መፅሐፈ ሔለማን

ሔለማን 

የኔፋውያን ታሪክ። የእነርሱም ጦርነትና ፀብ፣ እናም መለያየታቸው። እናም ደግሞ የሔለማን ልጅ በነበረው፣ የሔለማን መዝገብ መሰረት፣ እናም ደግሞ በልጆቹ መዛግብት መሰረት፣ ከክርስቶስ መምጣት በፊት እርሱ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ የነበረው የብዙ ቅዱሳን ነቢያት ትንቢቶች። እናም ደግሞ ብዙ ላማናውያን ተለውጠዋል። የመለወጣቸው ታሪክ። እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ መፅሐፈ ሔለማን ተብሎ በተጠራው በሔለማንና በልጆቹ መዝገብ መሰረት የላማናውያን ፅድቅና፣ የኔፋውያን ኃጢያት፣ እና እርኩሰት፣ እናም ሌሎች የመሣሰሉ ታሪኮች።
ምዕራፍ ፩

ፓሆራን ሁለተኛው ዋና ገዢ ሆነ፣ እናም በቂሽቁመን ተገደለ—ፓኩሜኒ የፍርድ ወንበሩን ስፍራ ያዘ—ቆሪያንተመር የላማናውያን ወታደሮችን መራ፣ ዛራሔምላን ወሰደና፣ ፓኩሜኒን ገደለ—ሞሮኒያሃ ላማናውያንን አሸነፈና፣ ዛራሔምላን በድጋሚ ወሰደ፣ እናም ቆሪያንቱም ተገደለ። ከ፶፪–፶ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

የሔለማን ልጅ፣ ሔለማን፣ ዋና ዳኛ ሆነ—ጋድያንቶን የቂሽቁመንን ቡድን መራ—የሔለማን አገልጋይ ቂሽቁመንን ገደለው፣ እናም የጋድያንቶን ቡድን ወደ ምድረበዳው ሸሹ። ከ፶–፵፱ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

ብዙ ኔፋውያን ወደ ሰሜን ምድር ተጓዙ—የስሚንቶ ቤቶችን ሰሩ፣ እና ብዙ መዛግብቶችን አስቀመጡ—በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ተለወጡ እናም ተጠመቁ—የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ ደህንነት ይመራል—የሔለማን ልጅ ኔፊ የፍርድ ወንበሩን ያዘ። ከ፵፱–፴፱ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ከኔፋውያን የተገነጠሉትና ላማናውያን ኃይላቸውን አቀላቀሉ፣ እናም የዛራሔምላ ምድርን ያዙ—የኔፋውያን ሽንፈት የመጣው በኃጢኣታቸው ምክንያት ነው—ቤተክርስቲያኗ ተመናመነች፣ እናም ህዝቡ እንደላማናውያን ደካማ ሆነ። ከ፴፰–፴ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

ኔፊ፣ እና ሌሂ እራሳቸውን ለስብከት ሰጡ—ስሞቻቸው እንደቅድመ አያቶቻቸው ህይወታቸውን ይመስሉበት ዘንድ ይጋብዛቸዋል—ክርስቶስ ንስሃ የሚገቡትን ያድናል—ኔፊና ሌሂ ብዙዎችን ለወጡ፣ እናም ወደ ወህኒ ተወሰዱና እሳት እነርሱን ከበባቸው—የጨለማው ጭጋግም ሶስት መቶ ሰዎችን ሸፈነ—መሬት ተንቀጠቀጠች፣ እናም ድምፅም ሰዎችን ንስሃ እንዲገቡ አዘዘ—ኔፊና ሌሂ ከመላዕክት ጋር ተነጋገሩ፣ እናም ብዙ ህዝብም በእሳት ተከበበ። በ፴ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ፃድቃን የሆኑት ላማናውያን ለኃጢአተኞቹ ኔፋውያን ሰበኩላቸው—ሁለቱም በሰላሙና በጥጋቡ ዘመን በለፀጉ—የኃጢያት ደራሲው፣ ሉሲፈር፣ የኃጢአተኞችን፣ እናም የጋድያንቶንን ዘራፊዎች በግድያና በክፋት ልባቸውን አነሳሳ—ዘራፊዎቹ የኔፋውያንን መንግስት ተቆጣጠሩ። ከ፳፱–፳፫ ም.ዓ. ገደማ።

የሔለማን ልጅ የኔፊ ትንቢት—ለኃጢአታቸው ንስሃ ካልገቡ የኔፊን ህዝብ እግዚአብሔር ፍፁም ለማጥፋት በቁጣው እንደሚጎበኛቸው አስፈራራቸው። እግዚአብሔር የኔፊን ህዝብ በቸነፈር መታ፤ ንስሃ ገቡ እናም ወደ እርሱ ተመለሱ። ላማናዊው ሳሙኤል ለኔፋውያን ተነበየ።

ከምዕራፍ ፯ እስከ ፲፮ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፯

ኔፊ በሰሜን ተቀባይነትን አላገኘም እናም ወደዛራሔምላ ተመለሰ—በአትክልቱ ስፍራ ግንብ ላይ ፀሎት አደረገ፣ እናም ለህዝቡ ንስሃ እንዲገቡ አለበለዚያም እንደሚጠፉ ተናገረ። ከ፳፫–፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

ምግባረ ብልሹ የሆኑት ዳብኛዎች ህዝቡ በኔፊ ላይ እንዲነሳሳ ፈለጉ—አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዜኖስ፣ ዜኖቅ፣ ኤፅያስ፣ ኢሳይያስ፣ ኤርሚያስ፣ ሌሂ እና ኔፊ ሁሉም ስለክርስቶስ መሰከሩ—ኔፊ በመንፈስ ተነሳስቶ የዋናውን ዳኛ መገደል አስታወቀ። ከ፳፫–፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፱

መልዕክተኞች ዋናው ዳኛ በፍርድ ወንበሩ ላይ ሞቶ አገኙት—እነርሱም ታሰሩ፣ በኋላም ተለቀቁ—በመንፈስ በመነሳሳት ኔፊ ሴአንቱም ገዳይ መሆኑን አሳወቀ—ኔፊ በጥቂቶች ነቢይ ተብሎ ተቀባይነትን አገኘ። ከ፳፫–፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

ጌታ ለኔፊ የማሰር ስልጣንን ሰጠው—በመሬትና በሰማይ እንዲያስር እናም እንዲፈታ ስልጣንን ሰጠው—ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ አለበለዚያም እንዲጠፉ አዘዘ—መንፈስ ከብዙ ህዝብ ወደ ብዙ ህዝብ ወሰደው። ከ፳፩–፳ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፩

ኔፊ ጌታ ጦርነታቸውን በረሃብ እንዲለውጠው ለመነ—ብዙ ሰዎች ጠፉ—ንስሃ ገቡ፤ እናም ኔፊ ዝናብ እንዲያመጣ ጌታን በጥብቅ ለመነው—ኔፊ እና ሌሂ ብዙ ራዕዮችን ተቀበሉ—የጋድያንቶን ዘራፊዎች በምድሪቱ ላይ ተቋቋሙ። ከ፳–፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፪

ሰዎች ያልተረጋጉ እናም፣ ሞኞች፣ እንዲሁም ክፋትን ለመስራት የፈጠኑ ናቸው—ጌታ ህዝቡን ይገስጻል—የሰዎች ከንቱነት ከእግዚአብሔር ኃይል ጋር ተነፃፀረ—በፍርድ ቀን ሰዎች የዘለዓለም ህይወትን ወይንም የዘለዓለም ፍርድን ያገኛሉ። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።

የላማናዊው ሳሙኤል ለኔፋውያን የሰጠው ትንቢት።

ምዕራፍ ፲፫ እስከ ፲፭ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፲፫

ላማናዊው ሳሙኤል ኔፋውያን ንስሃ ካልገቡ በቀር እንደሚጠፉ ተነበየ—እነርሱ እና ሀብታቸው የተረገሙ ናቸው—ነቢያትን አልተቀበሉአቸውም እናም በድንጋይ ወገሩአቸው፤ እነርሱም በአጋንንት ተከበቡ፣ እናም ክፋትን በመፈፀም ደስታን ፈለጉ። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፬

ሳሙኤል በምሽት ብርሃን እንደሚሆን እናም አዲስ ኮከብ በክርስቶስ መወለድ እንደሚሆን ተነበየ—ክርስቶስ ሰዎችን ከጊዜያዊው እንዲሁም ከመንፈሳዊው ሞት ያድናቸዋል—የሞቱም ምልክቶች የሶስት ቀን ጨለማ፣ የአለቶች መፈረካከስ፣ እናም ታላቅ የሆነ የምድር መናወጥን ያጠቃልላል። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፭

ጌታ ኔፋውያንን የሚገስጻቸው ስለሚወዳቸው ነው—የተለወጡ ላማናውያን በእምነታቸው ፅኑ እንዲሁም የማይነቃነቁ ናቸው—ጌታ በኋለኛው ቀናት ለላማናውያን መሃሪ ይሆናል። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፮

ሳሙኤልን የሚያምኑ ኔፋውያን በኔፊ ተጠመቁ—ሳሙኤል ንስሃ ባልገቡ ኔፋውያን ቀስቶች እንዲሁም ድንጋይ ሊገደል አልቻለም—ጥቂቶች ልባቸውን አጠጠሩ እናም ሌሎች መላዕክቶችን ተመለከቱ—የማያምኑት፣ በክርስቶስ እናም በኢየሩሳሌም ስለመምጣቱ ማመን ትርጉም የለውም አሉ። ከ፮–፩ ም.ዓ. ገደማ።