ምዕራፍ ፮
ንሰሃ የገቡት ሰዎች ተጠመቁ እናም የቤተክርስቲያኗን ህብረት አገኙ—ንሰሃ የገቡ የቤተክርስቲያን አባላት ይቅርታን ተቀበሉ—ስብሰባዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተከናውነዋል። ከ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።
፩ እናም አሁን ሀጥምቀትን በተመለከተ እናገራለሁ። እነሆ ሽማግሌዎች፣ ካህናት፣ እናም መምህራን ተጠምቀዋል፤ እናም ለእዚህም ለብቁ የሆኑ ትክክለኛ ፍሬ የሚያመጡ ካልሆኑ በስተቀር እነርሱ አይጠመቁም።
፪ ሀበተሰበረ ልብ እናም በተዋረደ መንፈስ ካልመጡ እናም ለኃጢአታቸው በሙሉ በእውነት ንሰሃ እንደገቡ ለቤተክርስቲያኗ ካልመሰከሩ በስተቀር ወደ ጥምቀቱ ማንንም አልተቀበሉም።
፫ እናም የክርስቶስን ስም ሀካልለበሱ እናም እስከመጨረሻውም እርሱን ለማገልገል ካልወሰኑ በቀር ማንንም በጥምቀት አልተቀበሉም።
፬ እናም ከተጠመቁ እናም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በላያቸው ላይ ከሰራ እናም ሀካነፃቸው በኋላ፣ ከክርስቶስ ቤተክርስቲያን ህዝቦች ጋር ተቆጥረዋል፤ እናም እነርሱን በትክክለኛው መንገድ ለማቆየት፣ የእምነታቸው ለደራሲ እና ፈፃሚ በሆነው በክርስቶስ በጎ ሥራ ላይ ብቻ ሐበመደገፍ ፀሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲሚቀጥሉ መለመጠበቅ፣ የእግዚአብሔርን መልካም ቃል በመመገብ ይታወሱ ዘንድ ሠስማቸው ተወስደዋል።
፭ እናም ሀለመፆም እናም ለመፀለይ፣ እናም እያንዳንዳቸው ለነፍሳቸው ደህንነት እርስ በርሳቸው እንዲናገሩ ዘንድ ለሁል ጊዜ ሐበቤተክርስቲያን ይገኛሉ።
፮ እናም ጌታ ኢየሱስን ለማስታወስ ዳቦውን እና ወይኑን ለመካፈል፣ ሁልጊዜ በአንድነት ይሰበሰቡ ነበር።
፯ እናም በመካከላቸው ሀክፉ ነገር እንዳይኖርም በጥብቅ ይጠነቀቃሉ፤ በመካከላቸው ክፉ ነገር ሲያደርጉ የተገኙ፣ እናም በቤተክርስቲያኗ ለሦስት ምስክሮች ሐበሽማግሌዎች ፊት ከተወቀሱ፣ እናም ንሰሃም ካልገቡ፣ እናም መካልተናዘዙ ስማቸው ሠይሰረዛል፣ እናም ከክርስቶስ ሰዎች ጋርም አይቆጠሩም።
፰ ነገር ግን በእውነተኛ ፍላጎት ንሰሃ ሀሁል ጊዜም ከገቡ፣ እናም ይቅርታን ከፈለጉ ለይቅር ይባላሉ።
፱ እናም ስብሰባዎችም በቤተክርስቲያኗ በመንፈስ ስራዎች እናም ሀበመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለይመራል፤ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልም እንዲሰብኩ፣ ወይም እንዲያስጠነቅቁ፣ ወይም እንዲፀልዩ፣ ወይም ወደጌታ እንዲማፀኑ ወይም እንዲዘምሩ ይመራቸዋል፣ እንዲሁም ይፈጸማል።