መፅሐፈ ያዕቆብ የኔፊ ወንድም

ያዕቆብ 

ለወንድሞቹ የሰበካቸው ቃላት። እርሱ የክርስቶስን ትምህርት ለማጥፋት የተመኘውን ሰው አሳፈረው። የኔፊን ህዝብ ታሪክ በተመለከተ ጥቂት ቃላት።
ምዕራፍ ፩

ያዕቆብና ዮሴፍ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑና ትዕዛዛቱን እንዲጠብቁ ለማሳመን ሞከሩ—ኔፊ ሞተ—ክፋት በኔፋውያን መካከል ተስፋፋ። ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

ያዕቆብ የሀብትን ፍቅር፣ ኩራትና፣ ምንዝርናን አወገዘ—ሰዎች ወገናቸውን ለመርዳት ሀብትን ሊሹ ይችላሉ—ጌታ ከኔፋውያን መካከል ማንኛውም ሰው ከአንድ በላይ ሚስት እንዳይኖረው አዘዘ—ጌታ በሴቶች ንፁህነት ይደሰታል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

በልባቸው ንፁህ የሆኑ የሚያስደስተውን የእግዚአብሔርን ቃል ይቀበላሉ—የላማናውያን ፅድቅ ከኔፋውያን ይልቃል—ያዕቆብ ሳያገቡ ስለሚያመነዝሩ፣ ስለዝሙትና ስለማንኛውም ኃጢያት አስጠነቀቀ። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ነቢያት ሁሉ አብን በክርስቶስ ስም አመለኩ—የአብርሃም ይስሃቅን ለመሰዋት ማቅረቡ የእግዚአብሔርና የአንድያ ልጁ አምሳል ነበር—በኃጢያት ክፍያው ሰዎች እራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ አለባቸው—አይሁዶች የመሰረቱን ድንጋይ አይቀበሉም። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

ያዕቆብ ከዜኖስ ስለለማው እና ስለዱር የወይራ ዛፍ ታሪክ ጠቀሰ—እነርሱም ከእስራኤልና ከአህዛብ ጋር የተመሳሰሉ ናቸው—የእስራኤል መበተን እና መሰባሰብ ቀድሞ ተጠቅሷል—ስለኔፋውያንና ላማናውያን እንዲሁም ስለእስራኤል ቤት ሁሉ ተጠቅሷል—አህዛብ ከእስራኤል ጋር ይዳቀላሉ—በመጨረሻም የወይኑ ስፍራ ይቃጠላል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ጌታ እስራኤልን በመጨረሻው ቀን ይሰበስባል—ዓለም በእሳት ትቃጠላለች—ከእሳቱ ባህርና ከዲኑ ለመዳን ሰዎች ክርስቶስን መከተል ይኖርባቸዋል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፯

ሼረም ክርስቶስን ካደ፣ ከያዕቆብ ጋር ተጣላ፣ ምልክትን በግድ ፈለገ፣ እናም በእግዚአብሔር ተቀሰፈ—ሁሉም ነቢያት ስለክርስቶስና ስለኃጢያት ክፍያው ተናግረዋል—ኔፋውያን በዘመናቸው እንደሚንከራተቱ፣ በመከራ እንደተወለዱና፣ በላማናውያን እንደተጠሉ ኖሩ። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።