ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፲፮


ምዕራፍ ፲፮

ኢየሱስ ሌሎችን የጠፉትን የእስራኤል በጎች ይጎበኛቸዋል—በኋለኛው ቀን ወንጌል ለአህዛብ እናም ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል—እግዚአብሔር ፅዮንን ዳግም በሚመልስበት ጊዜ የጌታ ሰዎች ዐይን ለዐይን ይተያያሉ። ፴፬ ዓ.ም. ገደማ።

እናም እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህች ምድር ወይም ከኢየሩሳሌም ወይም እኔ ካገለገልኩባቸውም ቦታዎች ዙሪያ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ።

የምናገርባቸውም ገና ድምፄን አልሰሙትምና፤ ወይም በማንኛውም ጊዜ ራሴን አልገለጽኩላቸውም።

ነገር ግን ወደ እነርሱ እንድሄድ ዘንድ፣ እናም ድምፄን ይሰሙና፣ ከበጎቼም ጋር ይቆጠሩ፣ እናም አንድም መንጋ፣ እረኛውም አንድ እንዲሆን ከአብ ትዕዛዝ ተቀብያለሁ፤ ስለዚህ ራሴንም ላሳያቸው እሄዳለሁ።

እናም እኔም ከሄድኩኝ በኋላ ይህንን የተናገርኩትን እንድትፅፉ አዛችኋለሁ፤ ይህ ከሆነ እኔን የተመለከቱኝና፣ በአገልግሎቴ ወቅት ከእኔ ጋር የነበሩት በኢየሩሳሌም ያሉት ህዝቦቼ ስለ እናንተ፣ እናም ደግሞ ስለሚያውቋቸው ሌሎች ነገዶች በመንፈስ ቅዱስ እውነትን ያገኙ ዘንድ አብን በስሜ ካልጠየቁ፣ በዚህም በአህዛብ ሙላት በኩል፣ ባለማመናቸው ምክንያት በምድር ገፅ ላይ የሚበተኑት የዘሮቻቸው ቅሪት እንዲመጡ ዘንድ፣ ወይም አዳኛቸው ወደሆንኩት ወደ እኔም እውቀት ይመጡ ዘንድ እናንተ የምትፅፏቸው እነዚህ አባባሎች ይጠበቃሉ እና ለአህዛብም ይገለጻሉ።

እናም ከምድሪቱ ከአራቱም ማዕዘናት እሰበስባቸዋለሁ፤ እናም አብ ከእስራኤል ቤት ከሁሉም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ።

እናም አህዛብ ስለእኔ እንዲሁም ስለእኔና ስለአብ ስለሚመሰክርላቸው መንፈስ ቅዱስ በማመናቸው የተባረኩ ናቸው።

እነሆ፣ አብም እንዲህ ይላል፣ በእኔም ስለሚያምኑ፣ እናም፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ስለማታምኑ በኋለኛው ቀን እውነት ለአህዛብ ትመጣለች፤ የእነዚህን ነገሮች ሙሉነት እነርሱ እንዲያውቁት ይሆናል።

ነገር ግን አብም ለማያምኑ አህዛብ ወዮላቸው ይላል—እነርሱ ወደዚህች ምድር ገፅ የመጡም ቢሆኑ፣ እናም የእስራኤል ቤት የሆኑትንም ህዝቦቼን ቢበትኑም፣ እናም ከእስራኤል ቤት የሆኑት ህዝቦቼ ከመካከላቸው ቢጣሉም፣ እናም በእነርሱም እግር ቢረገጡም፤

እናም አብ ለአህዛብ ባለው ምህረቱና፣ ደግሞ የእስራኤል ቤት በሆኑት ህዝቦቼ ላይ በአብ በነበረው ቅጣት የተነሳ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ እናም የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቦቼን እንዲመቱና፣ እንዲሰቃዩ፣ እናም እንዲገለሉና፣ ከመካከላቸው እንዲጣሉም፣ በእነርሱ እንዲጠሉና፣ በአህዛብ መካከል እንዲያፏጭባቸው እናም እንዲናቁ ካደረኩኝ በኋላ—

እናም እንዲህ እንድላችሁም አብ አዞኛል፥ አህዛብ በዚያ ቀን በወንጌሌ ላይ ኃጢያት ሲፈፅሙ፣ እናም የወንጌሌንም ሙሉነት አንቀበልም ሲሉና፣ ልባቸው ከሀገር ሁሉ በላይ፣ እናም በምድሪቱ ካሉት ሰዎች ሁሉ በላይ ልባቸው በኩራት ሲወጠር፣ እናም በሁሉም አይነት ውሸትና፣ በማጭበርበርም፣ በግብዝነትም፣ በመግደልም፣ በካህናት ተንኮልና በዝሙት፣ እናም በሚስጥር እርኩሰት የተሞሉ ሲሆኑ፤ እናም እነዚህን ነገሮች በሙሉ የሚያደርጉ ከሆነና የወንጌሌን ሙሉነት ካልተቀበሉ፣ እነሆ፣ አብ እንዲህ ይላል፣ የወንጌሌን ሙሉነት ከመካከላቸው እወስድባቸዋለሁ።

፲፩ እና ከዚያም፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለህዝቤ የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፣ እናም ወንጌሌንም ለእነርሱ አመጣለሁ።

፲፪ እናም የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አህዛብ በእናንተ ላይ ስልጣን እንደሌላቸው አሳያችኋለሁ፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት ሆይ ለእናንተ የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፣ እናም ወደ ወንጌሌ ሙሉ እውቀትም ትመጣላችሁ።

፲፫ ነገር ግን አብም እንዲህ ይላል፥ አህዛብ ንሰሃ ከገቡ፣ እናም ወደ እኔ ከተመለሱ፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ከህዝቦቼ መካከል የተቆጠሩ ይሆናሉ።

፲፬ እናም አብም እንዲህ ይላል፥ የእስራኤል ቤት የሆኑትን ህዝቦቼን በመካከላቸው አልፈው እናም እንደ ጭቃ እንዲረግጧቸው አልፈቅድም።

፲፭ ነገር ግን ወደ እኔ ካልተመለሱና፣ ድምፄን ካልሰሙ፣ እነርሱን አዎን፣ የእስራኤል ቤት የሆኑት ህዝቦቼ ወደ እነርሱ እንዲሄዱና፣ እንደጭቃም እንዲረግጧቸው እፈቅዳለሁ፣ እናም ጣዕሙን እንዳጣ ጨውም ሆነው፣ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከንቱ እንደሆኑ ነገር ግን እንደሚወረወሩ፣ እናም የእስራኤል በሆኑትም በህዝቦቼ የሚረገጡ ይሆናሉ።

፲፮ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ—ለዚህ ህዝብ ይህንን የርስት ምድራቸውን እንድሰጣቸው አብ እኔን አዞኛል።

፲፯ እናም ነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ ሲል የተናገራቸው ቃላት ይፈጸማሉ፥

፲፰ የአንቺ ጠባቂዎች ይጮሀሉ፤ ጌታም ወደ ፅዮን በተመለሰ ጊዜ፣ ዐይን ለዐይን ይተያያሉና፣ በአንድነት ድምጽም ይዘምራሉ።

፲፱ እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች፣ ጌታ ህዝቡን አፅናንቶአልና፤ ኢየሩሳሌምን ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፣ በአንድነትም ዘምሩ።

ጌታም የተቀደሰውን ክንዱን በሀገሮች ሁሉ ፊት ገልጿል፤ እናም በምድር ዳርቻም ያሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን መድሐኒት ያያሉ።