ክፍል ፻፴፪
በናቩ ኢለኖይ ውስጥ በሐምሌ ፲፪፣ ፲፱፻፵፫ (እ.አ.አ.) የተመዘገበው፣ ስለአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን፣ በተጨማሪም የጋብቻ ቃል ኪዳን ዘለአለማዊነትን እና ደግሞም ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት መሰረታዊ መርሆ በሚመለከት በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ምንም እንኳን ይህ ራዕይ በ፲፰፻፵፫ (እ.አ.አ.) የተመዘገበ ቢሆንም፣ ከዚህ ራዕይ ጋር የተገናኙ አንዳንድ መርሆች ለነቢዩ ከ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) መጀመሪያ ጀምሮ ታውቀው ነበር። አስተዳደሪያዊ አዋጅ ፩ን ተመልከቱ።
፩–፮፣ ዘለአለማዊ ክብር የሚገኘው በአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ነው፤ ፯–፲፬፣ የዚህ ቃል ኪዳን ምልክት እና ቅድመ ሁኔታዎች ተሰጥተዋል፤ ፲፭–፳፣ ሰለስቲያል ጋብቻ እና የቤተሰብ ስብስብ ቀጣይነት ሰዎች አማልክት እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፤ ፳፩–፳፭፣ ቀጭኑ እና ጠባቡ መንገድ ወደዘለአለም ህይወት ይመራል፤ ፳፮–፳፯፣ መንፈስ ቅዱስን መስደብ በሚመለከት ህግ ተሰጠ፤ ፳፰–፴፱፣ የዘለአለማዊ እድገት እና ዘለአለማዊ ክብር ቃል ኪዳን ለሁሉም ዘመን ነቢያት እና ቅዱሳን ተደርገዋል፤ ፵–፵፯፣ ጆሴፍ ስሚዝ በምድር ላይ እና በሰማይ ውስጥ ለማሰር እና ለማተም ሀይል ተሰጠው፤ ፵፰–፶፣ ጌታ በእርሱ ላይ ዘለአለማዊ ክብር አተመበት፤ ፶፩–፶፯፣ ኤማ ስሚዝ ታማኝ እና እውነተኛ እንድትሆን ተመከረች፤ ፶፰–፷፮፣ ከአንድ በላይ የሆኑ ሚስቶችን ስለማግባት የሚመሩ ህግጋት ተሰጥተዋል።
፩ በእውነትም ለአንተ አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ጌታ እንዲህ ይላል፣ እኔ ጌታ አገልጋዮቼን አብርሐምን፣ ይስሀቅን፣ እና ያዕቆብን፣ ደግሞም ሙሴን፣ ዳዊትን፣ እና ሰለሞንን ብዙ ሀሚስቶችና ዕቁባቶች የነበሯቸውን መሰረታዊ መርሆች እና ትምህርቶችን በሚመለከት እንዴት ከጥፋት ነጻ እንዳደረኳቸው እንዲገባህ እና ለማወቅ ከእጄ እንደጠየከኝ—
፪ እነሆ፣ እና አስተውል፣ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝ፣ እና ይህን ጉዳይ በሚነካም መልስን እሰጥሀልሁ።
፫ ስለዚህ፣ ልሰጥህ ያሉትን መመሪያዎች ለመቀበል እና ለማክበር ልብህን ሀአዘጋጅ፤ ይህ ህግ ለተገለጠላቸው ሁሉ ይህን ማክበር አለባቸውና።
፬ እነሆ፣ አዲስ እና ዘለአለማዊ ሀቃል ኪዳን ገልጬላችኋለሁና፤ እና ይህን ቃል ኪዳን ካልኖራችሁበት፣ ከዚያ ለየተኮነናችሁ ናችሁ፣ ማንም ይህን ቃል ኪዳን ሐሊቃወምና እና ወደ ክብሬ ይገባ ዘንድ አይችልምና።
፭ ከእጄ በረከት የሚያገኙም ለዚያ ሀበረከት የተመደበውን ለህግና አለም ከመመስረቷም በፊት በስራ ላይ የዋሉትን ቅድመ ሁኔታ ሊኖሩባቸው ያስፈልጋቸዋልና።
፮ እና ሀአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳንን በሚመለከት፣ በስራ ላይ የዋለው ለለክብሬ ሙላት ነበር፤ እና ይህን ሙላት የሚቀበል በህጉ ይኑር እና መኖርም አለበት፣ ወይም ይኮነናል፣ ይላል ጌታ አምላክ።
፯ እና እውነት እላችኋለሁ፣ የዚህ ህግ ቅድመ ሀሁኔታዎች እነዚህ ናቸው፥ በተቀባው፣ ለጊዜ እና ለዘለአለም፣ በዚህ ምድር ይህን ሀይል እንዲይዝ በመደብኩት (እና አገልጋዬ ጆሴፍን ይህን ሀይል በመጨረሻ ቀናት እንዲይዝ መድቤአለሁ እና የዚህ ክህነት ሀይል እና ለቁልፎች ይሰጠው ዘንድ የተገባ ከአንድ በላይ የለም) በእኔ በተቀባው በኩል ሐበራዕይ እና በትዕዛዝ እና ከሁሉም በላይ በሆነ መየቅዱስ ተስፋ መንፈስ ያልተሰሩ፣ ያልገቡና ሠያልታተሙ ቃል ኪዳናት፣ ስምምነቶች፣ የተፈረመባቸው መረጃዎች፣ ግዴታዎች፣ ረመሀላዎች፣ ስዕለቶች፣ ግንኙነቶች፣ ተባባሪነቶች፣ ወይም የሚጠበቅባቸው፣ በሙታን ትንሳኤ እና በኋላም ሁሉም ፍቱንነት፣ መልካምነት፣ ወይም ሀይል አይኖራቸውም፤ ለዚህም ውጤት ያልተገቡ ስምምነቶች ሰዎች በሞቱ ጊዜ መጨረሻው ይሆናል።
፰ እነሆ፣ ቤቴ የስርዓት ቤት ነው፣ ይላል ጌታ አምላክ፣ እና የግራ መግባት ቤት አይደለም።
፱ በስሜ ያልተደረጉትን ሀመስዋዕቶችን እቀበላለሁን? ይላል ጌታ።
፲ ወይም ሀያልመደብኩትን ከእጆቻችሁ እቀበላለሁን?
፲፩ እና እንዲሁም እኔ እና አባቴ ለእናንተ ከዚህ አለም በፊት ሀእንደሾምነው፣ በህግ ካልሆነ በስተቀር፣ ይላል ጌታ፣ እመድብላችኋለሁን?
፲፪ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፤ እና ይህን ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ—በእኔ እና ህጌ በሆነው በቃሌ በቀር ወደ አብ ሀየሚመጣ የለም፣ ይላል ጌታ።
፲፫ እና በአለም ያለው ሁሉም ነገር፣ በሰዎችም፣ ዙፋናት ወይም በጌትነት ወይም በአለቅነት ወይም በሥልጣናት ስም ባላቸው ነገሮች የተመደበ ቢሆንም፣ ምንም ቢሆኑ፣ በእኔ ወይም በቃሌ ካልሆኑ ይጣላሉ፣ ይላል ጌታ፣ እና ሰዎች ከሞቱም በኋላ፣ ወይም በትንሳኤ ወይም በኋላም እንዲሁ ሀአይቀሩም፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።
፲፬ የሚቀሩትም ማናቸውም ነገሮች በእኔ ናቸው፤ እና በእኔ ያልሆኑትም ማናቸውም ነገሮች ይናወጣሉ እናም ይደመሰሳሉ።
፲፭ ስለዚህ፣ ሰው በአለም ውስጥ ሚስት ሀቢያገባ፣ እና በእኔ ወይም በቃሌ ባያገባት፣ እና በአለም እስካለም ድረስ ከእርሷ ጋር እና እርሷም ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ቢገቡ፣ ሲሞቱና ከአለም ሲለዩ ቃል ኪዳናቸውና ጋብቻቸው ሀይል አይኖራቸውም፤ ስለዚህ፣ ከአለም ሲለዩ በምንም ህግ አይታሰሩም።
፲፮ ስለዚህ፣ ከአለም ሲለዩ ሀአያገቡም ወይም አይጋቡምም፤ ነገር ግን በሰማይ ውስጥ እንደ ለመላእክት ይመደባሉ፣ እነዚህም መላእክት ከዚህም በላይ፣ እና በክብርን በዘለአለም እድገት ከሁሉ ይልቅ ብቁ ለሆኑት ረጂ አገልጋዮች ናቸው።
፲፯ እነዚህ መላእክት በህጋቴ አልኖሩምና፤ ስለዚህ፣ ሊያድጉ አይችሉም፣ ነገር ግን ተለያይተው እና በብቸኝነት፣ ከፍ ሳይደረጉ፣ በዳኑበት ሁኔታ ዘለአለማዊ ክብር ሳይኖራቸው ይቆያሉ፤ እና ከዚያም ጊዜ ጀምሮ አማልክት አይደሉም፣ ነገር ግን ለዘለአለም የእግዚአብሔር መላእክት ናቸው።
፲፰ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰው ሚስት ቢያገባ፣ እና ለጊዜ እና ለዘለአለም ቃል ኪዳን ቢያደርግ፣ ያም ቃል ኪዳን በእኔ ወይም ህጌ በሆነው በቃሌ ባይጸና እና ለዚህ ሀይል በቀባሁት እና በመደብኩት በኩል በቅዱስ የተስፋ መንፈስ ያልታተመ ቢሆን፣ ከዚያም ከዚህ አለም ሲለዩ ጋብቻቸው ተቀባይነት ወይም ሀይል የለውም፣ ምክንያቱም በእኔ ወይም በቃሌ አልተሳሰሩምና፣ ይላል ጌታ፤ ከአለም ሲለዩም በዚያም ተቀባይነት አያገኝም ምክንያቱም በዚያ ሊያልፏቸው የማይችሉ መላእክት እና አማልክት ተመድበዋልና፤ ስለዚህ ክብሬን መውረስ አይችሉም፤ ቤቴ የስርዓት ቤት ነውና፣ ይላል ጌታ አምላክ።
፲፱ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ህጌ በሆነው በቃሌ እንዲሁም ሀበአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ሰው ሚስትን ቢያገባ፣ እና ይህም በተቀባው፣ የዚህን ሀይል እና የዚህን ክህነት ለቁልፎች በመደብኩለት አማካይነት፣ በቅዱስ ሐየተስፋ መንፈስ መይታተማል፤ እናም ለእነርሱም እንዲህ ይባላል—እናንተ በመጀመሪያው ትንሳኤ ትመጣላችሁ፤ እና ከመጀመሪያው ትንሳኤ በኋላም ቢሆን፣ በሚቀጥለው ትንሳኤ፤ እና ሠዙፋናት፣ መንግስታት፣ ጌትነቶች፣ እና ሀይላት፣ አለቅነት፣ ሁሉንም ከፍታና ዝቅታን ይወርሳሉ—ከዚያም በበጉ ረየህይወት መፅሀፍ ውስጥ ንጹህ ደም የማይፈስበት ግድያን እንደማይፈፅም ይጻፋል፣ እና በቃል ኪዳኔ ብትኖሩ፣ እና ንጹህ ደም የሚያፈስበትን ግድያ ባትፈጸሙ፣ በጊዜ እና በዘለአለም ሁሉ አገልጋዬ በእነርሱ ላይ የሚኖረው ማንኛውም ነገሮች ሁሉ ይደረጉላቸዋል፤ እና ከዚህ አለም ሲለዩም ሙሉ ሀይል ያለው ይሆናል፤ እና በዚያ በተቀመጡት በመላእክት እና አማልክት አልፈው፣ በራሳቸው ላይ እንደታተሙት በሁሉም ነገሮች ወደ ሰዘለአለማዊ ክብር እና ወደ ክብራቸው ይሄዳሉ፣ ይህም ክብር ለዘለአለም የሙላት እና ለዘራቸውም ቀጣይነት ያለው ይሆናል።
፳ ከዚያም እነርሱም አማልክት ይሆናሉ፣ ምክንያቱም መጨረሻ የላቸውምና፤ ስለሚቀጥሉም፣ በዚህም ከዘለአለም ወደዘለአለም የሚኖሩ ይሆናሉ፤ ከዚያም ሁሉም ነገሮች ለእነርሱ ተገዢ ስለሚሆኑ፣ ከሁሉም በላይ ይሆናሉ። ከዚያም ሀሁሉም ሀይል ስለሚኖራቸው፣ ለአማልክት ይሆናሉ፣ እና መላእክትም ተገዢ ይሆኑላቸዋል።
፳፩ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሀበህጌ ካልኖራችሁ በስተቀር ይህን ክብር አታገኙም።
፳፪ ወደ ዘለአለማዊ ክብር እና ወደ ቀጣይ ሀህይወት መቀጠል የሚወስደው ደጅ ለየጠበበ፣ ሐመንገዱም የቀጠነ ነውና፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው፣ በዚህ አለም ስላልተቀበላችሁኝ አታውቁኝም።
፳፫ ነገር ግን በዚህ አለም ብትቀበሉኝ፣ ከዚያም ታውቁኛላችሁ፣ እና ዘለአለማዊ ክብራችሁንም ትቀበላላችሁ፤ እኔ ሀባለሁበት እናንተም ደግሞ ትሆናላችሁ።
፳፬ እውነተኛ እና የጥበብ አምላክ ብቻ የሆነውንና ሀየላከውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች ለየዘለአለም ሕይወት ናት። እኔም እርሱ ነኝ። ስለዚህ ህጌን ትቀበላላችሁ።
፳፭ ወደ ሀሞት የሚመራው ደጅ ለሰፊ፣ እናም መንገዱም የሰፋ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፣ ምክንያቱም ሐአይቀበሉኝም ወይም በህጌም አይኖሩምና።
፳፮ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰው በቃሌ መሰረት ሚስት ቢያገባ፣ እና እኔም በመደብኩት መሰረት ሀበቅዱስ የተስፋ መንፈስ ቢታተሙ፣ እና እርሱ ወይም እርሷ በአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ላይ ምንም ኃጢአት ወይም መተላለፍ እና ሁሉንም አይነት መተላለፍ ባያደርጉ እና ንጹህንም ደም ለማፍሰስ ለባይገድሉ፣ በመጀመሪያው ትንሳኤ ይመጣሉ፣ እና ወደ ዘለአለማዊ ክብራቸውም ይገባሉ፤ ነገር ግን በስጋቸው የወደቁ ይሆናሉ፣ እና እስከቤዛም ቀን ሐበሰይጣን እንዲጎሰሙ መይሰጣሉ፣ ይላል ጌታ።
፳፯ መንፈስ ቅዱስን ሀመሳደብ ግን በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው ለስርየት የለውም፣ በዚያም አዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳኔን ከተቀበላችሁ በኋላ ንጹህን ደም በማፍሰስ የምትገድሉበት፣ እና በሞቴም የምትስማሙበት ነው፤ እና በዚህ ህግ የማይኖር ማንም ወደ ክብሬ ሊገባ አይችልም፣ ነገር ግን ሐይኮነናል፣ ይላል ጌታ።
፳፰ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝ፣ እና ለአንተም ከአለም ፍጥረት በፊት በእኔ እና በአባቴ እንደተመደበ፣ የቅዱስ ክህነቴን ህግ እሰጥሀለሁ።
፳፱ ሀአብርሐም በራዕይ እና ትእዛዝ፣ በቃሌ የተቀበለውን ሁሉንም ነገሮች ተቀበለ፣ እና ወደ ዘለአለማዊ ክብሩም ገብቷል እና በዙፋኑም ተቀምጧል ይላል ጌታ።
፴ አብርሐም ስለዘሩ እና ስለወገብም ፍሬው በሚመለከት ሀቃል ኪዳንን ተቀበለ—ከእርሱም ለወገብ፣ በስምም ከአገልጋዬ ዮሴፍ የመጣህ ነህ—እነዚህም በአለም ውስጥ እስከሚገኑ ድረስ ይቀጥላሉ፤ እና አብርሐምን እና ዘሩን በሚመለከት፣ ከአለም ውጪም ይቀጥላሉ፤ በአለም ውስጥ እና ከአለም ውጪም እንደ ሐከዋክብት በዝተውም ይቀጥላሉ፤ ወይም፣ በባህር ዳር ያለን አሸዋ ብትቆጥርም እነርሱን ልትቆጥራቸው አትችልም።
፴፩ ይህም ቃል ኪዳን ያንተም ነው፣ ምክንያቱም አንተ ሀከአብርሐም ነህና፣ እና ቃል ኪዳኑም ለአብርሐም ተሰርቶ ነበርና፤ እና በዚህ ህግም የአባቴ ስራ ይቀጥል ዘንድ፣ በዚህም እራሱን ያከብር ዘንድ ነው።
፴፪ ስለዚህ ሂድ እና የአብርሐምን ሀስራዎች አድርግ፤ ወደህጌም ግባ እናም ትድናለህ።
፴፫ ነገር ግን ወደ ህጌ ባትገባ ለአብርሐም የተገባውን የአባቴን ቃል ኪዳን አትቀበልም።
፴፬ እግዚአብሔር አብርሐምን ሀአዘዘው እና ለሳራ ለአብርሐም ሐአጋርን ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው። እና ይህን ለምን አደረገች? ምክንያቱም ይህም ህግ ነበር፤ እና ከአጋርም ብዙ ህዝብ ወጣ። ስለዚህ ይህም፣ ከሌሎች ነገሮች ጋር፣ ቃል ኪዳኖችን ያሟላ ነበር።
፴፭ ስለዚህ አብርሐም በኩነኔ ላይ ነበር? እውነት እላችኋለሁ፣ አልነበረም፤ እኔ ጌታ ይህን ሀአዝዤአለሁና።
፴፮ አብርሐም ልጁን ሀይስሀቅን ለመስዋዕት እንዲያቀርብ ለታዝዞ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ ሐአትግደል ተብሎ ተፅፎ ነበር። አብርሐም ግን እምቢ አላለም፣ እና ይህም መእንደፅድቅ ተቆጠረለት።
፴፯ አብርሐም ሀእቁባቶችን ተቀበለ፣ እና እነርሱም ልጆችን ወለዱለት፤ እና ይህም ለእርሱ እንደፅድቅ ተቆጥሮለታል፣ ምክንያቱም ለእርሱ ተሰጥተዋልና፣ እና በህጌም ኖሯል፤ ይስሀቅ እና ለያዕቆብም ከታዘዟቸው ነገሮች በስተቀር ምንም ሌላ ነገርን አላደረጉም፤ እና ከታዘዙትም ነገር ውጪ ምንም ሌላ ነገርን ስላላደረጉ፣ በቃል ኪዳኖች መሰረት ሐወደ ዘለአለማዊ ክብራቸው ገብተዋል፣ እና በዙፋናትም ተቀምጠዋል፣ እና መላእክት ሳይሆኑ አማልክት ናቸው።
፴፰ ሀዳዊትም ለብዙ ሚስቶች እና እቁባቶችን ተቀበለ፣ እና ከፍጥረት መጀመሪያ እስከዚህ ጊዜ ድረስ አገልጋዮቼም ሰለሞን እና ሙሴ፣ እና ብዙ ሌሎች አገልጋዮቼም ደግመው ተቀበሉ፤ እና ከእኔም ዘንድ ካልተቀበሏቸው ነገሮች በስተቀር፣ በምንም ኃጢአትን አልሰሩም።
፴፱ የዳዊት ሚስቶች እና እቁባቶች በአገልጋዬ በናታን እጅ እጅ እና የዚህ ሀይል ሀቁልፍ በተሰጣቸው በሌሎች ነቢያት እጅ አማካይነት ለእርሱ ለየተሰጡት ከእኔ ዘንድ ነበር፤ እና ሐከኦርዮ እና ሚስቱ ጉዳይ በስተቀር በእነዚህ ነገሮች በእኔ ላይ ምንም ኃጢአት አልሰራም፤ ስለዚህ ከዘለአለማዊ ክብሩም ወድቋል፣ እና የድርሻውንም ተቀብሏል፤ እና እነዚህንም ከዚህ አለም ውጪ አይወርሳቸውም፣ ለሌላ መሰጥቻቸዋለሁና፣ ይላል ጌታ።
፵ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ፣ እና ለአንተ ኣገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ሁሉንም ነገሮች ሀዳግም ትመልስ ዘንድ ሀላፊነት ሰጥቼሀለሁ። ያሻህንን ጠይቅ፣ እና በቃሌም መሰረት ይሰጥሀል።
፵፩ እና ስለ ማመንዘር ስለጠየቅህ፣ እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ ሰው በአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ሚስትን ቢቀበል፣ እና እርሷም በቅዱስ ቅባት ካልመደብኩላት ከሌላ ሰው ጋር ብትገኝ፣ አመንዝራለች፣ እና ትጠፋለች።
፵፪ በአዲስ እና ዘለአለማዊ ቃል ኪዳን ውስጥ ካልሆነች፣ እና ከሌላ ሰውም ጋር ብትሆን፣ ሀአመንዝራለች።
፵፫ እና ባሏ ከሌላ ሴት ጋር ቢሆን፣ እና ሀበመሀላም ላይ ቢሆን፣ መሀላውን ሰብሯል እና አመንዝሯል።
፵፬ እና እርሷ ካላመነዘረች፣ ነገር ግን ንጹህ ብትሆንና መሀላዋን ባትሰብር፣ እና ብታውቅም፣ እና እኔም ለአንተ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ብትገልጥልህ፣ ከዚያም በቅዱስ ክህነት ስልጣን ሀይል መሰረት እርሷን ለመውሰድ እና ላላመነዘረው፣ ነገር ግን ሀታማኝ ለሆነው ትሰጥ ዘንድ ሀይል አለህ፤ እርሱ በብዙዎች ላይ ገዢ ይሆናልና።
፵፭ የክህነትን ሀቁልፎችና ሀይል በላይህ አድርጌአለሁ፤ በዚህም ሁሉንም ነገሮች ለዳግም እመልሳለሁ፤ በጊዜውም ሁሉንም ነገሮች አሳውቅሀለሁ።
፵፮ እና እውነት፣ እውነት እልሀለሁ፣ በምድር ሀየምታትመው ሁሉ በሰማይ ይታተማል፤ እና በስሜ እና በቃሌ በምድር የምታሰረው ሁሉ በሰማያት ለዘለአለም ይታሰራል፣ ይላል ጌታ፤ በምድር ላይ ለየምትሰርዘው ኃጢአት ሁሉ በሰማይ ለዘለአለም ይሰረዛል፤ እና በምድር ላይ የምትይዘው ኃጢአት ሁሉ በሰማይ ለዘለአለም ይያዛል።
፵፯ ደግሜም፣ እውነት እላለሁ፣ የምትባርከውን ማንኛውንም እባርካለሁ፣ እና የምትረግመውን ማንኛውንም ሀእረግማለሁ፣ ይላል ጌታ፤ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝና።
፵፰ ደግሞም፣ አገልጋዬ ጆሴ እውነት እልሀለሁ፣ በምድር የምትሰጠው ማንኛውም ነገር፣ እና ለማንም በቃሌ እና በህጌ መሰረት ማንንም በምድር ላይ ምንም ብትሰጥ፣ ይህንም በእርግማን ሳይሆን በበረከት በሀይሌ እጎበኘዋለሁ፣ ይላል ጌታ፣ እና በምድር እና በሰማይ ያለኩነኔ ይሆናል።
፵፱ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝ፣ እና እስከ አለም ሀመጨረሻ ድረስ እና ለዘለአለም ሁሉ ከአንተ ጋር እሆናለሁና፤ በእውነትም ለዘለአለማዊ ክብርህን ሐአትምብሀለሁ፣ እና በአባቴ መንግስት ውስጥ መከአባትህ አብርሐም ጋር ዙፋንን አዘጋጅልሀለሁና።
፶ እነሆ፣ ሀመስዋዕቶችህን አይቻለሁ፣ እና ኃጢአቶችህንም ሁሉ እሰርያለሁ፤ ለነገርኩህ ለዚያ ታዛዥ በመሆን ያደረግኸውን መስዋዕትነት አይቻለሁ። ስለዚህ ሂድ፣ እና አብርሐም ልጁን ይስሀቅን ለመስዋዕት ያቀረበውን ለእንደተቀበልኩኝ፣ የምታመልጥበትንም መንገድ አዘጋጅቼአለሁ።
፶፩ እውነት እልሀለሁ፥ ለአንተ ለሚስትነት የሰጠሁህን ባሪያዬ ኤማ ስሚዝ ትረጋጋ ዘንድ እና እንድትሰጣትም ካዘዝኩህ በላይ እንዳትቀበል ትእዛዝን እሰጣታለሁ፤ ለአብርሐም እንዳደረግሁት፣ ለሁላችሁንም ለማረጋገጥ፣ እና ከእጆቻችሁ በቃል ኪዳን እና በመስዋዕት መስዋዕትን ለመጠየቅ ይህን አድርጌአለሁና ይላል ጌታ።
፶፪ እና አገልጋዬ ሀኤማ ስሚዝ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጡትን፣ በፊቴ ሰጋ ያላቸውና ንጹህ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ትቀበል፤ እና ንጹህ ያልሆኑት፣ እና ንጹህ ነን የሚሉት፣ ይጠፋሉ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።
፶፫ እኔ ጌታ አምላክሽ ነኝና፣ እና ድምጼንም አክብሪ፤ እና ለአገልጋዬ ጆሴፍም በብዙ ነገሮች ገዢ ይሆን ዘንድ ሰጥቼዋለሁ፤ በትንሽ ነገሮች ሀታማኝ ሆኗልና፣ እና ከዚህም ጊዜ ጀምሮ አበረታዋለሁ።
፶፬ እና ባሪያዬን ኤማ ስሚዝን ከአገልጋዬ ጆሴፍ ጋር እንድትኖር እና ከአገልጋዬ ጆሴፍ በስተቀር ከማንም ጋር እንዳትጣመር አዝዣታለሁ። ነገር ግን በዚህ ትእዛዝ ባትኖር ትጠፋለች፣ ይላል ጌታ፤ እኔ አምላክሽ ነኝ፣ እና በህጌም ባትኖር አጠፋታለሁ።
፶፭ ነገር ግን በዚህ ህግ ባትኖር፣ ከዚያም አገልጋዬ ጆሴፍ ሁሉንም ነገሮች፣ እንዲሁም እንዳለው፣ ለእርሷ ያድርግ፤ እና እኔም እባርከዋለሁ እናም አባዛዋለሁም እና ለእርሱም በዚህ አለም አባቶችና እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች፣ ቤቶችና መሬቶች፣ ሚስቶችና ልጆች ሀበመቶ እጥፍ፣ እና በዘለአለምም አለማት ለየዘለአለም ህይወትን አክሊል እሰጠዋለሁ።
፶፮ ደግሞም፣ እውነት እላለሁ፣ ገረዴ አገልጋዬን ጆሴፍ ለተላለፋቸው ይቅርታ ትስጠው፤ እና ከዚያም በእኔ ላይ በመተላለፍ ለተላለፈችው ሀይቅርታ ይሰጣታል፤ እና እኔ ጌታ አምላካችሁ እባርካታለሁ፣ እናም አባዛታለሁ፣ እና ልቧንም እንዲደሰት አደርጋለሁ።
፶፯ ደግሞም፣ እላለሁ፣ ጠላት መጥቶ እናም እንዳያጠፋውም፣ አገልጋዬ ጆሴፍ ንብረቱን ከእጆቹ አያውጣ፣ ሰይጣን ለማጥፋት ሀይፈልጋልና፤ እኔ ጌታ አምላክህ ነኝ፣ እና እርሱም አገልጋዬ ነውና፤ እና እነሆ፣ አስተውሉም፣ እኔ ከአባታችሁ አብርሐም ጋር፣ ለእስከ ዘለአለማዊ ክብሩ እንደነበርኩኝ፣ ከእርሱም ጋር ነኝ።
፶፰ አሁን፣ ሀየክህነት ህግን በሚመለከት፣ ይህን የሚመለከቱ ብዙ ነገሮች አሉ።
፶፱ እውነት፣ ሰው በአባቴ እንደ ሀአሮን በድምጼ፣ እና በላከኝም ድምፅ፣ ቢጠራ እና እነዚህንም የክህነት ለቁልፎች ባበረክትለት፣ በስሜ፣ በህጌና በቃሌ ምንም ነገንር ቢያደርግ፣ ምንም ኃጢአትን አይሰራም፣ እና እኔም ከጥፋት ነጻ አደርገዋለሁ።
፷ ስለዚህ ማንም አገልጋዬ ጆሴፍን አያጥቃ፤ እኔ ከጥፋት ነጻ አደርገዋለሁና፤ ለተላለፋቸው ከእጆቹ የምጠብቃቸውን መስዋዕቶች ያደርጋልና፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።
፷፩ ደግሞም፣ የክህነት ህግን በሚመለከት—ማንም ሰው ሀድንግልን ቢያገባ፣ እና ለሌላን ለማግባት ፍላጎት ቢኖረው፣ እና የመጀመሪያዋም ፈቃዷን ብትሰጥ፣ እና ሁለተኛይቱን ቢያገባ፣ እና እነርሱም ድንግል ቢሆኑ፣ እና ለሌላም ሰው መሀላ ባይገቡ፣ እርሱም አያጠፋም፤ እርሱም አያመነዝርም ምክንያቱም ለእርሱ ተሰጥተውታልና፤ ከእርሱ በቀር ለማንም ካልሆኑት ጋር አያመነዝርምና።
፷፪ በዚህ ህግ አስር ድናግል ቢሰጡትም፣ ሊያመነዝር አይችልም፣ የእርሱ ናቸውና፣ እና ለእርሱም ተሰጥተውታልና፤ ስለዚህ አይጠፋም።
፷፫ ነገር ግን አንድ ወይም ከአስር ደናግላን አንዷ ካገባች በኋላ ከሌላም ወንድ ጋር ብትሆን፣ አመንዝራለች እና ትጠፋለችም፤ እነርሱም የሰው በትእዛዜ መሰረት ነፍሳትን እንዲወልዱ፣ እና ከአለም መመስረት በፊት በአባቴ የተሰጠውን ቃል ኪዳን ለማሟላት፣ እና በዘለአለሙም አለማት ዘለአለማዊ ክብራቸው ሀእንዲበዛና ምድርን እንዲሞላ የተሰጡት ናቸውና፤ ይህም ይከበር ዘንድ የአባቴ ለስራ የሚቀጥልበት ነውና።
፷፬ ደግሞም፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የዚህን ሀይል ቁልፍ የያዘ ማንም ሰው ሚስት ቢኖረው፣ እና እነዚህን ነገሮች በሚመለከት የክህነቴን ህግ ቢያስተምራት፣ ከዚያም እርሷም ትመነው እናም ትደግፈው፣ ወይም ትጠፋለች፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤ እኔ አጠፋታለሁና፤ ህጌን የሚቀበሉ እና በህጌም የሚኖሩትን ሁሉ አጎላቸዋለሁና።
፷፭ ስለዚህ፣ ስላላመነች እና በቃሌ መሰረት ስላልረዳችው፣ ይህን ህግ ባትቀበል፣ እኔ ጌታ የምሰጠውን ማንኛዎቹን ነገሮች ሁሉ ለመቀበል ይህም በእኔ ዘንድ እንደ ህግ ይሆናል፤ እና ከዚያም እርሷም ህግ ተላላፊ ትሆናለች፤ እና እርሱም አብርሐም አጋርን እንዲያገባ ባዘዝኩት ጊዜ ለአብራም በህጉ መሰረት ከደገፈችው ከሳራ የህግ ግዴታ ነጻ ነው።
፷፮ አሁንም፣ ይህን ህግ በሚመለከት፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከዚህ በኋላ ተጨማሪን ነገር እገልጥላችኋለሁ፤ ስለዚህ፣ ለጊዜው ይህ ይብቃ። እነሆ፣ እኔ አልፋና ኦሜጋ ነኝ። አሜን።