ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፷፭


ክፍል ፷፭

ጥቅምት ፴፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በሀይረም ኦሀዮ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ስለጸሎት የተሰጠ ራዕይ።

፩–፪፣ የእግዚአብሔር የመንግስቱ ቁልፎች በምድር ለሰው ተሰጥተዋል፣ እናም ወንጌሉም አሸናፊ ይሆናል፤ ፫–፮፣ የአንድ ሺህ ዘመን መንግስተ ሰማያት ይመጣል እናም በምድርም በእግዚአብሔር መንግስት ጋር ተዋሀዳለች።

አድምጡ፣ እናም ሀያል እና ጠንካራ የሆነው፣ አካሄዱም እስከ ምድር ዳርቻ የሆነውን፣ አዎን ድምጹም ለሰዎች የሆነውን፣ ከላይም እንደተላከ ድምጽ የሆነውን፣ እነሆ—የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውንም አቅኑ፤

በምድርም ለሰው የእግዚአብሔር መንግስት ቁልፎችም ተሰጥተዋል፣ እናም ከዚህም ወንጌሉ፣ እጅም ሳይነካው ከተራራው ተፈንቅሎ ምድርን እስከሚሞላ ድረስ እንደሚንከባለለውም ድንጋይ፣ ወደ ምድር ዳርቻምይገፋል።

አዎን፣ ድምፅም ይጮሀል—የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ የበጉን እራት አዘጋጁ፣ ለሙሽራውም ተዘጋጁ።

ወደ ጌታም ጸልዩ፣ ቅዱስ ስሙንም ጥሩ፣ በአህዛብም መካከል ድንቅ ስራዎቹን እንዲታወቁ አድርጉ።

የዚህች ኗሪዎችም እንዲቀበሉት፣ መንግስቱም በምድር ላይ እንዲሄድ፣ ጌታን ጥሩ፣ እናም የሰው ልጅ የክብሩን ብርሀን ለብሶ ከሰማይ በምድር ከተሰራችው የእግዚአብሔርን መንግስት ጋር ለመገኛኘት በሚገለጥበት ወደ ፊት ለሚመጡት ቀናትም ተዘጋጁ።

ስለዚህ፣ መንግስተ ሰማያት እንድትመጣ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ወደ ፊት ይሂድ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰማይም እንዳከበርህ እንዲሁ በምድርም ትከበር ዘንድ፣ ጠላቶችህም ይዋረዱ ዘንድ፤ ክብርም፣ ኃይልም፣ እና ግርማም የአንተ ናትና፣ ከዘለአለም እስከዘለዓለም። አሜን።