ቅዱሳት መጻህፍት
፪ ኔፊ ፰


ምዕራፍ ፰

ያዕቆብ ከኢሳይያስ ማንበብ ቀጠለ፥ በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ ጌታ ፅዮንን ያፅናናል እንዲሁም እስራኤልን ይሰበስባል—የዳኑትም ወደ ፅዮን በታላቅ ደስታ ተከበው ይመጣሉ—ኢሳይያስ ፶፩ እና ፶፪፥፩–፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

እናንተ ፅድቅን የምትከተሉ ስሙኝ። የተቆረጣችሁበትን ድንጋይ፣ እንዲሁም የተቆፈራችሁበትን ጉድጓድ ተመልከቱ።

ወደ አባታችሁ አብርሃምና ወደ ወለደቻችሁ ሣራ ተመልከቱ፤ ብቻውን ጠራሁት፣ እናም ባረክሁትም።

ጌታ ፅዮንን ያፅናናል፣ በእርሷ ባድማ የሆነውን ቦታ ሁሉ ያፅናናል፤ እናም ምድረበዳዋንም እንደ ዔድን፣ እናም በረሃዋን እንደ ጌታ የአትክልት ስፍራ ያደርገዋል። ደስታና ተድላ፣ ምስጋና እና የዝማሬ ድምፅ ይገኝባታል።

ሕዝቤ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ወገኔ ሆይ፣ ስሙኝ፤ ህግ ከእኔ ይወጣልና፣ እና ፍርዴን ለህዝብ እንደ ብርሃን እንዲያርፍ አደርጋለሁ።

ፅድቄ ቀርቧል፤ ማዳኔም ወጥቷል፣ እናም ክንዴ በህዝቡ ይፈርዳል። ደሴቶች እኔን ይጠባበቃሉ፣ እናም በክንዴ ይታመናሉ።

ዐይኖቻችሁን ወደ ሰማያት አንሱ፣ እናም ወደታች ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደጢስ በንነው ይጠፋሉ፣ ምድርም እንደልብስ ታረጃለች፤ እናም የሚኖሩባት እንዲሁ ይሞታሉ። ነገር ግን ማዳኔ ለዘለዓለም ይሆናል፣ ፅድቄም አይፈርስም።

ፅድቅን የምታውቁ፣ ህጌንም በልባችሁ የፃፍኩባችሁ እኔን አድምጡኝ፣ የሰዎችን ዘለፋ አትፍሩ፣ ወይም ስድባቸውንም አትፍሩ

እንደልብስም ብል ይበላቸዋልና፣ እናም ትል እንደሱፍ ይበላቸዋል። ነገር ግን ፅድቄ ለዘለዓለም፣ እናም ማዳኔ ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናል።

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ! ተነስ! ኃይልንም ልበስ፣ እንደጥንቱ ቀናት ተነሳ። ረዓብን የቆራረጥክ፣ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?

ባህሩን፣ የታላቁን ጥልቅ ውሃ ያደረቅህ፣ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጥልቁን ባህር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?

፲፩ ስለዚህ፣ ጌታ ያዳናቸው ይመለሳሉ፣ በዝማሬም ወደ ፅዮን ይመጣሉ፤ እናም የዘለዓለም ደስታና ቅዱስነት በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ እናም ደስታና ተድላን ያገኛሉ፤ ሀዘንና ልቅሶም ይሸሻሉ።

፲፪ እኔ እርሱ ነኝ፤ የማፅናናችሁ እኔ ነኝ። እነሆ፣ የሚሞተውን ሰውና እንደሳርም የሚሆነውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?

፲፫ እናም ሰማያትን የዘረጋውንና፣ የምድርን መሰረት የሰራውን፣ ጌታ ፈጣሪህን ረሳህ፣ እናም ሊያጠፉህ የተዘጋጁ ይመስል በአስጨናቂዎችህ ቁጣ ምክንያት ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈራህ? እናም የአስጨናቂዎችህ ቁጣ የት አለ?

፲፬ ምርኮኛ እንዲፈታ፣ እና እርሱ በጉድጓድ እንዳይሞት፣ ወይም እንጀራም አይጐድልበት ይፈጥናል።

፲፭ ነገር ግን ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ ጌታ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ስሜም የሰራዊት ጌታ ነው።

፲፮ እናም ሰማያትን እዘረጋና ምድርንም እመሰርት ዘንድ፣ እናም ለፅዮን፣ እነሆ፣ አንቺ ህዝቤ ነሽ እንድላት ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፣ እንዲሁም በእጄ ጥላ ጋርጄሃለሁ።

፲፯ ከጌታ እጅ የቁጣውን አተላ በፅዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ ንቂ፣ ንቂ፣ ቁሚ፣ ከሚያንገደግድ ዋንጫ መራራን ጠጥተሻል—

፲፰ እናም ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ መካከል የሚመራትም የለም፤ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።

፲፱ እነዚህ ሁለቱ ወንዶች ልጆች ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ ላንቺ ማን ያዝንልሻል—መደምሰስሽና መውደምሽ፣ ረሃብና ሰይፍም—እንዲሁም በማን አፅናናሻለሁ?

ከእነዚህ ከሁለቱ በስተቀር ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤ በአደባባይ ላይ ተኝተዋል፤ በወጥመድ እንዳለ የሜዳ ኮርማ በጌታ ቁጣ፣ በአምላክሽ ተግሳፅ ተሞልተዋል።

፳፩ ስለዚህ አሁን ይህን ስሚ፣ አንቺ ተሰቃዪና ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ

፳፪ ጌታሽ ይላል፣ ጌታ እና አምላክሽ የወገኑ ጉዳይ ይማፀናል፤ እነሆ፣ የሚያንገደግድን ፅዋ፣ የቁጣዬንም ዋንጫ አተላውን ከእጅሽ ወስጃለሁ፣ ደግመሽም ከእንግዲህ አትጠጪውም።

፳፫ ነገር ግን ነፍስሽን እንሻገር ዘንድ ዝቅ በይ በሚሉት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፥ እናም ሰውነትሽንም ለሚሻገሩበት እንደ መሬት መንገድ አድርገሽ ዘርግተሽዋል።

፳፬ ፅዮን ሆይ ንቂ፣ ንቂ ሀይልሽን ልበሺ፤ ቅድስት ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ቆንጆ ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘና እርኩስ ከእንግዲህ አይገባብሽምና

፳፭ ትቢያን አራግፊ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተነሺ፣ ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የፅዮን ሴት ልጅ ሆይ የአንገትሽን እስራት እራስሽ ፍቺ።