ሞሮኒ 

ምዕራፍ ፩

ሞሮኒ ለላማናውያን ጥቅም ፃፈ—ክርስቶስን ያልካዱ ኔፋውያን ተገደሉ። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

ኢየሱስም ኔፋውያን ደቀመዛሙርት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እንዲሰጡ ስልጣንን ሰጣቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

ሽማግሌዎች እጃቸውን በካህናት እናም በመምህራን ላይ በመጫን ሾሙአቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ሽማግሌዎች እና ካህናት የቅዱስ ቁርባንን ዳቦ እንዴት እንደሚባርኩት ተገልጿል። ፬፻–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

የቅዱስ ቁርባኑን ወይን የሚባረክበት ስርዓት እንደሚከተለው ተገልጿል። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ንሰሃ የገቡት ሰዎች ተጠመቁ እናም የቤተክርስቲያኗን ህብረት አገኙ—ንሰሃ የገቡ የቤተክርስቲያን አባላት ይቅርታን ተቀበሉ—ስብሰባዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተከናውነዋል። ከ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፯

በጌታ እረፍት እንዲገቡ ሰዎች ተጋብዘዋል—በእውነተኛ ፍላጎት ፀልዩ—የክርስቶስ መንፈስ ሰዎች መጥፎውን ከጥሩ ለይተው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል—ሰይጣን ሰዎች ክርስቶስን እንዲክዱ እናም መጥፎ እንዲሰሩ ይገፋፋቸዋል—ነቢያት ስለክርስቶስ መምጣት ተናግረዋል—በእምነት፣ ድንቅ ነገር ይሰራል፣ እናም መላዕክቶችም ያገለግላሉ—ሰዎች ዘለዓለማዊ ህይወትን ተስፋ ማድረግ እናም ከልግስናም ጋር ፅኑ መሆን አለባቸው። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

ህጻናትን ማጥመቅ የከፋ ርኩሰት ነው—ህፃናት በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካይነት ህያው ናቸው—እምነት፤ ንሰሃ፤ የዋህነት እናም የልብ ርህራሄ፤ መንፈስ ቅዱስን መቀበል፣ እና እስከ መጨረሻው ፅኑ መሆን ወደ ደህንነት ይመራል። ፬፻፩–፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።

ሞርሞን ለልጁ ሞሮኒ የፃፈው ሁለተኛው ደብዳቤ።

ምዕራፍ ፱ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፱

ኔፋውያን እናም ላማናውያን ነውረኛ እና የረከሱ ናቸው—እነርሱም እርስ በርሳቸው ስቃይን እናም ግድያን ይፈፅማሉ—ሞርሞንም ፀጋ እና ቸርነት ለዘለዓለም በሞሮኒ ላይ እንዲሆን ፀለየ። ፬፻፩ ዓ.ም. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

የመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይመጣል—ለታማኞች የመንፈስ ስጦታዎች ይሰጣቸዋል—መንፈሳዊው ስጦታዎች ዘወትር እምነትን ይከተላል—የሞሮኒ ቃላት ከምድር ይናገራሉ—ወደ ክርስቶስ ኑ፤ በእርሱም ፍፁማን ሁኑ፣ እናም ነፍሳችሁን አንፁ። ፬፻፳፩ ዓ.ም. ገደማ።