ምዕራፍ ፳፰
የሞዛያ ልጆች ላማናውያንን ሊሰብኩ ሔዱ—ሁለቱን የባለራዕይ ድንጋዮች በመጠቀም ሞዛያ የያሬዳውያንን ሰሌዳዎች ተረጎመ። በ፺፪ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እንግዲህ እንዲህ ሆነ ሀየሞዛያ ልጆች እነዚህን ነገሮች ሁሉ ካደረጉ በኋላ ጥቂቶቹን ከእነርሱ ጋር ወሰዱ፣ እናም ወደ ንጉሱ አባታቸው ተመለሱ፤ እናም በዚህም እነርሱ ከመረጧቸው ጋር በመሆን፣ የሰሙአቸውን ነገሮች ይሰብኩ ዘንድ እናም የጌታን ቃላት ለወንድሞቻቸው ለላማናውያን ያካፍሉ ዘንድ ለወደኔፊ ምድር እንዲሄዱ እንዲፈቅድላቸው ፈለጉ—
፪ ምናልባት ወደጌታ አምላካቸው እውቀት ያመጧቸው ዘንድ፣ እናም የአባቶቻቸውንም ክፋት እንዲያሳምኑአቸው፤ እናም ምናልባት ወደኔፋውያን ካላቸው ሀጥላቻ ያድኗቸው ዘንድ፣ በጌታ በአምላካቸውም ደግሞ ወደመደሰት ያመጧቸው ዘንድ፣ እርስ በራስም ወዳጅ ይሆን ዘንድ፣ እናም ጌታ አምላካቸውም በሰጣቸው ምድር ሁሉ ከእንግዲህ ጠብም እንዳይኖር ለማድረግ ይችሉ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ፈለጉ።
፫ አሁን ደህንነት ለሁሉም ፍጡር መታወጅ እንደሚገባው ፍላጎት ነበራቸው፣ የማንም የሰው ሀነፍስ መጥፋቱን ለሊቀበሉት አልቻሉምና፤ አዎን ማንኛውም ነፍስ ሐመጨረሻ የሌለውን ቅጣት የሚቀበል መሆኑ ማሰባቸውም እንዲንዘፈዘፉና እንዲንቀጠቀጡ ያደርጋቸዋል።
፬ እናም የጌታ መንፈስ በእነርሱ ላይ ሰርቶ ነበር፣ እነርሱ ሀከሁሉም በላይ መጥፎ የሆኑ ኃጢአተኞች ነበሩና። እናም ጌታ ማብቂያ በሌለው ለምህረቱ እነርሱን ለማዳን አስፈላጊ መሆኑን ተረዳ፤ ይሁን እንጂ በክፋታቸው ምክንያት ብዙ የነፍስ ስቃይ ተሰቃዩ፣ እናም ለዘለዓለም እንጣላለን ብለው በመፍራታቸው የተነሳ ብዙ ተሰቃዩ።
፭ እናም እንዲህ ሆነ ወደ ኔፊ ምድር ይወጡ ዘንድ ከአባቶቻቸው ጋር ለብዙ ቀናት ተማፀኑ።
፮ እናም ንጉስ ሞዛያ ሄደና፣ ልጆቹ ከላማናውያን መካከል ሄደው ወንጌልን ለማስተማር ፍቃድ እንዲሰጣቸው እንደሚገባው ጌታን ጠየቀ።
፯ እናም ጌታ ለሞዛያ እንዲህ አለው፥ እንዲሄዱ ፍቀድላቸው፣ ብዙዎች በቃላቸው ያምናሉና፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል፤ እናም እኔ ወንድ ልጆቻችሁን ከላማናውያን እጅ ሀአድናቸዋለሁ።
፰ እናም እንዲህ ሆነ ሞዛያ በጠየቁትም መሰረትም እንዲሄዱና ያደርጉ ዘንድ ፈቀደላቸው።
፱ እናም በላማናውያን መካከል ቃሉን ለመስበክ ወደ ምድረበዳ ሀሄዱ፣ እናም ከዚህ በኋላ የታሪካቸውን ለዘገባ እሰጣለሁ።
፲ አሁን ንጉስ ሞዛያ መንግስቱን የሚሰጥበት ማንም አልነበረውም፣ ምክንያቱም ከልጆቹም ማንም መንግስቱን የተቀበለ አልነበረም።
፲፩ ስለዚህ እናም ለንጉስ ሞዛያ በሊምሂ እጅ የተሰጡትን በሊምሂ ህዝብ የተገኙትን ሀወርቃማ ሠሌዳዎች ከተረጎመና በመዝገብ እንዲፃፍ ካደረገ በኋላ፣ ለበነሃስ ሰሌዳና፣ ደግሞም በኔፊ ሠሌዳዎች ላይ የተቀረፁትንና፣ ሁሉንም በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት የተቀመጡትን እና የተጠበቁትን ነገሮች ወሰደ፤
፲፪ እናም ይህን ያደረገው በህዝቡ ታላቅ ጉጉት የተነሳ ነው፣ ምክንያቱም እነርሱ ስለጠፉት ሰዎች ለማወቅ ፍላጎታቸው ከልክ በላይ ነበርና።
፲፫ እናም አሁን በሁለቱ የቀስት ጫፎች ላይ በታሰሩት ሀድንጋዮች አማካኝነት ተረጎማቸው።
፲፬ አሁን እነዚህ ነገሮች ከመጀመሪያው ጀምሮ ተዘጋጅተዋል፣ እናም ቋንቋዎችን ለመተርጎም አላማም ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፈዋል፤
፲፭ እናም የምድሪቱን ሰዎች ክፋትና እርኩሰት ማንኛውም ፍጡር ያገኘው ዘንድ፣ በጌታ እጅ ተጠብቀዋል፣ እናም ተቀምጠዋል፤
፲፮ እናም እነዚህን ነገሮች ያሏቸው ሁሉ እንደጥንት ጊዜ አይነት ሀባለራዕይ ይባላሉ።
፲፯ አሁን ሞዛያ እነዚህን ታሪኮች ተርጉሞ ከጨረሰ በኋላ፣ እነሆ፣ ሀየጠፉትን ህዝቦች ከጠፉበት ጊዜ አንስቶ ለታላቁ ግንብ እስከተገነባበት፣ ጌታ የህዝቡን ቋንቋ ሐበቀለቀለበት ጊዜ እናም በምድር ገፅ ሁሉ እስከተበተኑበት፤ አዎን፣ እናም ከጥንት አዳም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ጭምር የህዝቡን ታሪክ ሰጠ።
፲፰ አሁን ይህ ታሪክ የሞዛያ ህዝብ እጅግ እንዲያለቅስ አደረገ፤ አዎን በሀዘን ተሞልተው ነበር፣ ይሁን እንጂ ብዙ እውቀትን ሰጥቷቸዋል፣ በእርሱም ተደስተዋል።
፲፱ እናም ይህ ታሪክ ከዚህ በኋላ ይፃፋል፣ እነሆም፣ በዚህ መዝገብ የተፃፉትን ነገሮች ሁሉም ሰው ማወቁ አስፈላጊ ነውና።
፳ እናም አሁን፣ እኔ እንዳልኳችሁ፣ ንጉስ ሞዛያ እነዚህን ነገሮች ካደረገ በኋላ ሀየነሃስ ሰሌዳዎቹን፣ እናም ያስቀመጣቸውን ሁሉንም ነገሮች ወሰደና፣ የአልማ ልጅ ለሆነው ለአልማ ሰጠው፤ አዎን፣ ሁሉንም መዛግብትና፣ ደግሞ ለመተርጎሚያውን፣ እናም ሁሉንም ለእርሱ ሰጠ፣ እንዲጠብቃቸውና ሐእንዲያስቀምጣቸው፣ ደግሞም የህዝቡን ታሪክ እንዲያስቀምጥ፣ ልክ ሌሂ ኢየሩሳሌምን ለቆ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እንደተላለፈው፣ ከአንዱ ትውልድ ወደሌላኛው እንዲያስተላልፍ አዘዘው።