ቅዱሳት መጻህፍት
መግቢያ


መግቢያ

ትምህርት እና ቃልኪዳኖች፣ በመጨረሻው ቀናት የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለማቋቋም እና ለማስተዳደር መለኮታዊ ራእዮች እና የተነሳሱ ምሪት የተሰጡ አዋጆች ስብስብ ነው። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ክፍሎች የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባላትን የሚመለከቱ ቢሆኑም፣ መልእክቶቹ፣ ማስጠንቀቂያዎቹ፣ እና ማበረታቻዎቹ ለሰው ዘር በሙሉ ጥቅም ናቸው፤ እንዲሁም በሁሉም ቦታ ላሉት ሰዎች ሁሉ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ድምጽ ለጊዜአዊ ጥቅማቸውና ለዘለአለማዊ ደህንነታቸው ሲናገራቸው እንዲሰሙ ግብዣን የያዙ ናቸው።

በዚህ ጥራዝ ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ራዕዮች በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ነቢይ እና ፕሬዘደንት በነበረው በጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ አማካኝነት የተሰጡ ነበሩ። ሌሎቹ በአመራሮቹ ውስጥ የእርሱ ተተኪ በሆኑት በኩል የተሰጡ ነበሩ (የክፍል ፻፴፭፻፴፮፣ እና ፻፴፰፣ እና የአስተዳደሪያዊ አዋጆች ፩ እና ርዕሶችን ተመልከቱ)።

መፅሐፈ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ይፋ ከሆኑት የቤተክርስቲያኗ ጽሁፎች፣ ከመጸሐፍ ቅዱስ፣ ከመጸሐፈ ሞርሞን፣ እና የታላቅ ዋጋ ዕንቁ፣ መካከል አንዱ ነው። ሆኖም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች የጥንት ጽሁፍ ትርጉም ባለመሆኑ ልዩ ነው፣ ነገር ግን ዘመናዊ ግኝት ነው እናም በእግዚአብሔር በተመረጡ ነቢያት አማካኝነት ለቅዱስ ስራው ዳግመኛ መመለስ እና በእነዚህ ዘመናት የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር ላይ ለማቋቋም የተሰጠ ነበር። በራዕዮቹ ውስጥ ለስላሳ ነገር ግን ፅኑ የሆነው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ድምፅ በዘመን ፍጻሜ እንደገና ሲነገር ይደመጣል፤ እናም በዚህ ውስጥ የተጀመረው ስራ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያት የተነገሩትን ቃላት በማሟላት እና በማስማማይ ለዳግም ምፅዓት መዘጋጂያ ነው።

ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ በሻሮን፣ ዊንድሰር አውራጃ፣ ቨርሞንት ውስጥ በታህሳሥ ፳፫፣ ፲፰፻፭ (እ.አ.አ.) ተወለደ። በህይወቱ መጀመሪያ ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር በምዕራብ ኒው ዮርክ በሚገኘው በዚህ ዘመን ማንቸስተር ወደሚባለው ሄደ። በዚያ አቅራቢያ እየኖረ ሳለ፣ በ፲፰፻፳ (እ.አ.አ.) ጸደይ፣ የአስራ አራት አመት ልጅ በነበረበት ወቅት ነበር የመጀመሪያውን ራእዩን የተቀበለው፣ በዚሁም በግል በእግዚአብሔር በዘለአለማዊው አባት፣ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ተጎብኝቶ ነበር። በእዚህ ራእይ በአዲስ ኪዳን የተመሰረተችው እና ሙላተ ወንጌልን ስታካሂድ የነበረችው እውነተኛይቷ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር ላይ እንደማትገኝ ተነግሮት ነበር። በብዙ መላዕክት ትምህርት እንዲሰጠው የተደረገበት ሌሎች መለኮታዊ መገለጦችም ተከትለው ነበር፤ እግዚአብሔር በምድር ላይ የተለየ ስራ ለእርሱ እንዳለው እናም በእርሱ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግመኛ ወደ ምድር ተመልሳ እንደምትመጣ እንዲያይ ተደርጎ ነበር።

ከጊዜ በኋላም፣ ጆሴፍ ስሚዝ በመለኮታዊ እርዳታ መጽሐፈ ሞርሞንን እንዲተረጉምና እንዲያሳትም ይችል ዘንድ ተደርጎ ነበር። በዚያም ጊዜ እርሱ እና ኦሊቨር ካውድሪ በግንቦት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በመጥምቁ ዮሐንስ ወደ አሮናዊ ክህነት ተሹመው ነበር (ት. እና ቃ. ፲፫ን ተመልከቱ)፣ እናም ብዙም ሳይቆይ፣ በጥንቶቹ ኃዋሪያት በጴጥሮስ፣ በያዕቆብ እና በዮሐንስ ወደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ተሹመው ነበር (ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፪ን ተመልከቱ)። ሌሎችም ሹመቶች ተከትለው ነበር፣ በዚህም በሙሴ፣ በኤልያስ እና በኤልያ፣ እንዲሁም በብዙ የጥንት ነቢያት የክህነት ቁልፎች ተስጥቷቸው ነበር (ት. እና ቃ. ፻፲፻፳፰፥፲፰፣ ፳፩ን ተመልከቱ)። እነዚህ ሹመቶች በእርግጥም ለሰው ልጅ የመለኮታዊ ስልጣኖች ዳግመኛ የተመለሱባቸው ናቸው። በሚያዝያ ፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በመለኮታዊ አመራር መሰረት፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ቤተክርስቲያኗን አደራጀ፣ እንዲህም እውነተኛዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዳግመኛ በሰዎች መካከል እንደ እምነት ተቋም ወንጌልን ለማስተማር እና የደህንነት ስርዓቶችን ለማከናወን በስልጣን ስራዋን ጀመረች። (ት. እና ቃ. ፳ን እና የታላቅ ዕንቁ ዋጋ፣ የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ ፩ን ተመልከቱ)።

እነዚህ የተቀደሱ ራዕዮች ችግር በነበረበት ጊዜ የተቀበሉት የጸሎት መልስ ነበሩ፣ እናም የመጡትም እውነተኛ ሰዎች ከተሳተፉበት ከገሀዱ የህይወት ጉዳዮች ነበር። ነቢዩ እና ተባባሪዎቹ የመለኮታዊ ምሪትን ፈልገው ነበር፣ እና እነዚህ ራዕዮችም እነርሱ ይህን እንደተቀበሉ ያረጋግጣሉ። በራዕዮቹም፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ዳግመኛ መመለሱንና መገለጡን፣ እናም የዘመኑ ፍጻሜም የተቃረበ መሆኑን አንድ ሰው ለመመልከት ይችላል። የቤተክርስቲያኗ ከኒው ዮርክ እና ፔንሲላቫኒያ ወደ ኦሃዮ፣ ወደ ሚዙሪ፣ ወደ ኢሊኖይ፣ እና በመጨረሻም ወደ ታላቁ የምዕራብ አሜሪካ ሸለቆ ከነበራት የምዕራብ እንቅስቃሴ፣ እና በአሁኑ ዘመን ቅዱሳን ፅዮንን ለመገንባት የሞከሩበትን ትግል በእነዚህ ራዕዮች ውስጥ ተመልክተዋል።

ቀደም ብለው ያሉት አብዛኞቹ ክፍሎች ስለመጽሐፈ ሞሮሞን መተርጎም እና ህትመት የተመለከቱ ነገሮችን ያካተቱ ናቸው(ክፍል ፫፲፯፣ እና ፲፱ን ተመልከቱ)። ወደኋላ ያሉት አንዳንዶቹ ክፍሎች የነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተነሳሳ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ስራውን የሚያንጸባርቁ ናቸው፣ በዚህም ጊዜ አብዛኞቹ ታላላቅ የትምህርት ክፍሎች ተገልጸዋል (ለምሳሌ ክፍል ፴፯፵፭፸፫፸፮፸፯፹፮፺፩ እና ፻፴፪ን ተመልከቱ፣ እያንዳንዳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ጋር አንዳንድ ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው)።

በራዕዮቹ ውስጥ፣ የአምላክ ስነ-ፍጥረትን፣ የሰው ልጅ አጀማመርን፣ የሰይጣን መኖርን፣ የምድራዊ ህይወት ዓላማን፣ የመታዘዝን አስፈላጊነት፣ የንስሃን አስፈላጊነት፣ የመንፈስ ቅዱስ ስራዎችን፣ ደህንነትን የተመለከቱ ስርዐቶችና አፈጻጸሞችን፣ የምድር ዕጣ ፈንታን፣ ከትንሳኤ በኋላ የሚኖረው የሰው ልጅ ሁኔታ እና ፍርድን፣ የጋብቻ ግንኙነት ዘላለማዊነትን፣ እናም የቤተሰብ ዘለአለማዊ የመሆን ሁኔታን በሚመለከት መሰራታዊ ነገሮች መግለጫ በመስጠት የወንጌል ትምህርቶች ተገልጸዋል። እንደዚሁ ከኤጲስ ቆጳሳት፣ ከቀዳሚ አመራር፣ ከአስራ ሁለቱ ቡድን፣ እና ከሰባዎቹ እና ከሌሎች የአመራር ሹመቶች እና ቡድኖች ጥሪዎች ጋር በሂደት የተገለጸው የቤተክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ቅርጾች ተገልጸዋል። በመጨረሻም ስለኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊነት፣ ግርማው፣ ፍጹምነቱ፣ ፍቅሩ፣ እና የማዳን ኃይሉ የተሰጠው ምስክርነት ይህንን መጽሐፍ ለሰው ልጆች ቤተሰብ ታላቅ ዋጋ ያለው እና “ለቤተክርስቲያኗም ከምድር ሀብት ሁሉ የበለጠ ዋጋ እንዲኖረው” ያደርገዋል (የት. እና ቃ. ፸ መግቢያ ተመልከቱ)።

ራዕዮቹ በመጀመሪያ የተመዘገቡት በጆሴፍ ስሚዝ ጸሀፊዎች ነበር፣ እናም የቤተክርስቲያኗ አባላት በእጅ የተጻፉ ቅጂዎችን እርስ በእርስ በደስታ ይካፈሉ ነበር። ቋሚ መዝገብ ለመፍጠር፣ ጸሀፊዎች እነዚህን ራዕዮች ባልታተሙ የመዝገብ መፅሀፎች ውስጥ በቅጂ አዘጋጁ፣ እነዚህንም የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ራዕዮችን ለማተም ለማዘጋጀት ተጠቀሙባቸው። ጆሴፍ ስሚዝ እና የመጀመሪያ የቤተክርስቲያኗ አባላት እነዚህን ራእዮች ቤተክርስቲያኗ በተመለከቱበት ሁኔታ ይመለከቷቸው ነበር፥ ህያው፣ ለውጥ የሚፈጥር፣ እና በተጨማሪ ራዕይ ለመጣራት የሚችል። ራዕዮችን በሚቀዱበት ጊዜ እና ለመታተም በሚዘጋጁበት ጊዜ ሳይታወቅ ስህተቶች ሊገቡባቸው እንደሚችሉም አውቀው ነበር። ስለዚህ፣ የቤተክርስቲያኗ ጉባኤ በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ “በመንፈስ ቅዱስ በኩል ሊያገኛቸው የሚችላቸውን እነዚያን ጉድለቶች እና ስህተቶች እንዲያስተካክል” ጠየቁት።

ራዕዮች ከተገመገሙ እና ከተስተካከሉ በኋላ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት በምዙሪ ውስጥ የነቢዩን ብዙ የመጀመሪያ ራዕዮች የያዘውን፣ A Book of Commandments for the Government of the Church of Christ (በርዕስ መጽሐፈ ትእዛዛት ለክርስቶስ ቤተክሪስቲያን አስተዳደር) የሚባለውን መፅሀፍ ማተም ጀመሩ። ነገር ግን፣ በሀምሌ ፳፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በጃክሰን የግዛት ክፍል ውስጥ የነበረውን የቅዱሳንን የእትመት ቢሮ በመደምሰሳቸው፣ ራዕዮችን ለማተም የተደረገው የመጀመሪያ ጥረት ቆመ።

የምዙሪ የእትመት ቢሮ እንደተደመሰሰ በሰሙበት ጊዜ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ራዕዮችን በከርትላንድ ኦሀዮ ለማተም ዝግጅት ጀመሩ። እንደገና ስህተቶችን ለማስተካከል፣ አባባሎችን ለመግለጽ፣ እና የቤተክርስቲያኗ ትምህርት እና ድርጅትን ለማሳወቅ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የአንዳንድ ራዕዮችን ጽሁፎች የማረም ስራን በመቆጣጠር እነዚህን በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) እንደ Doctrine and Covenants of the Church of the Latter Day Saints (መጽሐፈ ትእዛዛት ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቤተክሪስቲያን አስተዳደር) ለማሳተም አዘጋጀ። ጆሴፍ ስሚዝ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ሌላ ቅጂ እኒድታተም ፈቃድ ሰጠ፣ ይህም የታተመው በ፲፰፻፵፬ (እ.አ.አ.) ከነቢዩ ሰማዕትነት ጥቂት ወሮች ካለፉ በኋላ ነበር።

የመጀመሪያዎቹ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ለራዕዮቹ ታላቅ ዋጋ ሰጧቸው እናም እንደ እግዚአብሔር መልእክቶች ይመለከቷቸው ነበር። በ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ አንድ ጊዜ፣ ብዙ የቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች ጌታ በነፍሳቸው እነዚህ ራዕዮች እውነት እንደሆኑ እንደመሰከረላቸው የክብር ምስክራቸውን ሰጥተው ነበር። ይህ ምስክርነት በ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) የትምህርት እና ቃል ኪዳን ቅጂ ውስጥ በአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት የተጻፈ ምስክር በመባል ታትሞ ነበር።

የመጽሐፈ ትምህርት እና ቃል ቃል ኪዳኖች
እውነተኛነትን በተመለከተ የአስራ ሁለቱ
ሐዋሪያት ምስክርነት

በቤተክርስቲያኗ ድምጽ ለዚህ ዓላማ በተመደበው ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ አማካኝነት ለቤተክርስቲያኗ የሰጠውን ትዕዛዛት፣ ይኸውም የጌታ ትእዛዛት መጽሐፍን በተመለከተ የምስክሮች ምስክርነት፥

ስለዚህ እኛ በአለም ለሚገኙ ለሰው ዘር በሙሉ፣ በምድር ገጽታ ላይ ላሉ ፍጡራን ሁሉ፣ እነዚህ ትእዛዛት በእግዚአብሔር ምሪት ለሰዎች ሁሉ ጥቅም እንደተሰጡ እና እውነት መሆናቸውን ጌታ ለነፍሳችን እንደመሰከረልን፣ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነትም እንዳፈሰሰልን ምስክርነታችንን ለመስጠት ፈቃደኞች ነን።

ጌታ እረዳታችን ሆኖ፣ ይህን ምስክርነት ለዓለም እንሰጣለን፤ እናም ለዓለም ምስክርነታችንን እድንሰጥ ይህንን ዕድል እድናገኝ የተፈቀደልን በእግዚአብሔር አብ፣ እና በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ነው፣ እኛም የሰው ልጆችም ሁል ጊዜ በዚህ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ለጌታ እየጸለይን፣ በዚሁ ምስክርነት እጅግ በጣም ተደስተናል።

የአስራ ሁለቱ ስም ዝርዝር፥

  • ቶማስ ቢ ማርሽ

  • ዴቪድ ደብሊው ፓተን

  • ብሪግሃም ያንግ

  • ሂበር ሲ ኪምቦል

  • ኦርሰን ሀይድ

  • ዊሊያም ኢ መክለልን

  • ፓርለይ ፒ ፕራት

  • ሉክ ኤስ ጆንሰን

  • ዊሊያም ስሚዝ

  • ኦርሰን ፕራት

  • ጆን ኤፍ ቦይንቶን

  • ላይማን ኢ ጆንሰን

በተከታታይ የትምህርት እና ቃልኪዳኖች ቅጂዎች፣ ተጨማሪ ራእዮች እና ሌሎች መረጃዎች ብቁ በሆኑ ተሰብሳቢዎች ወይም በቤተክርስቲያኗ ጉባዔ ሲስተናገዱ እና ተቀባይነትን ሲያገኙ እንዲጨመሩ ተደርገዋል። በብሪገም ያንግ አመራር ስር በሽማግሌ ኦርሰን ፕራት የተዘጋጀው የ፲፰፻፸፰ (እ.አ.አ.) ቅጂ፣ ራዕዮችን በዘመን ቅድመ መከተል እና አዲስ ርዕሶችንና ታሪካዊ መግቢያዎች በመስጠት አዘጋጀ።

ከ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) ቅጂ ጀምሮ፣ ሰባት የመንፈሳዊ ትምህርት ትምህርቶች ተካተው ነበር፤ Lectures on Faith (የእምነት ንግግሮች) የሚል ርዕስ ተስጥቷቸው ነበር። እነዚህ ከ፲፰፻፴፬ (እ.አ.አ.) እስከ ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ፣ ኦሃዮ፣ ለነቢያት ትምህርት ቤት መጠቀሚያ የተዘጋጁ ነበሩ። ለትምህርት እና መመሪያ ቢጠቅሙም፣ ከ፲፱፻፳፩ (እ.አ.አ.) ቅጂ ጀምሮ እነዚህ ንግግሮች ከትምህርትና ቃል ኪዳኖች ውስጥ እንዲወጡ ተደርገዋል፣ ምክንያቱም አጠቅላይ ቤተክርስቲያኗን በሚመለከት የተሰጡ ወይም የቀረቡ ራእዮች ስላልሆኑ ነው።

በትምህርት እና ቃል ኪድኖች የ፲፱፻፹፩ (እ.አ.አ.) በእንግሊዝኛው ቅጂ ውስጥ ሶስት መረጃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨምረው ነበር። እነዚህም የመታን ደህንነት መሰረታዊ መርሆችን የሚመሰርቱት ክፍሎች ፻፴፯ እና ፻፴፰፣ እና ያለዘር እና የቀለም ልዩነት ብቁ የቤተክርስቲያኗ ወንድ አባላት ለክህነት ለመሾም እንደሚችሉ ያስተዋወቀው የአስተዳደራዊ አዋጅ ፪ ነበሩ።

እያንዳንዱ የትምርት እና ቃል ኪዳን ቅጂ የድሮ ስህተቶችን አስተካክለዋል እና አዲስ መረጃዎችን፣ በተለይም በክፍል ርዕሶች የታሪክ ክፍሎችን፣ ጨምረዋል። የዚህ ጊዜ ቅጂ ቀናትን እና የቦታ ስምችን ያጣራል እና ሌሎችንም በተጨማሪ ያስተካክላል። እነዚህ ለውጦች የተደረጉት ጽሁፎችን ከብዙዎቹ ትክክለኛው ታሪካዊ መረጃዎች ጋር እንዲስማሙ ለማድረግ ነው። በዚህ አዲስ ቅጂ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ልዩ ነገሮችም ራዕዮች የተቀበለበትን ቦታዎች የሚያሳዮ ካርታዎችን የተከለሱበት፣ በተጨማሪውም የቤተክርስቲያኗን ታሪካዊ ፎርትዎች፣ ማጣቀሻዎችን፣ የክፍል ርዕሶችን፣ እና የርዕስ ማጠቃለያዎችን የተሻሻሉበት ነበሩ፤ ሁሉም ማሻሻያዎች የተደረጉት አንባቢዎች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የተሰጡትን መልእክቶች እንዲረዱና እንዲደሰቱበት ለመርዳት ነበር። በክፍል ርዕሶች ውስጥ የሚገኙ መረጃዎችም የተወሰዱት ከቤተክርስቲያኗ ታሪክ ያልታተመ ፅሁፍ እና ከታተመው ከHistory of the Church [የቤተክርስቲያኗ ታሪክ] (እነዚህም በርዕሶች ውስጥ አንድ ላይ የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ ተብለው ይጠራሉ) እና ከ Joseph Smith Papers [የጆሴፍ ሚዝ ፅሁፍ] ውስጥ ነበር።