፩ ወይኑን የሚባረክበትም ሀስርዓት—እነሆ ዋንጫውን ወስደው እንዲህ ይላሉ፥
፪ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን ሀወይን የሚጠጡት ነፍሳት ሁሉ ለእነርሱ የፈሰሰውን የልጅህን ደም ለበማስታወስ ያደርጉት ዘንድ፣ ሁልጊዜ እርሱን እንደሚያስታውሱ ለአንተም፣ አቤቱ ዘለዓለማዊ አባት እግዚአብሔር ሆይ፣ ይመሰክሩ ዘንድ፣ በዚህም የእርሱ መንፈስ እንዲኖራቸው፣ ትባርከውና ትቀድሰው ዘንድ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠይቅሃለን። አሜን።