መፅሐፈ አልማ የአልማ ልጅ

አልማ 

የአልማ ልጅ፣ በኔፊ ህዝብ ላይ የመጀመሪያውና ዋናው ዳኛ፣ እናም ደግሞ የቤተክርስቲያኗ ሊቀ ካህን የሆነው፣ የአልማ ታሪክ። የመሣፍንት የንግስ፣ እናም በህዝቡ መካከል የነበረው የጦርነትና ፀብ ታሪክ። እናም ደግሞ የመጀመሪያውና ዋናው ዳኛ በሆነው በአልማ መዝገብ መሰረት በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል የነበረው የጦርነት ታሪክ።
ምዕራፍ ፩

ኔሆር ሀሰተኛ ትምህርት አስተማረ፣ ቤተክርስቲያንን አቋቋመ፣ የካህን ተንኮልን ጀመረ፣ እናም ጌዴዎንን ገደለው—ኔሆር የተሰቀለው በወንጀሉ ነው—የካህን ተንኮልና ስደት በህዝቡ መካከል ተስፋፋ—ካህናት ራሳቸውን በራሳቸው ይረዳሉ፣ ህዝቡ ለድሆች እንክብካቤ አደረጉ፣ እናም ቤተክርስቲያኗ በለፀገች። ከ፺፩–፹፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

አምሊኪ ንጉስ ለመሆን ፈለገ እናም በህዝቡ ድምፅ ተቀባይነት አላገኘም—ተከታዮቹ ንጉስ አደረጉት—አምሊኪውያን ከኔፋውያን ጋር ተዋጉ እናም ተሸነፉ—ላማናውያንና አምሊኪውያን ኃይላቸውን በአንድ ላይ አደረጉ፣ እናም ተሸነፉ—አልማ አምሊኪን ገደለው። ከ፹፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

አምሊኪውያን እንደ ትንቢቱ ቃል እራሳቸው ላይ ምልክት አደረጉ—ላማናውያን በአመፃቸው ተረገሙ—ሰዎች እርግማናቸውን በላያቸው ላይ ያመጣሉ—ኔፋውያን ሌሎች የላማናውያንን ሠራዊት አሸነፉ። ከ፹፯–፹፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

አልማ በሺህዎች የሚቆጠሩ የተለወጡትን አጠመቀ—ክፋት በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ገባ፣ እናም የቤተክርስቲያኗ እድገት ተገታ—ኔፊያሀ ዋና ዳኛ ሆኖ ተሾመ—አልማ ሊቀ ካህን በመሆኑ ራሱን ለአገልግሎት ሰጠ። ከ፹፮–፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት መሰረት ሊቀ ካህኑ የነበረው አልማ ለህዝቡ በከተማቸውና በምድሪቱ ባሉት መንደሮች በሙሉ የተናገረው ቃል።

ከምዕራፍ ፭ ጀምሮ።

ምዕራፍ ፭

ደህንነት ለማግኘት ሰዎች ንስሀ መግባትና ትዕዛዛቱን መጠበቅ፣ ዳግም መወለድ፣ በክርስቶስ ደም ልብሳቸውን ማፅዳት፣ ትሁት መሆንና፣ ከኩራትና ከምቀኝነት እራሳቸውን ማስወገድ እናም የፅድቅን ስራ መስራት አለባቸው—መልካሙ እረኛ ህዝቡን ይጠራል—ክፉ ስራ የሚሰሩ የዲያብሎስ ልጆች ናቸው—አልማ የትምህርቱን እውነተኛነት መሰከረ፣ እናም ሰዎች ንስሀ እንዲገቡ አዘዘ—የፃድቃኖች ስም በህይወት መዝገብ ይፃፋል። በ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

በዛራሄምላ ያለው ቤተክርስቲያን ከኃጢያት ጠርቷል እናም ተደራጅቷል—አልማ ለመስበክ ወደ ጌዴዎን ሄደ። ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

እንደራሱ መዝገብ መሰረት፣ በጌዴዎን ከተማ አልማ ለህዝቡ የተናገረው ቃላት።

ምዕራፍ ፯ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፯

ክርስቶስ ከማርያም ይወለዳል—የሞትን እስራት ይፈታል፣ እናም የሕዝቡን ኃጢያት ይሸከማል—ንስሐ የሚገቡ፣ የሚጠመቁ፣ እናም ትዕዛዛቱን የሚጠብቁ ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል—ርኩሰት የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አይቻለውም—ትህትና፣ እምነት፣ ተስፋና ልግስና አስፈላጊ ናቸው። በ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

አልማ በሜሌቅ አስተማረ፣ እናም አጠመቀ—በአሞኒሀ ተቀባይነትን አላገኘም እናም ወጥቶ ሄደ—መልአኩ እንዲመለስና ለህዝቡም ስለ ንስሃ እንዲጮህ አዘዘው—በአሙሌቅ ተቀባይነትን አገኘ፣ እናም ሁለቱ በአሞኒሃ ሰበኩ። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

በአሞኒሀ ምድር ለነበሩት ሰዎች በአልማ፣ ደግሞም በአሙሌቅ የታወጁት ቃላት። እናም በአልማ ዘገባ መሰረት፣ እነርሱ በወህኒ ቤት ተጣሉ፣ እናም በውስጣቸው ባለው ታምራታዊ የእግዚአብሔር ኃይልም ተለቀቁ።

ከምዕራፍ ፱ እስከ ፲፬ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፱

አልማ የአሞኒሀ ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ አዘዘ—ጌታ በመጨረሻው ቀን ለላማናውያን መሀሪ ይሆናል—ኔፋውያን ብርሃኑን ከተዉ፣ በላማናውያን ይጠፋሉ—የእግዚአብሔር ልጅ በቅርቡ ይመጣል—ንስሃ የገቡትን፣ የተጠመቁትንና፣ በስሙም ካመኑት ያድናቸዋል። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

ሌሂ ከምናሴ የዘር ሐረግ ነው—አሙሌቅ ለአልማ የሆነውን መለኮታዊ ትዕዛዝ አወሳ—የፃድቃኖች ፀሎት ህዝቡ እንዲድኑ ያደርጋል—ፃድቅ ያልሆኑት ጠበቆች እና ዳኞች ለህዝቡ ጥፋት መሰረትን ይጥላሉ። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፩

የኔፋውያን የገንዘብ አያያዝ ተገለፀ—አሙሌቅ ከዚኤዝሮም ጋር ተጣላ—ክርስቶስ ሰዎችን ከነኃጢአታቸው አያድናቸውም—መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት ብቻ ይድናሉ—ሰዎች ሁሉ በህያውነት ይነሳሉ—ከትንሳኤ በኋላ ሞት የለም። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፪

አልማ ከዚኤዝሮም ጋር ተነጋገረ—የእግዚአብሔር ሚስጥር ሊሰጥ የሚችለው ለሚታመኑበት ብቻ ነው—ሰዎች በሀሳባቸው፣ በእምነታቸው፣ በቃላቸውና በስራቸው ይፈረድባቸዋል—ኃጢአተኞች በመንፈሳዊ ሞት ይሰቃያሉ—ይህ ሞት ያለበት ህይወት የሙከራ ጊዜ ነው—የቤዛነት ዕቅድ ትንሳኤን እናም በእምነት የኃጢያትን ስርየት ያመጣል—ንስሃ የሚገቡ በአንድያ ልጅ አማካኝነት ምህረትን የመቀበል መብት አላቸው። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፫

ሰዎች በታላቁ እምነታቸውና በመልካም ስራዎቻቸው ሊቀ ካህን ተብለው ይጠራሉ—ትዕዛዛቱን ያስተምሩ—በፅድቅ ይቀደሳሉ እናም ወደጌታ እረፍት ይገባሉ—መልከ ጼዴቅ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነበር—መላዕክት የምስራች ወሬውን በምድሪቱ ያውጃሉ—የክርስቶስን በእርግጥ መምጣቱን ያውጃሉ። በ፹፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፬

አልማና አሙሌቅ ታሰሩ እናም ተመቱ—የሚያምኑትና ቅዱሳን መፃሕፍቶቻቸው በእሳት ተቃጠሉ—እነዚህ ሰማዕታት በጌታ በክብር ተወሰዱ—የወህኒ ቤቱ ግድግዳ ተሰነጣጠቀ እናም ወደቀ—አልማና አሙሌቅ ተለቀቁ እናም ያሰቃዩአቸው ተገደሉ። ከ፹፪–፹፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፭

አልማና አሙሌቅ ወደ ሲዶም ሄዱ እናም ቤተክርስቲያንን አቋቋሙ—አልማ በቤተክርስቲያኗ አባል የሆነውን ዚኤዝሮምን ፈወሰው—ብዙዎች ተጠመቁ፣ እናም ቤተክርስቲያኗ በለፀገች—አልማና አሙሌቅ ወደ ዛራሔምላ ሄዱ። በ፹፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፮

ላማናውያን የአሞኒሀን ህዝብ አጠፉ—ዞራም ኔፋውያን ላማናውያንን ድል እንዲያደርጉ መራቸው—አልማና አሙሌቅ እናም ሌሎች ብዙዎች ቃልን ሰበኩ—ከትንሣኤው በኋላም ክርስቶስ ለኔፋውያን እንደሚገለፅ አስተማሩአቸው። ከ፹፩–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ለእግዚአብሔር ቃል በመንግስቱ የነበራቸውን መብት የናቁት፣ እናም ላማናውያንን ለመስበክ ወደኔፊ ምድር የሄዱት የሞዛያ ልጆች፣ የስቃያቸውና የመዳናቸው ታሪክ—አልማ እንደመዘገበው።

ምዕራፍ ፲፯ እስከ ፳፯ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፲፯

የሞዛያ ልጆች የትንቢትና የራዕይ መንፈስ አላቸው—ቃሉን ለላማናውያን ለማወጅ ወደ ተለያዩ መንገዶች ተጓዙ—አሞን ወደ እስማኤል ምድር ተጓዘ፣ እናም የንጉስ ላሞኒ አገልጋይ ሆነ—አሞን የንጉሱን መንጋዎች አዳነ፣ እናም ጠላቶቹን በሴቡስ ወንዝ ገደለ። ከቁጥር ፩–፫፣ በ፸፯ ም.ዓ. ገደማ፣ ቁጥር ፬፣ ከ፺፩–፸፯ ም.ዓ. ገደማ፤ እናም ከቁጥር ፭–፴፱፣ በ፺፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፰

ንጉስ ላሞኒ አሞን ታላቁ መንፈስ እንደሆነ ገመተ—አሞን ንጉሱን ስለፍጥረት፣ እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር ስላለው አድራጎትና፣ በክርስቶስ ስለሚመጣው ቤዛነት አስተማረው—ላሞኒ አመነ፣ እናም በምድሪቱ ላይ የሞተ በመምሰል ወደቀ። በ፺ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፱

ላሞኒ የዘለዓለማዊውን ህይወት ብርሃን አገኘ፣ እናም አዳኙን ተመለከተ—ቤተሰዎቹም ተመሰጡ፣ እናም ብዙዎች መላዕክትን ተመለከቱ—አሞን ተአምራት ሁኔታ ተጠበቀ—ብዙዎችን አጠመቀ፣ እናም በመካከላቸው ቤተክርስቲያኗን አቋቋመ። በ፺ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳

ጌታ አሞንን የታሰሩትን ወንድሞቹን ከእስር እንዲያስለቅቅ ወደ ሚዶኒ ላከው—አሞንና ላሞኒ በምድሪቱ ላይ ንጉስ የሆነውን የላሞኒን አባት አገኙት—አሞን አዛውንቱን ንጉስ የወንድሞቹን መለቀቅ እንዲያፀድቅለት አስገደደው። በ፺ ም.ዓ. ገደማ።

አሮንና፣ ሙሎቄ፣ እና ወንድሞቻቸው ለላማናውያን የሰበኩበት ታሪክ።

ከምዕራፍ ፳፩ እስከ ፳፮ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፳፩

አሮን አማሌቂውያንን ስለክርስቶስና ስለኃጢያት ክፍያው አስተማረ—አሮንና ወንድሞቹ በሚዶኒ ታሰሩ—ከዳኑ በኋላ፣ በምኩራቦች አስተማሩ፣ እናም ብዙዎችን ለወጡ—ላሞኒ በእስማኤል ምድር ለሚኖሩ ህዝቦች የኃይማኖት ነፃነትን ሰጣቸው። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፪

አሮን ስለፍጥረት፣ ስለአዳም መውደቅ፣ በክርስቶስም ስላለው የቤዛነት ዕቅድ የላሞኒን አባት አስተማረ—ንጉሱ እና ቤተሰቦቹ በሙሉ ተለወጡ—በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል የመሬት ክፍፍሉ ተገልጿል። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፫

የኃይማኖት ነፃነት ታወጀ—በሰባት ምድሮች እና ከተሞች ያሉ ላማናውያን ተለወጡ—እራሳቸውንም አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች- ሌሂ ብለው ጠሩ፣ እናም ከእርግማኑ ነፃ ወጥተዋል—አማሌቂውያንና አሙሎናውያን እውነትን አልተቀበሉም። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፬

ላማናውያን የእግዚአብሔር በሆኑት ሰዎች ላይ መጡ—አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች በክርስቶስ ተደሰቱ፣ እናም በመልአክት ተጎበኙ—እራሳቸውን ከመከላከል ይልቅ በሞት መሰቃየትን መረጡ—በርካታ ላማናውያን ተለወጡ። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፭

የላማናውያን ወረራ ተስፋፋ—አቢናዲ እንደተነበየው የኖህ ካህናት ዝርያዎች ጠፉ—ብዙ ላማናውያን ተለወጡ፣ እናም ከአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ሰዎችን ጋር ተቀላቀሉ—በክርስቶስ አመኑ እናም የሙሴን ህግ ጠበቁ። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፮

አሞን በጌታ ተመካ—ታማኞች በጌታ ይጠነክራሉ፣ እናም እውቀት ይሰጣቸዋል—ሰዎች በእምነት ሺህ ነፍሳትን ወደንስሃ ያመጣሉ—እግዚአብሔር ሁሉም ዓይነት ስልጣን አለው እናም ሁሉንም ያውቃል። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፯

ጌታ አሞንን የአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ሰዎች በደህንነት ወደሚቀመጡበት ቦታ እንዲመራቸው አዘዘው—አልማን ባገኘው ጊዜ የአሞን ደስታ አቅም አሳጣው—ኔፋውያን ለአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች የኢየርሾንን ምድር ሰጡአቸው—እነርሱም የአሞን ህዝብ ተብለው ተጠሩ። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፰

ላማናውያን በአስገራሚው ውጊያ ተሸነፉ—በሺዎች የሚቆጠሩ ሞቱ—ኃጢአተኞች ማብቂያ ለሌለው መከራ ይሰጣሉ፤ ፃድቃኖች ማብቂያ የሌለውን ደስታ ያገኛሉ። ከ፸፯–፸፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፱

አልማ በመለኮታዊ ቅንዓት ንስሃን ለመጮህ ፈለገ—ጌታ ለሁሉም ሀገር አስተማሪዎችን ሰጠ—አልማ በጌታ ስራ፣ እናም በአሞንና በወንድሞቹ ስኬታማነት ተደሰተ። በ፸፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴

ፀረ ክርስቶስ የሆነው ቆሪሆር፣ በክርስቶስ፣ በኃጢያት ክፍያው እና በትንቢት መንፈስ ተሳለቀ—እግዚአብሔር እንደሌለ፣ የሰው ልጅ መውደቅ እንደሌለ፣ ለኃጢያትም ቅጣት እንደሌለና፣ ክርስቶስ እንደሌለ አስተማረ—አልማ ክርስቶስ እንደሚመጣና ሁሉም ነገር እግዚአብሔር መኖሩን እንደሚያመለክት መሰከረ—ቆሪሆር ምልክትን ፈለገና ዲዳ ሆነ—ዲያብሎስ ለቆሪሆር እንደመልአክ ታይቶት እናም ምን ማለት እንዳለበት አስተምሮት ነበር—ቆሪሆር ተረገጠ፣ እናም ሞተ። ከ፸፮–፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፩

አልማ ኃይማኖታቸውን የካዱትን ዞራማውያን ለመመለስ ተልዕኮውን መራ—ዞራማውያን ክርስቶስን ካዱ፤ በውሸት የምርጫ ሀሳብ አመኑ፣ እናም በተወሰነ ፀሎት አመለኩ—አገልጋዮች በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ—ስቃያቸው በክርስቶስ ደስታ ተውጠዋል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፪

አልማ ስቃያቸው ትሁት ያደረጋቸውን ድሆች አስተማረ—እምነት በዚያ በማይታየው እውነት በሆነው የሚደረግ ተስፋ ነው—አልማ መላዕክት ለወንዶች፣ ለሴቶች፣ እና ለልጆች እንደሚያገለግሉ መሰከረ—አልማ ቃሉን ከዘር ጋር አነፃፀረ—ይህም መተከልና እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባዋል—ከእዚያም የዘለዓለም ህይወት የሆነው ፍሬ ወደሚሰበሰብበት ያድጋል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፫

ዜኖስ ሰዎች በሁሉም ስፍራ መፀለይ፣ እና ማምለክ እንዳለባቸው፣ እናም ፍርድም በወልድ አማካኝነት እንደሚለውጥ አስተማረ—ዜኖቅ በወልድ አማካኝነት ምህረት እንደሚሰጥ አስተማረ—ሙሴ በምድረበዳው የእግዚአብሔርን ልጅ ምሣሌ የሆነውን አንስቷል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፬

አሙሌቅ ቃሉ ለቤዛነታቸው በክርስቶስ ውስጥ መሆኑን መሰከረ—የኃጢያት ክፍያው ካልተደረገ፣ የሰው ዘር ሁሉ መጥፋት ነበረበት—የሙሴ ህጎች በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ልጅ መስዋዕትነት ይጠቁማሉ—ዘለዓለማዊው የደህንነት ዕቅድ የተመሰረተው በእምነት እና በንስሃ ላይ ነው—ለጊዜያዊውና ለመንፈሳዊው በረከት ፀልዩ—ይህ ህይወት ሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የሚዘጋጁበት ወቅት ነው—በእግዚአብሔር ፊት በፍርሀት የ ራሳችሁን ደህንነት አከናውኑ። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፭

የቃሉ መሰበክ የዞራማውያንን ተንኮል ያጠፋል—ወደጌታ የተለወጡትን አስወጡአቸው፣ እነርሱም በኢየርሾን ከአሞንን ሰዎች ጋር ተቀላቀሉ—አልማ በህዝቡ ክፋት አዘነ። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

የአልማ ለልጁ ለሔለማን የሰጠው ትዕዛዛት

ምዕራፍ ፴፮ እስከ ፴፯ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፴፮

አልማ ለሔለማን መላዕክቱን ከተመለከተ በኋላ ስለመለወጡ መሰከረ—ለተኮነነ ነፍስ ስቃይን ተሰቃየ፤ የኢየሱስን ስም ጠራ፣ እናም ከእግዚአብሔር ተወለደ—ጣፋጩ ደስታ ነፍሱን ሞላው—እግዚአብሔርን የሚያወድሱ ብዛት ያላቸው መላዕክትን ተመለከተ—ብዙ የተለወጡ ቀምሰውታል እናም እርሱ እንደተመለከተው መንፈሳዊውን ነገር ተመልክተውታል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፴፯

የነሐስ ሰሌዳዎች እናም ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ነፍሳትን ወደ ደህንነት ለማምጣት ተጠበቁ—ያሬዳውያን በክፋታቸው የተነሳ ጠፉ—ሚስጥራዊው መሐላቸው እና ቃል ኪዳናቸው ከህዝቡ መጠበቅ አለበት—በስራችሁም ሁሉ ከጌታ ጋር ተማከሩ—ሊያሆና ኔፋውያንን እንደመራቸው የክርስቶስ ቃልም ሰዎችን ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት ይመራቸዋል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

አልማ ለልጁ ለሺብሎን የሰጠው ትዕዛዛት

ምዕራፍ ፴፰ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፴፰

ሺብሎን ለፅድቅነት ምክንያት ስደት ደረሰበት—ደህንነት የዓለም ህይወትና ብርሃን በሆነው በክርስቶስ ነው—ስሜቶቻችሁን በሙሉ ተቆጣጠሩ። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

አልማ ለልጁ ቆሪያንቶን የሰጠው ትዕዛዛት።

ከምዕራፍ ፴፱ እስከ ፵፪ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፴፱

የፍትህወት ኃጢያት እርኩሰት ነው—የቆሪያንቶን ኃጢያት ዞራማውያንን ቃሉን ከመቀበል አገዳቸው—የክርስቶስ ቤዛነት በፊት የነበሩትን ታማኞች ለማዳን ወደኋላ ተመልሶ የሚሠራ ነው። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵

ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ ትንሣኤ እንዲሆን አደረገ—ፃድቃን ሆነው የሞቱት ወደገነት ይሄዳሉ፣ እናም ኃጢአተኛ ሆነው የሞቱት እስከትንሳኤው ቀን ለመጠበቅ ወደ ድቅድቅ ጨለማ ይሄዳሉ—በትንሣኤ ሁሉም ነገር ወደ ተገቢው እናም ፍፁም ወደሆነው ቅርፅ ይመለሳል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፩

በትንሣኤ ሰዎች መጨረሻ ለሌለው ደስታ ወይንም መጨረሻ ለሌለው ስቃይ ይመጣሉ—ኃጢያት በጭራሽ ደስታ ሆኖ አያውቅም—ስጋ ለባሽ ሰዎች በዓለም ሳሉ ከእግዚአብሔር ጋር አይደሉም—ማንኛውም ሰው በትንሣኤው ወቅት፣ ሟች በነበረበት ጊዜ ያገኘውን ባህሪና ፀባይ እንደገና ይቀበላል። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፪

ሟችነት ሰዎችን ንስሃ እንዲገቡ እናም እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ የሚያስችል የሙከራ ጊዜ ነው—የአዳም መውደቅ በሰው ዘር ሁሉ ላይ ጊዜያዊ እናም መንፈሳዊ ሞትን አመጣ—ቤዛነት በንስሃ አማካይነት ይመጣል—እግዚአብሔር እራሱ ለዓለም ኃጢያት ክፍያን ይከፍላል—ንሰሃ የሚገቡ ምህረትን ያገኛሉ—ሌሎች በሙሉ በእግዚአብሔር ፍትህ ስር ናቸው—ምህረት በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት ይመጣል—እውነተኛ ንስሃ ገቢዎች ብቻ ይድናሉ። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፫

አልማ እና ልጆቹ ቃሉን ሰበኩ—ዞራማውያን እና ሌሎች ተቃዋሚ ኔፋውያን ላማናውያን ሆኑ—ላማናውያን በኔፋዉያን ላይ ለጦርነት መጡባቸው—ሞሮኒ ኔፋውያንን በሚከላከል ጥሩር አስታጠቃቸው—ጌታ ለአልማ የላማናውያንን የጦር ስልት አሳየው—ኔፋውያን፣ ቤቶቻቸውን፣ ነፃነታቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ኃይማኖታቸውን ተከላከሉ—የሞሮኒ እና የሌሂ ሠራዊት ላማናውያንን ከበቡአቸው። በ፸፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፬

ሞሮኒ ላማናውያን ከኔፋውያን ጋር ሰላም እንዲፈጥሩ አለበለዚያም እንዲጠፉ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አዘዘ—ዛራሄምናህ የቀረበውን ሀሳብ ተቃወመ፣ እናም ጦርነቱም ቀጠለ—የሞሮኒ ወታደሮች ላማናውያንን አሸነፉ። ከ፸፬–፸፫ ም.ዓ. ገደማ።

ሔለማን በዘመኑ ባስቀመጠው በምዝገባው መሰረት በሔለማን ዘመን የኔፊ ህዝብ የጦርነታቸው እና የፀባቸው ታሪክ።

ከምዕራፍ ፵፭ እስከ ፷፪ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፵፭

ሔለማን የአልማን ቃላት አመነ—አልማ ስለኔፋውያን ጥፋት ተነበየ—እርሱም ምድሪቱን ባርኳታል፣ እናም ረግሟታል—አልማ ምናልባት እንደሙሴ በመንፈስ ተወስዷል—ፀብ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ አደገ። በ፸፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፮

አማሊቅያ ንጉስ ለመሆን አሴረ—ሞሮኒ የነፃነት አርማን አነሳ—ሕዝቡንም እምነታቸውን እንዲከላከሉ አነሳሳቸው—እውነተኛ አማኞች ክርስቲያኖች ተብለው ተጠሩ—የዮሴፍ ቅሪቶች ይጠበቃሉ—አማሊቅያ እና የተገነጠሉት ወደ ኔፊ ምድር ሸሹ—የነፃነትን ጉዳይ የማይደግፉ እንዲሞቱ ተደረገ። ከ፸፫–፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፯

አማሊቅያ የላማናውያን ንጉስ ለመሆን ክህደትን፣ ግድያን፣ እናም ሴራን ተጠቀመ—ከኔፋውያን የተገነጠሉት ከላማናውያን የበለጡ ክፉዎች እና አስፈሪዎች ናቸው። በ፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፰

አማሊቅያ ላማናውያንን በኔፋውያን ላይ አነሳሳ—ሞሮኒ የክርስቲያን ጉዳዮችን እንዲከላከሉ ህዝቡን አዘጋጀ—እርሱም በመብትና በነፃነት ተደሰተ እናም የእግዚአብሔር ኃያል ሰው ነው። በ፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፵፱

ወራሪ ላማናውያን የአሞኒሀንና የኖህን የምሽግ ከተማዎች ለመያዝ አልቻሉም—አማሊቅያ እግዚአብሔርን ረገመ፣ እናም የሞሮኒን ደም ለመጠጣት ማለ—ሔለማንና ወንድሞቹ ቤተክርስቲያኗን ማጠናከር ቀጠሉ። በ፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶

ሞሮኒ ለኔፋውያን ምድር ምሽግ አደረገ—ኔፋውያን ብዙ አዳዲስ ከተሞችን ሰሩ—በኔፋውያን ላይ በክፋታቸውና በእርኩሰታቸው ዘመን ጦርነትና ጥፋት አረፈባቸው—ሞሪያንተንና ተቃዋሚዎቹ በቴአንኩም ተሸነፉ—ኔፋአያህ ሞተ፣ እናም ልጁ ፓሆራን የፍርድ ወንበሩን ያዘ። ከ፸፪–፷፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፩

የንጉሱ የሆኑትን ሰዎች ህጉን ለመለወጥ እናም ንጉሥን ለመምረጥ ፈለጉ—ፓሆራን እናም የነበረውን መንግስት የሚደግፉት በህዝቡ ድምፅ ተደግፈው ነበር—ሞሮኒ የንጉሱ የሆኑትን ሰዎች ሀገራቸውን እንዲከላከሉ አለበለዚያም እንዲገደሉ አስገደዳቸው—አማሊቅያ እናም ላማናውያን ብዙ የተመሸጉ ከተማዎችን ያዙ—ቴአንኩም የላማናውያንን ወረራ መለሰ እናም አማሊቅያን በድንኳኑ ውስጥ ገደለው። ከ፷፯–፷፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፪

አሞሮን የላማናውያን ንጉስ በመሆን አማሊቅያን ተካው—ሞሮኒ፣ ቴአንኩም፣ እናም ሌሂ ከላማናውያን ጋር ባደረጉት ጦርነት ኔፋውያንን በድል አድራጊነት መሩአቸው—የሙሌቅ ከተማ በድጋሚ ተወሰደች፣ እናም ዞራማዊው ያዕቆብ ተገደለ። ከ፷፮–፷፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፫

የላማናውያን እስረኞች የለጋስን ምድር እንዲመሽጓት ጥቅም ላይ ውለዋል—በኔፋውያን መካከል የነበረው አለመስማማት ላማናውያን እንዲያሸንፉ አደረገ—ሔለማን በሁለት ሺህ የአሞን ህዝብ ብላቴና ወንዶች ላይ ባለስልጣል ሆነ። ከ፷፬–፷፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፬

አሞሮን እና ሞሮኒ እስረኞቻቸውን ለመለዋወጥ ተደራደሩ—ላማናውያን እንዲወጡ እናም የሞት ጥቃታቸውን እንዲያቆሙ ሞሮኒ ጠየቀ—አሞሮን ኔፋውያን የጦር መሳሪያቸውን እንዲጥሉ፣ እናም በላማናውያን ስር እንዲሆኑ ጠየቀ። በ፷፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፭

ሞሮኒ እስረኞች መለዋወጥን ተቃወመ—የላማናውያን ጠባቂዎች በስካር ተጠመዱ፣ እናም ኔፋውያን እስረኞች ተለቀቁ—የጊድ ከተማም ያለደም መፋሰስ ተወሰደች። ከ፷፫–፷፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፮

ሔለማን ከላማናውያን ጋር የነበረውን ጦርነት ሁኔታ በመዘርዘር ለሞሮኒ ደብዳቤ ላከለት—አንቲጱስ እና ሔለማን በላማናውያን ላይ ታላቅ ድል አገኙ—የሔለማን ሁለት ሺህ ብላቴና ወንድ ልጆቹ በአስደናቂ ኃይል ተዋጉ፣ እናም ማናቸውም አልተገደሉም ነበር። ቁጥር ፩ በ፷፪ ም.ዓ. ገደማ፣ ከቁጥር ፪–፲፱ በ፷፮ ም.ዓ. ገደማ፤ እናም ከቁጥር ፳–፶፯ ከ፷፭–፷፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፯

ሔለማን የአንቲፓራን መያዝ፣ እናም የቁሜኒ ከተማን መከበብና፣ መከላከል በተመለከተ በዝርዝር አወራ—ወጣት አሞናውያኑ በጀግንነት ተዋጉ፤ ሁሉም ቆሰሉ፣ ነገር ግን አንድም አልተገደለም—ጊድ የላማናውያን እስረኞችን ሞትና ማምለጥ ሀተታ አቀረበ። በ፷፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፰

ሔለማን፣ ጊድ፣ እና ቴኦምነር የማንቲን ከተማ በዘዴ ወሰዱ—ላማናውያን ወጡ—የአሞን ህዝቦች ወንድ ልጆች ነፃነታቸውን፣ እና እምነታቸውን ለመከላከል ፀንተው በቆሙ ጊዜ ተጠበቁ። ከ፷፫–፷፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፶፱

ሞሮኒ የሔለማንን ወታደሮችን እንዲያጠናክር ፓሆራንን ጠየቀው—ላማናውያን የኔፋውያን ከተማ ያዙ—ሞሮኒ በመንግስቱ ላይ ተናደደ። በ፷፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፷

ሞሮኒ መንግስቱ ሠራዊቱን ችላ ማለቱን በተመለከተ ለፓሆራን ወቀሳ አቀረበ—ጌታ ፃድቃኖች እንዲገደሉ ይፈቅዳል—ኔፋውያን ከጠላቶቻቸው እራሳቸውን ለማስለቀቅ ያላቸውን ኃይል እንዲሁም ዘዴዎች በሙሉ መጠቀም ይኖርባቸዋል—ሞሮኒ ለሠራዊቱ እርዳታ ካልተደረገ ከመንግስት ጋር እንደሚዋጋ አስጠነቀቀ። በ፷፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፷፩

ፓሆራን በመንግስት ላይ ስለሆነው ሁከት፣ እና አመፃ ለሞሮኒ ነገረው—የንጉሱ ሰዎች ዛራሔምላን ያዙ፣ እናም ከላማናውያን ጋር አንድ ቡድን ሆኑ—ፓሆራን በአማፅያኑ ላይ ወታደራዊ እርዳታን ጠየቀ። በ፷፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፷፪

ሞሮኒ ፓሆራንን ለመርዳት ወደ ጌዴዎን ምድር ዘመተ—ሀገራቸውን ለመከላከል የተቃወሙት የንጉስ ሰዎች ተገድለዋል—ፓሆራን እናም ሞሮኒ ኔፋውያንን በድጋሚ ያዙ—ብዙ ላማናውያን ከአሞንን ሰዎች ጋር ተቀላቀሉ—ቴአንኩም አሞሮንን ገደለው እናም ቀጥሎም እራሱ ተገደለ—ላማናውያን ከምድሪቱ ተባረሩ፣ እናም ሰላም ሠፈነ—ሔለማን ወደ አገልግሎቱ ተመለሰ፣ እናም ቤተክርስቲያኗን አሳደገ። ከ፷፪–፶፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፷፫

ሺብሎን እናም በኋላ ሔለማን ቅዱሳን መፃሕፍቶቹን ወሰዱ—በርካታ ኔፋውያን ወደ ሰሜኑ ምድር ተጓዙ—ሐጋዝ በባህሩም በስተምዕራብ በኩል የሔዱትን መርከቦች ሰራ—ሞሮኒሀ ላማናውያንን በውጊያ አሸነፋቸው። ከ፶፮–፶፪ ም.ዓ. ገደማ።