ቅዱሳት መጻህፍት
ኤተር ፱


ምዕራፍ ፱

መንግስቱ ከአንዱ ወደ ሌላኛው በዘር፣ በማጭበርበር እናም በግድያ ተላለፈ—ኤመር የፅድቅነትን ልጅ ተመለከተ—ብዙ ነቢያት ለንሰሃ ጮኹ—ህዝቡም በረሃብና በመርዛማ እባቦች ተሰቃዩ።

እናም እንግዲህ እኔ ሞሮኒ ታሪኬን እቀጥላለሁ። ስለዚህ፣ እነሆ፣ እንዲህ ሆነ በአኪሽ እናም በወዳጆቹ ሚስጥራዊ ሴራዎች ምክንያት፤ እነሆ፣ የኦመርን መንግስት ገለበጡት።

ይሁን እንጂ፤ ጌታ የኦመርንና የእርሱን ጥፋት ለማይፈልጉት፣ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቹ መሃሪ ነበር።

እና ጌታ ኦመር ምድሪቷን ለቆ እንዲወጣ በህልሙ አስጠነቀቀው፤ ስለሆነም ኦመር ከቤተሰቦቹ ጋር ምድሪቱን ለቆ ወጣ፤ እናም ለብዙ ቀናትም ተጓዘ፣ እናም ወደ ሺም ኮረብታ መጥቶ ኔፋውያን በጠፉበት ቦታ ደረሱ፣ እናም ከዚያም ወደምስራቅ ሄደ፤ እናም በባህሩ ዳርቻም አብሎም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ደረሰ እናም በዚያ ስፍራ ድንኳኑን ተከለ፣ ደግሞ ከያሬድና ከቤተሰቦቹ በስተቀር ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ እናም ሁሉም ቤተሰቦቹ ድንኳኖቻቸውን ተከሉ።

እናም እንዲህ ሆነ ያሬድም በክፋት እጅ በህዝቡ ላይ ንጉስ ሆኖ ተቀባ፤ እናም ለአኪሽም ሴት ልጁን ለሚስትነት ሰጠው።

እናም እንዲህ ሆነ አኪሽም አማቱን ለመግደል ፈለገ፤ እናም በጥንት ጊዜ በማሉት መሃላም እነርሱን እርዳታ ጠየቃቸው፣ እናም አማቱ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ህዝቡን እየተነጋገረ እያለ ገድለውት ለእርሱም ራሱን ሰጡት።

ሚስጢራዊው እናም የኃጢአተኞቹ ሕብረት እጅግ በዝቶ ስለነበር፣ የሁሉንም ሕዝብ ልብ አበላሽቶ ነበር፤ ስለዚህ ያሬድ በዙፋኑ ላይ ተገደለ፣ እናም አኪሽ በእርሱ ቦታ ነገሰ።

እናም እንዲህ ሆነ አኪሽም በወንድ ልጁ መቅናት ጀመረ፤ ስለዚህ በወህኒ ቤትም ዘጋው፣ እናም እስከሚሞትም ድረስ ትንሽ ምግብ በመስጠት አቆየው።

እናም እንግዲህ እንዲሞት የተሰቃየው ልጅ ወንድም (ስሙም ኒምራህ ነበር) አባቱ በወንድሙ ላይ ባደረገው ነገር ተቆጣ።

እናም እንዲህ ሆነ ኒምራህ ጥቂት ቁጥር ያላቸውን ሰዎች በአንድነት ሰበሰበ፣ እናም ከምድሪቱ ሸሸ፣ እናም ሄደና ከኦመር ጋር ኖረ።

እናም እንዲህ ሆነ አኪሽም ሌሎች ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እናም በህዝቡም እምነትን አገኙ፤ ይሁን እንጂ እርሱ እንደፈለገው ሁሉንም አይነት ክፋት ለማድረግ ምለውለታል።

፲፩ አሁን አኪሽ ሥልጣን እንደሚፈልግ ሁሉ፣ የአኪሽ ህዝብም ጥቅም ለማግኘት ይፈልጉ ነበር፤ ስለዚህ፣ የአኪሽ ወንዶች ልጆች በገንዘባቸው ብዙ ሰዎች እንዲከተሉአቸው ሳቡአቸው።

፲፪ እናም ለብዙ ዓመታት የቆየ ጦርነትም በአኪሽ ወንድ ልጆች እና በአኪሽ መካከል ተጀመረ፤ አዎን፣ በዚያን መንግስት ስር የነበሩት ሰዎች፤ አዎን ከሰላሳዎቹ ሰዎች እናም ከኦመር ቤት ጋር ከሸሹት ሰዎች በስተቀር ሁሉም ጠፉ።

፲፫ ስለዚህ፣ ኦመር በድጋሚ ወደ ርስት ምድሩ ተመለሰ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ኦመርም አረጀ፤ ይሁን እንጂ፣ በእርጅናው ወቅት ኤመርን ወለደ፤ እናም በእርሱም ምትክ እንዲነግስ ንጉስ እንዲሆን ኤመርን ቀባው።

፲፭ እናም ኤመር ንጉስ እንዲሆን ከቀባው በኋላ ለሁለት ዓመታት ያህል በምድሪቱ ላይ ሠላምን አገኘ፤ እናም በሀዘን የተሞሉ እጅግ ብዙ የሆኖ ቀናትን እየተመለከተ ከኖረ በኋላ ሞተ። እናም እንዲህ ሆነ ኤመርም በእርሱ ቦታ ነገሰ እናም የአባቱንም አርአያ ተከተለ።

፲፮ እናም ጌታ እርግማኑን ከምድሪቱ በድጋሚ ማስወገድ ጀመረ፣ እናም በኤመር አገዛዝም የኤመር ቤት እጅግ በልፅጎ ነበር፤ እናም ለስልሳ ሁለት ዓመታትም እጅግ ሀብታም እስከሚሆኑ ድረስ እጅግ ጠንካሮች ሆነው ነበር፤

፲፯ ከሁሉም ዓይነት ፍራፍሬ፣ እናም እህል፣ እናም ሃር፣ እናም መልካም ናይለን፣ እናም ወርቅ፣ እናም ብር፣ እናም የከበሩ ነገሮች ነበሯቸው፤

፲፰ እናም ደግሞ ሁሉም ዓይነት የቀንድ ከብት፣ በሬዎች እናም ላሞች፣ እናም በግ፣ እናም አሳማ፣ እናም ፍየሎች፣ እናም ደግሞ ለሰዎች ለምግብነት ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ሌሎች እንሰሳት ነበሯቸው።

፲፱ እናም ደግሞ ፈረሶች፣ እናም አህዮች፣ እናም ዝሆኖች፣ እናም ኩረሎም፣ እናም ኮሞም፣ ነበሩአቸው፤ ሁሉም እናም በተለይ ዝሆኖቹ፣ እናም ኩረሎሞቹም እንዲሁም ኩሞሞቹ ለሰዎች ጠቃሚ ነበሩ።

እናም ጌታም በዚህች ከምድር ሁሉ በላይ በተመረጠችው መሬት ላይ በረከቱን እንደዚህ አፍስሶአል፤ እናም እርሱም ይህችን ምድር የያዘ ለጌታ እንደሚይዝ አለበለዚያ ግን በክፋት በደረሱ ጊዜ ግን እንደሚጠፉ አዟቸዋል፤ እንደዚህ አይነቶቹም ላይ፣ አለ ጌታ፥ የቁጣዬን ሙላት አፈስሳለሁና።

፳፩ እናም ኤመር በዘመኑ ሁሉ በፅድቅ ፍርድን ፈፅሟል፤ እናም ብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ እናም ቆሪያንቱምን ወለደ፣ እናም በእርሱ ቦታም እንዲነግስ ቀባው።

፳፪ እናም ቆሪያንቱም በእርሱ ምትክ እንዲነግስ ከቀባው በኋላ፣ ለአራት ዓመት ኖረ፣ እናም በምድሪቱም ላይ ሠላምን ተመለከተ፤ አዎን፣ እናም ደግሞም የጻድቅነትን ልጅ ተመልክቷል፣ እናም በዘመኑም ተደስቷል፣ እናም ከብሯል፣ እናም በሰላም ሞተ።

፳፫ እናም እንዲህ ሆነ ቆሪያንቱም የአባቱን ዱካ ተከተለ፤ እናም ብዙ ታላላቅ ከተሞችን መሰረተ፣ እናም በዘመኑ ሁሉ ለህዝቡ መልካም የነበረውን አበረከተ። እናም እንዲህ ሆነ በጣም እስከሚያረጅም ድረስ ልጆች አልነበሩትም።

፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ሚስቱም መቶ ሁለት ዓመት ሲሆናት ሞተች። እናም እንዲህ ሆነ ቆሪያንቱም በእርጅናው ወጣት አገልጋይ የሆነችን አገባ፣ እናም ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ስለዚህ አንድ መቶ አርባ ሁለት ዓመት እስከሚሆነው ድረስ ኖረ።

፳፭ እናም እንዲህ ሆነ ቆምን ወለደ፣ እናም ቆምም በእርሱ ምትክ ነገሰ፤ እናም እርሱም ለዓርባ ዘጠኝ ዓመታት ነገሰ፤ እናም እርሱም ሔትን ወለደ፤ እናም ደግሞ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።

፳፮ እናም ህዝቡም በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደገና ተሰራጩ፣ እናም በድጋሚ በምድሪቱ ላይ እጅግ ታላቅ የሆነ ኃጢያት ተጀመረ፤ እናም ሔትም አባቱን ለማጥፋት የጥንቱን ሚስጥራዊ ዕቅድ በድጋሚ ማቀፍ ጀመረ።

፳፯ እናም እንዲህ ሆነ እርሱም አባቱን በራሱ ጎራዴ በመግደል ከዙፋኑ ላይ አወረደው፤ እናም እርሱ በምትኩ ነገሰ።

፳፰ እናም እነርሱም የጌታን መንገድ ማዘጋጀት እንዳለባቸው፣ አለበለዚያ በምድሪቱ ላይ እርግማን እንደሚመጣ፣ አዎን ንሰሃ ካልገቡ ታላቅ ረሃብ እንደሚሆን በዚህም ብዙዎች እንደሚጠፉ የሚናገሩ፣ ለንሰሃ የሚጮኹ ነቢያት በድጋሚም በምድሪቱ ላይ መጡ።

፳፱ ነገር ግን ህዝቡ የነቢያቱን ቃላት አላመኑም፤ ነገር ግን እነርሱን አባረሩአቸው፤ እናም ጥቂቶቹን በጉድጓድ ጣሉአቸው፣ እናም እንዲሞቱ ተዉአቸው። እናም እንዲህ ሆነ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያደረጉትም በንጉሱ ሔት ትዕዛዝ መሰረት ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱም ላይ ታላቅ ድርቅ ተጀመረ፣ እናም ነዋሪዎቹም በድርቁ የተነሳ እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ ማለቅ ጀመሩ፣ በምድሪቱ ገፅ ላይ ምንም ዝናብ አልነበረምና።

፴፩ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ ደግሞ መርዛማ እባቦች መጡ፣ እናም ብዙ ሰዎችን ነደፉአቸው። እናም እንዲህ ሆነ ከብቶቻቸውም ከመርዛማው እባቦች ፊት በምድሪቱ በስተደቡብ በኩል በኔፋውያን ዛራሔምላ ተብሎ ወደሚጠራው ሸሹ።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ በሚሸሹበት ጊዜም ብዙዎች ሞቱ፤ ይሁን እንጂ፣ ጥቂቶቹም በምድሪቱ በስተደቡብ በኩል የሸሹ ነበሩ።

፴፫ እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እባቦቹ በማሳደድ እንዳይከተሉአቸው፣ ነገር ግን ህዝቡ ማለፍ እንዳይችሉ፣ ለማለፍ የሚጥሩትም በመርዛማዎቹ እባቦች ምክንያት እንዲወድቁ እንዲያሰናክሏቸው አደረገ።

፴፬ እናም እንዲህ ሆነ ህዝቡም አራዊቶች ያለፉበትን መንገድ ተከተሉ፣ እናም ሁሉንም እስኪመገቡ ድረስ የወዳደቁትን የከብት ስጋዎች ይመገቡ ነበር። እንግዲህ ህዝቡም መጥፋት እንዳለባቸው በተመለከቱ ጊዜ ለጥፋቶቻቸው ንሰሃ መግባት ጀመሩ፣ እናም ወደ ጌታ ጮኹ።

፴፭ እናም እንዲህ ሆነ በጌታም ፊት እራሳቸውን በብቃት ዝቅ ሲያደርጉ፣ እርሱም በምድሪቱ ገፅ ላይ ዝናብ ላከ፤ እናም ህዝቡም በድጋሚ ነፍስ ዘሩ፣ እናም በምድሪቱም ዙሪያ ሁሉ እናም በሃገሪቱ በስተሰሜን ፍራፍሬ በቀለ። እናም ጌታም ከረሃብ እነርሱን በመጠበቅ ኃይሉን አሳያቸው።