ቅዱሳት መጻህፍት
፫ ኔፊ ፯


ምዕራፍ ፯

ዋናው ዳኛ ተገደለ፣ መንግስቱም ጠፋ፣ እናም ህዝቡም በጎሳ ተከፋፈለ—ፀረ ክርስቶስ የሆነው ያዕቆብም የሚስጥራዊው ሴራዎች ንጉስ ሆነ—ኔፊ ንሰሃንና በክርስቶስ እምነትን ሰበከ—መላዕክት ዕለት በዕለት አገለገሉት፣ እናም ወንድሙን ከሞት አስነሳ—ብዙዎች ንሰሃ ገቡ፣ እናም ተጠመቁ። ፴–፴፫ ዓ.ም. ገደማ።

አሁን እነሆ፣ በምድሪቱ ላይ ንጉስ እንዳልመሰረቱ አሳያችኋለሁ፤ ነገር ግን በዚሁ ዓመት፤ አዎን፣ በሰላሳኛው ዓመት፣ በፍርድ ወንበሩ ላይ ጥፋትን አድርሰው ነበር፤ አዎን የምድሪቱንም ዋና ዳኛ ገደሉ።

እናም ህዝቡ እርስ በርስ ተከፋፍሎ ነበር፤ እናም እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡና በነገድና በጓደኞቻቸው በጎሳ ተከፋፍሎ ነበር፤ እንደዚህም የምድሪቱን አስተዳደር አጠፉ።

እናም እያንዳንዱ ጎሳ አለቃ ወይንም መሪ በራሱ ላይ ሾመ፤ እናም እነርሱ ጎሳዎችና የጎሳ መሪዎች ሆኑ።

እንግዲህ እነሆ፣ ብዙ ቤተሰብ እናም ነገድና ጓደኞች ያልነበሩት ማንም ሰው አልነበረም፤ ስለዚህ ጎሳዎቹም እጅግ ታላቅ ሆኑ።

እንግዲህ ይህ ሁሉ ተደረገ፤ እናም እስካሁን በመካከላቸው ጦርነት አልነበረም፤ እናም ለሰይጣን ኃይል እራሳቸውን የሰጡ ስለነበር ይህ ሁሉ ክፋት በህዝቡ ላይ መጥቷል።

እናም ነቢያቱን በገደሉት ጓደኛችና፣ ነገዶች ሚስጢራዊ ሴራዎች የተነሳ የመንግስት ደንቦች ጠፍተው ነበር።

እናም ይበልጥ ፃድቃን የነበሩት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ኃጢአተኞች እስከሚሆኑ ድረስ በምድሪቱ ታላቅ ፀብ እንዲሆን አደረጉ፣ አዎን፣ በመካከላቸው ጥቂት ፃድቃኖች ብቻ ነበሩ።

እናም አብዛኞቹም ሰዎች ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣ ደግሞም የታጠበች እሪያ በጭቃ ለመንከባለል እንደምትሄድ በድጋሚ ከፅድቅ ወደ ክፋት ሲዞሩ ስድስተኛው ዓመት አላለፈም ነበር።

እንግዲህ በህዝቡ ላይ ታላቅ ክፋትን ያመጣው ይህ ሚስጥራዊው ሴራ እራሳቸውን በአንድነት ሰበሰቡ፣ እናም ከበላያቸው ያዕቆብ ብለው የሚጠሩትን ሰው አስቀመጡ፤

እናም እርሱን ንጉሳችን ብለው ጠሩት፤ ስለዚህ እርሱም በክፉዎቹ ቡድን ላይ ንጉስ ሆነ፤ እናም እርሱ ስለ ኢየሱስ በመሰከሩት ነቢያት ላይ ድምፅ ከሰጡት ዋና የነበር ነው።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ እያንዳንዱ ህግጋቱን መሪዎቻቸው ከማቋቋሙ በስተቀር በአንድነት እንደተሰበሰቡት የጎሳ ሰዎች አይነት በቁጥር በርካታ አልነበሩም፤ ይሁን እንጂ እርስ በርስ ጠላቶች ነበሩ፤ ምንም እንኳን እነርሱ ፃድቃን ያልነበሩ ቢሆኑም አስተዳደሩን ለማጥፋት ወደ ቃል ኪዳኑ ከገቡት ጋር በጥላቻ አንድ ሆነው ነበር።

፲፪ ስለዚህ ያዕቆብ ጠላቶቻቸው ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ መሆናቸውን በመመልከቱ፤ የቡድኑ ንጉስ በመሆኑ፤ ህዝቡን በምድሪቱ በስተሰሜን ጫፍ በኩል እንዲሸሹና፣ ከተቃዋሚዎቹም ጋር እስከሚገናኙ ድረስ ለራሳቸው መንግስት እንዲያቋቁሙ (ብዙ ተቃዋሚዎችም እንዲኖሩ እነርሱን ሸንግሎአቸዋልና) እናም ከጎሳ ህዝብ ጋር ለመጣላት በተገቢው ሁኔታ እንዲጠናከሩ ህዝቡን አዘዘ፤ እናም ይህንንም አደረጉ።

፲፫ እናም ህዝቡን እስከሚያልፉ ድረስ እንዳይታገዱ ጉዞአቸው እጅግ ፈጣን ነበር። እናም ሠላሳኛው ዓመት እንዲህ ተፈፀመ፤ እናም የኔፊ ህዝብ ጉዳይም ይህ ነበር።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ በሠላሳ አንደኛው ዓመት እያንዳንዱ ሰው በቤተሰቡ፤ በነገድና በየጓደኞቹ በጎሳው ተከፋፍሎ ነበር፤ ይሁን እንጂ እርስ በርስ እንዳይዋጉ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፤ ነገር ግን አለቆቻቸው እናም መሪዎቻቸው በነበሩት አስተሳሰብ ስለሚመሩ በህግጋት እንዲሁም በመንግስታቸው አንድ አልሆኑም ነበር። ነገር ግን አንደኛው ጎሳ ሌላኛውን እንዳይተላለፍ ጥብቅ ህጎችን አወጡ፤ በዚህም የተነሳ በተወሰነ ደረጃ በምድሪቱ ላይ ሰላም ሆነ፤ ይሁን እንጂ ልባቸው ከጌታ ከአምላካቸው ተመልሶ ነበር፣ እናም ነቢያቶችን በድንጋይ ወግረዋልና ከመካከላቸውም አውጥተው ጥለዋቸዋል።

፲፭ እናም እንዲህ ሆነ ኔፊ—በመላዕክቶችና ደግሞ በጌታ ድምፅ በመጎብኘቱ፤ ስለዚህ መላእክቶችንም በማየቱ፣ እናም የዐይን ምስክር በመሆኑና፣ ስለክርስቶስ አገልግሎት በተመለከተ ያውቅ ዘንድ ሀይል ስለተሰጠው፣ እናም ደግሞ ከፅድቅ ሥራቸው ወደ ክፋትና እርኩሰታቸው በፍጥነት ስለመመለሳቸው የዐይን ምስክር በመሆኑ፤

፲፮ ስለዚህ በልባቸው ጠጣርነት እናም በአዕምሮአቸው መታወር በማዘኑ—በዚያው ዓመት ወደእነርሱ ሄደ፣ እናም በድፍረት ስለንስሃ እንዲሁም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ለኃጢያት ስርየት እንደሚገኝ መመስከር ጀመረ።

፲፯ እናም ብዙ ነገሮችን ሰበከላቸውና፣ ሁሉም ነገሮች ሊፃፉ አልቻሉም፣ እናም ግማሹን እንኳን ብቁ አይሆኑም፤ ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ አልተፃፉም። እናም ኔፊ በሃይል እንዲሁም በታላቅ ሥልጣን አገለገለ።

፲፰ እናም እንዲህ ሆነ ከእነርሱ የበለጠ ስልጣን ስለነበረው በእርሱ ተቆጥተው ነበር፤ የእርሱን ቃል ላለማመን አስቸጋሪ ይሆንባቸዋልና፣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እምነቱ ታላቅ ስለነበር መላእክት በየቀኑ ያገለግሉት ነበርና።

፲፱ እናም በኢየሱስ ስም ዲያብሎስን እንዲሁም እርኩስ መንፈስን አስወጥቷል፤ እናም በህዝቡ በድንጋይ ከተወገረና በሞት እንዲሰቃይ ከተደረገ በኋላ ወንድሙንም እንኳን ከሞት አስነስቷል።

እነም ህዝቡ ይህን ተመለከቱ፣ እናም ስለዚህም መስክረዋልና፣ በኃይሉም ምክንያት ተቆጥተው ነበር፤ እናም ደግሞ በኢየሱስ ስም በህዝቡ ፊትም ብዙ ተአምራትን አድርጓል።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ ሠላሳ አንደኛው ዓመት አለፈ፣ እናም ወደ ጌታ የተለወጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ነበሩ፤ ነገር ግን ብዙዎች በሚያምኑበት በኢየሱስ ክርስቶስ በነበረው የእግዚአብሔር ኃይልና መንፈስ እንዲሁም ሥልጣን እንደተጎበኙ በእውነት ለህዝቡ አስታውቀዋል።

፳፪ እናም ዲያብሎሶች ከውስጣቸው የወጣላቸውና፣ ከህመማቸውና፣ ከደዌም የዳኑ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ደርሶ በላያቸው ላይ እንደሰራና እንደተፈወሱ ለህዝቡ በእውነት ገልጸዋል፤ እናም ደግሞ ምልክቶችን አሳዩና፣ በህዝቡ መካከል ጥቂት ታምራቶችን ሰሩ።

፳፫ እንደዚህም ሠላሳ ሁለተኛውም ዓመት አለፈ። እናም በሠላሳ ሦስተኛው ዓመት መጀመሪያ ኔፊ ወደ ህዝቡ ጮኸ፤ እናም ንሰሃንና የኃጢያት ስርየትን ሰበከላቸው።

፳፬ እንግዲህ ወደ ንሰሃ ከመጡት በውሃ ያልተጠመቀ አንድም እንደሌለ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።

፳፭ ስለዚህ ንስሀ እንደገቡ እና ለኃጥያታቸው ስርየት እንዳገኙ በእግዚአብሔር እና በህዝብ ፊት ምስክር እንዲሆን ወደእነርሱ የሚመጡትን እንደዚህ አይነት ሰዎችም በእነርሱ በውሀ እንዲጠመቁ ዘንድ፣ ለዚህም አገልግሎት ሰዎች በኔፊ ተሹመው ነበር።

፳፮ እናም በዚህ ዓመት መጀመሪያ ለንስሃ የተጠመቁ ብዙዎች ነበሩ፤ እናም የዓመቱ አብዛኛው ክፍል አለፈ።