ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፲፰


ምዕራፍ ፲፰

ክርስቶስ እንደማሰናከያ ዓለት እና እንቅፋት ይሆናል—ጠንቋይን ሳይሆን ጌታን እሹ—ለመመሪያችሁ በህጉና በምስክርነቱ ላይ ተስፋ አድርጉ—ኢሳይያስ ፰ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ከዚህም በላይ፣ የጌታ ቃል እንዲህ አለኝ—ትልቁን ጥቅል ውሰድ፣ እናም ማሔር-ሻላል-ኸሽ-ባዝ ብለህ በሰው ብዕር ፃፍበት።

እናም እኔ የታመኑ ምስክሮችን፣ ካህን ኦርዮን እና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ለምዝገባው ወደ እኔ ወሰድሁ።

እናም እኔ ወደ ነቢይቱ ቀረብሁ፤ እርሷም ፀነሰች እናም ወንድ ልጅ ወለደች። ከዚያም ጌታ እንዲህ አለኝ፥ ማኻር-ሻላል-ሐሽ-ባዝ ብለህ ስሙን ጥራው።

እነሆም፣ ህፃኑ አባቱንና እናቱን መጥራት ሳያውቅ፣ የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሶር ንጉስ ፊት ይወስዳል።

ጌታ እንደገና ደግሞ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥

ይህ ህዝብ በቀስታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ውሃ እስከጠሉ፣ እናም በረአሶንንና በሮሜልዩም ልጅ በመደሰታቸው የተነሳ፤

ስለዚህ አሁን፣ እነሆ፣ ጌታ ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውሃ፣ የአሶርን ንጉስና ክብሩን ሁሉ ያመጣባቸዋል፤ እናም እርሱ መስኖዎችን ሁሉ ይሞላል፣ እናም በዳርቻውም ሁሉ ላይ ይፈስሳል።

እናም በይሁዳ ያልፋል፤ እያጥለቀለቀም ያልፋል፣ እስከ አንገትም ይደርሳል፤ እናም አማኑኤል ሆይ፣ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።

ህዝብ ሆይ ተባበሩ፣ እናም በትንንሹ ትከፋፈላላችሁ፤ እናንተም ሩቅ ሀገር ያላችሁ ሁሉ አድምጡ፤ ራሳችሁን አስታጥቁ፣ እናም በትንንሹ ትከፋፈላላችሁ፤ ራሳችሁን አስታጥቁ፣ እናም በትንንሹ ትከፋፈላላችሁ።

በአንድነት ተመካከሩ፣ እናም እርሱ ከንቱ ይሆናል፤ ቃሉን ተናገሩ፣ እናም አትፀናም፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና

፲፩ ጌታ በፅኑ እጁ እንዲሁ ተናግሮኛልና፣ እናም በዚህ ህዝብ መንገድ እንዳልራመድ እንዲህ ሲል አዘዘኝ፥

፲፪ ይህ ህዝብ ግብረ-አበራዊ ነው በሚለው ሁሉ ግብረ-አበራዊ ነው አትበሉ፣ መፈራታቸውንም ቢሆን አትፍሩ፣ አትደንግጡ።

፲፫ የሰራዊት ጌታ እራሱን ቀድሱት፣ እናም የእናንተ ፍርሃት እርሱ ይሁን፣ ስጋታችሁም እርሱ ይሁን።

፲፬ እናም እርሱ መሸሸጊያ፤ ነገር ግን ለሁለቱ ለእስራኤል ቤቶች፣ ለእንቅፋት ድንጋይና፣ ለማሰናከያ አለት፣ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለወጥመድና ለአሽክላ ይሆናል።

፲፭ እናም ብዙዎች ከእነርሱ ጋር ይሰናከላሉ እንዲሁም ይወድቃሉ፣ ይሰበራሉም፣ ይጠመዳሉም፣ እናም ይማረካሉ።

፲፮ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ምስክርነትን እሰር፣ ህጉንም አትም።

፲፯ እናም ከያዕቆብ ቤት ፊቱን የደበቀውን ጌታ እጠብቃለሁ፣ እናም እርሱን እፈልገዋለሁ።

፲፰ እነሆ፣ እኔና ጌታ የሰጠኝ ልጆቼ በእስራኤል በፅዮን ተራራ ከሚኖረው ከሰራዊት ጌታ ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።

፲፱ እናም የሚጮሁትንና፣ ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ ባሉአችሁ ጊዜ—ለህያዋን ከሙታን ለመስማት ህዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን?

ወደህግና ወደምስክርነት ተመልከቱ፣ እናም በዚህ ቃል መሰረት ካልተናገሩ፣ ምክንያቱ ብርሃን በውስጣቸው የለም።

፳፩ እነርሱም ይህን በጣም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ፤ እናም እንዲህ ይሆናል በተራቡ ጊዜ፣ በጣም ይቆጣሉ፣ እናም አምላካቸውንና ንጉሳቸውን ይረግማሉ፣ ወደ ላይም ይመለከታሉ።

፳፪ እናም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ እናም ችግርን፣ ጨለማን፣ የሚያስጨንቅ ጭጋግን ያያሉ፣ እናም ወደ ጨለማም ይሰደዳሉ።