ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፲፪


ክፍል ፻፲፪

በሀምሌ ፳፫፣ ፲፰፻፴፯ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ ስለአስራ ሁለቱ የጥቦው ሐዋሪያት በሚመለከት ለቶማስ ቢ ማርሽ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህን ራዕይ የተቀበለው ሽማግሌዎች ሂበር ሲ ኪምባል እና ኦርሰን ሀይድ በእንግሊዝ ሀገር ወንጌሉን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰበኩበት ቀን ነው። ቶማስ ቢ ማርሽ በዚህ ጊዜ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ፕሬዘደንት ነበር።

፩–፲፣ አስራ ሁለቱ ወንጌሉን ይላኩ እና ለሁሉም ሀገሮች እና ህዝብም የማስጠንቀቂያን ድምፅ ያንሱ፤ ፲፩–፲፭፣ መስቀላቸውን ይሸከሙ፣ ኢየሱስንም ይከተሉ፣ እና በጎቹንም ይመግቡ፤ ፲፮–፳፣ የቀዳሚ አመራርን የሚቀበሉ ጌታን ይቀበላሉ፤ ፳፩–፳፱፣ ጭለማ ምድርን ሸፈነ፣ እና የሚያምኑ እና የሚጠመቁ ብቻ ይድናሉ፤ ፴–፴፬፣ ቀዳሚ አመራር እና አስራ ሁለቱ የዘመን ፍጻሜ ሙላትን ቁልፎች ይዘዋል።

ለአገልጋዬ ቶምስ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፥ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እና በስሜ እንዲመሰክሩ እና በሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ህዝብ መካከል ወደ ውጪ እንዲላኩ በተመረጡት፣ እና በአገልጋዮቼ መሳሪያነት በተሾሙት በእነዚያ ወንድሞችህ ወኪል ያቀረብከው ምፅዋትህ እንደ ማስታወሻ ወደ እኔ ዘንድ መጥቷል።

እውነት እልሀለሁ፣ እኔ ጌታ በልብህ ውስጥ እና ከአንተም ጋር ያልተደሰትኩባቸው አንዳንድ ጥቂት ነገሮች አሉኝ።

ይህም ቢሆን፣ ራስህን እስካዋረድህ ድረስ ከፍ ትደረጋለህ፤ ስለዚህ ኃጢአቶችህ ሁሉ ተሰርየዋል።

ልብህ በፊቴ ሀሴትን ያድርግ፤ እና ለአህዛብ ብቻ ሳይሆን ደግሞም ለአይሁዶች ስለስሜ ትመሰክራለህ፤ እና ቃሌን ወደ ምድር ዳርቻዎች ትልካለህ።

አትጣላ፣ ስለዚህ ጠዋት በየማለዳው፣ በየቀኑ የማስጠንቀቂያህ ድምፅህ ይሂድ፤ እና ሲመሽም፣ በንግግርህ ምክንያት የምድር ነዋሪዎች ያንቀላፉም ዘንድ አትፍቀድ።

በፅዮን ውስጥም መኖሪያህ ይታወቅ፣ እና መኖሪያህንም አትቀይር፤ በሰዎች ልጆች መካከል ስሜን ታሳውቅ ዘንድ፣ እኔ ጌታ ታከናውነው ዘንድለአንተ ታላቅ ስራ አለኝና።

ስለዚህ ለስራውም ወገብህን አጥብቅ። እግሮችህም ይጫሙ፣ አንተ የተመረጥህ ነህና፣ እና መንገድህም በተራራዎች መካከል እና ከብዙ ህዝብ መካከል ነውና።

እና በቃልህም ከፍ ያሉት የዋረዱ ይሆናሉ፣ እና በቃልህም የተዋረዱት ከፍ ይላሉ።

ድምፅህም ለሚተላለፈው ግሳጼ ይሆናል፤ እና በግሳጼህም ስምን የሚያጠፋ ምላስም ጠማማነቱን ያቁም።

ትሁት ሁን፤ እና ጌታ አምላክህ እጅህን ይዞ ይመራሀል፣ እና ለጸሎቶችህም መልስ ይሰጥሀል።

፲፩ ልብህን አውቃለሁ፣ እና ስለወንድሞችህም ጸሎትህን ሰምቻለሁ። ለእነርሱ ከሌሎች በላይ በፍቅርህ አድሎን አታድርግ፣ ነገር ግን ለእነርሱ ያለህ ፍቅርህ እንደራስህ ይሁን፤ እናም ፍቅርህም ለሁሉም ሰዎችና ስሜን ለሚወዱ ሁሉ ይብዛ።

፲፪ ለአስራ ሑለቱ ወንድሞችህም ጸልይ። ስለስሜም ብለህ በብርቱ ገስጻቸው፣ እና ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ይገሰጹ፣ እና ስለስሜም በፊቴ ታማኝ ሁን።

፲፫ ከፈተናዎቻቸው እና ከብዙም ስቃይ በኋላ፣ እነሆ፣ እኔ ጌታ እፈልጋቸዋለሁ፣ እና ልባቸውን ባያጠጥሩ፣ እና አንገታቸውን በእኔ ላይ ባያደነደኑ፣ ይለወጣሉ፣ እኔም እፈውሳቸዋለሁ።

፲፬ አሁን፣ እልሀለሁ፣ እና ለአንተ የምለውን፣ ለአስራ ሁለቱ ሁሉ እላለሁ፥ ተነሳ እና ወገብህን አጥብቅ፣ መስቀልህንም ተሸከም፣ ተከተለኝ፣ እና በጎቼንም መግብ

፲፭ ራሳችሁን ከፍ አታድርጉ፤ በአገልጋዬ ጆሴፍ ላይ አታምጽ፤ በእውነት እልሀለሁ፣ ከእርሱ ጋር ነኝ፣ እና እጄም በእርሱ ላይ ይሆናልና፤ እና እኔ ለእርሱ፣ እና ዳግሞም ለእናንተም፣ የሰጠኋቸው ቁልፎችም እስከምመጣ ድረስ ከእርሱ አይወሰዱም።

፲፮ እውነት እልሀለሁ አገልጋዬ ቶማስ፣ በሀገሮች ሁሉ መካከል በውጪ ስላሉት አስራ ሁለቱን በሚመለከት፣ የመንግስቴን ቁልፎች እንድትይዝ የመረጥኩህ ሰው ነህ—

፲፯ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ እና አገልጋዬ ስድኒ፣ እና አገልጋዬ ሀይረም ሊመጡበት በማይችሉበት ስፍራ ሁሉ የመንግስትን በር እንድትከፍት ዘንድ፤

፲፰ በእነርሱም ላይ ለጥቂት ዘመን የቤተክርስቲያናትን ሽክሞች ሁሉ በእነርሱ ላይ አሳርፌአለሁና።

፲፱ ስለዚህ፣ የትም ቢልኩህ፣ ሂድ፣ እና እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እና ስሜን በምታውጅበት በማንኛውም ስፍራ ቃሌን ይቀበሉ ዘንድ ውጤታማ በርም ይከፈትልሀል።

ማንም ቃሌን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እና እኔን የሚቀበል ማንም፣ የላኳቸውን፣ ስለስሜም ለአንተ አማካሪዎች ያደረኳቸውን እነዚያን የቀዳሚ አመራርን ይቀበላል።

፳፩ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በስሜ፣ በወንድሞቻችሁ በአስራ ሁለቱ ድምፅ፣ በእናንተ ተገቢ ትእዛዝና ስልጣን፣ የምትልኳቸው ሁሉ፣ በምትልኳቸው በየትኛውም ሀገር የመንግስቴን በር የመክፈት ሀይል ይኖራቸዋል—

፳፪ ይህን የሚሆነው በፊቴ ራሳቸውን ትሁት እስካደረጉ፣ እና በቃሌም እስከኖሩ፣ እና የመንፈሴንም ድምፅ እስካደመጡ ድረስ ነው።

፳፫ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ጭለማ ምድርን፣ እና ታላቅ ጭለማም የህዝብን አዕምሮ ሸፍኗል፣ እና ስጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ በስብሰዋል

፳፬ እነሆ፣ በቀል፣ የቁጣ ቀን፣ የንዳድ ቀን፣ የጥፋት ቀን፣ የለቅሶ ቀን፣ የሀዘን ቀን በምድር ነዋሪዎች ላይ በፍጥነት መጥቷል፤ እና እንደ አውሎ ንፋስም በምድር ፊት ሁሉ ይመጣል፣ ይላል ጌታ።

፳፭ እና በቤቴም ላይ ይጀምራል፣ እና ከቤቴም ይሄዳል፣ ይላል ጌታ፣

፳፮ መጀመሪያ ስሜን እናውቃለን በሚሉ በማያውቁኝም፣ እና በቤቴም መካከል እኔን ስለሰደቡኝ ስለእነዚያ በመካከላችሁ ስላሉት፣ ይላል ጌታ።

፳፯ ስለዚህ፣ በዚህ ስፍራ ስላለው የቤተክርስቲያኔ ጉዳዮች እንዳታስቡበት ይሁን፣ ይላል ጌታ።

፳፰ ነገር ግን በፊቴ ልባችሁን አንጹ፤ ከዚያም ወደ አለም ሁሉ ሂዱ፣ እና ላልተቀበሉት ለእያንዳንዱ ፍጥረትም ወንጌሌን ስበኩ፤

፳፱ እና ያመነ እና የተጠመቀም ይድናል፣ እና ያላመነ፣ እና ያልተጠመቀ ይፈረድበታል

ለእናንተ ለአስራ ሁለቱና ለአማካሪዎቻችሁ እና መሪዎቻችሁ እንዲሆኑም ለተመደቡት ለእነዚያ ለቀዳሚ አመራር የዚህ ክህነት ሀይል የሙሉ ዘመን ፍጻሜ ለሆነው ለመጨረሻዎቹ ቀናት እና ለመጨረሻ ጊዜም ተሰጥቷል፣

፴፩ ሀይልን የምትይዙት፣ ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ በማንኛውም ዘመን ከተቀበሉት ሁሉ ጋር በተገናኘ ነው፤

፴፪ እውነት እላችኋለሁ፣ የተቀበላችሁት የዘመን ቁልፎች ከአባቶች የመጡ እና በመጨረሻም ወደ እናንት ከሰማይ የተላኩ ናቸውና።

፴፫ እውነት እላችኋለሁ፣ ጥሪአችሁ እንዴት ታላቅ እንደሆነ ተመልከቱ። የዚህ ትውልድ ደም ከእጆቻችሁ እንዳይጠየቁ፣ ልባችሁንና ልብሶቻችሁን አንጹ

፴፬ እስከምመጣም ድረስ ታማኝ ሁኑ፣ ቶሎ እመጣለሁና፤ እና ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ስራው እንዲከፈለው ደመወዙም ከእኔ ዘንድ ነው። እኔ አልፋ እና ኦሜጋ ነኝ። አሜን።