ሞዛያ 

ምዕራፍ ፩

ንጉስ ቢንያም ለልጆቹ የአባቶቻቸውን ቋንቋ እና ትንቢት አስተማረ—ኃይማኖታቸውና ስልጣኔያቸው የተጠበቁት በተለያዩ ሠሌዳዎች ላይ በተጠበቁት መዝገቦች ምክንያት ነው—ሞዛያ ለንጉስነት ተመርጧል እናም መዛግብቱና ሌሎችም ነገሮች አደራ ተሰጥተውታል። ከ፻፴–፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፪

ንጉስ ቢንያም ለህዝቡ ንግግር አደረገ—የንግስናውን ፍትሀዊነት፣ ተገቢነት፣ እና መንፈሳዊነት ገለፀ—የሰማዩን ንጉሳቸውን እንዲያገለግሉ መከራቸው—በእግዚአብሔር ላይ የሚያምፁ በማይጠፋው እሳት አይነት ጭንቀት ይሰቃያሉ። ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፫

ንጉስ ቢንያም ንግግሩን ቀጠለ—ሁሉን የሚገዛው ጌታ በጭቃ ሰውነቱ በሰዎች መካከል ያገለግላል—ለዓለም ኃጢአቶች ዋጋን ሲከፍል ደም ከሰውነቱ ቀዳዳ ሁሉ ይፈሳል—ደህንነት የሚመጣበት ብቸኛው ስም የእርሱ ነው—ሰዎች በኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ፍጥረታዊ ሰውነታቸውን መለወጥ እናም ቅዱሳን ለመሆን ይችላሉ—የኃጢአተኞች ስቃይ እንደባህር እሳትና ዲን ይሆናል። ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፬

ንጉስ ቢንያም ንግግሩን ቀጠለ—ደህንነት የሚመጣው በኃጢያት ክፍያው አማካኝነት ነው—ለመዳን በእግዚአብሔር እመኑ—የኃጢአታችሁን ስርየት በእምነታችሁ አግኙ—ያላችሁን ነገር ለድሆች አካፍሉ—ሁሉንም ነገር በጥበብና በስርዓት አድርጉ። ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፭

ቅዱሳን በእምነታቸው የክርስቶስ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ይሆናሉ—ከዚያም በክርስቶስ ስም ይጠራሉ—ንጉስ ቢንያም በመልካም ስራቸው እንዲፀኑ እናም የማይነቃነቁ እንዲሆኑ መከራቸው። በ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፮

ንጉስ ቢንያም የህዝቡን ስም መዘገበ እናም እነርሱን የሚያስተምሩ ካህናትን ሾመ—ሞዛያ ፃድቅ ንጉስ በመሆን ነገሰ። ከ፻፳፬–፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፯

አሞን ሊምሂ ንጉሥ የሆነበትን፣ የሌሂ-ኔፊ ምድርን አገኘ—የሊምሂ ህዝብ በላማናውያን ባርነት ስር ናቸው—ሊምሂ ታሪካቸውን ዘገበ—ነቢዩ (አቢናዲ) ክርስቶስ የሁሉም ነገሮች አምላክና አባት መሆኑን መስክሯል—መጥፎ የዘሩ አውሎ ነፋስን ያጭዳሉ፣ እናም በጌታ እምነታቸውን ያደረጉ ይድናሉ። ፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፰

አሞን የሊምሂን ህዝብ አስተማረ—ስለ ሀያ አራቱ ያሬዳውያን ሰሌዳዎች ተማረ—የጥንት ታሪኮች በባለራዕዮች መተርጎም ይችላሉ—ከባለራዕይነት የበለጠ ስጦታ የለም። ፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

የዜኒፍ መዝገብ—የዛራሔምላን ምድር ለቀው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ከላማናውያን እጅ እስከተለቀቁበት ጊዜ ድረስ ያለው የህዝቡ ታሪክ።

ከምዕራፍ ፱ እስከ ምዕራፍ ፳፪ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፱

ዜኒፍ የሌሂ-ኔፊን ምድር እንዲወርሱ ከዛራሔምላ ቡድንን መራ—የላማናውያን ንጉስ ምድሪቱን እንዲወርሱ ፈቀደላቸው—በላማናውያንና በዜኒፍ ህዝብ መካከል ጦርነት ሆነ። ፪፻–፻፹፯ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲

ንጉስ ላማን ሞተ—ህዝቡም አረመኔና የሚያስፈሩ እንዲሁም በሐሰት ባህል የሚያምኑ ነበሩ—ዜኒፍና ህዝቡ ድል አደረጉአቸው። ከ፻፹፯–፻፷ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፩

ንጉስ ኖህ በክፋት ገዛ—ከሚስቶቹና ከዕቁባቶቹ ጋር በቀበጠ ብልሹ አኗኗር ፈነጠዘ—አቢናዲ ህዝቡ ለባርነት እንደሚወሰድ ተነበየ—ንጉስ ኖህ ህይወቱን ሊያጠፋ ፈለገ። ከ፻፷–፻፶ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፪

አቢናዲ የህዝቡን ጥፋትና የንጉስ ኖህን ሞት በመተንበዩ ታሰረ—የሀሰት ካህናት ቅዱስ መፅሐፍትን ጠቀሱ እናም የሙሴንም ህግ ለመጠበቅ አስመሰሉ—አቢናዲ እነርሱን አስርቱን ትዕዛዛት ማስተማር ጀመረ። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፫

አቢናዲ በመለኮታዊ ኃይል ተጠበቀ—አሥርቱን ትዕዛዛት አስተማረ—ደህንነት በሙሴ ህግ ብቻ አይመጣም—እግዚአብሔር ራሱ የኃጢያት ክፍያ ያደርጋል፣ እናም ህዝቡን ያድናል። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፬

ኢሳይያስ ስለመሲሁ ተናገረ—የመሲሁ መዋረድና መሰቃየት ተገልፆአል—ነፍሱን ለኃጢያት መስዋዕት ሰጠ፣ እናም ለተላለፉት አማላጅ ሆነ—ኢሳይያስ ፶፫ን አነጻፅሩ። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፭

ክርስቶስ አባትም ልጅም እንዴት እንደሆነ—እርሱ ያማልዳል እናም የህዝቡን አመፅ ይሸከማል—እነርሱ እና ሁሉም ቅዱሳን ነቢያት ዘሮቹ ናቸው—ትንሳኤን ያመጣል—ህፃናት ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፮

እግዚአብሔር ሰዎችን ከጥፋትና ከውድቀት ሁኔታቸው ያድናል—በስጋ ያሉ ቤዛነት እንደሌለ ሆነው ይቀራሉ—ክርስቶስ መጨረሻ የሌለው ህይወትን ወይንም መጨረሻ የሌለው ኩነኔ ትንሳኤን አመጣው። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፯

አልማ የአቢናዲን ቃል አመነ እናም ፃፈ—አቢናዲ በእሳት ተቃጥሎ ሞተ—አቢናዲ በገዳዮቹ ላይ በሽታንና በእሳት ሞትን ተነበየ። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፰

አልማ በድብቅ ሰበከ—የጥምቀትን ቃል ኪዳን ገለፀ እናም በሞርሞን ውሃ አጠመቀ—የክርስቶስን ቤተክርስቲያን አዋቀረ እናም ካህናትን ሾመ—እነርሱም ራሳቸውን ረዱ እናም ህዝቡን አስተማሩ—አልማና ህዝቡ ከንጉስ ኖህ ወደ ምድረበዳው ሸሹ። ከ፻፵፯–፻፵፭ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፲፱

ጌዴዎን ንጉስ ኖህን ለመግደል ፈለገ—ላማናውያን ምድሪቱን ወረሩ—ንጉስ ኖህ በእሳት ሞተ—ሊምሂ እንደ ግብር ከፋይ ንጉስ ገዛ። ከ፻፵፭–፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳

አንዳንድ የላማናውያን ሴት ልጆች በኖህ ካህናት ተጠልፈው ነበር—ላማናውያን በሊምሂና በህዝቡ ላይ ጦርነት አደረጉ—የላማናውያን ሠራዊቶች አሸነፏቸውና አረጋጓቸው። ከ፻፵፭–፻፳፫ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፩

የሊምሂ ህዝብ በላማናውያን ተመቱ እናም ተሸነፉ—የሊምሂ ህዝብ አሞንን አገኙ፣ እናም ተለወጡ—ለአሞን ስለሃያ አራቱ የያሬዳውያን ሰሌዳዎች ነገሩት። ከ፻፳፪–፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፪

ህዝቡ ከላማናውያን ባርነት እንዲያመልጡ እቅዱ ታቀደ—ላማናውያን እንዲሰክሩ ተደረገ—ህዝቡ አመለጡ፣ ወደ ዛራሔምላ ተመለሱ፣ እናም በንጉስ ሞዛያ አገዛዝ ስር ሆኑ። ከ፻፳፩–፻፳ ም.ዓ. ገደማ።

በንጉስ ኖህ ህዝብ ወደ ምድረበዳ እንዲሰደዱ የተደረጉት የአልማና የጌታ የሆኑት ሰዎች ታሪክ።

ከምዕራፍ ፳፫ እስከ ምዕራፍ ፳፬ አጠቃሎ የያዘ።

ምዕራፍ ፳፫

አልማ ንጉስ መሆንን አልተቀበለም—እንደ ሊቀ ካህን አገለገለ—ጌታ ህዝቡን ገሰጸ፣ እናም ላማናውያን የሔላምን ምድር አሸነፉ—የንጉስ ኖህ የክፉዎቹ ካህናት አለቃ የሆነው አሙሎን፣ በላማናውያን አገዛዝ ስር ገዛ። ከ፻፵፭–፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፬

አሙሎን አልማንና ህዝቡን አሳደደ—የሚፀልዩ ከሆነ ይገደላሉ—ጌታ ሸክማቸውን ቀሊል እንዲመስል አደረገው—ከባርነት አዳናቸው፣ እናም ወደ ዛራሔምላ ተመለሱ። ከ፻፵፭–፻፳ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፭

በዛራሔምላ የሙሌቅ ወገኖች ኔፋውያን ሆኑ—ስለአልማና ስለዜኒፍ ህዝብ ተማሩ—አልማ ሊምሂንና ህዝቡን ሁሉ አጠመቀ—ሞዛያ አልማ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዲያቋቁም ስልጣን ሰጠው። በ፻፳ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፮

ብዙዎች የቤተክርስቲያኑ አባላት እምነት በሌላቸው ወደ ኃጢያት ተመሩ—አልማ የዘለዓለማዊ ሕይወት ቃል ተገብቶለታል—ንስሃ የሚገቡት እና የሚጠመቁ ይቅርታን ያገኛሉ—በኃጢያት ያሉት እና ኃጢአታቸውን ለአልማና ለጌታ የተናዘዙ የቤተክርስቲያን አባላት ይቅር ይባላሉ፤ አለበለዚያ ከቤተክርስቲያን አባላት ጋር አይቆጠሩም። ከ፻፳–፻ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፯

ሞዛያ ስደትን ከለከለ፣ እናም እኩልነትን አዘዘ—ትንሹ አልማና አራቱ የሞዛያ ልጆች ቤተክርስቲያኗን ለማጥፋት ፈለጉ—መልአክ ታያቸው፣ እናም መጥፎ ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ አዘዛቸው—አልማ በድንገት ዲዳ ሆነ—ሁሉም የሰው ዘር ደህንነትን እንዲያገኝ በድጋሚ መወለድ አለበት—አልማና የሞዛያ ልጆች የደስታ ምስራች አወጁ። ከ፻–፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፰

የሞዛያ ልጆች ላማናውያንን ሊሰብኩ ሔዱ—ሁለቱን የባለራዕይ ድንጋዮች በመጠቀም ሞዛያ የያሬዳውያንን ሰሌዳዎች ተረጎመ። በ፺፪ ም.ዓ. ገደማ።

ምዕራፍ ፳፱

ሞዛያ በንጉስ ቦታ ዳኛዎች እንዲመረጡ ሀሳብ አቀረበ—ፃድቃን ያልሆኑ ንጉሶች ህዝባቸውን ወደኃጢያት ይመራሉ—ትንሹ አልማ ዋና ዳኛ እንዲሆን በህዝቡ ድምፅ ተመረጠ—እርሱም ደግሞ በቤተክርስቲያኗ ላይ ሊቀ ካህን ነው—አልማ ትልቁና ሞዛያ ሞቱ። ከ፺፪–፺፩ ም.ዓ. ገደማ።