ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፳፪


ምዕራፍ ፳፪

ህዝቡ ከላማናውያን ባርነት እንዲያመልጡ እቅዱ ታቀደ—ላማናውያን እንዲሰክሩ ተደረገ—ህዝቡ አመለጡ፣ ወደ ዛራሔምላ ተመለሱ፣ እናም በንጉስ ሞዛያ አገዛዝ ስር ሆኑ። ከ፻፳፩–፻፳ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ አሞንና ንጉስ ሊምሂ ህዝቡን ከባርነት እንዴት እንደሚያስለቅቁ መመካከር ጀመሩ፤ እናም ህዝቡ ሁሉ እንኳ በአንድነት እንዲሰበሰቡ አደረጉ፤ እናም ይህንን ያደረጉት ሁኔታውን በተመለከተ የህዝቡን ድምፅ ለመስማት ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ፤ ሴቶቻቸውንና ልጆቻቸውን፣ እናም ከብቶቻቸውን፣ መንጋዎቻቸውንና፣ ድንኳናቸውን ወስደው ወደ ምድረበዳው ከመሸሽ በስተቀር እራሳቸውን ከባርነት የሚያስለቅቁበት ምንም መንገድ ለማግኘት አልቻሉም፤ ከባርነት በጎራዴ ለመላቀቅ ቢያስቡም ላማናውያን በቁጥር ብዙ በመሆናቸው የሊምሂ ህዝብ ከእነርሱ ጋር ለመጣላት የማይቻላቸው ነበር።

አሁን እንዲህ ሆነ ጌዴዎን ሔደና፣ በንጉሱ ፊት ቆመ፣ እናም እንዲህ አለው፥ አሁን ንጉስ ሆይ ከወንድሞቻችን ከላማናውያን ጋር ስንጣላ እስካሁን ብዙ ጊዜ ቃላቴን ሰምተሀልና።

እናም አሁን ንጉስ ሆይ እኔ የማልጠቅም አገልጋይ ሆኜ ካላገኘኸኝ ወይም በማንኛውም ደረጃ እስካሁን ቃሌን ካዳመጥህና ለእናንተም ጠቃሚ ከሆኑ፣ እንዲሁም በዚህ ጊዜ አንተም ቃሌን እንድትሰማኝ እፈልጋለሁ፣ እናም የአንተ አገልጋይ እሆናለሁ፣ ይህንንም ህዝብ ከባርነት አላቅቃለሁ።

እናም ንጉሱ ይናገር ዘንድ ፈቀደለት። ጌዴዎንም እንዲህ አለው፥

የኋለኛውን መተላለፊያ፣ በኋለኛው ግንብ በኩል፣ በከተማው በስተኋላ በኩል ተመልከት። ላማናውያን፣ ወይም የላማናውያን ጠባቂዎች በምሽት ይሰክራሉ፣ ስለዚህ በእነዚህ ህዝቦች መካከል ከብቶቻቸውንና መንጋዎቻቸውን በአንድ ላይ በመሰብሰብ ወደ ምድረበዳው እንዲሸሹ አዋጅ እንላክ።

እናም በትዕዛዝህ መሰረት ሄጄ የመጨረሻውን የወይን ግብር ለላማናውያን እከፍላለሁ፣ እነርሱም ይሰክራሉ፤ እናም እነርሱ ሲሰክሩና ሲተኙ በጦር ሠፈሩ በስተግራ ባለው በሚስጥር ማለፊያው እናልፋለን።

ከሴቶቻችንና ከልጆቻችን፣ ከከብቶቻችንና ከመንጋዎቻችን ጋር ወደ ምድረበዳ እንሸሻለን፤ እናም በሼምሎን ምድር አካባቢ እንጓዛለን።

እናም እንዲህ ሆነ ንጉሱ የጌዴዎንን ቃል አዳመጠ።

እናም ንጉስ ሊምሂ ህዝቡ መንጋዎቹን በአንድነት እንዲሰበስቡ አደረገ፤ እናም የወይኑን ግብር ለላማናውያን ላከ፤ ደግሞም እንደስጦታ ብዙ ወይን ላከላቸው፣ እናም ንጉስ ሊምሂ የላካቸውን ወይን በብዛት ጠጡ።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ የንጉስ ሊምሂ ህዝብ ከከብቶቻቸውና ከመንጋዎቻቸው ጋር በምሽት ወደ ምድረበዳው ሸሹ፤ እናም በምድረበዳ ውስጥ በሼምሎን ምድር ዙሪያ ሄዱና፣ በአሞንና በወንድሞቹ በመመራት አቅጣጫቸውን ወደ ዛራሔምላ ምድር አደረጉ።

፲፪ እናም ወርቃቸውንና ብራቸውንና የከበሩ ነገሮቻቸውን መሸከም የሚችሉትን ያህል፣ ደግሞም ስንቆቻቸውን ሁሉ ወደ ምድረበዳው ወሰዱ፤ እናም ጉዞአቸውን ቀጠሉ።

፲፫ እናም በምድረበዳ ውስጥ ብዙ ቀናት ካደረጉ በኋላ፣ በዛራሔምላ ምድር ደረሱ፣ እናም የሞዛያ ህዝብ አባል ሆኑ፣ እንዲሁም በአገዛዙ ስር ሆኑ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ሞዛያ በደስታ ተቀበላቸው፤ እናም ደግሞ መዝገባቸውንና ደግሞ በሊምሂ ህዝብ የተገኙትን መዝገቦች ተቀበለ።

፲፭ እናም አሁን እንዲህ ሆነ የሊምሂ ህዝብ በምሽት መሸሻቸውን ላማናውያን ባወቁ ጊዜ፣ እነርሱን እንዲከተሉ ወታደሮችን ወደ ምድረበዳው ላኩ፤

፲፮ እናም ለሁለት ቀናት ከተከታተሉአቸው በኋላ፣ ዱካቸውን መከተል አልቻሉም፤ ስለዚህ በምድረበዳ ውስጥ ተሰወሩ።