ምዕራፍ ፳፮
ብዙዎች የቤተክርስቲያኑ አባላት እምነት በሌላቸው ወደ ኃጢያት ተመሩ—አልማ የዘለዓለማዊ ሕይወት ቃል ተገብቶለታል—ንስሃ የሚገቡት እና የሚጠመቁ ይቅርታን ያገኛሉ—በኃጢያት ያሉት እና ኃጢአታቸውን ለአልማና ለጌታ የተናዘዙ የቤተክርስቲያን አባላት ይቅር ይባላሉ፤ አለበለዚያ ከቤተክርስቲያን አባላት ጋር አይቆጠሩም። ከ፻፳–፻ ም.ዓ. ገደማ።
፩ አሁን እንዲህ ሆነ የንጉስ ቢንያምን ቃል መረዳት የማይችሉ በማደግ ላይ ያሉ ትውልዶች ነበሩ፣ እነርሱም እርሱ ለዚህ ህዝብ በተናገረበት ጊዜ ትንሽ ልጆች የነበሩ በመሆናቸው፤ እናም የአባቶቻቸውን ባህል አያምኑም ነበር።
፪ የሙታን ትንሣኤንም ሆነ የክርስቶስን መምጣት በሚመለከት የተነገረውን አያምኑም ነበር።
፫ እናም አሁን ባለማመናቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሀሊረዱት አልቻሉም ነበር፤ ልባቸውም ጠጥሮ ነበር።
፬ እናም አይጠመቁም ነበር፣ የቤተክርስቲያኗም አባል አይሆኑም ነበር። እናም እምነታቸውን በተመለከተ የተለዩ ነበሩ፣ ከእዚያም በኋላ እንደዚያው ሆነው ቀሩ፣ ሀበስጋዊነታቸውና በኃጢአተኝነታቸውም ቢሆን፣ ወደ ጌታ አምላካቸው አይፀልዩም ነበርና።
፭ እናም አሁን በሞዛያ የንግስና ዘመን እንደ የእግዚአብሔር ሰዎች ግማሽ ያህል አልበዙም ነበር፣ ነገር ግን በወንድሞች መካከል ሀጥል ምክንያት በጣም በርክተው ነበር።
፮ እንዲህ ሆነ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩትን ብዙዎችን በሸንጋይ ቃላቸው አታለሉአቸው፣ እናም ብዙ ኃጢአቶችን እንዲፈፅሙ አደረጉአቸው፣ ስለዚህ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሆነው ኃጢያትን የፈፀሙ፣ በቤተክርስቲያኗ ሀመገሰፃቸው አስፈላጊ ነበር።
፯ እናም እንዲህ ሆነ ከካህናቱ ፊት አመጡአቸው፣ እናም በመምህራንም ለካህናቱ ተሰጡ፤ እናም ካህናቱ ሀሊቀ ካህን ከሆነው ከአልማ ፊት አመጧቸው።
፰ አሁን ንጉስ ሞዛያ አልማን በቤተክርስቲያኗ ላይ ስልጣን ሰጥቶታል።
፱ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ስለእነርሱ አያውቅም ነበር፤ ነገር ግን በእነርሱ ላይ ብዙ ምስክሮች ነበሩ፣ አዎን፣ ህዝቡ ቆሙና ስለኃጢአታቸው በብዛት መሰከሩ።
፲ አሁን በቤተክርስቲያኑ ፊት እንደዚህ ያለ ነገር ሆኖ አያውቅም፤ ስለዚህ አልማ በመንፈሱ ይጨነቅ ነበር፤ እናም ከንጉሱ ፊት እንዲመጡ አደረገ።
፲፩ እናም ለንጉሱ አለው፥ እነሆ ብዙዎቹን በወንድሞቻቸው የተከሰሱትን በአንተ ፊት አምጥተናል፤ አዎን፣ እናም በተለያዩ ክፋቶች የተያዙ ናቸው። እናም ስለኃጢአታቸው ንስሃ አይገቡም፤ ስለዚህ እንደወንጀላቸው ትፈርድባቸው ዘንድ በአንተ ፊት አምጥተናቸዋል።
፲፪ ነገር ግን ንጉስ ሞዛያ አልማን እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ እኔ አልፈርድባቸውም፣ ስለዚህ አንተ እንድትፈርድባቸው በእጅህ ሀአሳልፌ አሰጥሃለሁ።
፲፫ እናም አሁን የአልማ መንፈስ በድጋሚ ታወከ፣ እናም ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዐይን የተሳሳተ ነገርን እፈፅማለሁ በማለት ስለፈራ ወደጌታ ሄዶ ይህንን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ።
፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ነፍሱን ሁሉ ለእግዚአብሔር ካፈሰሰ በኋላ፣ የጌታ ድምፅ ወደ እርሱ እንዲህ ሲል መጣ፥
፲፭ አልማ አንተ የተባረክ ነህ፣ እና ሀበሞርሞን ውሃ የተጠመቁት የተባረኩ ናችው። የእኔ አገልጋይ በሆነው በአቢናዲ ቃል ብቻ እጅግ ለበማመንህ የተባረክህ ነህ።
፲፮ እናም እነሆ አንተ በተናገርካቸው ቃላት ብቻ እጅግ ስላመኑም የተባረኩ ናቸው።
፲፯ እናም በዚህ ህዝብ መካከል ሀቤተክርስቲያኗን በመመስረትህ አንተ የተባረክህ ነህ፤ እናም እነርሱም ይቋቋማሉ፣ የእኔም ሰዎች ይሆናሉ።
፲፰ አዎን፣ ስሜን ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ይህ የተባረከ ህዝብ ነው፤ ሀበስሜም ይጠራሉና፣ እናም እነርሱ የእኔ ናቸው።
፲፱ እናም እኔን ህጉን ስለተላለፉት በተመለከተ ስለጠየከኝ አንተ የተባረክህ ነህ።
፳ አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ፤ እናም ሀዘለዓለማዊ ሕይወት ይኖርህ ዘንድ ካንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ እናም ታገለግለኛለህም፣ በስሜም ትሄዳለህ፣ እናም በጎቼን በአንድነት ትሰበስባለህ።
፳፩ እናም ድምጼን የሰማ የእኔ ሀበግ ይሆናል፣ እናም እናንተ በቤተክርስቲያኗ ትቀበሉታላችሁ፤ እኔም ደግሞ እቀበለዋለሁ።
፳፪ እነሆም ይህች የእኔ ቤተክርስቲያን ናት፣ ማንም ሀየሚጠመቅ ንሰሃ በመግባት ይጠመቃል፤ እናም እናንተ የተቀበላችሁት ማንም ቢኖር በስሜ ያምናል፤ እናም እርሱን በነፃ ለይቅር እለዋለሁ።
፳፫ እኔ የዓለምን ኃጢያት ሀበራሴ ያደረግሁ ነኝና፤ እነርሱን ለየፈጠርኳቸው እኔ ነኝና፤ እናም እስከመጨረሻው ለሚያምነው በቀኜ ያለውንም ስፍራ የምሰጠው እኔ ነኝ።
፳፬ እነሆም፣ በስሜም ተጠርተዋል፤ እናም ሀየሚያውቁኝ ከሆነም ወደ እኔ ይመጣሉ፣ እናም በቀኝ እጄ በኩል ዘለዓለማዊ ስፍራ ይኖራቸዋል።
፳፭ እናም እንዲህ ይሆናል ሀሁለተኛው መለከት ሲነፋ እኔን በፍፁም ለያላወቁ መጥተው በፊቴ ይቆማሉ።
፳፮ እና ከእዚያም እኔ ጌታ አምላካቸው፣ አዳኛቸው መሆኔን ያውቃሉ፤ ነገር ግን አይድኑም።
፳፯ እናም ከዚያ በኋላ እኔ በጭራሽ ሀእንደማላውቃቸው እናዘዝላቸዋለሁ፣ እናም ለዲያብሎስና ለመላዕክቱ ወደተዘጋጀው ወደ ለዘለዓለማዊ እሳት ሐይሄዳሉ።
፳፰ ስለዚህ እንዲህም እላችኋለሁ፣ ቃሌን ሀየማይሰማ፣ እርሱ በቤተክርስቲያኔ አትቀበሉት፣ በመጨረሻውም ቀን እርሱን አልቀበለውምና።
፳፱ ስለዚህ እላችኋለሁ ሂዱ፣ እናም እኔን የተላለፈ ማንኛውንም እንደፈፀመው ሀኃጢያት መሰረት ለፍረድበት፤ እናም በእኔና በአንተ ፊት ኃጢአቱን ሐከተናዘዘ፣ እናም ከልቡ መንስሃ ከገባ እርሱን ሠይቅር ትለዋለህ፣ እኔም ደግሞ ይቅር እለዋለሁ።
፴ አዎን፣ እናም ህዝቤ ሀንስሃ እንደገባው ለመጠን በእኔ ላይ ያደረጉትን መተላለፍ ይቅር እላቸዋለሁ።
፴፩ እናም እያንዳንዳችሁ መተላለፋችሁን ሀይቅር ተባባሉ፤ እውነት እላችኋለሁ ጎረቤቱ ንስሃ በሚገባበት ጊዜ የጎረቤቱን መተላለፍ ይቅር የማይል እርሱ ራሱን ወደኩነኔ ያመጣል።
፴፪ አሁን እልሀለሁ፣ ሂድ፣ ለኃጢአቱ ንስሃ የማይገባ እርሱ ከህዝቤ ጋር አብሮ አይቆጠርም፤ እናም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ይህ ደንብ ይጠበቃል።
፴፫ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ይህንን ቃል በሰማ ጊዜ፣ እንዲኖሩት፣ እና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት የቤተክርስቲያን ሰዎችን ይፈረድባቸው ዘንድ ጻፋቸው።
፴፬ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ሄደና፣ እነዚያ በክፋት የተወሰዱትን በጌታ ቃል መሰረት ፈረደባቸው።
፴፭ እና ማንኛውም ለኃጢአታቸው ንስሃ የገቡ ሀየተናዘዙ፣ እነርሱ ከቤተክርስቲያኗ ሰዎች መካከል ቆጠራቸው።
፴፮ እናም ኃጢአታቸውን ያልተናዘዙና ለክፋታቸው ንስሃ ያልገቡ፣ እነርሱ ከቤተክርስቲያኗ ሰዎች መካከል አልተቆጠሩም፣ ናም ስማቸውም ሀተሰርዟል።
፴፯ እናም እንዲህ ሆነ አልማ የቤተክርስቲያኗን ጉዳዮች ሁሉ መራ፤ እናም ለቤተክርስቲያኑ ጉዳዮች ሰላምና ብልፅግና በድጋሚ እጅግ መሳካት ጀመሩ፣ በጥንቃቄም በእግዚአብሔር ፊት በመራመድ ብዙዎችን ተቀበሉ፣ ብዙዎችን አጠመቁ።
፴፰ እናም አሁን፣ በማንኛውም ትጋት በመራመድ፣ በሁሉም ነገር የጌታን ቃል በማስተማር፣ በሁሉም መከራ በመሰቃየት፣ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል ባልሆኑት ሁሉ በመሳደድ፣ እነዚህ ነገሮች በሙሉ አልማና በቤተክርስቲያኗ ላይ ያሉት ተከታይ አገልጋዮች ይህንን አደረጉ።
፴፱ እናም ወንድሞቻቸውን ሀገሰፁ፤ እናም በእግዚአብሔር ያለማቋረጥ ለእንዲፀልዩና ሐበሁሉም ነገር ምስጋናን እንዲሰጡም በመታዘዝ፣ እያንዳንዱ እንደ ኃጥያቱ፣ ወይም እንደፈፀመው ኃጢአቱ መሰረት በእግዚአብሔር ቃል ተገስጿል።