የኔፊ ሁለተኛ መጽሐፍ

፪ ኔፊ 

የሌሂ የአሟሟት ታሪክ። የኔፊ ወንድሞች በእርሱ ላይ አመጹ። ጌታ ኔፊን ወደ ምድረበዳ እንዲሄድ አስጠነቀቀው። በምድረበዳ የነበረው ጉዞና የሌሎች ነገሮች መዝገብ።
ምዕራፍ ፩

ሌሂ ስለነፃነቷ ምድር ተነበየ—የእስራኤልን ቅዱስ የሚቃወሙ ከሆነ ዘሮቹ ይበተናሉ እናም ይጠፋሉ—ወንዶች ልጆቹን የፅድቅን የጦር ዕቃ እንዲለብሱ አበረታታቸው። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

ቤዛነት በቅዱሱ መሲህ ይመጣል—የምርጫ ነፃነት (በራስ መነሳሳት) ለመኖርና ለማደግ አስፈላጊ ነው—ሰዎች ይኖሩ ዘንድ አዳም ወደቀ—ሰዎች ነፃነትን እና ዘለዓለማዊ ህይወትን ለመምረጥ ነፃ ናቸው። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

ዮሴፍ በግብፅ በራዕይ ኔፋውያኖችን አየ—ስለጆሴፍ ስሚዝ፣ የኋለኛው ቀን ባለራዕይ፤ እስራኤላውያንን ነፃ ስለሚያወጣው ሙሴ፤ እንዲሁም ስለመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ተነበየ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ሌሂ ዘሮቹን መከረ እንዲሁም ባረከ—ሞተና ተቀበረ—ኔፊ በእግዚአብሔር ቸርነት ተደሰተ—ኔፊ እምነቱን ለዘለዓለም በጌታ አደረገ። ከ፭፻፹፰–፭፻፸ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

ኔፋውያን እራሳቸውን ከላማናውያን ለዩ፣ የሙሴን ህግ ጠበቁ፣ እናም ቤተመቅደስ ሰሩ—ላማናውያን ባለማመናቸው ከጌታ ፊት ተለዩ፣ ተረገሙ፣ እናም ለኔፋውያን እንደ ጅራፍ ሆኑ። ከ፭፻፹፰–፭፻፶፱ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ያዕቆብ እንደገና የአይሁዶችን ታሪክ ተረከ፥ ስለባቢሎን ምርኮና መመለስ፤ ስለእስራኤሉ ቅዱስ አገልግሎትና ስቅለት፤ ከአህዛብ እርዳታን ስለማግኘታቸው፤ እና አይሁዶች በኋለኛው ቀን በመሲሁ ሲያምኑ ዳግሞ መመለሳቸውን። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፯

ያዕቆብ ከኢሳይያስ ማንበቡን ቀጠለ፥ ኢሳይያስ እንደ መሲሁ ይናገራል—መሲሁ የተማሩ ሰዎች ልሳን ይኖረዋል—ለሚገርፉት ጀርባውን ይሰጣል—እርሱ አያፍርም—ኢሳይያስ ፶ን አነጻፅሩ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

ያዕቆብ ከኢሳይያስ ማንበብ ቀጠለ፥ በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ ጌታ ፅዮንን ያፅናናል እንዲሁም እስራኤልን ይሰበስባል—የዳኑትም ወደ ፅዮን በታላቅ ደስታ ተከበው ይመጣሉ—ኢሳይያስ ፶፩ እና ፶፪፥፩–፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፱

አይሁዶች በቃልኪዳናቸው ምድር ላይ ሁሉ እንደሚሰበሰቡ ያዕቆብ ገለጸ—የኃጢያት ክፍያው ለሰው ከውድቀት ቤዛ ይሆናል—የሙታን አካል ከመቃብር እንዲሁም መንፈሳቸው ከሲኦልና ከገነት ይመጣል—ይፈረድባቸዋል—የኃጢያት ክፍያው ከሞት፣ ከሲኦል፣ ከዲያብሎስ፣ ማለቂያ ከሌለው ስቃይ ያድናል—ፃድቃን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ይድናሉ—የኃጢያት ቅጣቶች ተገልፆአል—የእስራኤሉ ቅዱስ የመግቢያው በር ጠባቂ ነው። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

አይሁድ አምላካቸውን እንደሚሰቅሉ ያዕቆብ ገለጸ—በእርሱም ማመን እስኪጀምሩም ድረስ ይበተናሉ—አሜሪካ ንጉስ የማይገዛባት የነፃ ምድር ትሆናለች— ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቁ፣ እናም በፀጋው መዳንን አግኙ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፩

ያዕቆብ መድኃኒቱን አየ—የሙሴ ህግ የክርስቶስ ምሳሌዎች ናቸው እናም የእርሱን መምጣት ያረጋግጣል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፪

ኢሳይያስ የኋለኛውን ቀን ቤተመቅደስ፤ የእስራኤልን መሰብሰብና የአንድ ሺህ ዘመን ፍርድን እና ሰላምን ተመለከተ—በዳግም ምፅአቱ ኩራተኞችና ኃጢአተኞች ትሁት ይሆናሉ—ኢሳይያስ ፪ አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፫

ይሁዳና ኢየሩሳሌም ባለመታዘዛቸው ይቀጣሉ—ጌታም ለህዝቡ ይማፀናል፣ እናም ሕዝቡን ይፈርዳል—የፅዮን ሴት ልጆች በዓለማዊነታቸው የተነሳ የተረገሙና የተሰቃዩ ናቸው—ኢሳይያስ ፫ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፬

ፅዮንና ሴቶች ልጆችዋ ይድናሉ፣ እናም በሺኛው ዘመን ይነፃሉ—ኢሳይያስ ፬ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፭

የጌታ የወይን አትክልት ስፍራ (እስራኤል) ባዶ ይሆናል፣ እናም የእርሱ ሕዝቦች ይበተናሉ—በአመፃና በመበተናቸው ጊዜ መከራ በእነርሱ ላይ ይመጣል—ጌታም ምልክቱን ያነሳል እናም እስራኤልን ይሰበስባል—ኢሳይያስ ፭ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፮

ኢሳይያስ ጌታን አየ—የኢሳይያስ ኃጢአቶች ይቅር ተብለዋል—እንዲተነብይ ተጠርቷል—አይሁዶች የኢየሱስን ትምህርት እንደሚያስወግዱ ተንብዮአል—ቅሪቶች ይመለሳሉ—ኢሳይያስ ፮ን አነጻፅሩ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፯

ኤፍሬምና ሶርያ በይሁዳ ላይ ጦርነትን አወጁ—ክርስቶስ ከድንግል ይወለዳል—ኢሳይያስ ፯ን አነጻፅሩ። ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፰

ክርስቶስ እንደማሰናከያ ዓለት እና እንቅፋት ይሆናል—ጠንቋይን ሳይሆን ጌታን እሹ—ለመመሪያችሁ በህጉና በምስክርነቱ ላይ ተስፋ አድርጉ—ኢሳይያስ ፰ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፱

ኢሳይያስ ስለመሲሁ ተናገረ—በጨለማ ያለ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ያያል—ህፃን ልጅ ተወልዶልናል—እርሱም የሠላም አለቃ ይሆናል በዳዊትም ዙፋን ላይ ይነግሳል—ኢሳይያስ ፱ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳

የአሶር መጥፋት ኃጢአተኞች በዳግም ምፅአት እንደሚጠፉት ምሳሌ ነው—ጌታ እንደገና ከመጣ በኋላ ጥቂት ሰዎች ይቀራሉ—የያዕቆብ ቅሪቶች በዚያን ቀን ይመለሳሉ—ኢሳይያስ ፲ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፩

የእሴይ ግንድ (ክርስቶስ) በጻድቅነት ይፈርዳል—ስለእግዚአብሔር የሚኖረው እውቀት በአንድ ሺህ ዘመን ምድርን ይሞላል—ጌታም አርማውን ያነሳል እናም እስራኤልን ይሰበስባል—ኢሳይያስ ፲፩ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፪

በአንድ ሺህ ዘመን ሰዎች ሁሉ ጌታን ያወድሳሉ—እርሱም በመካከላቸው ይኖራል—ኢሳይያስ ፲፪ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፫

የባቢሎን ጥፋት በዳግም ምፅአት የሚኖረው ጥፋት ምልክት ነው—የቁጣና የበቀል ቀን ይሆናል—ባቢሎን (አለም) ለዘለዓለም ትወድቃለች—ኢሳይያስ ፲፫ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፬

እስራኤል ትሰበሰባለች፣ የሺህ ዓመት እረፍትን ትደሰትበታለች—ሉሲፈር በአመፅ ምክንያት ከሰማይ ተጥሏል—እስራኤል ባቢሎንን (ዓለምን) ድል ታደርጋታለች—ኢሳይያስ ፲፬ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፭

ኔፊ በግልፅነት ይደሰታል—የኢሳይያስ ትንቢቶች በመጨረሻው ዘመናት ግልፅ ይሆናሉ—አይሁድ ከባቢሎን ይመለሳሉ፣ መሲሁንም ይሰቅላሉ፣ እናም ይበተናሉ፣ ይቀሰፋሉም—በመሲሁ ሲያምኑ ደግመው ይመለሳሉ—በመጀመሪያ ሌሂ ኢየሩሳሌምን ከለቀቀ ከስድስት መቶ አመት በኋላ ይመጣል—ኔፋውያን የሙሴን ህግ ይጠብቃሉ፣ የእስራኤሉ ቅዱስ በሆነው ክርስቶስም ያምናሉ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፮

ክርስቶስ ለኔፋውያን ያገለግላል—ኔፊ የህዝቡን መጥፋት አስቀድሞ አየ—ከምድር ውስጥ ይናገራሉ—አህዛብም ሀሰተኛ ቤተክርስቲያንን እናም ሚስጥራዊ ሴራዎችን ይሰራሉ—ጌታ በክህነት የሚደረገውን ተንኮል ይከለክላል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፯

ጨለማና ክህደት በመጨረሻው ዘመን ምድርን ይሸፍናታል—መፅሐፈ ሞርሞን ይመጣል—ሶስት ምስክሮች ስለመፅሐፉ ይመሰክራሉ—የተማረው ሰው የታተመውን መጽሐፍ ማንበብ አልችልም ይላል—ጌታ አስደናቂና ድንቅ ስራን ይሰራል—ኢሳይያስ ፳፱ን አነጻፅሩ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፰

በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሀሰተኛ ቤተክርስቲያኖች ይሰራሉ—ውሸትን፣ ከንቱነትን፣ እና የማይረባ ትምህርትንም ያስተምራሉ—በሐሰተኛ አስተማሪዎችም የተነሳ ክህደት ይበዛል—ዲያብሎስ በሰዎች ልብ ቁጣን ያመጣል—የተለያዩ ሐሰተኛ ትምህርቶችን ሁሉ ያስተምራል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፱

ብዙ አህዛብ መፅሐፈ ሞርሞንን አይቀበሉም—ሌላ መፅሐፍ ቅዱስ አያስፈልገንም ይላሉ—ጌታ ለብዙ ሀገሮች ይናገራል—በመጽሐፍት ላይ በሚፃፉት ዓለምን ይፈርዳል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴

የተለወጡት አህዛብ ከቃል ኪዳን ህዝብ ጋር ይቆጠራሉ—ብዙ ላማናውያንና አይሁዶች በቃሉ ያምናሉ እናም ያማሩ ይሆናሉ—እስራኤል ዳግም ትመለሳለች፣ እናም ኃጢአተኞች ይጠፋሉ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፩

ኔፊ ክርስቶስ ለምን እንደተጠመቀ ይናገራል—ሰዎች ለመዳን ክርስቶስን መከተል፣ መጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እናም እስከመጨረሻው መፅናት ይኖርባቸዋል—ንስሀ መግባትና ጥምቀት የጠባቡና ቀጭኑ ጎዳና መግቢያ ናቸው—የዘለዓለም ህይወት ከጥምቀት በኋላ ትዕዛዛትን ለሚጠብቁት ይመጣል። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፪

መላዕክት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይናገራሉ—ሰዎች መፀለይ እናም እውቀትን ከመንፈስ ቅዱስ ማግኘት አለባቸው። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፫

የኔፊ ቃላት እውነት ናቸው—ስለክርስቶስ ይመሰክራሉ—በክርስቶስ የሚያምኑ በፍርድ ወንበር ፊት ምስክር ሆኖ በሚቆመው በኔፊ ቃላት ያምናሉ። ከ፭፻፶፱–፭፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።