ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፴


ምዕራፍ ፴

የኋለኛው ቀን አህዛብ ንሰሃ እንዲገቡ፣ እናም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ፣ እና ከእስራኤል ቤትም ጋር እንዲቆጠሩ ታዘዋል። ከ፴፬–፴፭ ዓ.ም. ገደማ።

እናንት አህዛብ ሆይ፣ ስሙ፤ እናም እናንተን በተመለከተ እንድናገር ያዘዘኝን ህያው የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስን ቃላት አድምጡ፤ እነሆም እንዲህ ብዬም እንድፅፍ አዞኛል፥

አህዛብ ሁሉ ከኃጢያት መንገዳችሁ ተመለሱ፤ እናም ከክፉ ስራዎቻችሁ፣ ከውሸታችሁና፣ ከአታላይነታችሁ፣ እናም ከዝሙት ተግባራችሁና፣ በድብቅ ከምትፈፅሙት ርኩሰት፣ በጣዖት ማምለካችሁም፣ ከግድያችሁም፣ ከካህናት ተንኮላችሁም፣ ከምቀኝነታችሁም፣ ከፀበኝነታችሁም፣ እናም ከሁሉም ኃጢአቶቻችሁና ርኩሰታችሁ ሁሉ ንሰሃ ግቡ፣ እናም ለኃጢአቶቻችሁ ስርየትን ትቀበሉና፣ በመንፈስ ቅዱስ ትሞሉ ዘንድ፣ የእስራኤል ቤት ከሆኑት ህዝቦቼ ጋርም ትቆጠሩ ዘንድ ወደ እኔ ኑ፣ እናም በስሜ ተጠመቁ።