ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፩


ክፍል ፻፴፩

በግንቦት ፲፮ እና ፲፯፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) በራመስ ኢለኖይ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጡ መመሪያዎች።

፩–፬፣ የሰለስቲያል ጋብቻ ከፍ ባለው ሰማይ ዘለአለማዊ ክብር ለማግኘት አስፈላጊ ነው፤ ፭–፮፣ ሰዎች ለዘለአለም ህይወት እንዴት እንደታተሙ ተገልጿል፤ ፯–፰፣ መንፈስ ሁሉ ግዝፈት ያለው ነው።

በሰለስቲያል ክብር ውስጥ ሶስት ሰማያት ወይም ደረጃዎች አሉ፤

ከፍተኛውን ለማግኘት፣ ሰው ወደ እዚህ የክህነት ስርዓት መግባት አለበት [ይህም አዲስ እና ዘለአለማዊ የጋብቻ ቃል ኪዳን ማለት ነው]፤

እና ይህን ባያደርግ፣ ሊያገኘው አይችልም።

ወደሌሎቹ ለመግባት ይችላል፣ ነገር ግን ያም የሚያደርገው መጨረሻው መንግስቱ ነው፤ ተጨማሪም ሊያገኝ አይችልም።

[ግንቦት ፲፯፣ ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.)]። በተጨማሪ እርግጠኛ የትንቢት ቃል ማለት በራዕይ እና በትንቢት መንፈስ፣ በቅዱስ የክህነት ሀይል አማካይነት፣ ሰው ለዘለአለም ህይወት እንደታተመ አውቋል ማለት ነው።

ሰው በድንቁርና ይድን ዘንድ አይችልም።

ስለዚህ፣ ህልውና የሌለው ህልው ነገር የሚባል ነገር የለም። መንፈስ ሁሉ ህልውና ያለው ነው፣ ነገር ግን ይህም የጠራ እና ንጹህ ነው፣ እና ሰውም ሊለየው የሚችለው በነጹ አይኖች ብቻ ነው፤

እናየውም ዘንድ አይቻለንም፤ ነገር ግን ሰውነቶቻችን ሲነጹ ግዝፈት ያለው እንደሆነ ሁሉ እናያለን።