበየ—ከአይሁዶች መካከል መሲህ፣ አዳኝና፣ መድኃኒት እንደሚመጣ ተናገረ—እንዲሁም ሌሂ የእግዚአብሔርን በግ የሚያጠምቀው እንደሚመጣ ተናገረ—ሌሂ የመሲሁን ሞትና ትንሣኤ ተናገረ—እርሱም የእስራኤልን መበተንና መሰባሰብ ከወይራ ዛፍ ጋር አነፃፀረ—ኔፊ ስለእግዚአብሔር ልጅ፣ ስለመንፈስ ቅዱስ ስጦታና፣ ስለፅድቅ አስፈላጊነት ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፩

ኔፊ የጌታን መንፈስ አየ እና የህይወት ዛፍ በራዕይ ታየው—እርሱም የእግዚአብሔርን ልጅ እናት አየ እናም ስለእግዚአብሔር ትህትና ተማረ—እርሱም የእግዚአብሔርን በግ ጥምቀት አገልግሎትና ስቅለት አየ—እናም ደግሞ የአስራ ሁለቱን የበጉን ሐዋርያት ጥሪና አገልግሎት አየ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፪

ኔፊ የቃልኪዳኑን ምድር፣ የነዋሪዎችዋን ጻድቅነት፣ ኃጢያት እና ጥፋትን፤ የእግዚአብሔርን በግ በእነርሱ መካከል መምጣትን፤ አስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት እና አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እስራኤልን እንዴት እንደሚፈርዱ፣ እና በእምነት ማጣት የመነመኑትን አሰቃቂና መጥፎ ሁኔታ በራዕይ አየ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፫

ኔፊ በአህዛቦች መካከል የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን መቋቋምን፣ የአሜሪካ መገኘትና ቅኝ መያዝን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ብዙ የተከበሩና ግልፅ ክፍሎች መጥፋትን፣ የእዚህም ውጤት የሆነውን የአሕዛብ ክህደት ሁኔታን፣ የወንጌል መመለስን፣ የኋለኛው ቀን ቅዱስ መፅሐፍት መምጣትን፣ እና የፅዮንን ግንባታ በራዕይ አየ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፬

መልአክ በአህዛብ ላይ ስለሚመጡት በረከቶችና እርግማን ለኔፊ ነገረው—ሁለት ቤተክርስቲያናት ብቻ አሉ፥ የእግዚአብሔር በግ ቤተክርስቲያን እና የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን—በሁሉም ሀገሮች ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱሳን በታላቋና በርኩሰት ቤተክርስቲያን ተሰድደዋል—ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ ዓለም መጨረሻ ይፅፋል። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፭

የሌሂ ዘሮች በኋለኛው ቀናት ከአህዛብ ወንጌልን ይቀበላሉ—የእስራኤልም መሰባሰብ የተፈጥሮ ቅርንጫፎቹ መልሰው እንደሚጣበቁ የወይራ ዛፍ ጋር ይመሳሰላል—ኔፊ የህይወት ዛፍን ራዕይ ተረጎመ እናም እግዚአብሔር ኃጢአተኛን ከፃድቅ ስለሚለያይበት ፍትህ ተናገረ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፮

ኃጢአተኞች እውነትን ለመቀበል አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል—የሌሂ ወንዶች ልጆች የእስማኤልን ሴቶች ልጆች አገቡ—ሊያሆናው በምድረበዳ ውስጥ መንገዳቸውን መራቸው—ከጌታ የመጡ መልዕክቶች በተለያዩ ጊዜዎች በሊያሆናው ላይ ይፃፉ ነበር—እስማኤል ሞተ፣ ቤተሰቦቹም በስቃዮች ምክንያት አጉረመረሙ። ከ፮፻–፭፻፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፯

ኔፊ መርከብ እንዲሰራ ታዘዘ—ወንድሞቹ ተቃወሙት—ከእስራኤል ጋር እግዚአብሔር ያደረገውን ታሪክ በመንገር አበረታታቸው—ኔፊ በእግዚእብሔር ኃይል ተሞላ—ወንድሞቹ እንዳይነኩት ተከለከሉ፣ አለበለዚያ ልክ እንደደረቀ ሸንበቆ ይኮማተራሉ። ከ፭፻፺፪–፭፻፺፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፰

መርከቡ ተጠናቀቀ—የያዕቆብና የዮሴፍ መወለድ ተጠቀሰ—ህዝቡም ወደ ቃልኪዳኑ ምድር ተጓዙ—የእስማኤል ወንዶች ልጆችና ሚስቶቻቸው በፈንጠዚያውና በአመፃው ተቀላቀሉ—ኔፊ ታሰረ፣ እናም መርከቡ በኃይለኛ አውሎ ነፋስ ወደኋላ ተነዳች—ኔፊ ተፈታ፣ እናም በእርሱ ፀሎት ማዕበሉ ቆመ—ህዝቡም ወደ ቃልኪዳኑ ምድር ደረሱ። ከ፭፻፺፩–፭፻፹፱ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፱

ኔፊ ሰሌዳዎችን ከብረት አፈር ሠርቶ የህዝቡን ታሪክ መዘገበ—የእስራኤል አምላክ ሌሂ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀበት ከስድስት መቶ ዓመት በኋላ ይመጣል—ስለእርሱ መከራና ስቅለት ኔፊ ተናገረ—አይሁዶች ይጠላሉ፣ እናም ወደጌታ እስከሚመለሱ እስከ ኋለኞቹ ቀናት ድረስ ይበተናሉ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳

ጌታ ዓላማውን ለእስራኤል ገለጠ—እስራኤልም በመከራ እቶን ተመረጠች፣ እናም ከባቢሎን ትወጣለች—ኢሳይያስ ፵፰ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፩

መሲሁ ለአህዛብ ብርሃን ይሆናል እንዲሁም እስረኞችን ያስለቅቃል—እስራኤልም በኋለኛው ቀናት በኃይል ትሰበሰባለች—ንጉሶችም የእነርሱ አሳዳጊ አባቶች ይሆናሉ። ኢሳይያስ ፵፱ን አነፃፀር። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፪

እስራኤላውያን በምድር ሁሉ ገፅ ላይ ይበተናሉ—በመጨረሻው ቀናት አህዛብ እስራኤላውያንን በወንጌል ያጠቧቸዋልም ይመግቧቸዋልም—እስራኤላውያን ይሰበሰባሉ፣ ይድናሉም እናም ኃጢአተኞች እንደአገዳ ይነዳሉ—የዲያብሎስ መንግስት ይጠፋል፣ እንዲሁም ሰይጣን ይታሰራል። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።